HabitSystemV3: Amharic_sample.txt

File Amharic_sample.txt, 403.2 KB (added by xsuchom2, 7 years ago)
Line 
1የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን
2መስዋዕት አድርጎ በማቅረቡ የክህነት አገልግሎት
3ዋና ይዘት ፍቅር፣ ራስን ለቤተ ክርስቲያን
4አሳልፎ መስጠት መሆኑን አሳየን።
5ከጌታችን የባሕርይ ምንጭነት የተገኘው የአዲስ
6ኪዳን ክህነት ሐዋርያትን አረስርሶና አርክቶ በቂ
7የሆነ ክህነታዊ ተግባርም አሳይቶ አሁን ባሉ
8አባቶች ላይ ይገኛል።
9አምላካቸውን ያገኙ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን
10የምትፈጽማቸው ምሥጢራት ስላሏት፣ ምሥጢራቱ
11የሚፈጸሙትም የግድ በካህናት ስለሆነ ክህነት
12በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ
13አስፈላጊና የማይቀር ነው።
14ይህም በዓለም ያለው በእግዚአብሔር አርዓያና
15ምሳሌ የተፈጠረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን
16እንዲያይበትና ከእግዚአብሔር ጋር
17እንዲገናኝበት ነው።
18በሌላ በኩል ደግሞ በዓመታዊ የንግስ በዓላት
19ወቅት የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና
20የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
21ቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ማትያስ፣
22የቪክቶሪያ ዳግማዊ ቆልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ
23ክርስቲያን ካህናት፣ የሲያትል ደብረ ሰላም ቅዱስ
24ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናት
25እየመጡ ያገለግላሉ።
26በዓመት እስከ አራት ጊዜ ያህል ካናዳና አሜሪካ
27ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትንመምህራንን
28በመጋበዝ ለተወሰነ ጊዜ እየቆዩ ምዕመናንን
29ወንጌል እንዲያስተምሩ በመደረግ ላይ ነው።
30ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ
31እያደገ የመጣውን መንፈሳዊ አገልግሎትና
32እየጨመረ የሄደውን የካህናትና የምዕመናን ቁጥር
33እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ ይጠብቅልን።
34በአሁኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ
35በማገልገል ላይ የሚገኙት ካህናትና ዲያቆናት
36በፎቶው ላይ የሚታዩት ናቸው።
37በሀገራችን በኢትዮጵያ የዘመን ስሌት አዲሱን
38ዓመት በወርኃ መስከረም አንድ ብለን መቁጠር
39እንደጀመርን ከምናስተውላቸው ዓበይት ክስተቶች
40መካከል የውኃውን መጉደል፣ የሰማዩን መጥራት
41እንዳለ ሆኖ ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው የምድር
42በአበቦች ማጌጥ ነው፡፡ ዝርዝር ንባብ
43የመዝሙረ ዳዊት አራት ዋና ዋና ጥቅሞች - ስብከት
44በዲን ዶር ቴዎድሮስ በለጠ ፤ ፔርኒስ - ሮተርዳም
45የገዳማት ቀን ሃምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ።
46ም 2, 2015
47የሊቀ መልዐኩ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ንግስ
48በዓል አምስተርዳም በሚገኘው ደብረ ብስራት ቅዱስ
49ገብረዔል ቤተ ክርስቲያን በእለቱ እሁድ ሐምሌ
50፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓም ከሆላንድ፣ ከቤልጄም፣
51ከፈረንሳይ እንድዚሁም ከጀርመን ሃገራት የመጡ
52የኢትዮጵያ የኤርትራ እና የሶሪያ ኦርቶዶክስ
53ተዋሕዶ ቤክርስቲያናት ካህናት አባቶች
54ዲያቆናትና ምዕመና በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ
55ተከብሮ ዋለ።
56የበዓሉን አከባበር ከዚህ በታች ባሉት ቪዲዮች
57ይመልከቱ-
58ባሕታዊ አባ ገጊዮርጊስ የተባሉ በሆላንድ ሃገር
59በተለያዩ ከተሞች የስብከትና ሀብተ ፈውስ
60አገልግሎት እንደሚሰጡ በመግለጽ ምእመናን
61በጉባዔው እንዲሳተፉ የሚጋብዝ ጥሪ እየተሠራጨ
62ይገኛል ።
63እኝህ ሰው የመጡት በሆላንድ የኢኦተ ደብረ መዊዕ
64ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካው
65መንፍሳዊ ኮሚቴም ሆነ በአምስተርዳም፣
66በሮተርዳም፣ በአይንድ ሆቨን እና በአምስፎርት
67ከተሞች በቤተ ክርስቲያናችን ስር የሚገኙት
68የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተወካዮች የማያውቁት
69ስለሆነ ምእመኑ ጠንቅቆ እንዲገነዘብ ፅህፈት ቤቱ
70ያሳውቃል።
71ይህንን በሚመልክት ተቀማጭነቱ በጀርመን ሃገር
72የሆነው የኢኦተ ቤተ ክርስቲያን የምእራብ፣
73የምስራቅና የድቡብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ
74ጳጳስ ጽቤት፥ በፌስ ቡካቸው ላይ ያወጡትን
75መልእክት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ።
76የ፳፻፰ ዓም መስቀል በዓል አከባበር
77ፔርኒስ-ሮተርዳም በፎቶ ይህንን ይመስል ነበር
78የ፳፻፰ ዓም መስቀል በዓል አከባበር
79አምስተርዳም በፎቶ ይህንን ይመስል ነበር
80አንድ መጽሐፍ ጠፍቶብኝ መደርደሪያው ላይ ያሉትን
81ሳገላብጥ አንድ መጽሐፍ አገኘሁና አንዳንድ
82ትዝታዎችንም ሀሳቦችንም ጫረብኝ፤ ክንፈ
83አብርሃም ለፒኤችዲ የጻፈውና በኋላ ያሳተመው
84መጽሐፍ ነው፤ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ክንፈን
85በስዊድን አግንቼው ቤቱ ጋብዞኝ ከእሱና ከባለቤቱ
86ጋር ስንጫወት አመሸን፤ ስንሰነባበት ይህንን
87መጽሐፍ ሰጠኝ፤ለመጽሐፉ መግቢያ የጻፈለት ዶር
88ኃይሉ አርአያ ነው፡፡ የመጽሐፉ ርእስ
89በአማርኛ ምናልባት ከዘር ወደመደብ ልንለው
90እንችል ይሆናል፤ ወያኔ ጎሣን እንዳስተማረን
91ለደርግ ምስጋና ይድረሰውና በበኩሉ መደብ
92የሚለውን ቃል አስተምሮናል፤ ሁለቱም የቸገረው
93እርጉዝ ያገባል እንደሚባል ሆኖባቸው ነው፤ ይህ
94መጽሐፍ ግሩም የእውነተኛ ምሁር መጽሐፍ ነው፤
95እንዳጋጣሚ ሆኖ አሁን ባላስተውሰውም ከዚህ በፊት
96በአንዱ መጽሐፌ ውስጥ ጠቅሼዋለሁ፡፡ ዛሬ ላነሣ
97የፈለግኋቸው ሁለት ነጥቦች ናቸው፤ አንዱ በጎሣ
98ስሜት ተገፍተን ከአየናቸው ዶር
99ክንፈም አብርሃምም፣ ዶር
100ኃይሉም ትግሬዎች ናቸው፤ ነገር ግን ክንፈ
101መጽሐፉን ሲጽፍና ኃይሉ መግቢያውን ሲጽፍለት
102የተገናኙበትና የተስማሙበት በአንድ ጎሣ
103አባልነታቸው ሳይሆን በሰውነታቸውና
104በምሁርነታቸው ነው፤ በዚያን ጊዜ ሁለቱም ከጎሣ
105ደረጃቸው ከፍ ብለው በአንድ የሰውነት ደረጃ ላይ
106ነበሩ፤ ሁለቱም ከዘረኛ አስተሳሰብ ወደመደብ
107አስተሳሰብ መሸጋገር እድገት መሆኑን የተገነዘቡ
108ሰዎች ነበሩ፡፡ ሁለተኛው ነጥብ በድኅረ-ወያኔ
109የመጣው ለውጥ ነው፤ ክንፈ በእውቀቱና በሰውነቱ
110ሳይሆን በጎሣው ተመልምሎ የወያኔ መኳንንት
111አገልጋይ ሆነ፤ እንደክንፈ አብርሃም ያለ ምሁር
112ለሎሌነት አይመችም፤ ጠርሙሱን ወዳጅ ያደረገውም
113ይህንን ለመርሳት ይሆናል፤ በአንጻሩ ኃይሉ
114አርአያ ለጎሣው ሥርዓት በተቃዋሚነት ሲፈረጅ
115ቆይቷል፤ እስከዛሬም እንደዚያው ነው፡፡ በሠላሳ
116አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ይህንን ያህል
117ልዩነት በመሀከላቸው የተፈጠረው እንዴት ነው?
118ክንፈ ወደጎሣ ሎሌነት ወርዶ እግዚአብሔር ጠራው፤
119ኃይሉ አሁንም ከሰዎች ተራ አልወጣም፡፡
120ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት
121ግን ውርደትን ነው!
122ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና
123ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ
124መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት
125ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር
126ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ
127እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ
128አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት
129ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና
130አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ
131ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ?
132የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ
133የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን
134ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ
135ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት
136ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን
137ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን
138ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን
139እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም
140ክብር ይሆናሉ፡፡ ለፍቅር መተዋወቅ
141እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ
142ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ
143እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር
144ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ
145መረጃዎችን ላቅርብ፤ ---
1461
147የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣
148በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው
149የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል
150አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ
151ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል
152ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤ 2
153በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ
154ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች
155ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁ
156ማኅበር ታዛቢ አባል ነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት
157አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ
158አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤
159በዚህ ሁሉ መሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን
160ነች፤ 3
161የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን
162ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤
163ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤
164ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም
165የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ››
166ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼ ታስሬአለሁ፤ ስለዚህ
167አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው
168እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ
169እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤
170ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ
171ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ ጥጋብ ላይ ያሉ
172የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን
173ነው፡፡
174አሁን…!
175አሁን…!
176ባለፈው ሰሞን ነው።
177ወሮ አዜብ መስፍን መኪና እያሽከረከሩ የትራፊክ
178ፖሊስ ያስቆማቸዋል።
179ስህተት ሰርተሻል በማለት ያስቆማቸው ትራፊክ
180ጥፋቷን ይገልጽላታል።
181ወሮዋ ጥፋታቸውን አልሸመጠጡም።
182አዎ አጥፍቻለሁ አንዱን ግን ስታስቆመኝ ተደናግጨ
183ነው ስህተት የሰራሁት ይላሉ።
184የትራፊክ ፖለሱም የቅጣት ትኬቱን ጽፎ በጃቸው
185አስረክቦ የመንጃ ፈቃዳቸውን ይወስዳል።
186ይሄ በኢትዮጵያ የትራፊክ አሰራር የተለመደ ነው።
187እናም መንጃ ፈቃድ የሚወሰደው የትራፊክ መምሪያ
188ተኪዶ፤ ቅጣት ተከፍሎ ነው።
189ወሮ አዜብም መንጃፈቃዳቸውን ለትራፊክ ፖሊስ
190አስረክበው የማንነታቸውን ሳይገልጹ ወደ ቤታቸው
191ያመራሉ።
192እጅግ ይበል ሊያሰኝ ይችላል።
193የትራፊክ ፖሊሱ የመንጃ ፈቃዱ ባለቤት የማን
194መሆኗን በሰማ ሰአት ወደላይ ይበለው ወደታች፤
195ስኳር ይነሳበት፣ ደም ብዛት አላህ ይወቅ።
196ችግሩ… አዜብ አይደለችማ!?
197
198ወሮ አዜብማ ያለ መለስ ምንም ናት።
199አዜብ ያለመለስ ከአስናቀች፣ ከትብለጽ፣ ከጸዳለ
200በምንም አትለይም።
201እትየ አዜብ የሚለዩት የህወሀት መሪ፣ የኢህአዴግ
202ተጠሪ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር የሚባል ባል
203ስላላቸው ብቻ አይደለም።
204ከቅርብ ጓደኞቹ እስከ ሩቅ ወዳጆቹ፤ ከ10 አመት
205ህጻን ልጅ እስከ ሰማኒያ ኣመት አዛውንት በእጁ
206ያስጨረሰ፣ እጁ በማይነጥፍ የሰው ደም የጨቀዬ
207አረመኔ ባል ስላላት ጭምር እንጂ።
208አዜብ ስፔን ሄዳ ሚሊየን ዶላር ብታጠፋ ምን
209አለበት!?
210
211በአሁኑ ጊዜ እንኳን እሷ ሌላ ተራ የተባሉ
212የሀብታም ሚስቶችስ ያን ያህል ገንዘብ ያጠፉ
213የለም እንዴ?
214ችግሩ ያለው ህዝብ በርሀብ እንዲሰቃይ እና በስራ
215እጦት እንዲማስን ዋና ተጠያቂ የሆነ ባል ስላላት
216እንጂ?
217ጣጣ የሚመጣው እኮ ወሮ አዜብ የማእከላዊ ኮሚቴ
218አባል መሆን አለባት ስላለ የምትሆንለት።
219ያሻውን የሚያደርግ ባሏ መለስ ላይ እንጂ… መለስ
220ባይኖር እነ አቶ በረከት ተነስተው አዜብየ ግቢ
221ለሚቀጥለው ስልጣን ስለምንፈልግሽ የማእከላዊ
222ኮሚቴ አባል መሆን አለብሽ የሚሏት ይመስላችኋል?
223
224ለዚያም ነው ያ ትራፊክ ማንነቷን ሳይሆን
225የማንነቷን ሲያውቅ ምን ሊሆን እንደሚችል
226ለመማጸን ወደላይኛው እንድናጋጥጥለት
227የምለምነው።
228ስንት ልጆች ይኖሩት ይሆን…?
229በነገሬ ላይ ወያኔ ባዶ ሶስት የሚሉት የወሬ ጎስም
230ቡድን ነበረው።
231መለስ ምላሱን መላእኮች ሌሊት ሌሊት ክንፋቸውን
232ዘርግተው ይባርኩለታል ብላችሁ ወሬ ንዙ ከተባሉ
233ወይም ደግሞ ኢህአዴግ በኤሌክትሪክ የሚሰራ
234መሳሪያ ሊያስገባ ነው።
235ከአሁን በኋላ በጦርነት ሞት የሚባል አይኖርም፤
236የኢትዮጵያ ወታደር ከግብጽ ጋር ቢዋጋ ከመሀል
237አዲሳባ ሆኖ በኮምፒውተር ነው ጦርነት
238የሚያደርገው… ብዙ ብዙ አይነት ወሬዎችን
239ተቀብለው የሚያቀባብሉ።
240ባዶ ሶስቶች።
241የሚመለመሉት ከመንደር ቡና አንጫላጭ ወሬኛ
242እናቶች እስከ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ድረስ ባሉ “አደገኛ”ወሬኞችን
243በማካተት ነው።
244ወይንም ደግሞ ምንም ጉዳት የማያደርስ የዋህ ካለ
245ወሬው ለሱ እንዲደርስ ይደረጋል።
246እናም ወሬውን ከኋላ ያባርሩታል።
247ወሬው ጆሯችን ገብቶ እስኪያበቃ አይለቁትም
248ያባርሩታል።
249እነኝህ ሰዎች ኢትዮጵያ በነበርኩ ሰአት አንድ
250ወሬ ማስወራት ጀምረው ነበር።
251አቶ መለስ ተደብቀውና ራሳቸውን ቀይረው ገበሬ
252መንደር በመግባት ሰዎችን ያነጋግራሉ የሚል።
253ድንቅ ወሬ ነበር።
254ሸጋ።
255ግን ግን አቶ መለስ በአደባባይ ሰው ስለሚገድሉ፣
256ሰው እንዳሻቸው ስለሚያስሩ፣ ሀገርን በጎሳ
257ከፋፍለው ስለሚያስተዳድሩ ያ ገበሬ ሳያውቃቸው
258አስተናግዷቸው ይሆናል።
259ችግሩ ያለው አቶ መለስ ጭምብል አጥልቀው ገበሬ
260መሀል መግባታቸው ሳይሆን ራሳቸውን አቶ መለስን
261ሲሆኑ ነው።
262አቶ መለስ ራሳቸውን ደብቀው እንጂ ራሳቸውን
263ሆነው ህዝብ መሀል ቀርቶ ግለሰብ ዘንድ
264አይቀርቡም።
265ስራቸው ነዋ!
266ስራቸው ዋጋቸውን ሰጥታቸዋል ተከቦ መኖር።
267ምን እሳቸው ብቻ ልጆቻቸው ዘመዶቻቸውም ጭምር
268እንጂ…።
269እንደ አቶ መለስ ያሉ አምባገነኖች ለራሳቸው
270እንጂ ለልጆቻቸው እንኳን ግድ የማይሰጣቸው
271ፍጥረቶች መሆናቸውን በአርባ አመቱ መንበር ጋላቢ
272ጋዳፊ አየን።
273ሳዳምንም ተመለከትን፣ ቢን አሊም ታዩ፣ የኛኑ
274መንግስቱንም ማየት መልካም ነው።
275በነገራችን ላይ በቅርቡ የኮሎኔል መንግስቱ ልጅ
276ትምህርት መንግስቱ መሰለችኝ እዚህ ውቧ መንደር
277ቫንኩቨር ነበረች።
278ማንንም ሳታይ ማንም ሳያያት በአባቷ ሀጢያት
279የኋልዮሽ እያየች ትኖራለች።
280… አምባገነኖች አሁን ባለ ደስታ የኋላ ኋላ
281ልጆቻቸውን ጭምር ያሳቅቃሉ።
282እየተሹለከለኩ በየት ልግባ በየት ልውጣ ሲሉ፣
283የቅርቡን የኛኑ መንግስቱን አይቶ መማር ምን
284ያቅታል ጎበዝ፡፤ የመንግስቱ ልጆች በምንም
285አይነት መለኪያም ያጠፉት ቅንጣት ጥፋት የለም።
286በምንም አይነት መልኩ ቀናብለው መሄድ ግን
287አይችሉም።
288ጥፋት ቢኖርባቸው እንኳን ከነፍሰ በላው አባታቸው
289መፈጠራቸው ብቻ ነው።
290ያለሀጢያታቸው አሁንም ወልደው ከብደው እንኳን
291ከመሽሎክሎክ አላመለጡም።
292የቢን አሊም… የጋዳፊም… የሙባረክም… ሁሉም
293አንድ ነው የሚገጥማቸው።
294የአቶ መለስ ሴት ልጅ ያኔ ቅንጅት በህዝብ ድጋፍ
295አይሎ በነበረ ጊዜ ተስፋዋ ጨልሞባት ለአንድ
296መምህሯ “የአባየ ነገር አለቀለት” ማለቷን
297ከመምህሯ ጓደኛ ሰምቼ ነበር።
298የመለስ ልጅ አድጋለች፣ ነፍስ አውቃለች፣
299የአባቷን መጨረሻ ስታይ ምን ትል ይሆን?
300አሁንማ ለንደን አለላት፣ ዛሬማ ኦሀዮ የራሷ ነው።
301ሁሉ በእጇ የሆነላት ግንግን የራሷ የግሏ ያልሆነ
302ህይወት የምትኖር ፍጥረት።
303ታዲያ የዚህች በአምባገነን የምትማቅቅ ሀገር
304ተስፋ በማን ላይ ነው?
305ሀገር ቤት ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በውጭ ያለው
306ኢትዮጵያዊ ላይ ተስፋውን ጥሎ ወደ ላይኛው
307ማንጋጠጥ ይዟል።
308እኛ እዚህ የተደላደለ ኑሮ እያሳደድን የምንገኘው
309ዲያስፖራዎች ግን ነጋ ጠባ በማይረቡ ጉዳዮች
310ጭቅጭቅ ይዘናል።
311አቤት የንትርክ መአት፣ አቤት የስድድብ ብዛት…!
312አቤት አቤት የሚነሱ ሰንካላና የማይረቡ ንዝንዞች
313መአት።
314እነኝህ ንዝንዞች ታዲያ ኦስሎ ወይም ለንደን
315እንዳሉት ሁሉ አለያም ታላቋ የሀበሻ መናገሻ
316ዋሽንግተን ዲሲ ወይ ቶሮንቶ እንዲያም ካለ
317አትላንታም ሆነ ሎስ አንጀለስ እንዳለው ሁሉ
318በተመሳሳዩ እዚህ ቫንኩቨርም አለ።
319ውቧ መንደር ቫንኩቨር።
320ሸጋዋ… ደጓ ምድር ቫንኩቨር።
321ውጭ ሀገር መኖር ትልቁ ጥቅም ነጻነት ነው።
322እዚህ ስንኖር በምርጫችን ነው።
323አባ ጳውሎስንም ሆነ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ
324መርቀርዮስን ለመምረጥ መብቱ ያለን እዚህ
325በመኖራችን ብቻ ነው።
326እዚያ ነጻነት የለም እዚያ… ኢትዮጵያ ያለው
327ምርጫ አባ ጳውሎስ ወይም ስደት ገፋ ካለም ሞት ነው።
328እዚህ ግን እንደ ቫንኮቨሯ ማሪያም ቤተ
329ክርስቲያን ካልተሰረክና ካልተጭበረበርክ
330በስተቀር ነጻነት አለህ።
331የቫንኩቨሯ ማሪያም ታሪክ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ
332መነጋገሪያ ነበረች።
333በገለልተኛ ሽፋን በተሸሸጉ የአባ ጳውሎስ
334አሽከሮችና በአቡነ መርቀሪዮስ በሚመራው ሲኖዶስ
335ስር መተዳደር በሚፈልጉ ሰዎች መሀል ሰፊ ክርክር
336ነበር።
337የፈረንጅ ዳኛ ገላጋይ የገባበት።
338ማውራት የፈለኩት ስለቤተ ክርስቲያኗ ጣጣ
339አይደለም።
340የሱ ምእራፍ ተዘግቷል።
341ልናገር የፈለኩት ስለነዚያ ልጅ ተክሌ
342እንደሚላቸው የኢትዮጵያን ፖለቲካ በዚህም
343በዚያም ተጠቅመው የወጡ ይህንን አገዛዝ አጥብቀው
344ስለሚቃወሙና በነጻዋ ምድር ቫንኩቨር ላይ
345ድብብቆሽ ስለሚጫወቱት እንጂ።
346አንዱ ስሙን ቀይሮ በስልክ ሊያናግረኝ ቀጥሮኝ
347ብሄድ ስሙ ሌላ ወሬው ሌላ…
348ገለልተኛ ነን!
349
350እኛ ቤተክርስቲያኗ ወደ አባ ጳውሎስ እንድትሄድ
351አንፈልግም… በማለት ሲደሰኩርልኝ የነበረ ሰው
352ዛሬ ቤተክርስቲያኗ በጳውሎስ እጅ ወድቃ
353የቤተክርስቲያኗ አመራር ሆኖ ሲያየኝ ምን
354እንደሚሰማው አላውቅም።
355እኔ እሳቀቅለታለሁ።
356ቤተ ክርስቲያኗ ወደ አባ ጳውሎስ እያመራች ነው
357ሲባል… እኛ እያለን?
358… እንዴት ይደረጋል…?
359በኢንተርኔት ላይ ሲባል ነው የምሰማው እንጂ
360በፍጹም አይደረግም።
361ሲል የነበረ የማከብረው ትልቅ ሰው ዛሬ በጳውሎስ
362ስር ለመተዳደር ብቻ ሳይሆን የህወሀት ካድሬ
363መሆኑ የሚታማ ቄስ ተሹሞ ሲባርከው በምን አይነት
364ሞራል እንደሚቀበለው እግዜር ይወቅ።
365ቫንኩቨር ታዲያ ትችለዋለች ሁሉም አለ ሁሉም
366የለም።
367በቫንኩቨር።
368ልክ እንደ ኔዘርላንዱ ልክ እንደ ሲድኒው…
369እናንተየ ይሄ በየ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ጉድ ጉድ
370የሚል ሰው ወይንም አንዴ ለሰበካ ጉባኤ የተመረጠ
371ሰው ስልጣን አልለቅም ብሎ የሙጥኝ የሚለው ለምን
372ይሆን?
373… እዚያ አካባቢ ምን አይነት ጥቅም እንዳለ
374አላውቅም።
375ግን ግን ብዙ የሚሸት ነገር አለ!
376… በገንዘብ የማይጠረጥረው ግልሰብ ቦታዋ ላይ
377ሲደርስ የሙጥኝ ይላል… የምታከብሩት ሰው
378በየደብሩ ሲገባ የስራ ዘመኑ ቢያልቅ እንኳ
379መልቀቅ አይሻም!
380
381ምን ጉድ ነው እዛ ውስጥ ያለው?
382… ገንዘብ?
383አይመስለኝም… ስልጣን እንዳይባል ትርፉ እንዘፍ
384እንዘፍ ነው… የሰው መውደድ እንዳንለው… ሰው
385በቃ አዲስ ሰበካ ጉባኤ ይምጣ ሲል ትሰማላችሁ…
386ሌላ ምን ይሆን?
387
388ይሄንንም ቫንኩቨር ታያላችሁ ልክ እንደ ካልጋሪው
389ልክ እንደ ዳላሱ…
390በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እልህ ታያላችሁ ቡድንም
391አለ… ጎጥም እንዲሁ… ቫንኩቨር ደጋግ ሰዎች
392አሉባት ከኔ ቢጤ ኮስማና እስከ ታታላቅ በግልና
393በቡድን እስከሚሮጡ ጎበዛዛት፤ ቤተክርስቲያንን
394በጽናት ለማቆም ከሚሮጡት ጀምሮ ለማፍረስና
395በቡድን በመቧደን እስከሚሽከረከሩ… እነዚያ
396የዋሆቹ ሀገር ቤት ያሉ አባቶችና ምእመናን ነጻ
397ያወጡኛል ብለው የሚተማመኑባቸውና
398የሚጸልዩላቸው እዚህ ውጭ ሀገር ያሉ
399የቤተክርስቲያን ሰዎች እዚህና እዚያ ሆነው
400እንደሚናቆሩ ቢያዩ ልባቸው ምን ያህል ያዝን።
401በቫንኩቨር ታዲያ ፖለቲካም አለ።
402እንደሌሎቹ ሀገራት ሁሉ።
403እንደ ኖርዌይ እንደ ሲዊዘርላንድ እንደ ዊኒፕግ
404ሁሉ።
405ቫንኩቨርም ፖ…ለ…
406ቲ…ካ… አለ።
407በጽኑ ሞራልና ሰብእና ከተገነቡት እስከ ደፋርና
408እዩኝ እዩኝ ባዩ።
409ፖለቲካን ወኔ ብቻ ወንዝ አያሻግረውም።
410ብልህነት ይጠይቃል።
411የዲያስፖራው ፖለቲካ ችግሩ ወኔ አይደለም ባለ
412ወኔያሞችማ ሞልተውታል።
413ብልሀትና መከባባር ማጣት ጠፉ እንጂ… በቫንኩቨር
414ብልሀት የለም።
415ነፋሱ እንደነፈሰ ነው።
416መሮጥ… መሮጥ… ቀጥ ሲል ደግሞ ቀጥ ነው።
417ከእንደገና መሮጥ… ያው ወያኔ በየስድስት ወሩ
418እየነቀሰ ሚያስረውና የሚገለው ወይም የሚሰራው
419ትርኢት ሲኖር እዚህም ሩጫ ነው።
420በመሰረቱ ፖለቲካ በሜዳው ነው የሚያምረው።
421እዚያው።
422እዚህ ሲመጣ ስራችን ትንሽ ነው።
423ሁላችንም እንደምንስማማው ውጭ ሀገር የሚኖረው
424ህዝብ ሀገር ቤት ለሚደረግ ፖለቲካ የገንዘብ
425ድጋፍ መስጠት ወይም እዚህ ያለንበት ሀገር ላሉ
426ዜጎችና መንግስታት የዚያን አረመኔ መለስ አገዛዝ
427ምንነት ማሳወቅ።
428ይህችን ትንሽ ስራ ለመስራት ንትርኩ ብዙ ነው።
429ሀገር ቤት ያሉትን ፖለቲከኞች ወያኔ ድራሻቸውን
430ለማጥፋት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም አንዴ
431በሀገር ክህደት ሌላ ጊዜ በዘር ማጥፋት፤ ሲለው
432ህገመንግስቱን ለመናድ ሲያሻው በአዲሱ ትኬት…
433ሽብርተኛ ወንጀል ድራሻቸውን እያጠፋ ነው።
434ለነገሩ እኛ ራሳችንም እዚህ ያለን ዜጎች
435ከመጠየቅ አንድንም።
436አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2008 ኤፍ
437ቢሲ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎችን ህገወጥ
438ዝውውር ለመከላከልና የጥራት ደረጃውን
439ለማረጋገጥ የሚያስችል ሶፍትዌር መዘጋጀቱን
440የኢትዮጵያ የምግብ
441አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 13 ፣ 2008 ኤፍ ቢ ሲ
442በቢሾፍቱ ከተማ በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው
443የኮኖርያ አፍሪካ የጨርቃ
444አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2008 ኤፍ
445ቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው
446ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ጥሎት የቆየውን የጦር
447መሳሪያ ግዢ ማእቀብ
448አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2008 ኤፍ
449ቢሲ ለረዳት ምሩቅ የዩኒቨርሲቲ መምህርነት
450በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ፈተና ከወሰዱ
451እጩ ምሩቃን አብዛኛዎቹ ማለፍ
452አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2008 ኤፍ
453ቢሲ የስዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ሲሞኔታ ሶማሩጋ
454በኢትዮጵያ ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ለሶሰት ቀናት
455ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ
456አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13 ፣ 2008 ኤፍ ቢ ሲ ከጋና
457አቻው ጋር ለ2016ቱ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ
458የተጫወተው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች
459አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2008 ኤፍ
460ቢሲ የሰው ልጅን አካላዊ ሁኔታ በማየት
461ስለስብዕናው መናገር የተጀመረው ከብዙ ሺህ
462ዓመታት በፊት እንደሆነ
463አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2008 ኤፍ
464ቢሲ በአየርላንድ በኩል ወደ አሜሪካ ሲበር
465የነበረው የኢትዮጵያ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን
466ተመልሶ ወደ
467አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2008 ኤፍ
468ቢሲ የፎቶ እና የተንቀሳቃሽ ምስል ቪዲዮ
469መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚያስችል መተግበሪያ አፕሊኬሽን
470ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ከስላሴ በዓል
471ላይ ተባረሩ
472• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል
473ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡››
474የየካ ክፍለ ከተማ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ
475• ‹‹ገዥው ፓርቲ ጥላውን የማያምንበት ደረጃ
476ላይ ደርሷል!
477›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
478ዛሬ ጥር 72007 ዓም የዓመቱን የስላሴ በዓል
479ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ
480ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ
481ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ እንደተባረሩ
482የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
483ፖሊስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል!
484›› የሚል ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች
485ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ
486አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ ማባረሩን እማኞቹ
487ገልጸዋል፡፡ ከተባረሩት ወጣቶች መካከል
488አብዛኛዎቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚገቡትንና
489የሚወጡትን አማኞች በማስተባበር ላይ እንደነበሩ
490የተገለጸ ሲሆን የተባረሩት ወጣቶች ይታሰሩ
491አይታሰሩ የታወቀ ነገር የለም፡፡
492በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመጡ
493ከፍተኛ ኃላፊዎች ለጥምቀት በዓል ሰማያዊ ቲሸርት
494ያዘጋጁትን የጃንሜዳ አካባቢው የጥምቀት በዓል
495አስተባባሪዎች፣ ያዘጋጁት ሰማያዊ ቲሸርት በዓሉ
496ላይ እንዳይለበስ በተደጋጋሚ እያስጠነቀቁ
497እንደሚገኙ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
498በፖሊሶችና በደህንነቶች ተደጋጋሚ ጫናም
499ለጃንሜዳ አካባቢ ወጣቶች የተዘጋጀው ሰማያዊ
500ቲሸርትና ‹‹ያመነ፤ የተጠመቀ ይድናል››
501የሚለውን ጥቅስ በነጭ ቲሸርት እና በሌላ ጥቅስ
502እንድንቀይር ተገደናል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ
503የፈረንሳይና ቤላ አካባቢ ወጣቶች ሰማያዊ
504ቲሸርቱን እንዲቀይሩ ጫና ቢደርስባቸው
505አንቀይርም በሚል አቋማቸው መጽናታቸው ታውቋል፡፡
506በተመሳሳይ ጥር 6 የአዲስ አበባ መስሪያ ቤቶችና
507ወረዳዎች ኮሚኒኬሽን ኃላፊዎች አዲስ አበባ
508መዘጋጃ ቤት ባደረጉት ስብሰባ የየካ ክፍለ ከተማ
509ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ
510ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ‹የፈራ ይመለስ›
511የሚል ሰማያዊ ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ
512ሰንብቷል፡፡›› ሲል ሪፖርት ማቅረቡን
513የስብሰባው ተሳታፊዎች ለነገረ ኢትዮጵያ
514ገልጸዋል፡፡
515ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ
516ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ደህንነት፣
517ፖሊሶችና ካድሬዎች እያንዳንዱን የህዝብ
518እንቅስቃሴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በማገናኘት ወቀሳ
519የሚያቀርቡት ህዝብ ውስጥ ብሶት እንዳለ፣
520ሰማያዊም የህዝብን ብሶት እንደሚያሳማ
521ስለሚያውቁ፣ ከምንም በላይ ገዥው ፓርቲ የራሱን
522ጥላ የማያምንበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ ነው››
523ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ
524ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ባነሱባቸው ጊዜያት ሁሉ
525ገዥው ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲን ‹‹የሙስሊም ፓርቲ
526ነው›› በሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሰራጭ እንደነበርና
527ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰጠው የ‹‹አብዮታዊ
528ዴሞክራሲ›› ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲን ሲወቅስ
529እንደከረመ ያስታወሱት ኃላፊው አሁንም ፓርቲውን
530ከእያንዳንዱ የህዝብ እንቅስቃሴ ጋር እያገናኘ
531ቢበረግግ አያስገርምም ብለዋል፡፡
532የብፁዕ አባታችን የአቡነ መልከ ጼዴቅ ፪ኛ ዓመት
533የዕረፍት መታሠቢያ ቀን ነገ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓም
534በመላው ኢትዮጵያ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ባሉ
535አብያተ ክርስቲያናት በጸሎተ ፍትሐትና በቅዳሴ
536ታስቦ ይውላል።
537በይበልጥ ደግሞ በምሑር ኢየሱስ ገዳም ብዙ
538የመንፈስ ልጆቻቸው፣ አረጋውያን መነኮሳትና
539ተማሪዎች አስበዋቸው ይውላሉ።
540የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተስቦች አሁንም ቢሆን
541በመላው ዓለም የምትገኙ ሁላችሁም የብፁዕ
542አባታችን በርካታ ሥራዎችን ዳር ለማድረስ
543በምትችሉት ሁሉ እንድትራዱ እናሳስባለን።
544እግዚአብሔር አምላክ ደጋግ አባቶችን ያብዛልን፤
545የብፁዕ አባታችን ነፍስ በገነት መንግሥተ ሰማያት
546ያሳርፍልን።
547የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ ገቢው
548ብጹዕነታቸው ለሰበሰቧቸው ልጆች ማሳደጊያ እና
549ለጀመሯቸው ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚሆን ተንቦላ
550እያከፋፈለ ይገኛል።
551እጣው በጥቅምት ወር እንደሚወጣ የተገለጸው
552ተንቦላን በየእስቴቱ ለማከፋፈል በጉ ፈቃደኛ
553የሚሆኑ የብጹዕነታቸውን ወዳጆች ጥሪ እያቀረበ
554እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰቦች
555በ 202-656- 202-656-9268 በመደወል ኮሚቴውን ማነጋገር
556እንደሚችሉ ገልጻል።
557በተያያዘ ዜናም በአንድ አንድ ኢትዮጵያዊያን
558በሚበዙበት የአሜሪካ ግዛቶች በዲሲ
559እንደተደረገው አይነት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት
560ለማዘጋጀት እያሰቡ ያሉ ምዕመናን እንዳሉ
561የተገለገ ሲሆን ለዚህ ዝግጅት ማስተባበር ፈቃደኛ
562የሆኑ ካህናት አባቶች ሰንበት ተማሪዎች እና
563ምዕመናን በንዑስ ኮሚቴ ለማደራጀት ይቻል ዘንድ
564ከላይ በተገለጸው ስልክ በመደወል ኮሚቴውን
565ማነጋገር የሚቻል መሆኑን አሳስበዋል።
566ነገ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፫ ዓም ብፁዕ አባታችን
567ያረፉበት አንደኛ ዓመት መታሠቢያ ቀን ነው።
568በመላው ኢትዮጵያ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ባሉ
569አብያተ ክርስቲያናት በጸሎተ ፍትሐትና በቅዳሴ
570ታስበው ይውላሉ።
571በይበልጥ ደግሞ በምሑር ኢየሱስ ገዳም ብዙ
572የመንፈስ ልጆቻቸው፣ አረጋውያን መነኮሳትና
573ተማሪዎች አስበዋቸው ይውላሉ።
574አምላካችን እግዚአብሔር የብፁዕ አባታችንን
575ነፍስ በገነት መንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን አሜን።
576ሚያዚያ 23 2003 ከቀኑ 5፡30 ደብረ ምሕረት ቅዱስ
577ሚካኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ ለተገኘ ሰው ዛሬ
578ምን ተፈጥሮ ነው ሰዉ ሁሉ እንዲህ ተፍ ተፍ የሚለው
579ያስብላል።
580እናቶችና እህቶች የምግብ ማዘጋጃ ክፍሉን
581ተቆጣጥረውታል።
582ከፊሉ ወጣቶች አዳራሹን ሲያስውቡ ከፊሎቹ ደግሞ
583የቪዲዮ ፣ የድምፅ ፣ የፕኦጀክተር እንዲሁም
584ዝግጅቱን ለመላው አለም ለማስተላለፍ
585የሚረዷቸውን ኮምፒተሮች መልክ መልክ ያሲዛሉ።
586የመርሐ ግብሩ ሰዓት ደርሶ ከዲሲ እና አካባቢው
587የተጋበዙ እንግዶች ሲገኙ አዳራሹ አምሮና ሰምሮ
588ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ብዙ ሩጫ የነበረበት
589አይመስልም።
590ብፁዓን አባቶች፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፣
591ካሕናት አባቶችና ዲያቆናት ቦታቸውን ከያዚ በኃላ
592ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፀሎት ተከፍቶ
593በኮሚቴው ሰብሳቢ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፓርት ቀረበ
594፤ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
595አስተዳዳሪ መላከ ሕይወት ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ
596ባህሩና በብፁዕ አቡነ አብርሃም የዲሲና አካባቢው
597አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ መልከ ጼዴቅ
598በሕይወት በቆዩበት ጥቂት አመታት
599ለቤተክርስቲያን ስላበረከቱት መንፈሳዊ፣
600ማሕበራዊ እና የልማት እንቅስቃሴዎች ትንታኔ
601ከተሰጠ በኋላ የገቢ ማሰባሰቢየ ዝግጅት በቀሲስ
602ዘበነ እና በመምህር ሕዝቂያስ ተከናውናል።
603በጉባኤው ላይ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ እጅግ
604የሚያስደንቅ እና እውነትም ብጹዕነታቸው አንድ
605ጠይቀው ሁለት የሚያገኙ ናቸው የተባለውን ቃል
606እንድናስታውስ አርጎናል።
607የዝክረ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የሆኑት
608ቆሞስ አባ ፈቃደ ኢየሱስ ዝግጅቱን አስመልክቶ
609አነጋግረናቸው እንደገለጹልን ዝግጅቱ እጅግ
610ከተጠበቀው በላይ የተሳካ መሆኑን ገልጸዋል።
611አያይዘውም በወንድማቸው በብጹዕነታቸው እረፍት
612እጅግ በጣም እንዳዘኑ በማስታወስ አሁን ከዚህ
613ዝግጅት በኋላ ምን ተሰማዎት ብለን ለጠየቅናቸው
614ጥያቄ ሲመልሱ በፊትም ብጹዕነታቸው በአካል
615ስለተለዩን ሳይሆን በየቦታው ተሰርቶ የማያልቅ
616የሚመስል ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ጀምረው ፤ ልጆችን
617ለማሳደግ በየቦታው ሰብስበው በመሔዳቸው
618የተሰበሰበው ይበተናል፤ የተስተካከለው
619ይበተናል ነበረ ሀዘኔ።
620አሁን ብጹዕነታቸው “እኔ እግዚአብሔር
621ያመለከተኝን እጀምራለሁ የሚያስፈጽሙትን ደግሞ
622እሱ ያስነሳል” እንዳሉት ይኸው ብዙዎችን
623አስነስቷል ከእንግዲህ ወዲህ ሀዘን የለም
624ሥራዎችን በአግባቡ ማስፈጸም እንጂ ብለዋል።
625በመጨረሻም በዝግጅቱ አስፈላጊውን ሁሉ ላበረከቱ
626ምዕመናን በእግዚአብሔር ስም ምስጋና አቅርበዋል።
627ዝክረ መልከ ጼዴቅ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ
628በአካል በነበሩበት ጊዜ የጀመሩዋቸውን መንፈሳዊ
629ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ
630በመንፈሳዊ ልጆቻቸው የተቋቋመ ማኅበር ነው።
631ዋና አላማውም ብፁዕነታቸው ያስጀመሯቸውን አያሌ
632መርሃ ግብሮች ከግብ ለማድረስ ገንዘብ ማሰባሰብ
633ነው።
634ማኅበሩ ዋሽንግተን ዲሲ ማዕከል በማድረግ በአለም
635ዙሪያ ያሉ መንፈሳዊ በጎ አድራጊዎችን ለማቀፍ
636የተቋቋመ ነው።
637በአለም ዙሪያ ያላችሁ የብፁዕነታቸው ወዳጆች እና
638ልጆች አስፈላጊውን የገንዘብ ፣ የጊዜ ፣
639የባለሙያ እርዳታ ታደርጉ ዘንድ እንዲሁመ
640በእግዚአብሔር ስም ተጋብዛችኋል።
6411 - 2 በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው
642በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች
643ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት
644ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤
6453 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ
646ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
6474 ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ
648አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ
649ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።
6505 ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤
651አሜን።
6526 በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ
653ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት
654እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ 7 እርሱ ግን ሌላ
655ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ
656የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ
657አንዳንዶች አሉ እንጂ።
6588 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥
659ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን
660ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
6619 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ
662እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም
663ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
66410 ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ
665አሰኛለሁን?
666ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን?
667አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ
668ባልሆንሁም።
66911 ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ
670ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤ 12 ኢየሱስ
671ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው
672አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።
67313 በአይሁድ ሥርዓት በፊት እንዴት እንደ ኖርሁ
674ሰምታችኋልና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን
675ያለ ልክ አሳድድና አጠፋ ነበር፥ 14 ለአባቶችም
676ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ
677በዘመኔ ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ
678ነበር።
67915 - 16 ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ
680በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል
681ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ
682ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና
683ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ 17 ከእኔም በፊት
684ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥
685ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ
686ደማስቆ ተመለስሁ።
68718 ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ
688ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት
689ቀን ሰነበትሁ፤ 19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም
690ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።
69120 ስለምፅፍላችሁም ነገር፥ እነሆ፥
692በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት አልናገርም።
69321 ከዚያ ወዲያ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ አገር
694መጣሁ።
69522 በክርስቶስም ያሉት የይሁዳ ማኅበሮች ፊቴን
696አያውቁም ነበር፤ 23 ነገር ግን።
697ቀድሞ እኛን ያሳድድ የነበረ፥ እርሱ በፊት
698ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል
699ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ነበር፤ 24 ስለ እኔም
700እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር።
701ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ይጫኑ
702ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
703መዝ67፤31
704ኢትዮጵያ በጥንት የግብጻውያን ቋንቋ ጱንጥ፤ “ቶ”
705ኔቶር፤ ኩሽ፤ እየተባለች ትጠራ ነበር።
706ጱንጥ የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ካለው ፉጥ
707ከሚለው ስም ጋራ ይመሳሰላል።
708ዘፍ 10፤7 “ቶ”ኔቶር ማለትም ሀገረ እግዚአብሔር
709ማለት ነው ይላሉ የቋንቋው ባለቤቶች፤
710ሙሴ ብሉይ ኪዳንን ሲጽፍ ይህችን ቅድስት ሀገር
711የኩሽ ምድር እያለ የጻፈው በግብጽ ተወልዶ ያደገ
712እንደመሆኑ መጠን የ ግብጻውያንን ቋንቋ ያውቅ
713ስለነበር ነው፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኩሽ
714የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የካም
715የመጀመሪያው ልጅ እንደሆነ ነው።
716ዘፍ 10፤1-7 1ኛ ዜና 1፤810
717ኩሽ የሚለው ቃል ሀገርን ሲያመለክት ኢትዮጵያ
718ተብሎ ተተርጉሟል።
719ዘፍ 2፤13
720ኢትዮጵያ የሚለው የቃሉ ትርጉም የሕብር፤ የመልክ፤
721የሀገር ስም ሲሆን የትውልዱ ማንነት ሲመዘን
722ቁመቱ እንደአዛሄል ቀውላላ፤ እንደድንክም በጣም
723አጭር ያልሆነ መጠነኛ ቁመት ያለው ዜጋ ነው፡፡
724በጣምም ነጭ ያልሆነ ከመጠን በላይም እንደቁራ
725ያልጠቆረ፤ እንደለምጻምም ያልተንቦገቦገ፤ዓሣ
726የሚመስል ጠይም መልክ ያለው ነው፡
727ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ40
728ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ዘፍ 2፤13 ኤር 12፤23፤ ኢሳ 18፤1
729ሶፎ3፤102፤12 2ኛ ዜና 14፤9-45 2ኛ ነገ 19፤9፤ ናሆ 3፤8-10
730ወዘተ
731ኢትዮጵያ የኩሽ ምድር ለመባል የበቃችበት ዋናው
732ታሪካዊ ምክንያት ቀደም ሲል ከላይ እንደተገለጸው
733የካም የመጀመሪያ ልጅ የኩሽ ዘሮች ስለሰፈሩባት
734ነው የካም ልጆች ኩሽ ምጽራይ ፉጣ እና ከነዓን
735ናቸው።
736ዘፍ10፤1-8
737የኩሽ ልጆችም ሳባና አቢሳሰብታ ይባሉ ነበር ዘፍ
738107-8 ይህችው ሀገር በሌላ አጠራር የሳባ ምድር
739በተለይም በምዕራባውያን ዘንድ አቢሲኒያ
740እየተባለች ስትጠራ ቆይታለች ምናልባትም ይህን
741ስያሜ ያገኘችው እነዚህ የኩሽ ልጆች ሳባና አቢሳ
742ሰብታ ስለሰፈሩባት በስማቸው አስጠርተዋታል
743ማለት ነው ብለው ምሁራን አባቶቻችን ይተርካሉ፡
744ያስተምራሉ፡፡
745ለምሳሌ ያህል ከላይ የጠቀስናቸው ሁለቱ ታላላቅ
746የታሪክ ባለቤቶች ሮምንና አሌክሳንደርያን
747ከመሰረቱ በኋላ በራሳቸው ስም እንዳስጠሯቸው
748ኢትዮጵያም በ አቅኒዎቿ ስም ማለትም በሳባ የሳባ
749ምድር፤ በአቢሳ አቢሲኒያ እየተባለች ለብዙ
750ዘመናት ስትጠራ ቆይታለች አሁንም ትጠራለች።
751ሆኖም ግን የእኛ አላማ ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ
752ከየት እንደመጣና አቕኒዎቿም እነማን እንደነበሩ
753በመጠኑ ለትውልዱ ለመግለጽና ለማስተዋወቅ ያህል
754እንጂ ስለሮምና ስለአሌክሳንደርያ አመሰራረት
755ግድ ብሎን አይደለም አቢሲኒያ የሚለውን ቃል
756ዐረቦች ብዙ ጊዜ ሀበሽ በማለት ይጠቀሙበታል፡
757ይህውም ድብልቅልቅ፤ ውጥንቅጥ ለማለት ነው፡
758ነገር ግን የታሪክ ተመራማሪዎች በቂ መረጃ
759የለውም ይላሉ፡፡
760በ3600 ዘመን አካባቢ ከጌታ ልደት በፊት በየመን
761ይኖሩ የነበሩ ከነገደ ሴም የተከፈሉ ነገደ
762ዮቅጣን በባብ አልመንድብየመከራ በር ማለት ነውአካባቢ
763ገብተው ሰፈሩባት በዚህች ሀገር ከሚኖሩ የኩሽ
764ማለትም ከኗሪዎቹ ጋራ ተጋብተው እየተበራከቱ ሄዱ
765ሀገሪቱንም ምድረ አግዓዚት ምድረ አግዐዝያን፤
766ትርጉም ነጻ ሀገር፤ ነጻነት ያላቸው ስዎች ፤መኖሪያ
767ብለው ጠሯት በመጨረሻም ለዚች ሀገር የተሰጣት
768ስያሜ ኢትዮጵያ የሚል ነው፡፡
769በሀገራችን እንደሚተረከው “ኩሽ” ሁለት ስም
770ነበረው።
771ሁለተኛው ስሙ “ኢትዮጲስ” ይባል ነበር በዚህ
772መነሻነት አቅኒዎቹ ባባታቸው ስም ሀገሪቷን
773ኢትዮጵያ ብለዋታል።
774እነርሱም ኢትዮጵያውያን ይባላሉ እየተባለ
775ይተረካል።
776ነገር ግን በጽርዕግሪክ ቋንቋ “ኢትዮጲስ”
777የተባለው በዕብራይስጥ “ኩሽ” የተባለው
778የመጀመሪያው የካም ልጅ ነው።
779ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገጽ 248 ”ኢትዎፕስ” ማለት
780በጽርዕ ግሪክ ሁለት ዓይነት ትርጉምን ያሳያል።
781የስው ስም ሲሆን ጥቁር፤ የሀገር ስም ሲሆን ደግሞ
782ቆላ በረሃ፤ ምድረ-በዳ ማለት ነው፡፡ስምነቱም
783ኩሽ ከሞተ በኋላ በ2450 ዓመት ሰብዓ ሊቃናት ያወጡት
784ስም ሲሆን በሱዳን ዙሪያ ያለችውን ክፍል የኩሽ
785ልጆች የሚኖሩባት ሀገር ስለሆነች በሰብዓ ሊቃናት
786ትርጉም መሰረት ኢትዮጵያ ተብላለች፡፡ ዘፍ 2፤13
787በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን የተጻፈው
788መደበኛው ኢትዮጵያ ግን ታላቁን የሳራን በረሃ
789ጨምሮ ያለው ክፍል ነው።
7902ኛ ዜና 14፤9 12፤13 16፤8
791ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገጽ 248 “ይዌልጥኑ ኢትዮጵያዊ
792ማዕሶ ወነምር ሕንብርብሬሁ” በውኑ ኢትዮጵያዊ
793መልኩን ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ
794ዘንድ ይችላልን?
795ኤር 13፤23
796አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ ኢትዮጵያ የሚለው
797ቃል ከግሪኮች የተወረሰ ነው “ኢቶስ” ዋዕይሙቀት
798“ኦፕ” “ሲስ” ገጽ አርአያ ማለት ነው እነዚህ
799ሁለቱ ቃላት ሲጣመሩ “ኢቲኦፕያ”ወይም“ኢቲኦፕስ”
800የሚል ይወጣል፡ ይህም እንደመጀመሪያው “ኤቴኦፕያ”
801ቢል የሀገሪቱን ቆላነት ያመለክታል “ኢቲኦፕስ”
802ቢል የሕዝቧን ምንነት የሚገልጽ ይሆናል፡
803የግሪኮች የቅኔ ገጣሚ በሆነው በሆሜር መጽሐፍ
804ደግሞ ቀዩንም ኢትዮጵያ ብሎት ስለሚገኝ ኢትዮጵያ
805ማለት ጥቁር ብቻ ሳይሆን ቀይ ፤የቀይ ዳማ ቀለም
806ያለው ሕዝብ ማለት ነው፡የኢትዮጵያውያን ቅድመ
807አያት ኩሽ የነበረው በ2734 አካባቢ ሲሆን እርሱ
808በሞተ በ2450 ማለት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ284
809መሆኑ ነው መጻሕፍተ ብሉያትን ከዕብራይስጥ ወደ
810ጽርዕግሪክ የመለሱየተረጎሙ ሰብዓ ሊቃናት
811ነቢዩ ሙሴ ኩሽ እያለ በብሉይ ኪዳን የጻፈውን
812ኢትዮጵያ በሚል ቃል ለውጠውታል።
813ባለቅኔው ሆሜርም ስለኢትዮጵያ ሲናገር
814ኢትዮጵያውያን በጉልበት ኃያላን፤ በውበት
815የተደነቁ፤ የዋሆች በጠባይ ጭምቶች፤ ትህትናን
816ፍቅርን የተመሉ ናቸው ብሏል።
817ከዚህ የተነሳ ከግሪኮች 12 አማልክት አንዱ
818የመጀመሪያ ታላቁ እንደ-አባት የሚቆጠረው ዜውስ
819የተባለው ኢትዮጵያውያንን ለማየት፤ ከእነርሱ
820ጋራ ለመብላት ወደውቅያኖስ ወረደ ብሏል።
821ኢትዮጵያ በላስፎችና በታሪክ ሰዎች ዘንድ ብቻ
822ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ የታወቀች ሀገር፤ የሕዝቧ
823ማንነት በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸ፤ የጂኦግራፊ
824አቀማመጧ እና ከባቢ አየሯ ለፍጥረታት ሁሉ
825ተስማሚ የሆነ ነው፡፡ ሙሴ የስነ-ፍጥረትን
826ዝርዝር ሲጽፍ በአባይና በተከዜ የተከለለች
827መሆኗን ያወሳት በኢትዮጵያና በእግዚአብሔር
828መካከል ያለውን ፍቅር አስመልክቶ ነቢዩ ዳዊት
829ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች
830ሲል በግልጽ የተነበየላት ቅድስትና ውብ ሀገር
831ናት።
832መዝ 67፤31
833ስለ ኢትዮጵያ የሃይማኖትና የሞራል ክብር
834የተናገረ ሶፎንያስ ኢትዮጵያ በአንድ አምላክ
835የምታምን ሀገር መሆኗን ሲገልጽ “እምነ ማዕዶተ
836አፍላገ ኢትዮጵያ ያመጽኡ ሊተ መሥዋዕተ
837ከኢትዮጵያ ወንዝ ማዶ የሚሰግዱልኝ የተበተኑት
838ልጆቼ መባዬን ይዘው ወደኔ ይመጣሉ” ብሏል ሶፎ 3፤10
839ሃይማኖቷም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትባላለች
840ኦርቶዶክስ ቃሉ የጽርዕግሪክ ሲሆን ጥምር ቃል
841ነው” ኦርቶስ” ቅጽል፤ ርትዕት ቀጥተኛ
842ማለት ነው።
843“ዶክስ” ማለት ደግሞ “ዶኮ” ካለው ግስ
844የወጣ ሲሆን ትርጉሙ ማሰብ መገመት ማመን ማለት
845ነው “ኦርቶዶክስ” እንደ አንድ ስም ሆኖ ተጠቃሎ
846ሲፈታ ቀጥተኛ ሃሳብ፤ በሃይማኖትም የቀናች
847ቀጥተኛ ሃይማኖት ማለት ነው
848የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
849አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 1974 ዓም
850ሪቪል፡ ከመንፈሳዊነት ጋር ተያይዞ መዝፈን
851አቁመሻል?
852ዘሪቱ፡ መንፈሳዊነት ሁለገብና የሁለንተናችን
853ለውጥ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ደግሞ ከአለማዊነት
854ስንወጣ የማይነካ የህይወታችን ክፍል የለም፡፡
855ሁሉም ነገር እኔ እንደምለውና ዓለም
856እንደምትሰብከው ሳይሆን እግ ዚአብሄር
857እንደሚለው የማድረግና የመሆን ሂደት ነው፡፡
858በዚህ ውስጥ ታዲያ እንደ ሁሉ ነገሬ የጥበብ
859ስራየም ሳይፈተሸ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሙዚቃም
860ይሁን ፊልም፤ ብቻ ምንም ነገር ልስራ የማደርገው
861ነገር እግዚአብሄር የሚፈልገውን መለዕክት
862ያደርሳል ወይ?
863ሰዎችን ይጠቅማል ወይ?
864ደሞስ እንደሱ ፍቃድና ልክ ሰዎችን ያሳዝናል?
865ያስደስታል ወይ ብዪ በመጠየቅና ይልቁንም ከሱ
866ከራሱ መለዕክትን በመቀበል ወደ መስራት
867መንፈሳዊነት እያደኩ ነው፡፡ መዝፈን ይሁን
868መዘመር አላውቅም፡፡ የማውቀው እግዚአብሄር
869እንደሚከብርበት ነው፡፡
870ሪቪል፡ ግን ዝናና ገንዘብን መስዋትነት ማድረግ
871የሚከብድ አይደለም?
872ዘሪቱ፡ እኔ ለመተው የሚከብድ የገንዘብ ክምችት
873የለኝም፡፡ዝናንም በተመለከተ ዘማሪዎች
874ከዘፋኞች ባልተናነሰ ዝነኞች የሆኑበት ዘመን
875እንደሆነ ነው የማስበው፡፡ ከዝና ወደ ዝና
876ብሸጋገር አሁን ከምከፍለው ዋጋ የበለጠ
877እንደምከፍል አውቃለሁ፡፡
878ሪቪል፡ ቤት መኪናና ሌሎች አያስፈልጉም ብለሽ
879ነው የምታምኚው?
880ዘሪቱ፤ እኔ የማምነው ከሆነ ቦታ ተነስተህ የሆነ
881ቦታ ለመድረስ ትራንሰፖርት እንደሚያስፈልግ ነው፡፡
882መኪናው ያንተ ከሆ ጥሩ፤ ካልሆነም መኖርህን
883ለማታውቅበት ለዛሬ ባለቤትነትህ ያለው ፋይዳ
884ውስን ነው፡፡ የቤትም አስፈላጊነት መጠለያነቱ፤ትርጉሙም
885አብረውህ በሚኖሩት ሰዎች እንጂ በባለቤተረነት
886ካርታው አይደለም፡፡ የባለቤተረነት ዋስትና
887ለእኔ ትርጉም የለሽ ነው፡፡እግዚአብሄር ወዶ
888ለሚጨምርልኝ ለእያንዳንዱ ቀን የሚያስፈልገኝን
889ሁሉ እንደሚያዘጋጅልኝ አምናለሁ፡፡
890ሪቪል፤ እንደዚህ ያለ ህወት ግን ላገባችና
891በተለይም ልጆች እናት ለሆነች ሴት አይከብድም?
892ዘሪቱ፤ እንደዚህ ያለ ህይወት ለማንም ቀላል
893አይደለም፡፡ በተለይም እንዳልከው፤ቤተሰብ
894ላለን ሰዎች ደግሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ነገር ግን
895ይህ በስጋዊ አቅማችን ስንሞክረው ነው፡፡ ሰው
896የመሆንን ትርጉም ለመረዳት በፈቀድን መጠን ግን
897ራሱ እግዚአብሄር በእና ውስጥ ይችለዋል፡፡
898ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ማለት፤ ሰው በሀጢያት
899ከመውደቁ በፊት ወደ ነበረው ማንነት የመመለስ
900ጉዞ ማለት ነው፡፡ ያ ማንነት ደግሞ
901ከእግዚአብሄር የመሆንና ማንነቱን የማንፀባረቅ
902ህይወት ነው፡፡ በመሬታዊ ገደብ እሱን ማንፀባረቅ
903አይቻልም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አሰልጣኝነት
904ከመሬታዊ ገደብ ወደ እሱ ማንነት የሚያሻግረን
905መመሪያ ሁሉ ደሞ በቅዱስ ቃሉ ወስጥ አለ፡፡
906ኢየሱስ ለምን አይነት ክብር እንደጠራን ጠንቅቆ
907ስለሚያውቅ ከንግዳችን፣ ከቤተሰባችንና
908ከራሳችን ጭምር በላይ እሱን እንድናስቀድም ነው፡፡
909ይህ ሲሆን ብቻ ደቀመዛሙርቶቹ ልንሆን እንምንችል
910በግልፅ አስቀምጦልናል፡፡ ስለዚህ እሱን
911በመከተል ውስጥ ምንም አይነት አቋራጭ አልፈልግም፡፡
912ሪቪል፤ ባለቤትሽ በዚህ ደስተኛ ነው?
913ዘሪቱ፤ በጣም ደስተኛ ነው እንጂ፡፡ የምተገዛ
914ሚስት አድረጎለታል፡፡ ከዚህ ህይወት ጋር
915በተዋወኩባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በእኔ ላይ
916ባስከተለው የማንነት መናጋት ተከትለው በመጡ
917ጥፋቶች ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ ሚስትህ ፈርሳ
918እስክተሰራ መታገስ ቀላል ነገር አይደለም፡፡
919ከመጀመሪያዋ የተሻለች ሚስት እንዳለችው እሱ
920ምስክር ነው፡፡
921አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2008 ኤፍ
922ቢ ሲ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል
923ችሎት በእነ ሶሊያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ዛሬ
924ብይን ሰጥቷል።
925ጦማሪያን እየተባሉ የሚጠሩት እነዚህ ግለሰቦች
926ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ
927ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተከሰሱ ነበሩ።
928በዚህ የክስ መዝገብ ውስጥ ከሚገ
929አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2008 ኤፍ
930ቢሲ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው
931አምስተኛ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን
932ርዕሰ መስተዳድር እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
933መረጠ።
934በዚህም መሰረት አቶ አባይ ወልዱን ርዕሰ
935መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ ሲመርጥ፥ አምባሳደር
936ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ ደግሞ በምክትል ርዕሰ
937መስተ
938ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ
939ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ ሞላ አስገዶምን
940አስመልክቶ መስከረም 3 ቀን 2008 ዓም
941================================================= በኢትዮጵያ
942የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ
943ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓትኢህአዴግ
944የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠ
945ያኔ ስትዘፍን እና በየመሸታ ቤቱ ሰካራም
946ስታዝናና ምንም ያላላችኃት ሁላ ዛሬ ኢየሱስን
947ነው የምከተለው ስትል ምነዋ ለስድብ አፋቹ
948ተከፈተ?
949ነውር እንወቅ እንጂ ጎበዝ!
950አበዛቹት እኮ ሰው ዘፈን አቆምኩ ባለ ቁጥር
951ምንድን ነው መዘርጠጥ?
952ማንም እኮ የፈለገውን እምነት የመከተል ሙሉ
953መብት አለው።
954ደግሞስ ዘፈን ማቆም በየትኛው እምነት ነው
955ስህተት የሆነው?
956በየደብተራ መተተኛ ጠንቋይ መንደር ስር በበኣላት
957ስም ስታፈነድዱ ማን ሰደባቹ?
958እስኪ በቅድሚያ የገዛ እምነታቹን እወቁት ከዛ
959ኑሩት።
960ዝም ብሎ መቦርተፍ ያስገምታል።
961ምን ያሉ ጉድ ናቸው ባካቹ
962የኢትዮጵያ ሕዝብም ይፈታ!
963ለ484 ቀናት በር በሌለው እስር የቆየው ድምጻዊው
964ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ በር ያለው እስር ቤት
965የመፈታቱ ዜና አስደስቶናል የኢትዮጵያዊው
966የሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ መፈታት ጥቅሙ አብሮ ታስሮ
967የነበረውን የኢትዮጵያ ሙዚቃንም ይፈታዋል ሲሉ
968የሙዚቃ ባለሙያዎች ሲተነትኑ ተደምጧል አዎ ቴዲ
969አፍሮ ከታሰረ ወዲህ፤ የ2 ኤፍ ኤም ራድዮዎች
970መኖርም ታክሎበት በሀገራችን የሲዲ እና የካሴት
971ሽያጭ ወርዶ በርካታ የሙዚቃ አሳታሚዎች ሲያማርሩ
972ተደምጠዋል ካሁን በሗላ ቴዲ ተፈቶ የሚሰራው
973የሙዚቃ አልበም ገበያውን ያንቀሳቅሰዋል የሚል
974እምነት አለ ቴዲ ከእስር ቤት ከተፈታ በሗላ
975ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-ምልልስ ወቅት የተናገረው
976ነገር ቢኖር 'በቃሊቲ በርከት ያሉ ጥሩ ጥሩ ሰዎች
977እንዳጋጠሙትና መልካም ጊዜን እንዳሳለፈም
978ተናግሯል ከእነዚህ መልካም ሰዎች መካከል ደግሞ
979በኢሕአዴግ የታሰሩ የሕሊና እስረኞች
980እንደሚገኙበት አንጠራጠርም በኢሕአዴግ ዘመን
981ከታሰሩ የሕሊና እስረኞች መካከል ‘’በደህና"
982ሲለቀቅ ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያው ነው ለማለት
983እንደፍራለን በእርግጥ በደህና መፈታቱን ወይም
984ምን አይነት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተሰጡት ወደፊት
985ጊዜ የሚፈታቸው ሲሆን ቢያንስ ቢያንስ ግን ቴዲ
986እንደ ፕሮፌርሰር አስራት ሊሞት ሲል አለመውጣቱም
987ተመስገን ነው ቴዲ አፍሮን ለማስፈታት በርከት
988ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲጮኹ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ
989ቴዲ የፖለቲካ እስረኛ እንደሆነ በመመስከር
990እንዲፈታ ጭምር ሲታገሉ ነበር አሁን ቴዲን
991ካስፈታን ደግሞ ሌሎች የሕሊና እስረኞችን
992ለማስፈታትና 'ተቃወምከኝ ብሎ የማሰር" ፖለቲካ
993በኢትዮጵያ ቀርቶ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን መታገል
994አለብን ከነዚህ ውስጥ አንዷ ደግሞ በግፍ
995የታሰረችው ብርቱካን ሚደቅሳን ጀምሮ፤ ሰሞኑን
996ለኢሕአዴግ ሚዲያዎች የወሬ ወፍጮ የሆነው የኦነግ
997አባል ናቸው ተብለው የታሰሩት እነ በቀለ ጅራታና
998ሌሎች በኢሕአፓ፣ በአርበኞች ግንባር፣ በግንቦት
9997፣ በቅንጅትና በሌሎችም ምክንያት የታሰሩ
1000ንጹሀን የዲሞክራሲ ታጋዮች እንዲፈቱ ትግላችንን
1001የበለጠ ለማጠናከር ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል
1002የመለስ ዜናዊ አስተዳደር የሕሊና እስረኞችን
1003በአጠቃላይ አዲሱን የኢትዮጵያን ዓመት
1004በማስመልከት ይፈታል ብሎ ማሰብ ከዝንብ ማር
1005እንደመጠበቅ ቢሆንም ይህንን እንዲያደርግም
1006ግፊት የማድረጉ ሀላፊነት በእኛው እጅ ያለ
1007ይመስለናል የሕዝብ ልጅ የሆነውን ቴዲ አፍሮን
1008ፈትቶ ሌሎች ሺሕ ቴዲ አፍሮዎችን በእስር ቤት
1009ያጎረው ኢሕአዴግ በማናለብኝነት
1010የሚያደርጋቸውን የሰብአዊ ጥሰቶች እንዲያቆም
1011ቢመከር አልሰማ ካለ ሰንብቷል አምባገነን
1012ሥርአት መሆኑና የሕዝብ ድምጽን የማያከበር
1013መሆኑም ሲነጋ ሁሉም አውቆታል ለዚህም ነው
1014አሜሪካኖቹ ፊት የነሱት እንደ አፍሪካ ሕብረት
1015መቀመጫነቷ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም
1016ሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በአፍሪካ በተለያዩ
1017ሀገራት ሲዟዟሩ ኢትዮጵያን ሊያዩዋት ቢገባም
1018ሳያይዋት የቀሩትና መንግሥቱን እርቃኑን
1019ያስቀሩት በዚሁ በአምባገነንታቸው ነው ይህ
1020ሊሆን የቻለበት ምክንያት ደግሞ እኛ በውጭ
1021ያለነው ወገኖች በየቀኑ በምናደርገው በሰልፍ፣
1022በፒቲሽንና በሌሎችም መልኩ ማጋለጦች መሆኑን ልብ
1023ልንለው ይገባል ዛሬ በኢትዮጵያ ከሀገር ወዳድ
1024ፖለቲከኞች ውጭ በሀገራችን መዋዕለ ነዋያችንን
1025አፍስሰን፤ እኛም ተጠቅመን ወገናችንም የሥራ
1026እድል ያግኝ ብለው የንግድ ድርጅት ያቋቋሙ
1027ባለሀብቶች በገበያ ተወዳድረው በሀዜብ መስፍን
1028የሚመራውን የኢሕአዴግ ግዙፍ የንግድ ተቋም
1029በመጣላቸው እየታሰሩ ለመሆኑ ለዚህ መልእክት
1030አንባቢዎች መንገር ለቀባሪው እንደማርዳት
1031ይሆናል ሆኖም ግን ለወገናችን የሥራ እድል
1032የፈጠሩ ባለሀብቶችም ካለ አግባብ 'የሙስና" ታፔላ
1033ተለጥፎላቸው ሲታሰሩም ዝም ማለት የለብንም
1034የመንግስት ባለስልጣናት እንደፈለጓቸው
1035የፈለጉትን ሲያስሩ፣ ሲፈቱ፣ ሰብአዊ መብቱን
1036ሲጥሱ እኛ ጋር ካልደረሰ ምን ቸገረን ብለን
1037በቸልተኝነት መመልከት የለብንም የሀገራችን
1038ሰው ሲተርት "ባልጀራህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ"
1039ነውና ዛሬ የምናውቀው ሲታሰር የነገው ባለተራ
1040እኛም እንደሆንን ማሰብና ከወዲሁ በቃችሁ
1041ልንላቸው ይገባል በቀጣዩ ዓመት ይደረጋል
1042በሚባለው "ምርጫም" ትክክለኛ እንደ ጋና ያለ
1043የሚያስቀና ምርጫ ተደርጎ የመለስ ዜናዊ
1044አስተዳደር ስልጣኑን በሕዝብ ለተመረጠ ፓርቲ
1045አስረክቦ ከእስር እንደማንወጣ የታወቀ ነው ይህ
1046ከሆነ ደግሞ በቀጣዩ 5 አመታት በርከት ያሉ ቴዲ
1047አፍሮዎችና በርከት ያሉ ብርቱካን ሚደቅሳዎች
1048እንደሚታሰሩ አንጠራጠር ስለዚህ መብታችንን
1049አውቀን ስለመብታችን እንጠይቅ ሰዎች ሰብአዊ
1050መብታቸው ሲደፈር፤ ሲንኳሰሱ፤ ሲገለሉ ለምን?
1051ማለት እንጀምር ዛሬ ቴዲ አፍሮ በር ከሌለው
1052እስር ቤት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደታሰረበት
1053እስር ቤት ነው የተዛወረው እንጂ እሱም
1054አልተፈታም ማለት እንችላለን ላለፉት ዓመታት
1055ታስሮ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብም በነጻ
1056የመናገርና የማሰብ እንዲም የፈለገውን
1057አመለካከት እንዲያራምድ፤ የፈለገውን የፖለቲካ
1058አቋም እንዲይዝ፣ በአጠቃላይ የዲሞክራሲ መብቱ 100%
1059ተክብሮ ይፈታ ዘንድ እንታገል®
1060ኢትዮጵያውያን ጀማሪ እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም
1061የሚለውን ለመሻር
1062በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲ
1063እንዲሰፍን ብዙ የጻፍን ወቅታዊ መረጃዎችን
1064ስናደርስ የከረምን እውነትን ስለያዝን የታሰርን
1065ታስረን የተፈተንን የእስር ፈተና ሳይበግረን
1066ስደት የገባን ስደት ብዙ ፈትንኖን ብዙ አስተምሮ
1067ብዙ አሳይቶ እዚህ ያደረሰን የኢትዮጵያ ነጻ
1068ጋዜጠኞች ማህበር ኢነጋማ አባል የሆንን
1069ጋዜጠኞች ነን በተለይ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ እና
1070አሳታሚ የሆነው ሔኖክ አለማየሁ በስደት ከሀገር
1071ወጥቶ በሱዳን በሊቢያ ብዙ ግፎችንና መከራዎችን
1072የተቀበለና ያሳለፈ ሲሆን በሀገረ ሶሪያ እና
1073በቱርክ ብዙ ሕይወቶችን አሳልፎ እዚህ የደረሰ
1074ነው እነዚህ የስደት ታሪኮች አምድ ተሰጥቷቸው
1075በጋዜጣችን ላይ ሕይወት እንዲህ መራራም ጣፋጭም
1076እንደሆነች የሚያሳይ ጽሑፍ ከዚህ እትም ጀምሮ
1077ቀርቧል ይከታተሉት ብዙ ጊዜ የውጭ ሀገር ሰዎች ''ኢትዮጵያውያን
1078ጀማሪዎች እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም"" ሲሉ
1079ይተቹናል ይህን የሚሉበት ምክንያት ጥንት
1080ከዓለም በፊት ሥልጣኔን ወደ ሀገራችን አስገብተን
1081ዛሬ ዓለም የቀደመንን እንደምሳሌ በማንሳት ነውእናም
1082እናንተም የማንበብ የውዴታ ግዴታችሁን
1083ከተወጣችሁ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ጀማሪ ብቻ ሳትሆን
1084ታሪክ ሠሪም መሆን ትችላለች በነገራችን ላይ
1085ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ጀማሪ እንጂ ጨራሾች
1086አይደላችሁም የሚለውን ለመሻር ሁላችንም
1087በተሰማራንበት የሥራ መስክም ሆነ የኑሮ አቅጣጫ
1088መታገል አላማችንን ከግብ የማድረስ
1089የአባቶቻችንን የቆራጥነት መንፈስ እላያችን ላይ
1090ማሳረፍ ይኖርብናል እኛም ጀማሪ ብቻ ሳይሆን
1091ጨራሽም ለመሆን ዛሬ አንድ ብለን የጀመርናትን
1092ጋዜጣ እንድታነቡልን ስንጋብዝ በጋዜጣው ላይ
1093የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ የአዘጋጁን አቋም
1094እንደማያንጸባርቁ እንድታውቁልን እንፈልጋለን
1095የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር በሚያዘን መንገድ
1096ወገኖቻችንን በማንኛውም መልኩ ለማገልገል
1097መጥተናል እንኳን ደህና መጣችሁ በሉን
1098በመስከረም በቀለ እኛ ሴቶቹን ለሰላምታ ስንስም
1099እንደው ባህሉን ለመጠበቅ ያህል ቦረሽ ቦረሽ
1100አርገውን ነው የሚሄዱት።
1101ሴትና ሴት ሲሳሙ ግን
1102ዳኮታ የሚኖሩ አበሾች አብዛኛዎቹ የሚሰሩት በሬ
1103እየታረደ የሚከፋፈልበት የሥጋ መሸጫ ፋብሪካ
1104ውስጥ ነው።
1105አንደኛው ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት ተለቅ ያሉ
1106ሰውዬ ስለ ስራቸው ጠይቄያቸው ደስተኛ እንደሆኑ
1107ነግረውኛል።
1108“እንደውም” አሉ ሲያጫውቱኝ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ
1109ሚስታቸውን “ምሳ ቋጥሪልኝ” ሲሏት በብልቃጥ
1110አዋዜ እንደምትሰጣቸው አጫውተውኛል።
1111ሁሌ ፋሲካ ማለትም አይደል?
1112የአሜሪካ አገር የሥራ ባህል ከኛ አገር ጋር በጣም
1113የተለየ ነው ። ከሁሉም ነገር ለኛ የሚከብደን ግን
1114የሽያጭ ሥራ ስንቀጠር ገብያተኛ ሲመጣ “ፈገግ
1115በሉ” የሚሉን ነው።
1116ትዝ ይለኛል የመጀመሪያ ሥራዬ አለቃዬ “ጎበዝ
1117ጎበዝ” ሲለኝ 8፡00 ሰዓት ሙሉ ጥርሴን አግጥጩ ማታ
1118ቤት ስገባ ጉንጩን ስትራፖ ይዞኝ እንደ ቦክሰኛ
1119ጉንጬን ቫዝሊን ተቀብቼ ነው ያደርኩት።
1120ጮክ ብሎ ማውራትም ሌላው ችግር ነው።
1121አሜሪካኖች ጮክ ብሎ አለማውራትን እንደድክመት
1122ያዩታል።
1123እኛ በባህላችን ጮክ ብሎ የሚያወራ ሰው ገገማ
1124ወይም ባለጌ ነው የሚባለው፤ እኛ ቤት ጮክ ብለን
1125የምናወራው ከአሜሪካ ስልክ ሲደውል ወይም ፈተና
1126ወድቀን ስንገረፍ ብቻ ነው።
1127አንድ ቀን አንድ እብድ የሚያክል አለቃዬ…
1128በነገራችን ላይ እኛ ሰፈር ያሉት እብዶች
1129እንደአጋጣሚ ቀጫጮች ናቸው።
1130ስለዚህ ለምሳሌ ያህል የናንተን ሰፈር እብዶች
1131ተጠቀሙ።
1132አፍንጫዬ ሥር ቆሞ ምራቁን ግንባሬ ላይ
1133እያፈናጠቀ ጆሮዬን በጩኸት ሲቀደው ለሱ ሲያወራ
1134አንድ ሰውዬ ትዝ አሉኝ።
1135ሰውዬ ጆራቸውን ደከም ብሏል።
1136እዚሁ አሜሪካ ለሚኖረው ልጃቸው “እባክህ ጆሮ
1137ላይ ተሰክቶ የሚያሰማ መሳሪያ አለ አሉ “ሄሪንግ
1138ኤድ” የማይሰራውን ገዝተህ ላክልኝ”፤ ልጁም ግራ
1139ተጋብቶ ለምንድን ነው የማይሰራውን የምልክልህ?
1140ቢላቸው እሳቸውም “አይ ልጅ እኔ የ 85 ዓመት
1141ሽማግሌ ነኝ ከአሁን በኋላ ስንት ጊዜ እንደምኖር
1142አላውቅም።
1143አንተንም ባለቀ ሰዓት ከማከስርህ የማይሰራውን
1144ላክልኝና ላርገው እሱን ጆሮዬ ላይ ሲያይ ይሄ
1145ሽማግሌ ጆሮው ችግር አለበት ብለው ጮክ ብለው
1146ያወራሉ አሉ።
1147እኔም ታዲያ ድሮ አንዴ ይሄ ግለሰብ ድምጼ ቀጠን
1148ስላለ ጆሮዬ የማይሰማ መስለው እንዴ ስል ነበር።
1149ካሊፎርኒያ ደግሞ ከ600 በላይ የሚሆኑ አበሾች
1150የሚሰሩበት ካምፓኒ አለ።
1151ጠዋት ጠዋት አበሾች ወደ ሥራ ሊገቡ ሲሉ ካምፓኒው
1152በር ላይ ሰላምታ እየቀያየሩ እየተሳሰሙ ፈረንጆች
1153አላስገባ ስላሏቸው ባለፈው ዓመት የካምፓኒው በር
1154ላይ “ ” መሳሳም ክልክል ነው የሚል ሳይን “
1155” ከሚለው ጎን ፈጥረዋል።
1156እንደው የከንፈር ሊስትሮ አትበሉኝና ሰላምታ ላይ
1157መሳሳም ከሚወዱት ውስጥ አንዱ ነኝ።
1158የካምፓኒው ችግር ከወንዶች የመጣ አይመስለኝም።
1159እኛ ሴቶቹን ለሰላምታ ስንስም እንደው ባህሉን
1160ለመጠበቅ ያህል ቦረሽ ቦረሽ አርገውን ነው
1161የሚሄዱት።
1162ሴትና ሴት ሲሳሙ ግን በተለይ አንዳንዶቹ
1163በእያንዳንዱ መሳሳም መሃል የፉገራ ወሬ ያወራሉ።
1164“የጠፋ ሰው” ሳም ዛሬ ደግሞ በጠዋቱ ፏ ብለሻል፤
1165ሳም…
1166ፀጉርሽ ደግመሽ ተቀባሽው እንዴ?
1167”…
1168ሳም… የኔ ስልክ ነው ወይስ ያንቺ የሚጮኸው?
1169” ሳም።
1170
1171®
1172ከሊሊ ሞገስ ያንን ዋሽንት አምጡት ዋ ባይ ትካዜው
1173ቢለቀኝ መቼም ያለ ሀሳብ ዋ ባይ ምንም ዘመድ የለኝ
1174ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋስንቱ ልበል በዋሽንቱ
1175''ኩኩ መለኮቴ'' ከተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ላይ ''ዋ
1176ስንቱ'' የተሰኘችዋን ምርጥ ዜማ ነበር ግጥሟን
1177የቆነጠርኩላችሁ የእድሜን እና የትውልድ አመተ
1178ምህረተ ምህረቱን ነገር ለእናቱ ወይም ለአባቱ
1179እንተወው እና ይሁኔ በላይ በአጭሩ የተወለደው
1180በጎጃም ክፍለ ሀገር በፍኖተ ሰላም ከተማ ነው
1181ዛሬ የትራንስፖርት ችግሩ በመጠኑም ቢሆን
1182የተቃለለበት ወቅት ይሁን እንጂ በዛ ዘመን ወደ
1183ባህር ዳር አልያም ጎንደር ሲሄዱ አዳር
1184ፍኖተሰላም ነበር በፍኖተ ሰላም ግሮሰሪዎች
1185መንገድ ላይ እና በአጠቃላይ ሆቴል ቤቶች ማስንቆ
1186ያነገቡ ብዙ አዝማሪዎችን አላያችሁም?
1187
1188ታለንትድ ከሆኑት እነዚህ ሕጻናት አዝማሪዎች
1189መካከል አሁን ብዙዎቹ ወደሙዚቃው አለም ገበተዋል
1190- ጥቂቶቹ እንደ ይሁኔ በላይ ተሳክቶላቸዋል
1191ከቤተሰቦቹ 3 ልጆች የመጨረሻው የሆነው ይሁኔ
1192ከላይ ብዙዎች እንደሚመሰክሩለት ማንነቱን
1193አይረሳም የሙዚቃ ፍቅሩና ታለንቱ ወደ ጥብበ
1194የመራችው ብዙዎቹ ''የጎጃም አምባሳደር'' የሚሉት
1195ይሁኔ በላይ ግሽ አባይ ባንድ ውስጥ በመግባት
1196ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራት የሙዚቃ ክሊፕ ሙዚቃዊ
1197ድራማውን ለሕዝብ አደረሰ ''አንቱዬዋ''
1198የተሰኘችው ድራማዊ ሙዚቃ ሰማህኝ በለውን ሳይቀር
1199ያካተተች ስትሆን ለይሁኔ በላይ መታወቅ በሩን
1200የከፈትችለት ዜማ ነበረች ግሽ አባይ ባንድ
1201በርካታ የባህል ሙዚቀኞችን ለሕዝብ ያደረሰ
1202ለባህል ሙዚቃችን እድገት ትልቁን ሚና የተጨወተ
1203ስብስብ ነበር ''በልጅነታችን በግሽ አባይ ውስጥ
1204የምንሰራቸው ሥራዎች የሚገርሙ ነበሩ'' የሚለው
1205ይሁኔ ስለ አንቱዬዋ የሙዚቃ ድራማ አውርቶ
1206አይጠግብም ''ፈጠራውን እስከአሁን ድረስም
1207አደንቃለሁ'' የሚለው አርቲስቱ ''ከሕዝብ ጆሮ
1208ዜማዋ ከደረሰች ጊዜ ጀምሮ የእኔ ሕይወት አንድ
1209በአንድ እየተለወጠ መጣ'' በማለት የሕይወት
1210መስመሩን ይህ ስራው እንደጠቆመው ተናግሯል ''የእኔ
1211የሙዚቃ ሕይወት የሚጀመረው ከአካባቢ ነው ቆላ
1212ደጋ ዳሙት የሚል ፍላጎት ያላቸው ልጆች
1213ስሜታቸውን የሚያስደስቱበት የወረዳ የሙዚቃ
1214ቡድን ነበረ እዚያ እየተሰባሰብን ራሳችንን
1215ከማስደሰት አልፎ በአንዳንድ ዝግጅቶች ላይ
1216ሥራዎቻችን ማቅረብ ጀመርን'' የሚለው ይሁኔ የሙያ
1217መሰረቶቹን አንድ በአንድ ያስረዳል ''ከዚህ
1218በፊት ግን በትምህርት ቤት ለጓደኞቼ ስዘፍን
1219አስተማሪዬ አይተው አንተ በኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ
1220ዘፋኝ ትሆናለህ ብለው የሰጡኝ ማበረታቻ ለዛሬው
1221መሰረት ሆኖኛል ይላል ''እረ ነይ ግቢ ግቢ ግቢ
1222አረ ነይ ግቢ ግቢ
1223አንቺ ልጅ ግቢ ግቢ እረ ተይ ግቢ ግቢ
1224በኔ ሞት ግቢ ውጡና አነጋግሯት አንድ ሁለት
1225ሆናችሁ የቆመችበትን ምክንያት ጠይቃችሁ
1226እሷ ውጭ ቆማ
1227በር ተቀምጣ ማን እህል ሊበላ ማን ማን ውሀ ሊጠጣ
1228የታለች በር ቆማለች
1229; አስገቧት አልገባም አለች!!
1230'' ‘’ሙሉቀንን ማዳመጥ፤ ማድነቅና የእርሱን
1231መድረክ ውሎን ፊት ለፊት እያየሁ ከሥር ከሥሩ
1232የእርሱን ፈለግ ልከተል፤ እርሱ በዋለበት መድረክ
1233ለመሰማራት ልቤ ተሰቅሎ ደፋ ቀና ስል ከመቅስፈት
1234ከዘፈኑ ዓለም ተሰወረ ይሁንና ጋሼ ሙሉቀን
1235አዘፋፈኑ ማለቴ ድምጽ አወጣጡ፤ ግጥምና ዜማ
1236መርጦ በማዋሀድ ያቀርባቸው የነበሩት ዘፈኖቹ
1237ዛሬም፤ ነገም ለእኔም ሆነ ለመላው አድናቂዎቹ
1238መጽናኛ ሆኖናል በተረፈ ግን ድምጻዊ ሙሉቀንን
1239የሚተካ ዘፋኝ ይፈጠራል የሚል ግምት የለኝም’’
1240ለድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ አድናቂዎች የኢንተርኔት
1241መረብ ይሁኔ በላይ የሰጠውን አስተያየት ነው
1242የቆነጠርኩላችሁ ከዚህ የይሁኔ በላይ ንግግር
1243የምንረዳው ለሙዚቃ መሰረቱ ሙሉቀን መለስ
1244እንደሆነ ይሁን እንጂ የይሁኔ የሙዚቃ ሕይወት
1245ስኬት በር ከፋቹ መምህሩ እንደሆኑ በአንድ ወቅት
1246በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው
1247ላይ አትቷል ‘ '
1248 
1249 
1250 
1251 !
1252’ ጆስ የተሰኘው የመረጃ መረብ ስለ ይሁኔ
1253የተናገረው ነው ከሙዚቃ ቡድኑ አልፎ የመጀመሪያ
1254አልበሙን ለሕዝብ ያቀረበው ይሁኔ የአዘፋፈን
1255ስታይሉ ሙሉ በሙሉ ባህል የተላበሰ እና
1256እንቅስቃሴውም ከዘፈኑ ጋር አንድ አይነት በመሆኑ
1257ቶሎ ሕዝብ ሊቀበለው ችሏል ''ያገሬ ልጅ ባለጋሜ
1258ትውልዷ ጎጃሜ'' የተሰኘችው የይሁኔ የመጀመሪያ
1259አልበም በመላው ኢትዮጵያ የተደመጠ ሲሆን በባህል
1260ሙዚቃ የካሴት ሽያጭም የወቅቱ አንደኛ እንደነበር
1261ይነገራል ይህ ሥራው ስኬትን ያጎናጸፈው
1262በትክክልም የጎጃም ''አምባሳደር'' ቢባል
1263የማያንሰው ይሁኔ ''አሎ ሉሎ''ን አልበም አከለ
1264ይህም አልበም እንደወጣ የሕዝብ ጆሮ ለመግባት
1265ጊዜን አልፈጀበትም ''ብዙዎች እድለኛ ነህ
1266ይሉኛል በእርግጥም እድለኛ ነኝ በጥቂት
1267ጊዜያት ውስጥ ቶሎ ሕዝብ ጋር ለመድረስ ችያለሁ''
1268የሚለው ይሁኔ ለዚህ ሁሉ ስኬቱ ግን ያሳለፈውን
1269ችግር እና መከራ አይዘነጋም ''ብዙ ነገሮች
1270በሕይወቴ ውስጥ ደርሰውበኛል ሁሉም
1271በእግዚአብሄር ሀይል አልፌ ለዚህ በቅቻለሁ'' ሲል
1272ፈጣሪውን ከምንም በላይ ያመሰግናል ይሁኔ 3ኛ
1273አልበም ሲወጣ ስታይሉም እያደገ እንደመጣ አሳየ
1274ከባህል ሙዚቃዎች ወጣ ብሎም ወደ አፍሪካ ስልት
1275ሙዚቃዎችም የኢትዮጵያን ባህል አስገብቶ መስራት
1276ጀመረ ''ብ
1277ብ ከፊላው ስር'' የምትባለው አልበሙ የብቃቱን
1278ደርጃ እጅግ አድርጋ ማደጉን ያሳየች አልበም
1279ነበረች ይሁኔ ከዛም ኩኩ መለኮቴ የተሰኘውን
1280አልበሙን ሲያወጣ ከአሜሪዋ የወቅቱ ፕሬዚዳንት
1281ከነበሩት የቢል ክሊንተን ባለቤት ሚስ ሂላሪ
1282ክሊንተን ጋር ለመገናኘት እና ካሴቱን በስጦታ
1283ለማበርከት ችሏል የሙዚቃ ሥራውን በመጠኑም
1284ቢሆን ከቃኘን ወደ ግል ሕይወቱ ስንመለስ ይሁኔ
1285ከባለቤቱ የሺመቤት ቱቱ ጋር በአሌክሳንደሪያ
1286ቨርጂኒያ ውስጥ ከአንድ ወንድ ልጁ እና ሴት ልጁ
1287ጋር በፍቅር ይኖራል ይሁኔ ለልጆቹ የኢትዮጵያን
1288ባህል እንዳይዘነጉ ትምህርት እንደሚሰጣቸው
1289አስታውቆ ብዙ ጊዜ ልጁን የጎጃም ሕጻናት
1290የሚለብሱትን የባህል ካኪ ልብስ እንደሚያለብሰው
1291እና ምንነቱን ጠንቅቆ እንደሚያሳውቀው የቅርብ
1292ወዳጆቹ ይናገራሉ ይሁኔ በላይ የልጆቹ ስሞች
1293ፍቅር ይሁኔ እና ሰላም ይሁኔ ይባላሉ በአሁኑ
1294ወቅት ይሁኔ ከዘፋኝነቱ ሌላ የተሳካለት ነጋዴም
1295ሆኗል በአሜሪካን ሀገር የሚታተም የሎ ፔጅስ
1296አለው ይህ የሎ ፔጅስ ታርጌት የሚያደርገው
1297በአብዛኛው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብን ነው
1298ሻሎም!!
1299®
1300ኢትዮጵያውያን ቆንጃጅት በዓለም ላይ ነገሡ ሚስ
1301ሚሊኒየም ተብላ በኢትዮጵያ አሸንፋ የነበረችው
1302ሞዴል ኪዳን ተስፋሁን የአለማችን ምርጥ የሴቶች
1303ሞዴል 2009 በመባል በስፔን ተመረጠች
1304 የተባለው ድርጅት ስፔን ላይ ባዘጋጀው
1305ውድድር ላይ ያሸነፈችው ኢትዮጵያዊቷ ኪዳን 18
1306ሜትር የሚለካ ቁመት አላት የ24 አመቷ ኪዳን
1307ካሸነፈች በሗላ በሰጠችው ቃል በሀገራችን
1308እምብዛም ያልተለመደውን የሞዴልነት ሞያ በደንብ
1309ለማጠናከር ጠንክራ እንደምትሰራ ተናግራለች
1310ከዚህ ቀደም 2008 ተብላም ያሸነፈችው
1311ኪዳን በስፔን ማሸነፏ ሀገራችንን ስሟን በመልካም
1312ጎኑ ያስጠራል ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጥቂት
1313ወራት በፊት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችው ሳራ
1314ኑሩ በጀርመን የሞዴል ውድድር ማሸነፏ የሚታወስ
1315ሲሆን ቆንጆዋ ለሥራ ወደ ኒውዮርክ መዘዋወሯን
1316ኮስሞፖሊታን የተሰኘው ታዋቂው የሴቶች የውበት
1317መጽሄት ዘግቧል የጀርመን ቁጥር አንድ ሞዴል ሆና
1318የተመረጠችው ሳራ ኑሩ ዝናዋ ባመጣላት ጸጋ ከእጅ
1319ስልክ አምራቹ ሶኒ ኤሪክስን ኩባንያ ጋር
1320የማስታወቂያ ውልአድርጋለች፣ በዚሁ መሰረት
1321የሶኒ ኤሪክስን ስልኮች ሲወጡም ሆነ በየቦታው
1322በሚደረገው ማስታወቂያ ሥራ ኑሩ ፈገግ እንዳለች
1323የሚያሳየው ፎቶዋአብሮ ይወጣል።
1324አዲሱ የሶኒ ኤሪክሰን ስልክ ፎቶ የሚያነሳው ሳቅ
1325ሲሉለት ብቻ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ
1326ሳራም ፈገግታዋን እያሳየች ስልኩን
1327ታስተዋውቃለች ማለት ነው።
1328® ወጋየሁ ደግነቱ አረፈ "የሰው የእንስሣት
1329የአራዊት… እናት እኮነች መድኃኒት”" በሚል
1330ዜማው የምናውቀው ተወዳጁ ድምጻዊ ወጋየሁ ደግነቱ
1331አረፈ ከአባቱ ከአቶ ደግነቱ ጅማ ከእናቱ ከወሮአበራሽ
1332ወዳጆ ጥር 12 ቀን 1940 ዓም በሀረርጌ ክሀገር
1333በወበራ አውራጃ በጐሮ ጉቱ ወረዲ ልዩ ስሙ መካኒሳ
1334በተባለው ስፍራ ተወልዶ የመጀመሪያ ደረጃ
1335ትምህርቱን በሀረር ልዑሌ መኮንን አንደኛ ደረጃ
1336ትቤት ተከታትሎ በነበረው ልዩ የሙዚቃ ፍቅር
1337የተነሳ መጋቢት 1 ቀን 1955 ዓም በሀረርጌ ክሀገር
1338ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል በታዳጊነት ዕድሜው ተቀጠረ፡፡
1339ከ1957 ዓም ጀምሮ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪ
1340ድምፃዊ ለመሆን የበቃው ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ፤
1341በ1959 ዓም ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ የሀረር ፖሊስ
1342ሙዚቃ ክፍል የተወዛዋዥ ቡድን አሰልጣኝ፣ የዜማና
1343የግጥ ም ደራሲ ሆኗል ስለእናት በዘፈነው ዘፈን
1344እና 'ፈንዲሻ" በተባለው ሙዚቃው የሚታወቀው
1345ወጋየሁ ከሙዚቃው ጎን በተማረው የህግ ሙያ
1346በጥብቅና ሙያ እስከአረፈበት ጊዜ ድረስ
1347ሲያገለግል ነበር ለቤተሰቦቹ መጽናናትን
1348ለነብሱ ገነትን ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ትመኛለች®
1349ሕይወት ሽንኩርት ናት ስትላጥ ብታስለቅስም
1350ስትበስል ግን ትጣፍጣለች ከሕይወት ስንክሳሮች
1351መካከል ደግሞ አንዱ ስደት ነው የሰው ልጅ
1352የተሻለ ኑሮን ወይንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ሲሰደድ
1353እንደሽንኩርቷ በችግር ሲላጥ አልቅሶ;
1354የተፈተነበት ውጤት ሲያልፍ ደስተኛ ይሆናል
1355የዛሬዋ እንግዳችን በሚኒሶታ ብቸኛዋ የታክሲ
1356ሹፌር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ቅድስትም በሕይወት
1357ስንክሳር ብዙ ተፈትና ዛሬ እዚህ ደርሳለች
1358የዚህችን ሴት ታሪክ ሰማንና የጋዜጣችን እንግዳ
1359ለማድረግ ወደ ስልኳ በተደጋጋሚ ደወልን ከስልኳ
1360የምናገኘው
1361የሚለውን አናዳጅ ምላሽ ነበር ሆኖም ግን በነዚህ
1362ቃላት መካከል "ኪኪ" የሚል ድምጽ ስናገኝ ስልኳ
1363የእርሷ መሆኑን አረጋግጠን ድወላችንን ቀጠልን
1364ምላሽ ስናጣም የድምጽ መልዕክት አስቀመጥን;
1365ቅድስት ወይም ኪኪ ወዲያውኑ ስልካችንን መለሰች
1366ከዛም የሚከተለውን እዛው የምትሠራበት ፖስት ሮድ
1367ተቀጣጥረን የታክሲዋን መስኮት ከፍተን አወራን
1368ዘ-ሐበሻ- ተጀመረ!
1369ቅድስት- ምኑ?
1370ዘ-ሐበሻ- ቃለ ምልልሱ!
1371ቅድስት- ሳቅ
1372 ዘ-ሐበሻ- ምነው?
1373አልተዘጋጀሽበትም እንዴ?
1374ቅድስት- ኸረ እንደውም!
1375ዘ-ሐበሻ- የፈራሽ ትመስያለሽ?
1376
1377ቅድስት- እንዴ እኔ ለኢንተርቪው አዲስ
1378አይደለሁም እኮ!
1379
1380ድሮ እኔም ራሴው ኢንተርቪው አደርግ ነበር
1381ዘ-ሐበሻ- ኦው!
1382ጥሩ ታዲያ ራስሽም ቃለ-ምልልስ ታደርጊ ከነበረ;
1383እንዲሁም ብዙ ሰው ቃለ-ምልልስ ሲደረግለት
1384አይተሻልና ጋዜጠኞች ብዙ ጊዜ አስቀድመው
1385የሚጠይቁት ነገር ስለምንድን ነው?
1386ቅድስት- ስለማንነት!
1387
1388ከራሳቸው ላይፍ ስታይል
1389ከስማቸው ያሉበትን የመጡበትን
1390ዘ-ሐበሻ- ታዲያ እኛም ከእርሱ እንጀምር?
1391
1392ቅድስት- እንደፈለክ!
1393ዘ-ሐበሻ- ይሄንን በቅድሚያ ብጠየቅ የምትይው
1394ነገር ካለ?
1395ቅድስት- ይሄን ብጠየቅ?
1396ዘ-ሐበሻ- አዎ!
1397ቅድስት- ሳቅ!
1398
1399 የሥራ ሁኔታ እንዴት ነው?
1400አንቺ ሴት ሆነሽ እንዴት እዚህ ቦታ እንዴት መጣሽ?
1401ብቻሽን ነሽና እንዴት ልትመጪ ቻልሽ ምናምን
1402ነው መስለኝ ጥያቄው የሚመስለኝ
1403ሳቅ እና ተደሰቺበታለሽ ወይ በሥራው?
1404ይመስለኛል
1405ዘ-ሐበሻ- እሺ ቅድስት ማናት ብለን እንጀምር!
1406
1407ቅድስት- ቅድስት ታዬ ዘ-ሐበሻ- ይህን ጋዜጣ
1408ለሚያነቡ ሰዎች ራስሽን አስተዋውቂ ብትባይ
1409እንዴት ራስሽን ትገልጪዋለሽ?
1410ቅድስት- የመጣሁት ከኢትዮጵያ ነው ተወልጄ
1411ያደግኩትም ጅማ ውስጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ
1412ከተማርኩና ከሰራሁ በሗላ ወደ አውሮፓ ሄድኩኝ
1413ከአውሮፓ ወደ እዚህ መጣሁ ወደዚህ ሙቭ ሀገር
1414የቀየርኩት ያደረግኩት በ1998 ነው ዘ-ሐበሻ-
1415አውሮፓ የት ነበርሽ?
1416ቅድስት- ስዊድን ነበርኩ!
1417
1418ዘ-ሐበሻ- እንዴት ነበር ወደ አሜሪካ የመጣሽው?
1419ቅድስት- መጀመሪያ ያው በደርግ ጊዜ ነው ከሀገር
1420የወጣሁት ስዊድን ሀገር ሄጄ ከዛ በሗላ 10
1421ቆየሁ እዛ እያለሁ; እኔ እንኳን አልሞላሁም
1422ጓደኞቼ ዲቪ ሞልተው ላኩልኝና መልሱ ሲመጣ በእኔ
1423አድራሻ መጣ ዘ-ሐበሻ- ስዊድን ሆነሽ ማለት ነው?
1424ቅድስት- አዎ!
1425ዘ-ሐበሻ- ኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነበር ሞያሽ?
1426ምንድን ነበር የምትሰሪው?
1427እዛም እንደዚሁ ታክሲ ትነጂ ነበር?
1428ቅድስት- ሙያ የሚባል ነገር ያው ሀይስኩል
1429ከጨረስኩ በሗላ ባንክ ትንሽ ሰርቻለሁ ዘ-ሐበሻ-
1430ቅድም የጋዜጠኝነት ሙያው አለኝ; በራዲዮ ሰርቼ
1431ነበር ስትይኝ ነበር?
1432ቅድስት- ጋዜጠኝነት እንኳን ሳይሆን በራዲዮ ነው
1433የራዲዮ ፕሮግራም እናዘጋጅ ነበር - በቤተ
1434ክርስቲያን ውስጥ በኢቫንጀሊካል ቤተክርስቲያን
1435ፕሮግራም እያዘጋጀን ስዊድን ሀገር ለ5 አመታት
1436ሰርቼበታለው ዘ-ሐበሻ- አሜሪካ ከመጣሽ በሗላ
1437የታክሲ ሹፌርነቱ ሥራ የመጀመሪያ ሥራሽ ነው?
1438ቅድስት- አይደለም መጀመሪያ ኤርፖርት ውስጥ
1439እሠራ ነበር ለ2 ወራት በኤርፖርት ሥራዬ
1440ሴክዩሪቲ ሆኜ ነበር የሠራሁት ከዛ በሗላ ደግሞ
1441የአፍሪካ ሕጻናት እና ሴቶች እንክብካቤ ቡድን
1442ውስጥ ሰርቻለሁ በዚህ መሥሪያ ቤት ውስጥ በሰዎች
1443"አብዩዝ" የተደረጉ ልጆችን እና ሴቶችን መርዳት
1444ነበር ሥራችን ከ6 እስከ 8 ወር ለሚሆን ጊዜ
1445ሰርቻለሁ ዘ-ሐበሻ- በሀገር ቤትም; በስዊድን
1446ቆይታሽም የታክሲ ሾፌር ካልነበርሽ እንዴት
1447አሜሪካ መጥተሽ ይህንን የሥራ ክፍል ልትመርጪው
1448ቻልሽ?
1449ቅድስት- ባንክ ሰርቼ ነበር በዌልስ ፋርጎ
1450 ባንክ ውስጥ እየሰራሁ አብሬያቸው ቸርች
1451የምሄዳቸው ልጆች እነርሱ ታክሲ ይነዳሉ እና ብዙ
1452ጊዜ አንዳንድ ቦታ ለመሄድ አንድ ነገር ለማድረግ;
1453በሕብረት የሆነ ነገር ለማድረግ እነርሱ ፍሪ ጊዜ
1454አላቸው ናቸው እኔ ማስፈቀድ ምናምን ስላለብኝ
1455አይመቸኝም ከዛም ለምን እኔም እንደነርሱ
1456አልሰራም ብዬ አስብ ነበር ይህ ሀሳብ በአእምሮዬ
1457ውስጥ እንዳለ አንድ ቀን መንገድ ላይ ስሄድ
1458አንዲት ሶማሌ የባሏን ታክሲ ይዛ ነው መሰለኝ
1459ስትነዳ አየሗትና እንዴት የሱማሌ ሴት ታክሲ
1460የነዳች እኔን ያቅተኛል ብዬ ካልጀመርኩኝ ሞቼ
1461እገኛለሁ አልኩ ዘ-ሐበሻ- ከዛስ?
1462ቅድስት- ከዛማ አብረውኝ ቸርች የሚሄዱትን
1463የታክሲ ሹፌሮች አነጋግሬያቸው ታክሲ ሥራ
1464ለመጀመር እንዴት እንደማደርግ ፕሮሰሱን ነገሩኝ
1465እና ጀመርኩት ዘ-ሐበሻ- አንዴ ኢንተርቪውን
1466ላቋርጠው
1467ጉንፋን ይዞኛልና አፍንጫዬን ማጸዳዳት
1468ይኖርብኛል ቅድስት- ሶፍት ልስጥህ?
1469ዘ-ሐበሻ- አይ ተይው!
1470
1471ግን ጉንፋኔን እንዳላጋብብሽ?
1472ቅድስት- !
1473
1474ሳቅ
1475 ዘ-ሐበሻ- ከጥቂት ቆይታ በሗላ እሺ አሁን
1476መቀጠል እንችላለን
1477እና ያቺ ሱማሌ ነች መነሻ የሆነችሽ ማለት ነዋ!
1478ቅድስት- አዎ ሱማሌዋ ናት መጀመሪያ አእምሮዬ
1479ውስጥ የነበረውን ሀሳብ በደንብ አጠናክሬ እዚህ
1480ሥራ ውስጥ ያደረገችኝ ማለት ይቻላል በጣም ሞራል
1481ሰጠችኝ የሶማሌ ሴት የነዳች እንዴት ያቅተኛል
1482ብዬ ገባሁበት ዘ-ሐበሻ- የታክሲ ሾፌር ከሆንሽ
1483በሗላ ሥራውን እንዴት አገኘሽው?
1484ቅድስት- በጣም ቀላል ሥራ ሆኖ ነው ያገኘሁት
1485ስለእውነት ለመናገርም የሚከብድ ሥራ አይደለም
1486ደግሞ ከእኔ በፊትም የሚገርምህ ሁለት
1487ኢትዮጵያውያን ሴት የታክሲ ሾፌሮች ነበሩ ሆኖም
1488ጥቂት ጊዜ ሰርተው ጥለው ወጡ ወዲያው ዘ-ሐበሻ-
1489አሁን ግን እዚህ የኤርፖርት ታክሲ ላይ አንቺ ብቻ
1490ነሽ ሴት?
1491ቅድስት- ያው ከሀበሻ እኔ ብቻ ነኝ ከነጮች ግን
1492አንድ ሴት አለች 5 ይሆናል ብቸኛዋ ሴት
1493የሀበሻ የታክሲ ሾፌር እኔ ነኝ ያለሁት ዘ-ሐበሻ-
1494ከብዙ የታክሲ ሾፌሮች እንደምሰማው ሥራውን
1495የምትሰሪው ትንሽ ሀላፊነት ወስደሽ ነው
1496ወንጀለኛ ሊያጋጥም ይችላል ሰካራምና
1497በአደንዛዥ እጽ የደነዘዘ ሰው መጫን አለ
1498አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰው ጭነሽ መንገድ የመጥፋት
1499ነገር አለ እና አንቺ በዚህ ሥራ ውስጥ ያጋጠመሽ
1500ነገር ምንድን ነው?
1501ቅድስት- ጥሩ ጥያቄ ነው ወንጀለኛ እንኳን
1502አጋጥሞኝ አያውቅም በጣም የሚያጋጥመኝ ያው
1503መንገድ መጥፋት ነው በታክሲ ስራ ውስጥ መንገድ
1504መጥፋት ነው ይሄ እ
1505
1506እንደማሰብ አለችና አንድ ጊዜ እንደውም ምን
1507አጋጠመኝ መስለህ?
1508አንዱን ደንበኛዬን ሆቴል እየወሰድኩት እያለ
1509ሰውዬውም እኔም ሆቴሉ ያለበትን ቦታ አናውቀውም
1510እየነዳሁ ሆቴሉ ጋር ስልክ ደውለን አድራሻውን
1511ጠየቅኳቸው በየት በየት እንደምሄድ የነገሩኝ
1512በትክክል አልገባኝም
1513በቃ ሰውዬውን ይዤው ጠፋሁ ይገርምሀል ሰውዬው
1514ምንም ነገር አይናገርም ዝም ብሎ ብቻ ነገሩን
1515ይከታተላል ከተማውን ዞሬ ዞሬ እንደገና ሆቴሉ
1516ጋር ስደውል የሚነግሩኝ መንገድ አይገባኝም
1517ቢቸግረኝ ስልኩን ለተሳፋሪው ሰጠሁት ከዛ በሗላ
1518በይ ከዚህ በኩል ተመለሺ ብሎኝ በተሳፋሪዬ
1519እየተመራሁ ሆቴሉ አደረሰኩት ካሁን ካሁን
1520ጮኸብኝ ብዬ ስፈራ እሱ እንደውም ቲፕ አድርጎ
1521ሲከፍለኝ እኔ 'ይሄን ያህል ገንዘብ አይመጣም;
1522እንደውም ጊዜህን ሁሉ ስላጠፋሁብህ
1523አላስከፍልህም' ስለው እርሱ ጥሩ ሰው ስለነበር
1524ከነቲፑ ሰጥቶኛል ሆኖም ግን ወንጀል ምናምንም
1525አጋጥሞኝ አያውቅም ዘ-ሐበሻ- አንቺ የታክሲ ስራ
1526አስከፊ ጎን የምትይው ምንድን ነው?
1527ቅድስት- መቼም በእኔ አስከፊ አድርጌ የምወስደው
1528መንገድ መጥፋትን ነው ሰው ይዞ መጥፋት በጣም
1529በጣም የሚያስፈራ ነው ሌላው ደግሞ ማታ መሥራት
1530ትንሽ አደገኛ ሊሆን ይችላል አንዳንድ ጊዜ
1531የሰከረ ሰው ሊያጋጥም ይችላል ማታ መሥራት ጥሩ
1532አይደለም በተለይ ወደ ኖርዝ ሚኒያፖሊስ ማታ
1533ከሆነ ሰው ይዞ መሄድ ብዙም ጥሩ አይደለም
1534ዘ-ሐበሻ- አንቺ ማታ ማታ አትነጂም ማለት ነው?
1535ቅድስት- ማታ በጣም አላመሽም ዘ-ሐበሻ-
1536በሴትነትሽ ተሳፋሪ ሆኖ የሚተናኮልሽ የለም?
1537ቅድስት- ማለት የኤርፖርት ታክሲ ስለሆነ
1538የምሰራው ብዙም እንደዚህ ያለው ነገር አያጋጥምም
1539ብዙ ጊዜ ከኤርፖርት ራሳቸውን ችለው; የኤርፖርት
1540ትኬት ገዝተው የሚሄዱ ሰዎች ወደ ቤታቸው ወይም
1541ወደ ሆቴል አንዳንዴም ወደ ሥራቸው ስለሆነ ብዙም
1542እንደዚህ አይነት ሰዎች የሉም የሲቲ ታክሲ
1543ስለማልሰራ ብዙም አልጨነቅም የሲቲ ታክሲ ግን
1544ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያለው ነገር ሊከሰት ይችላል
1545ዘ-ሐበሻ- በሚኒሶታ በሲቲ ታክሲ ውስጥ ሴት ሹፌር
1546አለች እንዴ?
1547ቅድስት- !
1548የለችም ዘ-ሐበሻ- እዚህ ሚኒያፖሊስ-ሴንትፖል
1549ኤርፖርት ታክሲ ሥራ ላይ የተሰማሩ ስንት
1550ኢትዮጵያውያን አሉ?
1551ቅድስት- እስከ 150 የምንሆን ይመስለኛል
1552ዘ-ሐበሻ- እንግዲህ ከነዚህ ሁሉ መካከል አንዷ
1553ብቸኛ ሴት አንቺ ነሽና ውሎሽ ከወንዶች ጋር ነው
1554ማለት ይቻላል ቅድስት- በሚገባ!
1555
1556ዘ-ሐበሻ- ታዲያ ከወንዶች ጋር እንደመዋልሽ
1557ወንዶችን ምን ታዘብሻቸው?
1558ቅድስት- ረዥም ሳቅ
1559 እኔ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ወንዶችን ናቸው ጓደኞቼ
1560ከሴቶች በላይ ከወንዶች ጋር ነው የምውለው
1561አንዳንድ ጊዜ ሴት መሆኔንም የሚረሱበት አጋጣሚ
1562አለ እነርሱ ብዙ ነገር ነው የሚያወሩት ሳቅ
1563 በጣም ደስ ብሎኝ ነው ከወንዶች ጋር የምውለው
1564ምንም ያየሁባቸው የታዘብኳቸው ነገር የለም
1565ደግሞ እንደየአካባቢያችን እና
1566እንደምንግባባቸው ሰዎች ነው የምንቆመው
1567አብረውኝ የሚቆሙት ተራ እስኪደርስ ለመጠበቅ
1568ማለቷ ነው ያሉት "ኩል" የሆኑ ናቸው ዘ-ሐበሻ-
1569ብዙ ጊዜ ወንዶች ስለምንድን ነው የሚያወሩት?
1570ቅድስት- ሳቅ
1571 እሱ ጠፍቶህ ነው እኔን የምታደርቀኝ?
1572ሳቅ
1573 ብዙ ጊዜ ሴት ያወራሉ ስለማህበራዊ ጉዳይ
1574ያወራሉ ግን አብዛኛውን ጊዜ ስለሀገር ጉዳይ
1575በማውራት ነው የሚያሳልፉት ስለሀይማኖት
1576ጉዳይም ያወራሉ ግን ብዙ ትኩረት የሚሰጡት
1577በሀገር ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ነው ዘ-ሐበሻ-
1578አላማሽ ምንድን ነው?
1579ቅድስት- አላማዬ መማር ነው ከዚህ ቀደምም ተምሬ
1580አቋርጬው ነው አሁን እሱን ከተማርኩ በሗላ ወደ
1581ሀገሬ መግባትና ከሕጻናት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን
1582መስራት እፈልጋለሁ ሕጻናትን በጣም ስለምወድ
1583እነርሱን ማስተማር ደስ ይለኛል የወሰድኩትም
1584ትምህርት ከዚሁ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በዚህ
1585ዙሪያ መሥራት እፈልጋለሁ ዘ-ሐበሻ- ብዙ
1586ኢትዮጵያውያን ሀገሬ መግባት እፈልጋለሁ ይላሉ
1587ልክ እንዳንቺ; ግን ሲገቡ አይታዩም ለምን
1588ይመስልሻል?
1589ቅድስት- መቼም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እዚህ ይኑር
1590እንጂ ልቡ ያለው ሀገር ቤት ነው ስለሀገሩ
1591የማያስብና የማይናፍቅ የለም ያለመሙላት ጉዳይ
1592ነው እንጂ ሁሉም ቢገባ ደስ ይለዋል እኔም
1593ከወጣሁ ቆይቻለው ሰውን ወደ ሀገሩ እንዳይሄድ
1594የሚያደርገው የገንዘብ ጉዳይ ነው እዛ ሄዶ ከዚህ
1595ዝቅ ብሎ መኖር ስለማይፈልግና ኢትዮጵያ ሄጄ
1596ከዚህ ያነሰ ልኖር?
1597እያለ ስለሚፈራ; እሄዳለሁ እንዳለ ሳይሳካለት
1598እዚሁ ይቀራል እኔም የምፎክረው ገንዘብ ቢኖረኝ
1599ዛሬ እሄዳለሁ እያልኩ ነው ዘ-ሐበሻ- ወደ ሥራሽ
1600እንመለስና; ከመኪና ጋር አብሮ መዋል ብዙ አደጋ
1601አለው ችግርም ያጋጥማል ለመሆኑ መንገድ ላይ
1602እየሄድሽ ጎማ ቢፈነዳብሽ ራስሽ ነሽ የምትቀይሪው?
1603ቅድስት-ሳቅ
1604 ኸረ እኔ አልችልም ጎማ ቢፈነዳብኝም
1605ቢበላሽብኝም መኪናዬን አስገፍቼም ቶው አስደርጌ
1606ይዤ ወደ መካኒክ ነው የምሮጠው ዘ-ሐበሻ-
1607የሚኒሶታ አየር ትንሽ ይከብዳል በተለይ
1608በክረምቱ ጊዜ ያለው በረዶ ጠንከር ያለ ነው
1609አንቺ እንዴት ነው ይህንን አስቸጋሪ የክረምት
1610ወራት ካለ አደጋ በረዶ ላይ በመንዳትና; በረዶ ላይ
1611ቆሞ ወረፋ በመጠበቅ የምትሰሪው?
1612ቅድስት- ይገርምሀል እኔ የሚኒሶታ ክረምት
1613አይከብደኝም እንደውም ተስማምቶኝ ነው
1614የምሰራው ለምን መስለህ ስዊድን ሀገር ከዚህ
1615የባሰ በረዶ ስኖው አለ እናም ተስማምቶኝ ነው
1616የምሰራው በደንብ ከለበስክ ከሚኒሶታ በጋ
1617ክረምቱን እመርጣለሁ መንዳቱም ቢሆን
1618ተጠንቅቀህ ከነዳህ መንሸራተትም አደጋም የለም
1619ለታክሲ ስራ ገበያ የሚኖረው የክረምቱ ጊዜ
1620እንደሆነም አትርሳ ሳቅ ስለዚህ ክረምቱን
1621እወደዋለሁ ዘ-ሐበሻ- ኢትዮጵያውያን ወንዶች
1622በቤት ስራ ደካሞች ናችሁ እንባላለንና አንቺም
1623ከእነርሱ ጋር እንደመዋልሽ ሙያውም ጠፍቶብሽ
1624ይሆን?
1625ቅድስት- ሳቅ
1626 አልክድም እንደ ሴት መንጎዳጎድ አይሆንልኝም
1627እንደውም እዚህ ያሉት በጣም ይፈታተኑኛል
1628ሳቅ ሙያሽን እንቅመሰው እስኪ አገልግል
1629ፈትፍተሽ አምጪ ይሉኛል; ግን አይሆንልኝም እኔም
1630ሴትነቱ ጠፍቶኛል መሰለኝ አላበላም ብዬ ቁጭ
1631ብያለሁ አልሞከርኩትም እንጂ ሳይጠፋኝ
1632አይቀርም ለራሴም ቀባ ቀባ አድርጌ ነው የምበላው
1633እንደወንዶቹ ቀለል ያሉ የፈረንጅ ምግብ; ሩዝ
1634ወይም ፓስታ እያበሰልኩ ነው የምመገበው ወጣ
1635ወጡን ነገር ሳልረሳው አልቀርም ዘ-ሐበሻ-
1636አግብተሻል?
1637ቅድስት- አላገባሁም ዘ-ሐበሻ- ለምን አላገባሽም
1638ብዬ አልጠይቅሽም ግን ብዙ ጊዜ ከወንዶች ጋር
1639ስለምትውይ ተጽእኖ አሳድሮብሽ ይሆን?
1640ቅድስት- ኖ!
1641ላሳደረብኝም የራሴ የሆነ ፐርሰናል ጉዳይ
1642ያለማግባት ጉዳይ ነው ዘ-ሐበሻ- እሺ እንተወው
1643የሕይ ወት ፍልስፍናሽ ምንድን ነው?
1644ቅድስት- እኔ በእግዚአብሄር የማምን ሰው ነኝ
1645የቤተክርስቲያን ሰው ነኝ ያደግኩትም
1646ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ነው በሕይወቴ
1647የሚያጋጥሙኝ ነገሮችና የሚፈጠሩት ሁኔታዎች ሁሉ
1648በእግዚአብሄር ፈቃድ ብዬ ነው የማምነው ከዛ
1649በተረፈ እኔ ማድረግ ያለብኝን ነገር ሁሉ
1650አደርጋለሁ ቀጥሎ ያለው በእግዚአብሔር የሚሆን
1651ነው ዘ-ሐበሻ- በመጨረሻም ምን ትያለሽ?
1652ቅድስት- ማለት የምፈልገው?
1653ብዙ ጊዜ ለሀበሾች ታክሲ ነው የምነዳው ስል
1654አንዳንዱ ይደነግጣል; አንዳንዱ ይገረማል;
1655አንዳንዱ አብረታቶኝ ያልፋል አብዛኛው ሴት ሆኜ
1656የታክሲ ሥራ ላይ ሲያየኝ 'ጉድ' ይላል እኔ የምለው
1657ግን በተለይ ሴቶች የታክሲ ሥራ አያስፈራም; ቀላል
1658ነው; ኑና ሞክሩት ነው የምለው ብዙ ጊዜ የእኛ
1659ሴቶች ፈሪዎች ነን መንገድ እንፈራለን
1660አይናፋር ነን
1661ግን ኑ የታክሲ ሥራ ቀላልና የሰነፍ ሥራ ነው
1662የምለው ሴቶች መጥተው ቢሞክሩት ደስ ይለኛል
1663ዘ-ሐበሻ- እናመሰግናለን ቅድስት ቅድስት- እኔም
1664አመሰግናለሁ ®
1665ካሳሁን ገርማሞ በ1939 ዓም አዲስ አበባ ተወለደ
1666ወላጅ እናቱ ወሮ ዘነበች አንጩ፣ አባቱ ገርማሞ
1667ወናዬ ይባላሉ፡፡ ካሳሁን አዲስ አበባ ይወለድ
1668እንጂ ያደገው ግን ተፈሪ ኬላ በምትባል አገር ነው፡፡
1669እድሜው ለትምህርት እንደደረሰም ተፈሪ ኬላ
1670አንደኛ ደረጃ ትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ
1671እዚያው ትምህርቱን በመከታተል ላይ እንዳለ
1672ቤተሰቦቹ ተመልሰው ወደአአ በመምጣታቸው እሱም
1673ወደ ትውልድ አገሩ ተመለሰ፡፡ አአ መጥቶ ልዑል
1674መኮንን ትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ፡፡
1675ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገባ በተማሪዎች
1676መማከርት በነበረው ንቁ ተሳትፎ ‹‹የባለታሪካችንን››
1677ገፀ ባህሪይ ወክሎ ተማሪዎች ፊት መታየት ጀመረ፡፡
1678በግጥሞችም የሁለገብ ችሎታውን አሳየ፡፡
1679ካሳሁንም እንዲህ እያለ ትምህርቱን ጨረሰ፡፡
1680ትምህርቱን ጨርሶ ግን አልቆመም ቀጥታ ያመራው
1681ወደ ፖሊስ ሙዚቃና የቴአትር ክፍል ነው፡፡
1682በወቅቱም እንደርሱ ያለ ሰው ያስፈልግ ስለነበር
1683ታህሳስ 1961 ዓም የቅጥር ውል ፈጽሞ በቋሚነት
1684ስራውን ጀመረ፡፡ እዛም በመስራት ላይ እያለ
1685ለታዋቂ ድምጻዊያኖች ግጥምና ዜማ በመስጠት
1686ይታወቃል ግጥምና ዜማ ከሰጣቸው ድምጻዊያኖች
1687መካከል ሒሩት በቀለ፣ ታደለ በቀለ፣ በኃይሉ
1688እሸቴና ተስፋዬ በላይ…በግንባር ቀደምትነት
1689ይጠቀሳሉ፡፡ ‹‹ካሳሁን ከመድረክ
1690አስተዋዋቂነት ጎን ለጎን ግጥም ይጽፋል፣ ዜማ
1691ይደርሳል፣ አዳዲስ የውዝዋዜ ስልቶችን ያወጣል፣
1692ሙዚቃ አሬንጅ ያደርጋል የመድረክ አስተዋዋቂ ነው
1693ቀልድና ቁምነገር በአንድ ላይ ማዋሀድ ይችልበታል፡፡
1694በ1960ዎቹ ዓም በፖሊስ ሰራዊት ሙዚቃና ቴአትር
1695ክፍል ውስጥ ካሳሁን ገርማሞ መድረኩን ሲመራ
1696ጥላዬ አራጌ ስትወዛወዝ ሁለቱም ወጣቶች ለፍቅር
1697ተጫጩ፤ የመድረክ ተወዛዋዥ ጥላዬ የተመልካችን
1698አይን ብቻ ሳይሆን ካሳሁንንም ቀልብ ገዛች፡፡
1699እሷም በልዩ የመድረክ አቀራረብ ለዛው ተሳበች
1700ተፈላለጉ ተዋደዱ ጐጆ ለመቀለስ ወሰኑ፡፡ በሐምሌ
1701ወር 1967 ዓም የጋብቻ ስነስርዓታቸውን ፈጸሙ
1702በሐምሌ ወር 1968 ዓም ቴዎድሮስ ካሳሁን ተወለደ
1703ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ ስለአባቱ
1704ከተናገረው፡- አባቴና እናቴ የተገናኙበትን ጊዜ
1705በትክክል ባላውቀውም መስሪያቤታቸው አንድ ላይ
1706መሆኑን አውቅ ነበር እሱ የመድረክ መሪ እሷ ደግሞ
1707የመድረክ ተወዛዋዥ ነበረች፡፡ የተጋቡት በ1967
1708ዓም ነው እናቴ ጥላዬ አራጌ የ17 ዓመት ወጣት
1709ነበረች፡፡ እርሱ ደግሞ ወደ 20ዎቹ መጨረሻ ነበር
1710ሲሉ አውቃለሁ በተጋቡ በአንድ አመታቸው እኔ
1711ተወለድኩኝ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ብዙ አመት
1712አብረው አልኖሩም የተለያዩበትን ቀን በትክክል
1713ባላውቀውም ለ6ኛ የልደት ቀኔ እለት ግን እናቴ
1714አልነበረችም፡፡ አባቴ ከዚያ በኋላ ለራሱ
1715አልኖረም እናትም አባትም ሆኖ አሳደገኝ የኖረው
1716ለኔ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት ቤት አስተምሮኛል፡፡
1717በዘመናዊ አስተዳደግና በጥሩ ስነምግባር
1718አሳድጐኛል።
1719አባቴ ሙዚቀኛ እንድሆን ፈጽሞ አይፈልግም
1720አስቦትም አያውቅም ምክንያቱም በነሱ ዘመን
1721በኪነጥበቡ አካባቢ የነበሩ ሰዎችን በኑሮ ውጤታማ
1722አለመሆንን በማየት ይመስለኛል በተጨማሪም ልክ
1723የምስራ ሳይሆን የማጠፋ ስለሚመስለው የኔን
1724ሙዚቀኝነት አልወደደውም ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን
1725የስራ ውጤቴን የኔንም ስነስርዓት ሲያየው ሞያዬን
1726እየተቀበለው መጥቶ ነበር፡፡ ግን መጨረሻውን
1727ሳያየው ቀረ የምወደው አባቴ በ1993 ዓም ከዚህ
1728አለም በሞት ተለየ፡፡ ‹‹ከአርቲስት ቤተሰብ
1729መፈጠሩ ደስ ይለኛል›› ክቡር ዶር ድምጻዊ
1730ጥላሁን ገሠሠ አባቱ ካሳሁን ገርማሞ የፖሊስ
1731ኦርኬስትራ አስተዋዋቂና የፖሊስ ፕሮግራም
1732ጋዜጠኛ ነበር፡፡ እናቱ ወይዘሮ ጥላዬ እዚያው
1733ክፍል ውስጥ በተወዛዋዥነት ሰርታለች፡፡
1734ቴዎድሮስ ከአርቲስት ቤተሰብ በመፈጠሩ በጣም ደስ
1735ይለኛል፡፡ ከዚያ ቤተሰብ ወጥቶ ለዚህ መብቃቱ
1736እጅግ ያኮራል፡፡ ልጁን እንደተመለከትኩት
1737የእድሜ ማነስ ሳይሆን ቁም ነገር ያለው ተግባር
1738ለመፈጸም እንደሚችል አውቃለሁ፡፡ በድምጹም ሆነ
1739በስራው አደንቀዋለሁ፡፡ ሊሰራ የፈለጋቸውን
1740ነገሮች ሁሉ አስቦ በራሱ ዜማ፣ በራሱ ግጥም፣
1741በራሱ ድምጽ አገናኝቶ መሰራት የሚችል ብቁ
1742አርቲስት ነው ማለት እችላለሁ፡፡ ‹‹ዘውድ
1743ብጭንና ቢዘፍንልኝ አልጠላም›› አቶ ውብሸት
1744ወርቅአለማሁ የማስታወቂያ ስራ ባለሙያ ስለሱ
1745ለመግለጽ በቂ ሀይል ያለው ቃል የሚገኝ
1746አይመስለኝም፡፡ ልጁ’ኮ ከስንት አንዴ ብቅ የሚል
1747ውብ ጀምበር ነው፡፡ ባቀረባቸው አራቱ ምርጥ
1748የመታሰቢያ ስራዎች፣ ለኃይሌ፣ ለግርማዊነታቸው፣
1749ለቀነኒሳና ለቦብማርሌ በዘፈናቸው ስራዎች
1750እንዳከብረው አድርጐኛል፡፡ አጥንት ሰብረው
1751ይገባሉ አእምሮው ከዘፈነላቸው ሯጮች በላይ
1752እንደሚፈጥን ይሰማኛል፡፡ አእምሮህን
1753እወደዋለሁ፡፡ ሸራተን ሆቴል መድረክ ላይ ሲጠየቅ
1754በቅርብ አይቼዋለሁ፡፡ የመልሱ ፍጥነት ችሎታውን
1755ገላጭ ነው፡፡ ምኞቴ፤ በዓለም ላይ የማይጠገቡ
1756አራት ነገሮች አሉ፡፡ ሀብት፣ እድሜ፣ ስልጣንና
1757ፍቅር እንዲያገኝ ነው፡፡ ልጁ ደግሞ ገንዘብ፣
1758ውበት፣ ዝና ወጣትነትና ብስለት አለው፡፡ ፍጹም
1759ለትዳር የተመቸ ነው፡፡ ግብዝ አይደለም፡፡
1760ቢሆንማ ኖሮ እስካሁን ይበላሽ ነበር፡፡
1761በመጨረሻም ዘር ቆጥሬ ‹‹ዘውድ›› ብጭንና
1762ቢዘፍንልኝ አልጠላም።
1763‘በከበሮ ጀመረ ዛሬ ለዚህ በቃ’ - አጐቱ አቶ
1764ሃይሉ ገርማሞ የልጅነት ምኞቱ ምን ነበር?
1765፦ የማትለየው ትንሽ ከበሮ ነበረች፡፡ እሷን ሁሌ
1766ይደልቃል፡፡ ዘፍነህ የት ልትደርስ ነው; እለው
1767ነበር፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ያውቃል፤ አንድ ቀን
1768ታየኛለህ›› ይለኛል፡፡ያሳደገችው እህቴ
1769ለፀጉር መቀጠያ ያመጣችውን አርቴፊሻል ፀጉር አፄ
1770ቴዎድሮስን ሆኖ ለመስራት ከቤት ይዞ ጠፋባትና
1771ስለምትወደው ተወችለት፡፡ በከበሮ ጀመረ ዛሬ
1772ለዚህ በቃ፡፡ ‹‹የሳይንስ ትምህርት ፍላጎት
1773ነበረው›› መምህሩ ሐጎስ አርአያ ቤቴልሔም
1774ትምህርት ቤት ውስጥ 6ኛ ክፍል ሳይንስ
1775አስተምሬዋለሁ የሳይንስ ትምህርት ፍላጐት
1776ነበረው፡፡ በክፈለ ጊዜው ለእረፍት ያህል መሐል
1777ላይ መዝናኛዎች አይጠፉም የልብና የአንጀት
1778ስዕሎች ሳቀርብ ቴዲ በግጥም ይገልጻቸዋል፡፡ ንቁ
1779ተማሪ ነው፡፡ እያዝናና ጭንቅላታቸው ውስጥ
1780እንዲቀረጽ ያደርጋል፡፡ ወደሌላ ክፍል
1781እወስደውና ያነብላቸዋል በዚህ ምክንያት ሁሌም
1782ተሰጥኦ እንዳለውና እንዲገፋበት እነግረው ነበር፡፡በትምህርት
1783ቤት ክበባት ውስጥ በስነጽሁፍ ጥያቄና መልስ
1784ውድድር ላይ ይወዳደራል ግጥሞቹንም በዘፈን መልክ
1785ያቀርባቸዋል፡፡ አድጐ ‹‹ባይገርምሽ ገና
1786እወድሻለሁ›› እያለ በቴሌቪዥን ሲጫወት ማየቴ
1787ትንግርት ሆነብኝ ‹‹ይህ ልጅ ትልቅ ሰው ሆነ››
1788አልኩኝ፡፡ ከዘፈኖቹ ‹‹ታሪክ ተሰራ›› እና ‹‹ባይገርምሸን››
1789እወዳቸዋለሁ ‹‹አቡጊዳንም›› የራሱን ስልት
1790ካሳየባቸው ስራዎች አንዱ ነው፡፡ ወደፊት
1791የሱዳንና የጃፓን ስልቶችን በሙዚቃው ውስጥ
1792ቢያካትት እመርጣለሁ፡፡ ‹‹ቴዲ ችሎታ ያለው
1793ድምጻዊ ነው›› አቶ አዲሱ ገሠሠ የቴዎድሮስ
1794ካሳሁን ማኔጀር ከጂጂ ጋር ብቻ ነበር የሰራነው፡፡
1795ተሰጥኦ ስላላት በዓለም ላይ ላስተዋውቃት
1796ሞክሬያለሁ፡፡ ቴዲን በመጀመሪያ ወደ አሜሪካን
1797ወሰድኩት፡፡ ዋሽንግተን ባቀረበው ስራ ተስፋ
1798እንዳለው አወቅሁ፡፡ ከብዙ ሰዎች ጋርም
1799አስተዋወቅሁት ተሰጥኦውን እንዲያውቁለት፣
1800ችሎታውን እንዲያደንቁለት አደረኩ፡፡ ከዚያም
1801ወደአረብ ሀገራት በመሔድ የተለያዩ ዝግጅቶችን
1802አቅርቧል፡፡ በዘፈኑ በኩል አንዳንዴ ትንሽ ልጁን
1803ያለመረዳት ችግር እንዳለ አይቻለሁ፡፡ በተለያዩ
1804ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰርቷል፡፡ ያው እንደተለመደው
1805ብዙዎቹ የኪነጥበብ ሰዎች የሚያቀርቧቸው የፈጠራ
1806ስራዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚተረጎምባቸው
1807አውቃለሁ፡፡ ቦብ ማርሌም ይህ ደርሶበታል፡፡ ቴዲ
1808ችሎታ ያለው ድምጻዊ ነው፡፡ በቀረበበት መድረክ
1809ሁሉ ተቀባይነቱ እጅግ የደመቀ ነበር፡፡ እሱን
1810ይዤ በመስራቴ እደሰታለሁ፡፡ በተለይ ስራዎቹን
1811ከቤተሰቦቼ ጋር ሆነን ስናየው የተለየ ስሜት
1812አሳድሮብናል፡፡ እንደእኔ አስተያየት አልበም
1813ማውጣት ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የሰዎችን ፍላጐት
1814ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከተለያዩ አርቲስቶች ጋር
1815እንደመኖሬ ቴዲ ለየት ይላል፡፡ ሙዚቃ ህይወቴ ወ
1816ካሣ መንፈስ በቱባው ቋንቋ ተው ልጄ ኪነት- ከሀሁ
1817ታረቅ በአንቺ ሆዬ ቃና- ዮራይስመሌ በጉራጊኛ
1818በትዝታ ቃና- ፈርዲዳ ማሣርቦ በአንቺ ሆዬ ቃና-
1819ደርፊ ምስ ጓላይ በትግሪኛ ቶሌ ቶሌ ያሚ ጋሪ
1820ናቃሪ ፈያ በኦሮምኛ ወላይታ ካአ በወላይትኛ
1821ሙዚቃ ህይወቴ ግዕዝና ዕዝል አራራይ የተሰጠች
1822ከላይ ያሬዳዊ ስልቱ የሰማይ ፀጋ አቆራኘኋት
1823ነፍሴን ከአንቺ ጋ፡፡ በአገሬ ቅኝት የብሔር
1824ቋንቋ እደሰታለሁ እኔ አላዝነም በቃ፡፡ በአፋር
1825ሲዳማ በጋምቤላ ቶም ልርገጥ ዳንኪራ እኔ
1826አላዝንም ከቶም፡፡ መሀያበያባ መሃያበያባ በአፋርኛ
1827ሃያባያ መሃያበያባ ሀያብዬ እኔስ ለአብዬ፡፡
1828ሙዚቃ ህይወቴ ግዕዝና ዕዝል አራራይ የተሰጠች
1829ከላይ ተው ቢል አልሰማ በልጅነቴ ገርፎ ሲቀጣኝ
1830ሲመክረኝ አባቴ ስንት ያየሁብሽ ሙዚቃ ህይወቴ
1831ቆመህ ካላየህ አታምንምና ላባብልህ ዛሬ በክራሬ
1832ቃና ለሟች ማዘን የለም ባለው መጽናናት ነው ብለህ
1833እንዳስተማርከኝ ባንተው ምክር ሄጄ በአንተው
1834አስጨከንከኝ እሱ እንዳለው ያ ሎሬቱ ሞትም ይሙት
1835የታባቱ በሞትህ ላይ ፎክሬበት በዳንኪራ ትነሳለህ
1836ከእኔ ጋራ መሀያበያባ መሃያበያባ ሀያብዬ
1837አልሞትክም አብዬ መሃያበያባ መሃያበያባ ሃያብዬ
1838እኔ አለሁ አብዬ፡፡ ሙዚቃ ህይወቴ ግዕዝና ዕዝል
1839አራራይ የተሰጠች ከላይ በዚህ ኑሮ ብሎ ከላይ
1840ካዘዘ ልጁ ምን ያድርግ ክራሩን ያዘ፡፡
1841አትዘንበት አደራ አብዲ አባቴ ማርኮት ቅኝቱ ምን
1842ያድርግ ኧዲ፡፡ እኔ መሃያበያባ መሃያበያባ
1843ሃያባያ መሃያበያባ መሃያበያባ መሃያበያባ
1844ሃያብዬ ጀነቱን ለአብዬ፡፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን በቴዲ
1845አፍሮ ‹‹ስራዎቹ የላቀ ኢትዮጵያዊ ስሜት
1846አላቸው›› ተዋናይ፣ ፀሐፌተውኔት፣ አዘጋጅና
1847ገጣሚ ጌትነት እንየው የግጥሞቹ ይዘት፦ የቴዲ
1848የዘፈን ግጥሞች፣ ይዘታቸው፣ ስፋት አላቸው፡፡
1849ከሌሎች ከምንሰማቸው በጾታ ፍቅር ርዕስ ላይ
1850ከሚያጠነጥኑት የላቀ ነው፡፡ ወደኋላ ታሪካዊ
1851የሆኑ ድርጊቶችን ያነሳሉ፡፡ ጀግኖች ያወድሳሉ፡፡
1852ስለ አፄ ኃይለስላሴ፣ ስለኃይሌ ገብረስላሴ፣ ‹‹እንደየሩሳሌም››
1853የሚለውና ስለሩጫው የሰማነው ሁሉ ብሔራዊ ስሜትን
1854የሚቀሰቅሱ ናቸው፡፡
1855ጭብጦች፦ የሚያነሳቸው ጭብጦች በፍቅር ብቻ
1856የተወሰኑ አይደሉም፡፡ ብሔራዊ ማንነትን
1857ይገልጻሉ፡፡ ይሔ ,,, የሚለው የእኛ አቡጊዳ ነው
1858ከልጅነት የህይወት ያህል ይሰፋል፡፡ አሁን ላይ
1859ሆኜ ስሰማው ያኔ ቁምጣ ለብሼ ቄስ ትምህርት ቤት
1860ውስጥ በጅራፍ ተገርፌ አንገቴ ያበጠውን
1861አስታውሳለሁ፡፡ ስራዎቹ የላቀ ኢትዮጵያዊ ስሜት
1862አላቸው፡፡ በአንድ ምሽት እንደዚያ በጣም ስሜት
1863የሚቀሰቅስ ጽሁፍ ድንገት የሚመጣ አይደለም፡፡
1864አቀራረብ፦ ከህጻናት እስከ ሀገር መሪዎች ድረስ
1865ያደነቁት ሰፊና ታሪካዊ የሆኑ ጭብጦችን በቀላል
1866ቋንቋ የመግለጽ ብቃት ስላለው ነው፡፡ ምናባዊ፣
1867ውስጣዊ የሚል ትርጓሜ ኖሮት ቃላቱ ሲፈቱ
1868አይከረሙም፡፡ ይሰማል ይገባል፡፡ በቀላል ቋንቋ
1869ለመግጠም የራስ የሆነ ብቃት ይጠይቃል፡፡ ለምሳሌ
1870መንግስቱ ለማቀላል በሆኑ ቃላት፣ ቀለል ባሉ
1871አገላለጽ የሚያፈላስፉ ጉዳዮችን ያነሳሉ፡፡
1872ቀላልና ተራ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ቀለል
1873ያለው ቋንቋ አጠቃቀም ሙዚቃ ወዲያው እንዲገባ
1874ይረዳል፡፡ እንደ መንግስቱ ለማ ጥልቅ ሀሳብን
1875በቀላል ቋንቋ የሚያቀርቡ ጥቂት ናቸው፡፡ በዘፈኑ
1876በኩል ቴዲን አግኝተናል፡፡ ‹‹እስካሁን
1877እንድሮጥ አድርጐኛል አርጅቼም በከዘራ ሳልሮጥ
1878አልቀርም!
1879›› አትሌት ኃይሌ ገስላሴ ክቡር ዶር • ዘፈንና
1880ስሜት፦ - ‹‹አልሆንልህ አለኝ›› የሚለው ዘፈኑ
1881ከምስል ጋር ተቀናብሮ መታየቱን ነገሩኝ፡፡ ያኔ
1882አቴንስ ነበርኩ፡፡ ዜማውን በመጠኑ በስልክ
1883አሰሙኝ፡፡ ብዙም ጥራት አልነበረውም፡፡ ስመጣ
1884ከቤተሰቦቼ ጋር ተመለከትኩት ያስለቅሳል፡፡
1885ውስጤ የሆነ ነገር ተላወሰ፡፡ ያንን መግለጽ
1886ይከብደኛል፡፡ ስሜትን ይረብሻል እውነተኛ
1887ህይወት ውስጥ ይከታል፡፡ የሚደነቅ አይነት ነበር፡፡
1888ያንን እያየሁ መተኛትም ሆነ መቀመጥ
1889አልነበረብኝም ኦፕራሲዮን ሆኜ ሮጫለሁ፡፡ •
1890የዜማ ኃይል፦ - ‹‹መርቆ ሸኝቶ ሀገር›› የሚለው
1891ይስበኛል፡፡ ሽማግሌው ሲመጡ ሳይ፣ ቀነኒሳ
1892ወደኋላ እየዞረ ሲመለከት ‹‹አንተን ጥሎ መሔድ…››
1893ሲል እነሱ ቦታዎች በጣም ይረብሹኛል፡፡
1894በመጀመሪያ ስለ እኔ በዘፈነው እስካሁን እንድሮጥ
1895አድርጐኛል ለዚህ ደግሞ እኔ እንጃ አርጅቼም
1896በከዘራ ሳልሮጥ አልቀርም፡፡ ‹‹እውነትን በዜማ
1897ይነግረናል›› ደራሲና የፊልም ዳይሬክተር
1898ተስፋዬ ማሞ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ምን ያህል
1899ተዋህደው እንደሚኖሩ አንድ ምሳሌ ላንሳ፣ ወሎ
1900ውስጥ አንድ ቤተክርስቲያን አለ፡፡ ስሙን
1901ካልተሳሳትኩ ሩጋ ሚካኤል ይባላል፡፡ እዚያ
1902የሚኖሩት አብዛኞቹ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ቀሳውስቱ
1903በቁጥር ያንሳሉ፡፡ ካህናቱ ቤተክርስቲያኑን
1904ለማስተዳደር አንስተው ደሴ ለማድረግ ያስባሉ
1905ይሔኔ የአካባቢው ሙስሊሞች ይቃወማሉ፡፡
1906ተባብርን የጐለደውን አሟልተን ትኖራላችሁ እንጂ
1907አትሔዱም ብለው ይከለክሏቸዋል፡፡ ኮሚቴ ተቋቁሞ፣
1908ገንዘብ ተዋጥቶ ቤተክርስቲያኑ እስካሁን እዚያው
1909ይኖራል፡፡ ቴዲ ይህንን ነው በጥሩ ቋንቋ
1910የገለጸው፡፡ ይህ ለኛ ብቻ አይደለም ለዓለም
1911ሊሸጥ ይችላል፡፡ ዛሬ በአክሪራነት በግራና ቀኝ
1912አለም በምትተራመስበት ሰዓት ኢትዮጵያ
1913እንደትልቅ ተምሳሌት እንድትቆጠር ያደርጋታል፡፡
1914በመሆኑም በቴዲ እንኮራበታለን በልጅነቱ ያገር
1915ሽማግሌ ስራ እንደመስራቱ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
1916‹‹ልቤ መጮህ ይፈልጋል›› ትርፌ ማንያህልሃል ዲጄ
1917ኪን ቴዲ በግጥሞቹ፣ በዜማዎቹ እና በቅላጼው
1918ትልቅ ስራ አበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ብዙ ነገሮች
1919ማካተትን ችሏል፡፡ ቴዲን እንደጥላሁን ገሠሠ ነው
1920የማየው በስሜት ነው የሚዘፍነው፡፡ የሰውን የልብ
1921ትርታ የሚያውቅ ይመስለኛል ለዚህም ሳይሆን
1922አይቀርም አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል
1923ዘፈኖቹን ያዳምጣቸዋል፡፡ እኔ አስከማውቀው
1924ድረስ ለቦብ ማርሌ አድናቆት አለው፡፡ ከልቡ
1925ይወደዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የሬጌን የሙዚቃ
1926ስልት ሲሞከር አይቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ የጀማይካ
1927ሳይሆን የኢትዮጵያ ስልት ይጐላበታል፡፡ እናም
1928የኛን ፈጥሯል ማለት እችላላሁ፡፡ ቴዲ ስለዘፈኑ
1929ሲነግረኝ ልቤ መጮህ ይፈልጋል ይለኛል፡፡
1930እግዚአብሔር በሰጠኝ ተሰጥኦ ለህዝቡ ማገልገል
1931አለብኝ ይላል፡፡
1932ቀዩን ቲሸርት በጥቁር መነጽር አድጎ ከ16 ወራት
1933እስራት በሗላ የተፈታው ድምጻዊው ቴዎድሮስ
1934ካሳሁን በታሰረ ወቅት አብሮ ለታሰረው የኢትዮጵያ
1935ሕዝብ ያለውን አክብሮት ገለጸ ድምጻዊው ከእስር
1936ከተፈታ በሗላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለምልልስ 'በእስር
1937ቤቱ ከበርካታ መልካም ኢትዮጵያውያን ጋር ጥሩ
1938ጊዜ ማሳለፉን' ገልጧል በታሰረበት ወቅት
1939ከአድናቂዎቹ የመጡለትንና ሲገለገልበት የነበረ
1940ውን መጽሀፍት ለማረሚያ ቤቱ ቤተ-መጽሀሐፍት
1941የሰጠው ቴዲ ያሉትን ልብሶቹን እና ቁሳቁሶቹንም
1942ጠያቂ ለሌላቸው እስረኞች ጋር አከፋፍሏል
1943በሐምሌ ወር እናት እና አባቱ ተጋብተው፣ በሐምሌ
1944ወር የተ ወለደው፣ በሐምሌ ወር ለተወለዱት
1945ለቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴ ዘፍኖ ሁለት ሐምሌዎችን
1946በእስር ያሳለፈው ቴዎድሮስ ካሣሁን ገርማሞ
1947ጥቅምት 23 ቀን 1 999 ዓም ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት
1948ከአስር ደቂቃ ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17
1949ክልል በቤተ መንግሥት አካባቢ ንብረትነቱ የግሉ
1950በሆነው ኮድ 2-59868 አ ዲስ አበባ አው ቶሞቢል
1951መኪናቸው ደጉ ይበልጣል የተባለ እግረኛ ገጭቶ
1952ገድሎ አምልጧል በሚል በቀረበበት ክስ በወቅቱ
1953ቴዲ አፍሮ በመኪና ገጭቶ ገድሎ ታል በሚል
1954የተጠረጠረበትን የሟ ች ደጉ ይበልጣል የሕይወት
1955ታሪክ በወቅቱ “ፎር ቹን” የተባለ የእንግሊዘኛ
1956ጋዜጣ የሟች አባት አ ቶ ታምሩ ተፈሪን ጠቅሶ
1957እንደዘገበው፤ ሟች ከጎ ጃም መጥቶ ሽሮ ሜዳ
1958አካባቢ ከአጎቱ ጋር ይኖር የነበረ የ18 ዓመት
1959ወጣት ነው።
1960ደጉ መጠጥ ከሚ ጠጡ ልጆች ጋር በመግጠሙ ቤቱን ጥሎ
1961ለጎዳ ና ሕይወት ይዳረጋል።
1962ነገር ግን በሣምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ወደ
1963ቤተሰቦቹ በመምጣት ይጠይ ቃቸው እንደነበር ነው
1964ቴዲ በወቅቱ ለአዲስ አድማስ ና ሪፖርተር ጋዜጣ
1965የሰጠው መልስ “ሰውን የሚያህል ክቡር ነገር
1966ገጭቼ ላመልጥ አልችልም፣ እኔ ድርጊቱ ተፈጸመ
1967በተባለበት ቦታ አልነ በርኩም፣ 'ሰው ገጭቶ
1968አምልጧል' የተባለው ወሬ ሐሰትና ጉዳዩም ክብሬን
1969የሚነካ ነው” ነበር ያለው።
1970"እኔ ሀገር ውስጥ የገባሁት በጥቅምት 23 ቀን ነው፣
1971የምኒልክ ሆስፒታል ማስረጃ እንደሚያስረዳው
1972ደግሞ ሟች የሞተው በጥቅምት 22 ቀን ነው።
1973” ብሎ በፍርድ ቤት ሲከራከር የቆየው ቴዲ አፍሮ 6
1974አመት በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተፈረደበት ወቅት "ዳኛው
1975በቅንነት ክሴን አልተመለከቱትም" ሲል መክሰሱ
1976ይታወሳል በዚህም የተነሳ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት
1977ይግባኝ ያቀረበው ቴዲ እስሩ ወደ 2 አመት
1978ተቀንሶለት በአመክሮ ተፈቷልበቴዲ አፍሮ ዙሪያ
1979የተጠናቀሩ ዘገባዎችን በውስጥ ገጽ ይፈልጉ።
1980የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ ድምጻዊው
1981ቴዲ አፍሮ በእስር ቆይታው ሰለሜ በሚለው የሙዚቃ
1982አልበሙ አንድ ሰአሊ ሥራዬን ተጠ ቅሟል በሚል የ100
1983ሺህ ብር ክስ ቢመሰርትበትም ቴዲ በዚህም ክስ
1984ከዚህ ቀደም ነጻ መውጣቱ ይታወሳል ስለ ፍቅርና
1985ስለአንድነት የዘፈነው ቴዲ አፍሮ በተደጋጋሚ
1986ፖለቲከኛ አለመሆኑን ቢገልጽም እንደኢትዮጵያ
1987ባሉ ሀገራት ስለ አንድነት መስበክም ሆነ ማውራት
1988ምን ያህል ጥርስ ውስጥ እንደሚያስገባ የቴዲ
1989ጉዳይ ያሳየናል የሚሉ ተንታኞች በርካታ ናቸው ®
19901 የቴዲ አፍሮ ጉዳይ ፖለቲካዊ መምሰሉና ጠበቃው
1991አቶ ሚሊዮን አሰፋ የኢህአዴግ ደጋፊና የምርጫ
1992ቦርድ ጠበቃ ሆኖ፣ የቅንጅት አመራሮች እስር ቤት
1993በነበሩበት ወቅት እስሩን ደግፎ ሞት ሊፈረድባቸው
1994ይገባል እያለ በመንግሥት ራዲዮና በኢትዮጵያ
1995ቴሌቭዥን በየቀኑ መግለጫ ሲሰጥ የነበረ ጠበቃ
1996መሆኑ፤ 2 ሁለተኛ ወንጀል ችሎት የነበሩትና
1997ለሁለት ዓመታት የዘለቀውንና የቅንጅት አመራሮች
1998 የተከሰሱበትን ችሎት በቀኝ ዳኝነት ሲያስችሉ
1999የነበሩት አቶ ልዑል ወማርያም በድንገት 8ኛ
2000ወንጀል ችሎት መገኘት፤ አቶ ልኡል ለበርካታ
2001ጋዜጠኞች መሰደድ መታሰር እና መታረዝ ዋና
2002ምክንያት ነው ሰሞኑን አዲስ አበባ ከተማ
2003በተደረገው የታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ የቴዲን ስም
2004የጠሩና ፎቶ ግራፉ ያለበትን ቲሸርቱን የለበሱ
2005መታሰራቸው፤ በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል የሚመራው
2006መኢአድ በአዲስ አበባ አደባባዮች የመኪና ላይ
2007ቅስቀሳ ሲያደርግ በቴዲ አፍሮ ሙዚቃዎች
2008እንዳይቀሰቅሱ መከልከላቸው፤ 3 ምኒልክ ሆስፒታል
2009በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦርጅናል የአስከሬን
2010የምርመራ ውጤትን 'ተሳስቷል' በሚል መቀየሩ፤ 4
2011ችሎት በሚኖርበት ጊዜ በርካታ ቁጥር ያላቸው
2012ደህንነቶች ችሎቱን ማጨናነቃቸውና ችሎት
2013ተከታታዩን ሰው ማስጨነቃቸው፤ 5 በቴዲ የፍርድ
2014ቤት ንግግር ያለቀሱ አድናቂዎቹ መታሰርና
2015መንገላታት 6 የቅንጅት አመራሮችን ሲጠብቁ
2016የነበሩ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች
2017ሳይታክቱ በችሎት በመገኘት ጥብቅ ቁጥጥር
2018ማድረጋቸው፤ 7 ቃሊቲ ከገባ በኋላ ለብቻው መታሰሩ፤
20198 ከተወሰኑ ሰዎች በስተቀር ማንም እንዳይጠይቀው
2020መከልከሉ፤ በመኪና ሰው ገጭተሃል በሚል ተጠርጥሮ
2021ለታሰረ ሰው ያልተለመዱ ድርጊቶች ናቸው።
2022''ኢትዮጵያዊ ኤልቪስ ፕሪስሊ '' ይሉታል የዛ ዘመን
2023ሰዎች በሙዚቃ ሥራው በዛም ዘመን በእኛም ዘመን
2024አዲስ ና ልዩ እንዲሁም የራሱ ፈጠራ ያለው ሰው ሆኖ
2025እዚህ ደርሷል ''አዲስ አበባ ቤቴ አዲስ አበባ
2026ቤቴ ሸጋ ልጅ ቆንጆ ልጅ አለች ጎረቤቴ '' ታዋቂው
2027የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ ''አለማየሁ
2028እሽቴን እንዴት አድርገህ ትገልጸዋለህ ?'' በሚል
2029መነን በሚባል መጽሄት ለቀረበለት ጥያቄ ትንሽ
2030ቆም ብሎ በማሰብ ''ሦስት ነግሮች አሉት '' ሲል
2031ይጀምራል ''አለማየሁ የራሱ የሆነ ፈጠራ አለው
2032ከሁሉም ዘፈኞች ወጣ ያለ ባህሪ እንዲኖረው
2033ይፈልጋል ከዚህም በላይ ለአዲስ ነገር ቅርብ
2034ነው '' ሲል ይገልጸዋል ይህ የጥላሁን ገለጻ
2035በእርግጥም ትክክል ነው በሾላ አካባቢ በገዛው
2036መሬት የሚኖረው አለማየሁ እሸቴ አብዛኞቹ የሙያ
2037አጋሮቹ ትዳር እና ሴት ሲቀያይሩ እስኩ ግን
2038እሳካሁን በአንድ ሴት እንደጸና አለ በሁለተኛ
2039ደረጃ ለአዲስ ነገር ቅርብ ነው ለሚለው የመጨረሻ
2040ካሴቱን መመልከት ይቻላል ከ 2 አመት በፊት
2041በአምባሰል ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ያወጣው ካሴቶ
2042እጅግ ተወዳጅ የነበረ ሲሆን በክሊፑም ዘንድ
2043የተዋጣለት መሆኑን አሳይቷል በ 3ኛ ደረጃ
2044አሌክስን ልዩ የሚያደርገው ራሱን ከዘመኑ ጋር
2045መለወጡ እና በቆመበት አለመቅረቱ ሲሆን ዘፈኖቹ
2046ከምንም በላይ በምክር እና በትምህርት ላይ
2047እንዲያተኩሩ ማድረጉ ላይ ነው ''ወደ ሙዚቃው ሙያ
2048ለመግባት መሰት የሆነኝ ለኤልቪስ ያለኝ ፍቅር
2049እና ክብር ነው '' የሚለው አለማየሁ ወደ ሙዚቃው
2050ሕይወቱ ሲገባ በቤተሰቦቹ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ
2051ጫና ነበረበት በተለይ አባቱ ከሽመል በበለጠ
2052እስከ ጠምንጃ መምዘዝ የደረሱበት ጊዜ ነበር ያኔ
2053 የዛ ዘመን ሰው ሙዚቀኛን እና ወርቅ አንጣሪን
2054እንዴት ይመለከት እንደነበር ማስታወሱ በቂ ነው
2055አለማየሁ ይቀጥላል ''
2056በተለይ አባቴ በሙዚቃ ሕይወት ውስጥ ጠልቄ
2057መግባቴን አልወደደልኝም ስዘፍን ውዬ ስመጣ
2058ማምሻውን እቤቴ ዱላ ይጠብቀኛል የዛን ጊዜ
2059የምንሰራው ለገንዘብ ሳይሆን ለሙያ ፍቅር ነበር
2060እናም አንድ ዘፈን አወጣሁ ያ ዘፈን - የሴት ልጅ
2061ከመባል ዘወትር የሚል ነበር ይህ ዘፈን
2062መልእክቱ አባት መሞት እንደሌለበት አባት ከሞተ
2063ልጅ የሴት ልጅ ቀማኛ ዱርዬ ተብሎ
2064እንደሚሰደብ መልእክት ያለውና የአባትን ጥቅም
2065አጉልቶ የሚያሳይ ነበር እናም አባቴ ይህን
2066ዘፈን በራዲዮና በሽክላ ሲሰማ ለሙያዬ ልዩ ፍቅር
2067አደረበት መኪና ገዝቶ ሰጠኝ ከዛም ያበረታታኝ
2068ጀመር '' የአለማየሁ የሙዚቃ ሕይወት ጅማሮ ይህን
2069ሲመስል በሙዚቃው ሕይወቱ እውቅናው በመላው
2070ኢትዮጵያ እየተሰራጨ በመጣበት ወቅት በምጽዋ
2071በኩል ጠፍቶ ወደ ሆሊውድ በባህር ጠፍቶ ሊሄድ ሲል
2072ተይዞ መመለሱን ያስታውሳል ''ያኔ ወጣት እያለሁ
2073ወደ ሆሊውድ መሄድ ፈልጌ ነበር ይህ ህልሜ
2074ቢያሳካ ኖሮ በአለም ላይ ታዋቂ ሰው እሆን ነበር ''
2075ይላል - አሌክስ ከአለማየሁ እሽቴ ጋር በጋራ
2076ለመዝፈን እድሉ ካጋጠማቸው አርቲስቶች መካከል
2077አንዷ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ነበረች አርቲስቷ
2078ለአለማየሁ ያላትን ክብር የምትገልጸው በቃል ብቻ
2079ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ''አለማየሁ ''
2080ትላለች ''ዳንሱና የዘፈን ግጥሞቹና መልእክቶቹ
2081ደስ ይሉኛል '' ትላለች አድናቂው እንደሆነች
2082የምትናገረው ኩኩ አብራው በመዝፈኗ እድለኛ
2083እንደሆነች ጭምር ታብራራለች በአራዳ ፒያሳ
2084አካባቢ የቆርቆሮ የሙዚቃ ባንድ ሰርተው የሙዚቃ
2085ጥማቸውን እጃቸው ላይ ልክ ማይክ እንዲመስል
2086እንጨት ወይንም ማንኪያ ይዘው እየዘፈኑ ሙዚቃን
2087የጀመሩት አሌክስና ጓደኞቹ እሱ በሙዚቃው ሥራውን
2088አንቱታን ሲያተርፍ ሌሎቹ ግን በሌላ ሥራ ላይ
2089እንደተሰማሩ ይናገራል በግልጽነቱና በትዳሩ
2090ታማኝነቱ በምሳሌነት ከአርቲስቶቻችን
2091የሚጠቀሰው አሌክስ - በ 1955 ፖሊስ ኦኬስትራ
2092ውዝዋዜ ለመቀጠር ለመሰልጠን ሄዳ ፍቅር
2093የሸመተችው እጅጋየሁ እስከዛሬ የአለማየሁ እሸቴ
2094ሚስት ነች አለማየሁ እንደ አርቲስት ቀበጥ
2095አይደለም ማለቴ ሲያገባ ሲፈታ የኖረ አይደለም
2096ትዳሩን አክባሪ ነው በአንድ ወቅት ለትዳሩ እና
2097ለልጆቹ ያለውን አመለካከት ሲነግረኝ ''ለሚስቴም
2098ሆነ ለልጆቼ ያለኝን ፍቅር የሚተካውም ሆነ
2099የሚለውጠው ምንም የለም ያለኝን ትርፍ ሰአት
2100ከእነሱ ጋር ባሳልፍ ደስተኛነኝ ""ነው ያለኝ ''አሁንም
2101ቅድምም ታሽካካለች ዶሮ እኔ አንቺን ማግኘቴ
2102ሕልም ነው ዘንድሮ አዲስ አበባ ቤቴ አዲስ አበባ
2103ቤቴ ሸጋ ልጅ ቆንጆ ልጅ አለች ጎረቤቴ አረ እንዳው
2104ይመኙሻል አረ እንዳው ይመኙሻል በምኞት ቢጓዙ
2105ወዴት ያገኙሻል '' እኚህ በፎቶ ግራፍ ላይ
2106የምትመለከ ቷቸው ግለሰብ አምሀ እሸቴ ይሰኛሉ
2107አምሀ እሸቴ የአባታቸው ስም ከአሌክስ አባት ጋር
2108ሲመሳሰልባችሁ ወንድሙ እንዳይመስሏቸው
2109ይልቅዬ በዛ ዘመን ታዋቂ የሙዚቃ አሳታሚ ነበሩ
2110በ 1944 የመጀመሪያ የሸክላ ካሴቱን ለሕዝብ
2111ሲያደርስ ሸክላውን ያሳተሙለት እኚሁ ግለሰብ
2112ነበሩ አምሀ እሸቴ የሙዚቃ አሳታሚ የሚል
2113ድርጅት የነበራቸው እኚሁ አባት ዛሬ በህይወት
2114አይኑሩ እንጂ ከጥላሁን ገሰሰ ጀምሮ በዛ ዘመን
2115የነበሩ ዘፈኞችን ዘፈኖቻቸውን በሽክላ
2116አሳትመውላቸዋል በሙዚቃ ሕይወቱ ከአንድ መቶ
2117በላይ ዘፈኖችን ለሕዝብ ያደረሰው አለማየሁ እሸቴ
2118እስካሁን በካሴትና በሲዲ የሰራቸው ዘፈኖቹ 8 ብቻ
2119ናቸው ''ኢትዮጵያዊ ኤልቪስ ፕሪስሊ '' አለማየሁ
2120እሸቴ ከአማርኛ ሙዚቃዎች ሌላ የእንግሊዘኛ
2121ሙዚቃዎች የሚዘፍን ሲሆን በተለይም አረብኛ
2122ሙዚቃዎችን በሱዳንኛ ዜማ ይዘፍናል ከዚህም
2123በተጨማሪ ሱማሊኛ ይዘፍናል አሁን ባለው ሥርአት
2124በእጅጉ የማይወደደው አለማየሁ ለዚህ ምክንያቱ
2125እንደ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች በተለያዩ
2126የተቃዋ ሚ ፓርቲዎች መድረክ በተለይም በአብዮት
2127አደባባይ ከሕዝብ ጋር ለተቃውሞ መውጣቱ በገዢው
2128መደብ ሰዎች ጥርስ እንዲነክስበትና አንዳንድ
2129ጫናዎችም እንዲደረጉበት ሆኗል
2130''ማን ይሁን ትልቅ ሰው ማን ይሁን ትልቅ ሰው ማን
2131ይሁን ትልቅ ሰው ማ ን ይሁን ትልቅ ሰው
2132ያንዱን ቁጅ አንደኛው ሲያኮስሰው ማን ይሁን
2133ትልቅሰው ያንዱ ቤት ሲጎድል አንዱ እየተረፈው
2134ክፉና ደጉን ዘመን ካሳለፈው እኔ ግን መራመድ ከቶ
2135አልቻልኩም ገና ትኋን !
2136ትኋን ደሜን መጦ ደሜን መጦታልና ጊዜው ጎዳኝ
2137እንጂ እኔ ሰው አላማም ዋ ያህያ ልጅ በቅሎ
2138ወርቅ ተሽልማ ብናገር ወረኛ ባለጌ ይሉኛል ብቻ
2139ግን በሆዴ ቢቀር ይሻለኛል !! የአሌክስን ይህን
2140ተወዳጅ ሙዚቃ በድምጹ ሲያንቆረቁረው ለመስማት
2141 ላይ 13ኛውን ሙዚቃ
2142ያዳምጡ አለማየሁ እሸቴ ከሞላ ጎደል ይህን
2143ይመስላል በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላውን ጥበብ አብረን
2144እንቆነጥራለንð
2145ከሔኖክ ዓለማየሁ በሥራ ላይ እድገት አግኝተሽ
2146ወደ ቤት ለመሄድ ቸኩለሻል ከመኪናሽ እንዴት
2147እንደወረድሽ ራሱ ትዝ አይልሽም ለባለቤትሽ
2148ይህን ታላቅ የምስራች ለመናገርና ደስታሽን
2149አብራችሁ በመፈንደቅ ለማሳለፍ አቅደሻል "ፐ
2150አሁን ባለቤቴ ሲሰማ እንዴት ይደሰት ይሆን?
2151መቼም እቅፍ አድርጎ አንገቱ ስር ጠምጥሞ
2152አስገብቶኝ ይስመኛል የእኔ ባለቤት እኮ አንበሳ
2153ነሽ ይለኛል" እያልሽ በአይነ ሕሊናሽ እያሰብሽ
2154ነበር መኪናሽን በፍጥነት እየነዳሽ ቤት የገባሽው
2155የባለቤትሽን ስም እየተጣራሽ በየክፍሉ
2156ስትፈልጊው ባለቤትሽ የለም "ውዴ
2157የእኔ ፍቅር
2158የት ነህ?
2159" እየደጋገምሽ እየተጣራሽ ነው ግን ባለቤትሽ
2160በቤት ውስጥ የለም በሁኔታው በጣም ተደናግጠሽ
2161ወደ ቤትሽ ጀርባ ስትሄጂ ባለቤትሽ ብቻውን
2162ባልተመለደ መልኩ ተቀምጧል እሱን ከቁብ
2163ሳትቆጥሪ ደስታሽን መናገር ቀጠልሽ ""የሥራ
2164እድገት አገኘሁ እኮ"" ብለሽ ስትነግሪው ባለቤትሽ
2165እንዳሰብሽው ከእቅፍሽ አስገብቶ ሳይስምሽ ወይም
2166ደስታሽ ደስታዬ ነው ሳይልሽ ጥሎሽ ቢሄድ ምን
2167ትያለሽ?
2168
2169በትዳርሽ ውስጥ አንድ ትልቅ ችግር አለ ማለት ነው
2170ይህን እንዳወቅሽ ከባለቤትሽ ጋር ንትርክ
2171ትጀምሪያለሽ ወይስ ምን ታደርጊያለሽ?
2172የዛሬው የመጀመሪያው የ"ዘ-ሀበሻ" ጋዜጣ
2173የመጀመሪያው እትም የሳይኮሎጂ አምድ ጽፉፌ
2174በስኬታማ ትዳር ላይ ያተኩራል አብረን እንቆይ
2175በሺዎች የሚቆጠሩ ትዳሮች ውስጥ ባልና ሚስት በቤ
2176ት ውስጥ የጎሪጥ የመተያየታቸው ነገር ይታያል
2177የአብዛኞቹ ትዳር ውስጥ ፍቅር በፍቅረኛነት ዘመን
2178ያለቀ ይመስል አንድ ቤት ውስጥ አንድ ሶፋ ላይ
2179ተቀምጠው ጀርባና ፊት መሰጣጠት የተለመደ ሆኗል
2180ሁለታችሁም ከሥራ ገብታችሁ አንቺ ወደ ጓደኞችሽ
2181ደውለሽ ስልክ የምታወሪ ከሆነ እሱም ጋዜጣ ይዞ
2182ተቀምጦ የሚያነብ ከሆነ ፍቅራችሁ ውስጥ
2183መሰለቻቸት የገባ አይመስላችሁም?
2184አብሮ ተቻችሎ መኖር እጅግ ከባድ ነገር ቢሆንም
2185ይህንን የሚወጡ ባለትዳሮች ከጀግናም በላይ ጀግና
2186አድርገው ሳይኮሎጂስቶች የሚጠሯቸው ለምን
2187ይመስላችኍል??
2188የሀገሬ ሰው ''ባል እና ሚስት ከአንድ ባልዲ
2189ይቀዳሉ"" ብሎ የተረተውም ከላይ ያልኩትን ሀሳብ
2190ያወፍርልኛል ባልና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ
2191ሲባል ሁለቱን አንድ አይነት ሀሳብ ያስባሉ ማለት
2192ብቻ ሳይሆን በአይን ተነጋግረው ይግባባሉ
2193በአይን ብቻ ፍቅር ይሰራሉ የሚፋቀሩ ከሆነ ቢጣሉ
2194እንኳን የትም ዞረው ይገናኛሉ የሚሉትንም
2195ያጠቃልላል የትዳር አጋሩን ሀሳብና ፍላጎት
2196የማይረዳ ካለ እርሱ ከትዳር አጋሩ ጋር በአንድ
2197ባልዲ ውስጥ እንዳለ ውሀ አይደለም ማለት ነው
2198በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ወይም ሰላማዊ
2199ትዳር ላለመምራት እክል ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች
2200የታወቁ ቢሆኑም ብዙ ጊዜ ልብ ብለን እነዛን
2201ነገሮች ለማስተካከል ስለማንሄድ ችግሩ አፍጦ
2202መጥቶ ጋብቻን እንደ ከርቸሌ እስር ቤት
2203የምንቆጥር ብዙ ነን ከጭንቀት እና ፍርሀት
2204ረዥም ሰአት ከመስራት ከድካም የሰው ወሬ
2205ከመስማት ያለሆነ ነገር በአእምሮ ፈጥሮ ከማሰብ
2206የተነሳ የትዳር አጋርን ጣል ጣል የማድረግ ነገር
2207ይመጣል ""ረዥም ሰአት የሚሠራ ፍርሀት እና
2208ጭንቀት ያለበት እንዲሁም የሚደክመው ሰው ችግሩን
2209ቀስ ብሎ ከማስረዳት ይልቅ ቁጣ ቁጣ ይለዋል""
2210የሚሉት የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ""ንግግሩ ሁሉ
2211የፍቅርና ትህትህናን የተሞላ ሳይሆን የንቀትና
2212በጣም የጮኸ ስለሚሆን የትዳር አጋርን ሊበጠብጥና
2213ወደ አልተፈለገ ንትርክ ሊመራ ይችላል"" ይላሉ
2214እነዚህ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ለዚህ
2215እንደመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርቡት ባልና ሚስት
2216ረዥም ሰአት የሚፈጅ ሥራ መስራት እንደሌለባቸው
2217ነው ሁለት ሙሉ ሰአት ሥራ የሚሠራ አንድ ወገን ለ16
2218ሰአታት ከሚስቱ ተለይቶ በሥራ ላይ ተወጥሮ ውሎ በ17ኛው
2219ሰአት እቤቱ ሲገባ አልጋው ነው የሚናፍቀው ወይስ
2220ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ የፍቅር ጨዋታ መጫወት?
2221አብዛኞቻችን በትዳር ውስጥ ችግሮች እንዴት
2222እንደሚፈጠሩ በልምድም ልናውቀው ስለምንችል ወደ
2223መፍትሄዎቹ ብናመራ የተሻለ ይሆናል
2224ታደምጣታለህ ወይ?
2225የትዳር አጋርህ ላንተ ልክ እንደ ሴት አያትህ ናት
2226ይላሉ የስነልቦና ባለሙያዎች አያቶች ለልጅ
2227ልጆቻቸው እድሜያቸው በገፋ ቁጥር ብዙ ማውራትን
2228እና ብዙ መምከርን ያበዛሉ ስላሳለፉት ነገርም
2229በብዛት ያወራሉ አያቶች ዝም ብሎ ጆሮ ሰጥቶ
2230የሚያዳምጣቸውን እንደሚወዱት ሁሉ የትዳር
2231አጋርህም እንደዚያው ናት ምንም ዝምተኛ ሚስት
2232አገባው ብትልም ሚስት ከባሉዋ የምትደብቀው
2233የላትምና ያሳለፈችውን ውሎ ስትነገርህ ማዳመጥ
2234አለብህ ወሬው የሚያስጠላ ቢሆን እንኳ
2235በአጽንኦት እየተከታተልክ መሆንን ለማረጋገጥ ''እህ""
2236""አሀ"" ""ከዛስ?
2237'' እያልክ በማዳመጥ ልታበረታታት ይገባል
2238ከትንሽ ጀምሮ ሚስትህን የምታደምጣት ከሆነ ጸብ
2239ቢፈጠር እንኳ የመደማመጡ ባህልን ስላዳበርክ
2240በአጭሩ እሳትን ማብረድ ትችላለህ እርሷ
2241ስትናደድ ምን ታደርጋለህ?
2242እርሷ ተናዳ በነገር ልትቆሰቁስህ ትችላለች ጮክ
2243ብላ እየተናገረች ታቆስልሀለች በዚህ ወቅት
2244አንተም እንደ እርሷ እሳት ትሆናለህ?
2245መልስህ አዎ ከሆነ ተሳስተሀል አንዲት ሴት ልጅ
2246ጮክ ብላ በንዴት ከተናገረች ""የጎደለኝ አለና
2247ስማኝ"" እያለችህ መሆኑን ማስተዋል አለብህ
2248የጎደለባትን ነገር ለማስተካከል መፍትሄ
2249ከመፈለግ ይልቅ አብረሀት ብትጮህ እና ብትለፋልፍ
2250ቃላት ብትወራወር ትርፉ ራስን ማዋረድ ነው ቃላት
2251በተወራወርክ ቁጥር የሚያደማ ቃል ትነጋገሩና
2252ቁርሾ ማሳደር ይሆናል ነገርን ከመፍታት ይልቅም
2253የባስ ትልቅ ጦርነት በቤትህ አወጅክ ማለት ነው
2254ለዚህ ነው በተለመዶ ""ትዳሩን መምራት ያልቻለ ሰው
2255ለሀላፊነት አይበቃም"" የሚባለው ስለዚህ
2256ለማዳመጥ የፈጠንክ ለመልስ የዘገየህ ሁንላት
2257ይባስ ብለህ እንደውም እርሷ በምትበሳጭበትና ጮክ
2258ብላ በምትናገርበት ወቅት ንዴት ውስጥ ብትሆንም
2259ዓይን ዓይኑዋን እና ከንፈር ከንፈሯን ብቻ
2260ተመልከት ይላሉ የስነ-ልቦና ሊቆች እርሷ በንዴት
2261ውስጥ ሆና አንተ ዓይን ዓይኑዋን የምትመለከታት
2262ከሆነ ንዴቷ እየበረደ ከመሄዱም በላይ
2263ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ በዛች ቅጽበት ውስጥ
2264አስታውሳ እርሷም ታጋሽ ባል አለኝ ብላ
2265እንድትኮራብህ ታደርጋታለህ ትንሽ በረድ ካለች
2266በሗላ ደግሞ ከንፈሯ አተኩእርህ በመመልከት
2267ከአንገት በላይ ከእርሷ ጋር አንድ ለመሆን
2268ፍላጎትህን አሳያት ለስለስ ያለ የከንፈር
2269ለከንፈር መሳሳም ቁጣን አብርዶ እቤትህ ውስጥ
2270ሰላምን እንደሚፈጥርልህ ሁልጊዜም አስተውል
2271ስልክ ባታነሳስ?
2272አንተ ሥራ ቦታ ነህ እንበል እርሷ እቤት ውስጥ
2273ነች ወይም ከቤት ውጭ ወጥታለች ባለቤትህ ናፍቃህ
2274ወደ እርሷ ቴሌፎን ስትደውል የስልክ ጥሪ
2275ባትመልስ ምን ታደርጋለህ?
2276እንደ የስነልቦና ሊቆች አጠቋቆም ከ100 አስር
2277የሚያህሉት እንኳ ሚስታቸው ቴሌፎን አለማንሳቷን
2278በጥሩ ጎኑ አይመለከቱትም አብዛኛው ወንድ
2279የሚያስብው ""ስልኩን ከሌላ ወንድ ጋር
2280እያወራችበት ነው ወይኔ በእኔ ላይ ደርባ
2281ይዛብኛለች"" ብሎ ነው ወዲያው የሚያስበው
2282ምናልባት በኔት ወርክ ምክንያት እየጠራ እርሷ
2283ጋር ላይሰማ ይችላል የቴሌፎን ባትሪ አልቆባት
2284ይሆናል ምን አልባት ስልክ ማውራት የማትችልበት
2285ቦታ ይሆናል ወይም ሥራ ቦታ ውጥረት ውስጥ
2286ትሆናለች ብሎ የሚያስብ ከስንት አንድ ነው
2287አንተም ለአጋርህ ስትደውል ስልክ የማትመልስ
2288ከሆነ ወዲያውኑ በመጥፎ ጎኑ የምትመለከተው ከሆነ
2289አመለካከትህ መልካም ስላለሆነ ለመቀየር ሞክር
2290እድሜ ለቴክኖሎጂ ""የድምጽ መልእክት
2291ማስተላለፊያ"" ተፈጥሮልናልና ይህን
2292ተጠቀምበት ስልኩ ጠርቶ የማይነሳ ከሆነ ""የእኔ
2293ፍቅር
2294እንደዚህ ያሉትን ቃላት በጸብም ሆነ በፍቅር ጊዜ
2295አትርሳ የእኔ ፍቅር ናፍቀሺኝ ደውዬልሽ ነበር
2296ሆኖም ስልክ ማናገር በማትችይበት ሁኔታ ውስጥ
2297እንዳለሽ እገምታለው ስለዚህ በሗላ
2298እንደዋወላለን እወድሻለው"" የሚል አይነት
2299ትህትናንና ፍቅርን የተላበስ መልእክት
2300አስቀምጥላት እንደዚህ ያሉት መልእክቶች
2301ሚስትህ አንተ እንደምትጠረጥረው ከሌላ ወንድ ጋር
2302እንኳ ሄዳ ቢሆን ትህትህናን እና አስተዋይነትህን
2303አይታ ራሷን ትሰበስባለች ""ባለቤቴ ራሱን
2304ስለሚያምን እኮ ነው እኔን የሚያምነኝ"" ብላ
2305እንድታስብ ታደርጋታለህ አለበለዚያ ግን ለምን
2306ስልክ አታነሺም እያልክ የምትጮህ ከሆነ የስልክ
2307ጥሪ አለመመለሱዋንም በመጥፎ መንገድ የምታየው
2308ከሆነ ""ራሱን የማያምን ሰው ሰውን አያምንም""
2309የሚለውን ብሒል እውን እንዲሆን ታደርጋለህ
2310የፍቅረኛነት ዘመንን የሚያስታውስ ትዝታን
2311ትፈጥራለህ ወይ?
2312በፍቅረኛንት ዘመንህ ታሳያት የነበረህን
2313የሰጪነት የለጋስነት ባህርይ ትዳር ውስጥ
2314የሚከለከል እንዳይመስልህ ትዳር እስር ቤት
2315አይደለም እንደውም በፍቅረኛንት ዘመን
2316ከነበርክበት ጊዜ በበለጠ አሁን ከአጋርህ ጋር
2317በነጻነት የምትገናኙበት ጊዜ ነውና ይበልጥ
2318ለጋስነትህን ማሳደግ ይኖርብሀል ምንም እንኳ
2319በፍልስፍና ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ""ሴቶች
2320ፍላጎታቸውን አይደለም ወንድ ራሳቸውም
2321አያውቁትም"" ቢሉም እንደፍላጎቷ ሁንላት
2322በመንገድ ላይ ስትሄዱ የልብስ መሸጫ ሱቅ አጠገብ
2323ስታልፉ ""ይህ ልብስ ያምራል"" ብትልህ
2324እንድትገዛላት ፍላጎቷን እያሳየችህ ነው
2325ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አብረሀት ልብሱን አድንቅ
2326እንጂ ""አንቺ ደግሞ ሁሉም ያምርሻል"" ብለህ
2327ፍላጎቷን ኩም አታድርገው ዛሬ ባትገዛላት ሌላ
2328ጊዜ እንደምትገዛላት በፍቅር ቃላት ንገራት
2329ይሄኔ ልብሱን የለበሰችው ያህል ከአፍህ የወጣው
2330የትህትና ቃል ሰውነቷን ይሞላዋል ልክ እንደዚሁ
2331ሁሉ በትዳር ውስጥ አብረህ በምትኖርበት ወቅት
2332በተቻለህ መጠን የተዋወቃችሁበትን ቀን ሁልጊዜ
2333አንተ አስተዋሽ ሆነህ አነሰም በዛም ስጦታ ስጣት
2334ሴቶች እንደዚህ የሚያደርግን ወንድ እንደ ንጉሥ
2335የመመልከት ባህርይ ስላላቸው በተቻለህ መጠን
2336እርሷን ድንገት የሚያስደስቱ ነገሮችን
2337ለማድረግ ሞክር በተለይ አመታዊ የትውውቅ
2338በዓላችሁን ስታከብሩ ድሮ በፍቅረኛነት ዘመን
2339ትዝናኑበት የነበረው ሆቴል ይዘሀት ሄደህ ራት
2340ጋብዛት እዛም እደሩ ይህን ካደረግክ ቤቷ
2341እንዲናፍቃት ከማደረግህ በላይ የፍቅረኛነት
2342ጣፋጭ ጊዜያችሁን በትዝታ መነጽር ዞር ብላ
2343እንድታስታውስ ታደርጋታለህ ይህ ሲባል ግን ራት
2344ይዘሀት የምትወጣው የግድ በዓላትን መጠበቅ
2345የለብህም አብሮ ለሚኖር ሰው ሁልጊዜ በዓል ነውð
2346ሱዳን ላይ ውሃ ሲጠማህ የምትጠጣው ከዚህ እንስራ
2347ቀድተህ ነው
2348ምናልባት ትል እ ና ትናንሽ እንቁራሪቶች
2349ሊገኙበት ቢችሉም ውሃ ስለሚጠማህ ብቻ ዝም ብለህ
2350መጠጣት ነው
2351ሰው በተለያየ አጋጣሚ ይሰደዳል እኔ ስደትን
2352በሁለት አይነት እከፍለዋለሁ አንደኛው
2353የቅንጦት ስደት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአስገዳጅ
2354ሁኔታዎች የሚከሰት ስደት ነው የቅንጦት ስደት
2355በኢትዮጵያ ሀገሩ መኖር እየቻለ የምእራብያውያን
2356ናፋቂ የሆነው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ
2357ብዙሀኖቻችንን የሚወክል ይመስለኛል ጥቅምት 221997
2358አ ም ነበር ከኢትዮጵያ የወጣሁት በዚህ ቀን
2359ከሀገሬ ከመውጣቴ በፊት አንድ ነገር በጣም
2360አስገርሞኛል እሱም የኢትዮጵያን ደህንነት
2361አሰራር የታዘብኩበት ነው ጋዜጠኛ እስክንድር
2362ነጋ በጣም ይፈለግ ስለነበር በኤርፖርትም
2363በድንበርም ከሀገር እንዳይወጣ ስሙ ተላልፎ ነበር
2364ለጊዜው ስሙን ወደማላውቀው ሀገር አንድ
2365አውሮፕላን ይነሳል በዚህ አውሮፕላን ላይ
2366እስከዳር ነጋ የምትባል ሴት ተሳፍራለች
2367አውሮፕላኑ እንደተነሳ አየር ላይ 20 ደቂቃ
2368እንደፈጀ ተመልሶ እንዲያርፍ ተደረገ
2369የኢትዮጵያ ደህንነቶች ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
2370አመለጠን ብለው ተራወጡ መጨረሻ ላይ
2371አውሮፕላኑን አስመልሰው ሲፈትሹ የተገኘችው ወሮ
2372እስከዳር ነጋ ናት እንግዲህ ይታያችሁ ወንድና
2373ሴት መለየት የማይችሉ ስዎችን አውሮፕላኑን
2374ደግመው ከማሳረፍ ከአየር መንገዱ የበረራ ሪፖርት
2375መመዝገቢያ ላይ የሴትየዋን ማንነት ማረጋገጥ
2376ይሻላል ወይስ?
2377
2378በዚህ የተነሳ የመተማን ድንበር አቋርጬ ወደ
2379ሱዳን ለመግባት ምንም ፍራቻ አላደረብኝም
2380እንደነ ነዋይ ደበበ ''በገዳሪፍ ካርቱም''
2381የሚለውን ዘፈን እየዘፈንኩ ገዳሪፍን አልፌ
2382ካርቱም ገባሁ ተወርቶ የማያልቅላት ዴም
2383ካርቱምና የሀበሻ ስም ከተነሳ 'ዴም ' አትቀርም
2384ዴም ዛሬ አውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ ሊቢያን ለረገጡ
2385ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሕይወታቸው አንድ
2386ክፍል ናት ብል አላጋነንኩም ለምሳሌ እስኪ ዴም
2387አዝመራን ; እማማ ነብሳቸውን ይማር ከሞቱ አመት
2388ሊሞላቸው ነው የማያውቅ ማነው?
2389በተለይ እማማ ቤት ግድግዳ ላይ ከተጻፉ የግድግዳ
2390ላይ ጽሁፎች በተለይ የጨርቆስ አካባቢ ልጆች
2391የሳቸው ድንበኛ ነበሩ እማማ ሥራቸው አንድ
2392ትልቅ ቤት ተከራይተው ''ኬሻ በጠረባ '' ሊባል
2393በሚችል አተኛኘት በቀን 2 የሱዳን ሊራ እየተቀበሉ
2394የሚያሳድሩ ሴት ናቸው ካርቱም ላይ በሙቀት
2395የተነሳ ከቤት ውጭ ስለሚተኛ ለሳቸው ገበያ በጣም
2396ተስማሚ ነው ምክንያቱም ያቺን የሲባጎ አልጋ ማታ
2397ማታ እየዘረጉ ያሳድራሉ በጣም የሚገርመው እማማ
2398ቤት በአንድ ለሊት እስከ 60 ሊደርስ የሚችል ሰው
2399ማደሩ ነው ''ትንሽ ጨቅጫቃ ናት ; ግን የዋህ ናት ''
2400የሚል ስም ያላት አዝመራ ቤት ውስጥ ከተለጠፉ
2401ጥቅሶች መካከል ይህን ጽፌ ነበር-
2402ይህ ጥቅስ የሚያሳየው የካርቱም የሀበሻ ኑሮ
2403ምነኛ አስቀያሚ እንደሆነ ያሳያል ከምግብ ውስጥ
2404ርካሹ ፉል ነው ሱዳን ውስጥ ይህ የሚጠፋበት ጊዜ
2405ብዙ ነው ለብዙዎቻችን ፉል እንኳ መግዢያ የሱዳን
240650 ሳንቲም ጅኔ ይጠፋል እናም ይህን ለማሳየት
2407ነው ጥቅሱ የተጻፈው ካርቱም ላይ እጅግ ታዋቂ
2408ከሆኑ ሰዎች ሁለቱን ከጠቀስኩ ከዴም ጀምሮ ;
2409ከሰሀፋ ዘለጥ እስከ ጅሬፍ; ከአባሁማማ እስከ
2410አንዱርማን እና ሌሎችም ሰፈሮች የቃረምኳቸውን
2411ታሪኮች ተራ በተራ ላስነበብ ሣራ ሣራ የብዙ
2412ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መጠሪያ ስም ነው ካርቱም
2413ላይ አንዷን ሴት አግኝተህ ማነው ስምሽ ብትላት
2414ሣራ ትልሀለች ለምንድን ነው ዋና ስምሽን
2415የምትቀይሪው ስትላት 'ለአጠራር እንዲመች' የሚል
2416ተልካሻ ምክንያት ያቀርቡልሀል ዋናው
2417ምክንያታቸው ራሳቸውን ለመደበቅ እንደሆነ
2418የታወቀ ነው ራሳቸውን ከማን ይደብቃሉ ?
2419እንዳትሉኝ ዛሬ ሳራ የሆነቸው ሴት ነገ 'ሀያት '
2420ከነገ ወዲያ 'ኢማን ' ይሆኑላችኍል ለምን
2421ስማቸውን ይቀይራሉ?
2422በቀጣይ ዘገባዎቼ መልስ ታገኛላችሁ በዚህ
2423የተነሳ የሱዳን ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሴት ሁሉ ሣራ
2424ይመስላቸዋል አንዲትን ኢትዮጵያዊትን ሴት
2425መንገድ ላይ ሲጣሩ እንኳ ሣራ ነው የሚሉት በብዛት
2426ተክለሀይማኖት አካባቢ እንደተወልደች
2427የምትናገረው ሣራ የሱዳንን ምድር ከረገጠች 2
2428አመት ሊሞላት የቀናት እድሜ ብቻ ነበር የቀሯት
2429ለምን ወደ ሱዳን መጣሽ?
2430ነበር ያልኳት - የምትሰራበት የላስቲክ ሻይ መሸጫ
2431ቤት ውስጥ ገብቼ ቁጭ ካልኩና ብዙ ከእርሷ ጋር
2432ከተግባባው በኍላ 'ከዚህ ቀደም በሌላ አረብ
2433ሀገር ነበር የምኖረው የአረብ ገረድ መሆን
2434መረረኝ እስኪ የአውሮፓን ሕይወት ልይ ብዬ ወደ
2435ሱዳን መጣሁ' ስትል ትረካዋን የጀመረችው ሳራ 'ወሬውን
2436የሰማሁት አዲስ አበባ እያለሁ ነው ብዙ ስዎች
2437ሱዳንን አቋርጠው በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን
2438ይገባል ሲሉ ሰምቼ መጣሁ ከእኔ ጋር የመጣች ልጅ
2439አሁን ሊቢያ ትገኛለች እኔ እድሌ ሆኖ ሱዳን ቀረሁ
2440' አለችን በቁጭት ለሳራ ሊቢያ መግባት ትልቅ
2441ስኬት ነው ሊቢያ ምን ስቃይ ይኑር ; ይሙቅ ይድላ
2442የምታውቀው የላትም ብቻ እሷ ሰዎች ያንን መንገድ
2443ተጠቅመው ጣሊያን ስለሚገቡ ብቻ ሊቢያ የስኬቷ
2444ምንጭ ነው ጥያቄዬ አላቋረጠም 'ለምን አልሄድሽም
2445ታዲያ ?' አልኳት እምባዋ በአይኖቿ ጎን ብቅ
2446ማለት ጀመሩ ታሪኬ ብዙ ነው ተወኝ አለችና
2447እንደመመናቀርም ብላ ወደ ጓዳ ገባች በጣም ጓጓሁ
2448ልጅቷ አንድ የተደበቀ ምስጢር አላት አልኩ ታዲያ
2449ይህን ለማግኘት የግድ እርሷን መቅረብ ይገባኛልና
2450ቀረብኳት ከብዙ ውትወታ በኍላ ልጅቷን 'አማራት'
245141 የሚባለው ሰፈር የሚገኘው ጋልፍ መዝናኛ
2452ቀጠርኳት ሱዳን ላይ በተለይ ሴት ልጅ ጋር ቀጠሮ
2453የምትይዘው እሑድ አሀድ ወይም ጁምአ አርብ ነው
2454እነዚህ ሁለት ቀኖች ብዙ ኢትዮጵያዊያን ኢጃዛ እረፍት
2455 የሚወጡበት ቀን ነው ለምን ቀጠሮውን
2456አረፈድሽ አልኳት ብዙ እንዳስጠበቀችኝ
2457ለማስገንዘብ 'ሴትየዋ ጨቅጫቃ ናት ቶሎ
2458አትለቀኝም አሁንም አኩርፋ ነው የመጣሁት እኔ
2459ከቤት ስወጣ አትወድም' የትኛዋ ሴትዮ ብዬ
2460ሳልጠይቃት የምትሰራበት በላስቲክና በሸምበቆ
2461የተወጠረው ሻይ ቤት የሌላ ሀበሻ ሴት ንብረት
2462እንደሆነና እሷ በቀን 10 የሱዳን ዲናር
2463እየተከፈላት እንደምትሰራ ነገረችኝ 'አየህ
2464ሱዳኖች ወንዶቹ የኛን ሴቶች ይፈልጋሉ የኛን
2465ሴቶች ለማየት ሲፈልጉ ወደሻይ ቤታችን ይመጣሉ
2466ሻይ ፍለጋ ሳይሆን እኛን ' የምትለው ሳራ ወደ ሻይ
2467ሥራ ለምን እንደገባች ስታስረዳ ታሪኩ ብዙ ነው
2468ትላለች በወር 150 ዶላር ደመወዝ ይከፍልሻል
2469ብለው ወደሱዳን ያመጡዋት አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ
2470ደላሎች ናቸው ለሱዳን 5 ሺህ ብር ክፍላ መምጣቷ
2471ሳያንስ በሱዳን አሰሪዎቿ የደረሰባት ነገር እጅግ
2472ያሳዝናል- 'አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ
2473እንደወትሮዬ ከሁሉም ቀድሜ ተነስቼ ቤቱን
2474የማጸዳው እኔ ስለነበርኩ አይኔን ሳልገልጥ ስወጣ
2475ቤቱ ደጃፍ ላይ ድመት ታርዶ አንገቱና ሰውነቱ
2476ተለያይቶ ተጥሎ አገኘሁ ' ''የታረደውን ድመት
2477እንዳየሁ አዞሮኝ ወደቅኩ ከዛ በኍላ ራሴን
2478ያወቅኩት ከአንድ ቀን በኍላ ነው የሴትዮዬ ማዳሟን
2479ነው ባል ከአጠገቤ ተቀምጦ ነበር ከዛም
2480የሆነውን ሁሉ ጠየቅኩት ድመት አርደው በር ላይ
2481እንዲጥሉ ያደረጋቸው እምነታቸው እንደሆነ
2482ነገረኝ '' የምትለው ሳራ ከዛ በኍላ ራሷም
2483የእምነቱ ተከታይ በመድሐኒት እንዳደረጓት
2484እምባዋ እየወረደ ነገረችኝ ሱዳን በሳይንስ
2485የተረጋገጠ መረጃ ባላገኝም እንደሚወራው ከሕንድ
2486ቀጥሎ ሁለተኛዋ የባድ ስፕሪት ጠንቋይ ሀገር ናት
2487ሙአሰላት አውቶቡስ ውስጥ እየሄድክ ከአጠገብህ
2488ጀለቢያ ያደረገ ቁመተ ረዥም ሱዳኒ ማግኘት
2489የአፈር ያህል ነው ይህን ሱዳን ትንሽ
2490እንዳወራህው ስለ ግል ህይወቱ ብትጠይቀው ጥንቆላ
2491እንዳለበት ካለምንም ማፈር ይነግርሀል አንድ
2492ቀን የሀበሻ ምግብ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ በምሰማት
2493ጥቂት አረብኛ ቋንቋ አንዱ ጠብደል ሱዳን ለኛ ሴት
2494ክንዱ ላይ በቁልፍ የታሰረ ቀበቶ ያሳያታል እሱም
2495ይህን እያሳያት የሚነግራት ነገር ያሰረው በቁልፍ
2496የታሰረው ቀበቶ ማንኛዋም ያናገራት ሴት
2497እንድታፈቅረው እንደሚያደርግ እና ጥይት
2498ቢተኮስበት እንኳን ይህ እንደ ሚከላከልለት
2499ሲነግራት ስምቻለሁ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ሱዳን
2500ውስጥ ስለ ጥንቆላ ማውራት በጣም አይቸግርም
2501ይህን ስል ሱዳን ያሉ የእኛም ሰዎች ጤነኛ ናቸው
2502ማለት አይደለም አብዛኞቹ ቀን ቀን ካርቱም
2503መድሐኒአለም ማታ ማታ ሱቀል ዴም ያለው ጠንቋይ
2504ቤት አይጠፉም ብዙሀኑን የሀበሻ የላስቲክ ቤት
2505ሻይ ቤቶች ስትጎበኙም መሬቱን ስታዩ ጥቁር
2506አዝሙድ ተንስንሶ ታያላችሁ ጥቁር አዝሙድ እና
2507ጥንቆላ ምን አገናኘው ብዬ ጠይቄ ግን ምላሽ
2508ማግኘት አልቻልኩም **** **** ***** እምባሽን አቁሚ
2509ብዬ እያባበልኩ ጨዋታዋን እንድተቀጥልልኝ
2510አደረግኩ ሱዳንና ሱዳናውያንን እየቃኘን ነው
2511የኛ ሰው በሱዳን ምን እንደሚመስል እያየን ነው
2512አብዛኞቹ በባእድ አምልኮ ወደውም ይሁን ሳይወዱ
2513እንዴት እንደሚገቡ ለማሳየት እየሞከርኩ ነው
2514ሳራ በታረደ ድመት ዞሮባት የባእድ እምነቱን
2515መከተል ጀምራለች ''ከወደቅኩበት እንደተነሳው
2516የተነገረኝ ነገር ቢኖር ያዳነኝ አምላክ ድመቱ
2517የታረደለት እንደሆነ ነበር '' ያለችኝ ሳራ
2518የአሰሪዋ እናት በካርቱም ታዋቂ ጠንቋይ እንደሆኑ
2519አስረግጣ ነገረችኝ ከዛስ?
2520'ከዛማ ወደ አባይ ወንዝ ካርቱምን የሚያቋርጠው
2521መሄድ ጀመርኩ አንድ ምሽት ሴትዮዬ ልጃቸው እና
2522እኔ ሆነን ወደ ባህር ሄድን ከሌሊቱ 6 ሰአት
2523አካባቢ ነው ባህሩ ከምሰራበት አንዱርማን የ 30
2524ደቂቃ መንገድ ቢኖረው ነው እዛ ሄደን ከመኪናው
2525እንደወረድን ሴትዮዬ ቀድማ ወደ ባህሩ ተጠጋች
2526ከዛም መኪናው ውስጥ ከያዝነው የተቀጣጠለ ክሰል
2527ጋር እጣን ነስንሳ ወደ ባህሩ ጋር ተጠጋች
2528የሚሆነው ነገር ሁሉ በጣም እያስገረመኝ መጣ
2529ሴትዬዋ ተንበርክካ እያለቀሰች አንዳንዴም
2530እያጓራች እጣኑን ወደባህሩ ይዛው ትንሽ ገባ
2531አለች የዛን ጊዜ ከወንዙ ውስጥ ያሉት አሶች
2532ወደላይ እየዘለሉ እየወጡ ሲገቡ ተመለከትኩ
2533በጣም ደነገጥኩ አጠገቤ ያለው ልጃቸውና ሚስቱ
2534ተንበርከክው ማጉዋራት ጀመሩ ራሴን ስቼ ወደቅኩ''
2535በሚል ታሪኳን ተረከች ተመስጬ እያዳመጥኳት ነው
2536''ከሁለት ቀን በኍላ ነው የነቃሁት ሴትዮዬ ስነቃ
2537ወደ እኔ መጥታ ከአሁን በኍላ እኔ ቤት ሥራ
2538አትሠሪም የባህሩና የድመቱ አምላክ ላንቺ
2539የሚሆንሽን ሰው መርጦልሻል'' ብላ ከአንድ ሀብታም
2540የዚህ ባእድ አምልኮ ተከታይ ሱዳን እንዳጋባቻትና
2541ከዚህ ሰው ጋር አብራ ለጥቂት ጊዜ እንደኖረች
2542ነገረችኝ ከዛም ይህ ሱዳን እሷን የሚፈልገውን
2543ያህል ከተጫወተባት በኍላ ለሥራ ቤቱ ከተቀጠረች
2544ሌላ ኢትዮጵያዊት ጋር ግንኙነት ጀምሮ በእኩለ
2545ሌሊት ከእቤት እንዳስወጣት ጨምራ እያለቀሰች
2546ነገረችኝ የምትነግረኝ ነገር ስሜቴን እየጎዳው
2547ነው በዛ ላይ የምታነባው እምባ በጣም ልብን
2548ይነካል ሰው መሆንንና መፈጠርን ሁሉ ያስመርራል
2549 መጨረሻዋ ሻይ ቤት መሥራት ይሁን እንጂ እዚህ
2550ላይ እንዴት እንደደረሰች ጠየቅኳት ''አንዱርማን
2551የሚኖሩ ሀበሾች አብዛኞቹ የተጣባቸው ባእድ
2552አምልኮ ስላለ እነሱ ምንም ይረዱኛል ብዬ ሳላስብ
2553ወደ ካርቱም መጥቼ ዴም ያሉ ሀበሾች ይረዱኝ ዘንድ
2554መጣሁ እዛ እንደመጣሁ ወደ ሊቢያ የሚሄዱ
2555የአዲስ አበባ ልጆች አገኘሁ ስምሽ ማነው ሲሉኝ
2556ቤቲ አልኳቸው ስሜን ለሦስተኛ ጊዜ መቀየሬ ነው
2557የደረሰብኝን ሳልነግራቸው አዲስ መጤ
2558እንደሆንኩና ሱዳንን ምንም እንደማላውቅ ብሎም
2559ገንዘብ እንደሌለኝ እያለቀስኩ ነገርኳቸው
2560አዘኑና እኛም ቤት የለንም ቢሆንም በቀን ሁለት
2561ብር እየከፈልን የምንኖረው አዝመ ራ ቤት ነው
2562ሥራ እስከምትጀምሪ ድረስ እኛ የምንበላ ውን ፉል
2563እየበላሽ ትኖሪያለሽ; የአልጋም እንከፍላለን አሉ
2564''ከእነሱ ጋር ለ3 ቀናት ያህል እንደተቀመጥኩ 'ማዳም
2565ቤት' የሰው ቤት ሥራ ማለት ነው ሥራ አገኘሁ
2566ቢቸግረኝም አልሰራም አልኩ ልጆቹ ለምን አሉ?
2567ሥራ አትወጂም ማለት ነው ብለው የሚያስከፋ
2568ቃላትን ሰነዘሩብኝ እኔ ማዳም ቤት ሥራ አልሰራም
2569ያልኩት የደረሰብኝ አሰቃቂ አደጋ እንዲደገም
2570ስለማልፈልግ እንጂ ለሌላ አልነበረም ቢሆንም
2571ልጆቹ ጥሩ ነገር ቢያደርጉልኝም ስሜቴ ቶሎ
2572ስለሚጎዳ ትቼ ወጥቼ መንገድ ላይ ስሄድ አንድ
2573ሀበሻ አግኝቶኝ እኚህ ሴትዮ ቤት ሥራ አስገባኝ ''
2574አለች የቀድሞዋ ሣራ የአሁኗ ቤቲ በጣም
2575የሚያሳዝነው የቤቲ ሕይወት ከድጡ ወደማጡ ነው
2576ከሱዳን ቤት የወገኔ ቤት ይሻለኛል ብትልም
2577እኚህም ሴት ያው ናቸው ለምሳሌ አንድ ቀን
2578እሳቸው ቤት ሻይ ልጠጣ ከካርቱም ጓደኞቼ ጋር
2579ገብቼ ሳላውቅ አንድ ጥግ ስር የጎዘጎዙትን ሳር
2580የበተኑትን ጥቁር አዝሙድና ፈንዲሻ ረግጭባቸው
2581ሁለተኛ እዚህ ቤት እንዳትደርስ ብለው አባረውኛል
2582 ግን ዝንጉ ስለሆኑ በሌላ ቀን ስሄድ
2583አስገብተውኛል ''በቀን 5 ጊዜ ለአሮጊቷ ቡና
2584ማፍላት አለብኝ ጠዋት የላስቲክ ቤቱን ሻይቤት
2585ከመክፈቴ በፊት እግሯን የተቆረጠች እርግብ
2586አለቻቸው ለእርሷ ስንዴ መበተን አለብኝ ያንን
2587ባላደረግኩ ቀን ገበያ የለም ቤቱ ጭር ብሎ
2588ይውላል ታዲያ ማታ ሂሳብ ስንሰራ ሂሳቡ
2589ሲያንስባቸው አሮጊቷ አያስቀምጡኝም ለምን
2590ለእርግቧ ስንዴ አልበተንሽም ; ለምን ጥቁር
2591አዝሙድ መሬቱ ላይ አልነሰነስሽም በሚል ብዙ
2592ውርጂብኝ ያወርዱብኛል '' ብላኛለች ያው የእኔ
2593ሥራ ከማዳመጥ በቀር መጠየቅ ነውና ለምን ታዲያ
2594ቤቱን ለቀሽላቸው አትወጪም ስላት ''ምን
2595እንዳዞሩብኝ አላውቅም አንዲትም ቀን ቤቱን
2596ስለመልቀቅ አላስብም የምፈልገውን ቢዝነስ
2597አገኛለሁ'' አለችኝ ቢዝነስ በካርቱም ሌላ
2598ትርጉም አላት አብዛኞቹ ሻይ ቤት የሚሰሩ
2599ሴቶቻችን ቢዝነስ አላቸው ምን?
2600ሐበሻ በሱዳን
2601በቀጣዩ እትም ይቀጥላል።
2602
2603ወደ ታሪኩ ከመግባታችን በፊት ቆም ብለን
2604ራሳችንን እንጠይቅ፤ ዛሬ አብሮሽ በትዳር ያለ
2605ጓደኛሽ ወይም በወሲብ የምታውቂው እጮኛሽ የኤች
2606አይቪ ቫይረስ በደሙ እንዳለ እያወቀ ካንቺ ጋር
2607አልጋ ላይ ቢወድቅና አንቺም ትዳር ላይ ከገባችሁ
2608በኋላ ይሕንን ብታውቂ ምን ታደርጊያለሽ?
2609ያንቺን ውሳኔ እወቂና ምህረት አስቻለው
2610ያጠናቀረውን እውነተኛ ታሪክ ተከታተይ።
2611ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራ
2612አካባቢ ነው፡፡ ምሽት አሥራ ሁለት ሠዓት ገደማ
2613ወደ አንድ ደሳሳ ቤት ጠጋ ብለን በር አንኳኳን
2614ምንም ምላሽ አላገኘንም፡፡ ደግመን ስናንኳኳ ግቡ
2615የሚል የወንድ ድምፅ ከወደ ውስጥ ሠማን፡፡
2616የቆርቆሮውን በር ገፋ አድርገን ስንገባ ፊት
2617ለፊት በግምት እድሜው ሦስት ዓመት የሚሆን ህፃን
2618ፊት ለፊት ወንበር ላይ፣ አይናቸው ላይ መሀረብ
2619ጣል አድርገው ጠባብ አልጋ ላይ ተንጋለው የተገኙ
2620አዛውንት ተመለከትን፡፡ አዛውንቱ ህፃኑን
2621እናቱን እንዲጠራ አዘዙት፡፡ ስሟ እንዲጠቀስ
2622ያልፈለገችው ወሮ ተወልዳ ያደገችው አዲስ ዘመን
2623የሚባል አካባቢ እንደሆነ፤ ትዳር የመሠረተችውም
2624አዛውንቱን ያገባችው በቤተሰብ በኩል እንደሆነ
2625ገልፃልናለች፡፡ ጋብቻ የመሠረቱት 1986 ዓም ላይ
2626ነበር፤ በዚያ ወቅት ባለቤቷ በጦር ሠራዊት ውስጥ
2627ያገለግሉ እንደነበርም አስታውሳለች፡፡ ሦስት
2628ልጆችን አፍርተዋል፡፡ የመጀመሪያው የአሥራ
2629አራት፣ ሁለተኛዋ የዘጠኝ ዓመት፣ በር ከፍተን
2630ስንገባ የተመለከትነው ህፃን ደግሞ የመጨረሻ
2631ልጃቸው ሲሆን ሦስት ዓመቱ ነው፡፡ ከጡረታ
2632በሚገኝ ገንዘብና አትክልት እየቸረቸረች
2633ወይዘሮዋ ቤተሰባቸውን ታስተዳድራለች ልጆቿንም
2634ታስተምራለች፡፡ “ባለቤቴ በተደጋጋሚ ይታመም
2635ነበር፡፡ ሁለተኛዋ ልጄም ዘወትር ትታመም
2636ስለነበር ጥርጣሬ አደረብኝ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ
2637በኋላ ደግሞ ባለቤቴ ከጦር ሠራዊት ተሰናበተ፡፡
2638የባለቤቴም የዘጠኝ ዓመት ልጄም ህመም ቀን ከቀን
2639እየበረታ መጣ፡፡ ባለቤቴ ይጠጣል በዚህም ዘወትር
2640እንጋጫለን፡፡ ትዳራችን በብዙ መልኩ ችግር ውስጥ
2641ገባ” ብላለች፡፡ ህፃን ልጇ በጣም መታመም
2642ስለጀመረች ወደ ሆስፒታል መሄድ የግድ ሆነ፡፡
2643ለህፃኗ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ የህፃኗ እናት
2644መሆኗን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንድታመጣና እሷም
2645የኤች
2646አይ
2647ቪ ምርመራ እንድታደርግ እንደተነገራት
2648አስታውሳለች፡፡ የኤች
2649አይ
2650ቪ ቫይረስ በህፃኗም በእሷም ደም ውስጥ መኖሩ
2651ተነገራት፡፡ ይህን ካወቀች በኋላ ትዳራቸው
2652መፍረስ እንዳለበት በማመን ባለቤቷን እንዲፋቱ
2653ጠይቃቸዋለች፡፡ ባለቤቷ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው
2654ፍርድ ቤት በማመልከት ፍቺ ጠይቃለች፡፡ ጉዳያቸው
2655በመታየት ላይ እያለ ባለቤቷና ሌሎቹ ልጆቿ የኤች
2656አይ
2657ቪ ምርመራ አድርገው እነሱም ቫይረሱ በደማቸው
2658ውስጥ መኖሩ ሊታወቅ ችሏል፡፡ ይህ ደግሞ
2659የወይዘሮዋን ቁጣ አባባሰው፡፡ “የልጃገረድ
2660ባለቤቴ ነው፡፡ ከተጋባንም ወዲያ እኔ የማውቀው
2661ነገር አልነበረኝም፡፡ እሱ ግን ስለህመሙ እያወቀ
2662እንድንጋባ፤ ከዚያም እነዚህን ልጆች
2663እንድንወልድ ማድረጉ በጣም አስቆጣኝ፡፡ በትዳር
2664በቆየንባቸው ጊዜያት ሁሉ አንድም ቀን ምንም ብሎ
2665አያውቅም” ትላለች፡፡ ወይዘሮዋ እንደምትለው፣
2666ቀደም ሲል በተለይም ገጠር እያለች ስለ ኤች
2667አይ
2668ቪ ብዙም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡
2669ባለቤቷና ህፃን ልጅዋ በተደጋጋሚ ይታመሙ
2670ስለነበር ይህም ጥርጣሬ ይፈጥርባት የነበረ
2671ቢሆንም የኤች
2672አይ
2673ቪ ቫይረስ በእሷና በባለቤቷ እንዲሁም በሦስት
2674ልጆቿ ደም ውስጥ መገኘቱን መቀበል በጣም ፈታኝ
2675ሆኖባት ነበር፡፡ ባለቤቷ፣ እሷና ሁለተኛ ልጇ
2676ቫይረሱ በደማቸው መኖሩ እንደታወቀ ወዲያው
2677ፀረ-ኤች
2678አይ
2679ቪ መድኃኒት ጀምረዋል፡፡ “እያወቀ እኔን
2680እንዳገባኝና እነዚህ ልጆችም እንዲፈጠሩ አደረገ
2681ብዬ ባለቤቴን ሠላም አሳጣሁት፡፡ ቤት ውስጥ
2682ሠላም ጠፋ፡፡ ባለቤቴም ከቤት ወጥቶ ሔዶ ነበር፡፡
2683እኔም በአንድ በኩል ህመምና ድህነት፤ በሌላ
2684በኩል ብስጭት አእምሮዬን እንድስት አደረገኝ፡፡
2685ጉዳያችንን ፍርድ ቤት እየተመለከተው እያለ እኔም
2686እየተረጋጋሁ መጣሁ፡፡ ከባለቤቴ ጋር ተለያይቼ
2687የማገኘው የተሻለ ነገር የለም፡፡ ምን አልባትም
2688ህይወት ሊከብደኝ ይችላል ብዬ አሰብኩኝ” በማለት
2689ትዳሯን የማፍረስ ሃሳቧን ቀይራ በይቅርታ
2690ከባለቤቷ ጋር ለመኖር መወሰኗን ነገረችን፡፡
2691ህመም በርትቶባት በተለያዩ ጊዜአት ተኝታ ነበር፡፡
2692ባለቤቷም በተደጋጋሚ ይታመማሉ፡፡ ከሁሉም
2693በይበልጥ የምትታመመው ግን ህፃን ልጇ ነች፡፡
2694ጐረቤቶች በተለያየ አጋጣሚ ሽንት ቤት
2695እንዳትጠቀም በማድረግና በለሎች ነገሮች
2696አግልለዋት ነበር፡፡ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ግን
2697ጐረቤቶቿ ከማግለል ይልቅ ሊያቀርቧት
2698እንደሚፈልጉ፤ እሷ ግን ያለፈውን ትታ በይቅርታ
2699እንደቀድሞ ከጐረቤቶቿ ጋር መቀራረብ አለመቻሏን
2700በሀዘኔታ ገልፃልናለች፡፡ “ተመርምረን
2701ራሳችንን ካወቅን ሁለት ዓመት ሆነን፡፡ በጣም
2702አስቸጋሪ የሆነብኝ የሴቷ ልጄ ሁኔታ ነው፡፡
2703ዘጠኝ ዓመቷ ነው ግን ዘወትር ስለምትታመም
2704ሠውነቷ ድቅቅ ያለ ነው” በማለት የሦስት ዓመቱን
2705የመጨረሻ ልጇን ጭንቅላት በመዳሰስ “እሱን ነው
2706የምታክለው” አለችን፡፡ “በቂ ምግብ
2707ስለማታገኝም እንደሆነ አላውቅም መድሀኒቱን
2708አልቻለችውም፡፡ ሁለት ጊዜ አስቀይሬላታለሁ፡፡
2709መድኃኒት የምትወስድበትን ሠዓት ለይታ
2710ስለምታውቅ በዚያ ሠዓት ወደ መንደር ሔዳ
2711ትጠፋብኛለች፡፡ የዋጠች መስላ ትተፋዋለች፡፡
2712እሷን ለመቆጣጠር ብዬ እኔም እሷም መድኃኒት
2713የምንወስድበት ሠዓት አንድ ዓይነት አደረግኩት”
2714የመጀመሪያ ልጇ አሥራ አራት ዓመቱ ቢሆንም ስለ
2715እናትና አባቱም ሆነ ስለታናሽ እህቱ ህመም
2716የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ስለራሱ ውጤትም
2717አልተነገረውም፡፡ ፀረ-ኤች
2718አይ
2719ቪ መድኃኒት የምትወስደው ህፃን ግን ሁሌም
2720መድኃኒት ውሰጂ ስትባል ለምን እያለች ትጠይቃለች፣
2721ላለመውሰድም ትታገላለች፡፡ð
2722በአፍሪካ ሕብረት መዲና አዲስ አበባ እና በሌሎች
2723ትላልቅ ከተሞች ''ኦባማ ቅዱስ ገብርኤል ይከተልህ''
2724''ይቻላል"" እና የተለያዩ መፈክሮች ያሉበት
2725የኦባማን ምስል የያዙ ቲሸርቶች ከምርጫው በፊት
2726ገበያውን ሲመሩት ነበር እያንዳንዱ ሕዝብ
2727የአሜሪካንን ምርጫ በአጽንኦት ሲከታተል የነበረ
2728ሲሆን በአዲስ አበባ ሰፊ ተመልካች ያላቸው
2729አልጀዚራ እና ሲኤንኤን የቲቪ ቻናሎች ሕዝባችንን
2730በመረጃ ቀልበውታል ''ኦባማ የአፍሪካውያን ተስፋ""
2731የሚሉት አፍሪካውያን ከምርጫው ማሸነፍ ማግስት
2732በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ምርጫው
2733ከተጠናቀቀ በሗላ ደግሞ ኦባማን ተስፋ በማድረግ
2734ላይ ይገኛሉ እንደሚታወቀው አፍሪካችን
2735የመልካም አስተዳደር እጦት; ረሀብ; ጦርነት [ዲሞክራቲክ
2736ኮንጎ በዚህ ወቅት በጦርነት ላይ ናት]; የኢኮኖሚ
2737ቀውስ; ስደት; አለመደማመጥ; በሽታ; እና ሌሎችም
2738ነገሮች እያሰቃዩዋት ይገኛሉ በተለይ የሀገሬ
2739ሰው እንደሚተርተው 'በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ''
2740እንዲሉ በአሜሪካ ባንኮች ላይ የደረሰውን ኪሳራ
2741ተከትሎ በዓለም ላይ የደረሰው የኢኮኖሚ መናጋት
2742ለአፍሪካ ትልቅ ራስ ምታት ነው በዚህ ወቅት
2743አፍሮ- አሜሪካዊው የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት
2744ባራክ ኦባማ መጥቷል አፍሪካ እጆቿን ወደ ባራክ
2745ኦባማ ትዘረጋለች
2746ቀጣዩን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ ይከታተሉ
2747ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ ምናልባት መጠኑን
2748በትክክል ለመናገር ያዳግት እንደሆን እንጂ
2749በአፍሪቃ ልማት ላይም ተጽዕኖ እንደሚኖረው
2750የሚታመን ነው።
2751ታዲያ ይህ ስጋት አፍሪቃ ችግሩን ለመወጣት
2752የራሷን አቅም እንድታዳብር ግፊት መፍጠሩ
2753አልቀረም።
2754በአሜሪካ የቤት ባለቤቶች ዕዳና የባንኮች ክስረት
2755ሳቢያ ዓለምን ያዳረሰው የፊናንስ ቀውስ ለአፍሪቃ
2756ልማትም ቢቀር በአማካይና በረጅም ጊዜ ብዙ ችግር
2757እንዳይፈጥር አሳሳቢ ነው የሆነው።
2758ሁኔታው በተለይም የክፍለ-ዓለሚቱን የኤኮኖሚ
2759ባለሥልጣናት ብርቱ ስጋት ላይ ሲጥል ያለፉት
2760ዓመታት የዕድገት ሂደት እንዳይሰናከል ገቺ
2761ዕርምጃዎችን የመውሰዱም አስፈላጊነት ጎልቶ
2762መታየቱ አልቀረም።
2763በዚሁ የተነሣም የአፍሪቃ የፊናንስ ሚኒስትሮችና
2764የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪዎች ቱኒስ ላይ
2765ተሰብስበው መፍትሄ ለማፈላለግ ያቅዳሉ።
2766የአፍሪቃ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ኮሜሣር ዶርማክስዌል
2767እምኩዌዛላምባ ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይ
2768በዓለምአቀፉ የፊናንስ ላይ ስላለው አመለካከት፣
2769በዓለምአቀፉ የምንዛሪ ተቁዋም ሚና፣ በልማት
2770ዕርዳታና በክፍለ-ዓለሚቱ የራስ መፍትሄ ፍለጋ
2771ሃሣብ አዲስ አበባ ላይ ሰፋ ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ
2772ሰጥተው ነበር።
2773የሕብረቱን ጥረት ዓላማም ለማብራራት ሞክረዋል።
2774“ስብሰባው የታቀደው በአንደኛ ደረጃ ዓለምአቀፉ
2775የፊናንስ ቀውስ በአፍሪቃ ኤኮኖሚ ላይ ያሳደረውን
2776ተጽዕኖ መመርመር ሲሆን በአፍሪቃ የልማት ባንክ
2777ተግባራት ላይ የሚያስከትለውን ግፊትም ያጤናል።
2778ዓለምአቀፉ የዕርዳታ አቅርቦት ሁኔታም ትኩረት
2779የሚሰጠው ጉዳይ ነው” የአፍሪቃ ሃገራት ኤኮኖሚ
2780ብዙም ከዓለምአቀፉ የፊናንስ ገበዮች ጋር
2781የተሳሰረ ባለመሆኑ በዚሁ የሚገጥመው ተጽዕኖ
2782ከባድ አይሆንም የሚሉ አይታጡም።
2783ይሁንና በበለጸጉት ሃገራት በፊናንሱ ችግር
2784የተቀሰቀሰው የኤኮኖሚ ቀውስ አደጋ ቢቀር
2785በንግድና በመዋዕለ-ነዋይ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ
2786እንደሚኖረው የአፍሪቃው ኮሚሢዮን ባለሥልጣን
2787ዕምነት ነው።
2788“ሁላችንም እንደምናውቀው በርካቶቹ የአፍሪቃ
2789ሃገራት ከበለጸጉት መንግሥታት ጋር ብዙ የሚነግዱ
2790ናቸው።
2791እና በዚያ እያሰጋ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ የተነሣ
2792የንግዳችን ሂደት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል።
2793የንግዱና የመዋዕለ-ነዋዩ ፍሰት ጉድለት በምርት
2794ዕድገትና በሥራ መስኮች ላይ የሚከሰት ነገር ነው።
2795እና ለብዙ የአፍሪቃ ሃገራት ሁኔታው እክል
2796ሳይፈጥር የሚቀር አይመስለኝም” አፍሪቃ
2797በበለጸገው ዓለም የልማት ዕርዳታ ላይ በሰፊው
2798ጥገኛ መሆኗ ይታወቃል።
2799በፊናንሱ ቀውስ ሳቢያ የልማት ዕርዳታው መቀነስ
2800ደግሞ አፍሪቃ ከ 2015 የሚሌኒየም ግቦች ለመድረስ
2801የያዘችውን ጥረት ከንቱ ሊያደርግ የሚችል ነው።
2802በአውሮፓና በአሜሪካ የተፈጠረው የፊናንስ ችግር
2803በመጪዎቹ ዓመታት የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰትንና
2804የልማት ዕርዳታን ጋብ እንደሚያደርግ ብዙም
2805አያጠራጥርም።
2806የበለጸጉት መንግሥታት የልማት ዕርዳታቸውን ከፍ
2807ለማድረግ የገቡት ቃልም ገቢር ይሆናል ብሎ
2808መጠበቁ የሚያድግት ነው።
2809በመሆኑም የአፍሪቃ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ
2810ኮሜሣር ዶርማክስዌል እምኩዌዛላምባ የራስን ዘዴ
2811መመርመር ግድ ነው ባይ ናቸው።
2812“ችግሩን ጠለቅ አድርጎ መረዳቱ አስፈላጊ መሆኑን
2813እንረዳለን።
2814በመሆኑም በወቅቱ ከአፍሪቃ የኤኮኖሚ ኮሚሢዮንና
2815ከአፍሪቃ የልማት ባንክ ጋር በጉዳዩ ጥናት
2816እያካሄድን ነው።
2817የዚህ ጥናት ውጤት ለቱኒስ ሰብሰባ ቀርቦ ንግግር
2818ይደረግበታል።
2819ከዚሁ ተያይዞ የዓለምአቀፉ ምንዛሪ ተቁዋም የ
2820ሚናም የሚጤን ጉዳይ ነው” የዓለምአቀፉ ምንዛሪ
2821ተቁዋም የፊናንስ ዕርዳታ በምሥራቅ አውሮፓ
2822በሰፊው ማተኮር በአፍሪቃውያኑ ዘንድ ችላ
2823የመባልን ስሜት ማሳደሩ አልቀረም።
2824“የምንዛሪው ተቁዋም የኤኮኖሚ ዕድገትን
2825ለማራመድ ተብሎ የሚቀርብለትን ገንዘብ በዓለም
2826ዙሪያ የሚገኙ ሃገራትን ለመደገፍ እንዴት በሥራ
2827ላይ እንደሚያውል መጤን አለበት።
2828 በቅርቡ ለኡክራኒያ 16 ቢሊዮን፤ ለሁንጋሪያም 15
2829ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ወስኗል።
2830, በግልጽ ለመናገር ለሌሎች አገሮች በተለይም
2831ለአፍሪቃ ብዙ ገንዘብ አይተርፍም ማለት ነው”
2832ምርጫው በአንድ በኩል በዓለምአቀፍ ደረጃ
2833ተደማጭነውን ማግኘት መቻል ሲሆን ይበልጡን ግን
2834አቅምን አሰባስቦ ችግሩን በራስ ለመወጣት
2835ተገቢውን ሁኔታ ማመቻቸት ነው።
2836ከዚሁ እንዱም የአፍሪቃን ማዕከላዊና
2837የመዋዕለ-ነዋይ ባንኮች፤ እንዲሁም የምንዛሪ
2838ተቁዋም በክፍለ-ዓለም ደረጃ ለመፍጠር የተያዘው
2839ጥረት ሲሆን ይህም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
2840ለአፍሪቃ ልማት የሚያስፈልገውን የራስ ብቃት
2841ለማረጋገጥ ተግባሩ መፋጠን የሚኖርበት ነው።
2842እንደ ሕብረቱ የኤኮኖሚ ኮሜሣር ከሆነ ይህ
2843ዕርምጃ በአፍሪቃ አገሮች መካከል ያለውን ንግድም
2844የሚያጠናክር ሲሆን ከወቅቱ መሰል ቀውስ ምታትም
2845ሊሰውር የሚችል ነው።
2846የአፍሪቃ ሕብረት ለክፍለ-ዓለሚቱ ልማት ማራመድ
2847ከሚኖርበት ነገሮች አንዱ ውስጣዊውን ንግድ
2848ማጠናከሩ ይሆናል።
2849በዚሁ ረገድ የአፍሪቃ የአካባቢ የኤኮኖሚ
2850ማሕበረሰቦች በጋራ ነጻ የገበያ ክልል ለመፍጠር
2851በቅርቡ ካምፓላ ላይ ተስማምተዋል።
2852የታሰበው ከሆነ በ 624 ሚሊያርድ ዶላር የሚገመት
2853አጠቃላይ ምርት ያለውን ገበያ ትስስር የሚያሰፍን
2854ነው የሚሆነው።
2855የኡጋንዳው ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ እንዳሉት
2856ታላቁ የአፍሪቃ ጠላትና ዋነኛው የድክመቷ መንስዔ፤
2857አንድነት ማጣት፤ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ትስስር
2858በጥቂቱ እንኳ ማስፈን አለመቻል ናቸው።
2859ታላቅ ገበዮች ሕዝቡን ከድሀነት ለማሳቀቅ ስልታዊ
2860መሣሪያዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል።።
2861ነጻውን የጋራ የንግድ ክልል የሚፈጥሩት ወገኖች
2862የምሥራቅና ደቡብ አፍሪቃ ማሕበረሰብ ኮሜሣ፣
2863የምሥራቃዊው አፍሪቃ ማሕበረሰብ እንዲሁም
2864የደቡባዊው አፍሪቃ የልማት ማሕበር ናቸው።
2865ትስስሩ ደረጃ በደረጃ እንዲሰፍን የታሰበ ሲሆን
2866ትክክለኛው የጊዜ ገደብ በአንድ ዓመት ውስጥ ይፋ
2867እንደሚሆን ይጠበቃል።
286826 ሃገራትን የሚያቅፈው ነጻ የንግድ ክልል ዕውን
2869ቢሆን ለዕድገት ታላቅ ሚና እንደሚኖረው አንድና
2870ሁለት የለውም።
2871በአጠቃላይ ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ
2872በተነሳባት በአሜሪካ በባራክ ኦባማ ፕሬዚደንት
2873ሆኖ መመረጥ አዲስ የተሥፋ ዘመን ተከፍቷል።
2874ተሥፋው የአሜሪካውያን ብቻ ሣይሆን የመላው ዓለም
2875ነው።
2876የአፍሪቃም ጭምር!
2877ð
2878በትንሾቹ የአሳ ማስገሪያ ጀልባዎች የኤደንን
2879ባሕረ ሰላጤ ተሻግረው ወደ የመን ለመግባት
2880ሲሞከሩ ሰጥመው ህይወታቸውን ያጡ ስድሳ የጀልባ
2881ስደተኞች አስከሬኖች በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ
2882በየመን ጠረፍ አቅራቢያ መገኘቱን ድንበር
2883የማይገድበው የሀኪሞች ድርጅት አስታወቀ።
2884ከሱማሊያ ወደ የመን ለመግባት ሲሞክሩ በባህር
2885ሰጥመው ሲሞቱ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ
2886አለመሆናቸውን የጠቆመው በዚህ ዓመት ብቻ ከ400
2887በላይ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ስደተኞች በዚህ
2888ባህር ውስጥ ሰጥመው ቀርተዋል አሁን ከሞቱት ወደ
2889ስድሳ የሚጠጉት ስደተኞች መካከል ምን ያህሉ
2890የሶማሌያ ምን ያህሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች
2891መሆናቸው አልታወቀም በየመን የሚገኙት
2892የድርጅቱ ባለስልጣን አንድሪያስ ኩፒፓስ
2893ለጀርመን የዜና ወኪል እንዳስረዱት፡ ስደተኞቹ
2894የሞቱት ህገ ወጦቹ የጀልባዎቹ ሰራተኞች በተለያየ
2895ምክንያት ባሕር ውስጥ እንዲዘሉ ባስስገደዱበት
2896ጊዜ ነበር።
2897በሕገወጥ መንግድ ባህርን አቋርጦ የአንድን ሀገር
2898ድንበር ሰብሮ ለመግባት በሚደረግ ትግል ምናልባት
2899ድንበር ጠባቂ ፖሊስ እጅ ላለመግባት ሲሉ
2900የጀልባዎቹ ሰራተኞች ደላሎች ስደተኞችን ወደ
2901ባህር እንዲሰምጡ እንደሚያስገድዷቸው ያወሱት
2902እኚሁ ባለስልጣን በተለይ በዚህ አመት በኤደን
2903ባህር የሞቱት ቁጥር ከፍ ማለቱ አሳስቧቸዋል
2904በሀገር ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ
2905ችግር ለመቋቋም የተሳናቸው ኢትዮጵያው ያን
2906ኤርትራዊያን ሶማሊያውያን ስደተኞች በሊቢያ ወደ
2907ጣሊያን በሞሮኮ ወደ ስፔን በቱርክ ወደ ግሪክ
2908ለመግባት በሚያደርጉት የባህር ጉዞ በርካቶች
2909ለሞት ይዳረጋሉ እነዚህ ሁሉ መከራዎች አልፈው
2910ለስኬት የበቁ ጥቂት ሰዎች እንደሚናገሩት ""የአንድን
2911ሀገር ድንበር ስታቋርጥ መሞት መታሰር ወይም
2912የምትፈልገው ሀገር መድረስ ይኖራል እነዚህን
2913ሁሉ ለማድረግ ገንዝብ ያስፈልጋል
2914የምታቋርጠበት ሀገር ፖሊስ ገንዝብ ከፍለህ እዛ
2915እንደደረስክ ስለሚያውቅ ሊረዳህ አይችልም
2916እንደውም ገንዝብ ካልከፈልክ እስር ቤት
2917ትማቅቃለህ"" ይላሉ በየመን የኤደን ባህረ
2918ሰላጤን አቋርጠው ምናልባት ከሞት እና በፖሊስ
2919ካለመያዝ ቢተርፉ እንኳ የመን ውስጥ ገብቶ ሥራ
2920ሰርቶ ለመኖር እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ በርከት
2921ያሉ በስፍራው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች
2922ይናገራሉ በዩናይትድ ኔሽን ተመዝግቦ እንኳ ወደ
29233ኛ ሀገር ለመሄድ በየመን እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ
2924እንዳለ የሚናገሩት ስደተኞች ''የየመን ፖሊሶች
2925የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰጠውን
2926የስደተኛነት ወረቀት እስከመቅደድ ይደርሳሉ
2927ለዚህም የሚናገራቸው የለም"" ይላሉ አንድ
2928በሱማሊያ አድርጎ የመን የገባ ስድተኛ ሲናገር ''ሞትን
2929አምልጬ የመን ገባሁ አሁንም ላለመሞት
2930እየታገልኩ ነው"" ይላል ይህ በእንዲህ እንዳለ
2931ወደ ሕትመት እየገባን ባለንበት ወቅት የጀርመን
2932ድምጽ ራዲዮ ባሰራጨው ዘገባ በዚሁ በየመን
2933የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ላለመያዝ ፣ ህገ-ወጥ
2934በሆነ መንገድ ሰዎችን በአደን ባህረ-ሰላጤ በኩል
2935ወደ የመን የሚያሸጋግሩ ሰዎች 240 ስደተኞች
2936ከመርከብ ወደ ባህር አየዘለሉ እንዲዋኙ
2937በማስገደዳ ቸው 18 ሲሰጥሙ ከ 70 በላይ የሚሆኑት
2938ደብዛቸው መጥፋቱ ተነገረ።
2939የተረፉት ደቡብ የመን ከተማ ፣ አህዋር
2940መግባታቸው ተገልጿል።
2941ስደተኞቹ፣ በአመዛኙ ከሶማልያ ጥቂቶቹም
2942ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ተመልክቷል።
2943ð
2944በኢትዮጵያ የተከሰተዉ የዉጪ ምንዛሪ እጥረት
2945በመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች ላይ አሉታዊ ተፅኖ
2946እያሳደረ ነዉ ዛሬ የሀገሪቱ ሕዝቦች ችጋር እና
2947የኑሮ ውድነት ስንግ ይዟቸው መንግስት በፍጠረው
2948ችግር ምክንያት ከዓለም የደሀዎች ደሀ
2949የምትመደበው ሀገራችን ይህ የውጭ ምንዛሬ እጥረት
2950መከሰቱ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል የመንግስት
2951ባለስልጣናት ''በእኛ አመራር የመጣ ልማት ነው;
2952ኢኮኖሚያችን ከሚገባው በላይ አድጓል"" እያሉ
2953በሰፊው እየተናገሩ ቢሆንም ችግሮች አግጥጠው
2954እየታዩ ይገኛሉ ረሀብ እና የኑሮ ውድነት
2955እያሰቃየው ያለው ሕዝብ ችግሬ ከዛሬ ነገ
2956ይቃለላል እያለ በተስፋ እየተጠባበቀ ባለበት
2957ወቅት የውጭ ምንዛሬ በሀገሪቱ ባለመኖሩ
2958ፋብሪካዎች በአደጋ ላይ ሲሆኑ ሰራተኞችም
2959በመበተን አደጋ ውስጥ ወድቀዋል ሙሉ ለሙሉ
2960በብሔራዊ ባንክና በንግድ ባንክ ውስጥ የውጭ
2961ምንዛሬ የሌለ በመሆኑ ነጋዴዎች ጥሬ እቃ ከውጭ
2962ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከመቸገራቸውም
2963በላይ በሀገር ውስጥ የተሰማሩበት ሥራ በመቆሙ
2964ሀገሪቱ ወትሮ ከነበረችበት ችግር የባስ አዘቅት
2965ውስጥ እየገባች መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች
2966ይገልጻሉ ነዳጅ በዓለም አቀፍ ላይ ከ50 ዶላር
2967በታች እያሽቆለቆለ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ግን
2968በሚገርም ሁኔታ ላይ ነው ያለው በአሜሪካ ከሁለት
2969ወር በፊት ከነበረው የነዳጅ ዋጋ አሁን በግማሽ
2970ያህል እየተሸጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን በሳንቲም
2971ደረጃ ቅናሽ ያደረገው ይህ የሆነበት ምክንያት
2972የረከሰውን ነዳጅ ለመግዛት የውጭ ምንዛሬ
2973ስለሌላቸው በነዳጅ እጥረት ሕዝቡ እየታመሰ
2974ይገኛል አሁን የተከሰተው የውጭ ምንዛሬ እጥረት
2975መንግሥት የልማት እቅዶቹን በቁነና እንዲያፅ
2976ፈፅም ወይም በጣም-አስፈላጊና አስፈላጊ የሚል
2977ቅደም ተከተል እንዲያወጣ እያስገደደዉ ነዉ
2978ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖችና የምጣኔ ሐብት
2979አዋቂዎች እንደሚሉት በእጥረቱ ምክንያት
2980መንግሥት በጣም አስፈላጊ ለሚላቸዉ የልማት
2981ፕሮጄክቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ አስገድዶታል ይህ
2982ደግሞ የሀገሪቱን ደሀ ሕዝብ በእጅጉ ይጎዳል
2983መንግስት የምንዛሬው እጥረት የመጣበትን
2984ምክንያት በውል እንደማያውቅ ቢገልጽም
2985ተቃዋሚዎች ግን ''በብድር እና በእርዳታ
2986የሚመጣውን የውጭ ሀገር ገንዝብ በራሳቸውና
2987በቤተሰቦቻቸው ስም እየቦጠቦጡ በውጭ ሀገር
2988ባንኮች ውስጥ እያከማቹ ሀገሪቱን ባዶ
2989በማስቀረታቸው የንግዱ ማሕበረሰብ የንግድ
2990እንቅስቃሴ እንዳያድግ ሲገደብ; አሁን ደግሞ ብዙ
2991ፋብሪካዎች ለመዘጋት እንደተገደዱ'' ይናገራሉð
2992ከሮቤል ሔኖክ ድሬደዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ
2993በአስተዳደር የምትመራ ሁለተኛዋ ከተማ ናት
2994ድሬደዋ ከኦሮሚኛ ወደ አማርና ሲተረጎም "የመድሀኒት
2995ሜዳ" ማለት ሲሆን ከሶማሊኛ ወደ እንግሊዘኛ
2996ሲረጎም ደግሞ " "
2997የሚል ትርጓሜ እንዳለው በሱማሊኛ የተጻፉ ጽሁፎች
2998ይጠቁማሉ የድሬደዋ አስተዳደር በሁለት
2999ወረዳዎች የተከ ፈለ ሲሆን አንደኛው ኢሳ
3000ሁለተኛው ጉርጉራ ይሰኛሉ በኢትዮጵያ ፓርላማ 2
3001መቀመጫ ቦታም አላቸው በድሬደዋ 40 ኪሎ ሜትር
3002ርቀት ላይ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲገኝ በከተማዋ
3003ደግሞ 'አባ ጤና ደጃዝማች ይልማ ኢንተርናሽ ናል
3004ኤርፖርት""; አንድ ስታዲየም; የምድር ባቡር እና
3005የተለያዩ የገበያ ቦታዎች ይገኛሉ የአዲስ አባባ
3006ጅቡቲ ምድር ባቡር መስመርን ተከትሎ በ1902 አም
3007የተቆረቆረችው ድሬደዋ ከአስር አመታት ወዲህ
3008ለሁለት ጊዜያት በጎርፍ አደጋ መመታቷ የሚዘነጋ
3009አይደለም በነዚህ የጎርፍ አደጋዎች በርከት ያለ
3010ሰው ሕይወት እና የንብረት ላይ አደጋ ከመድረሱ
3011በተጨማሪ ለብዙዎች መሰደድ ምክንያት ሆኗል
3012በወቅቱ የዓለማችንን ሚዲያ ትኩረት ሥቦ የነበረው
3013የድሬደዋ በጎርፍ አደጋ መጥለቅለቅን ተከትሎ ዛሬ
3014የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ባራክ
3015ኦባማ በሥፍራው ተገኝተው መመልከታቸውን
3016የምናስታውስ አለን?
3017በፎቶ ግራፉ ላይ የምንመለከተው ኦባማ ኦገስት 30
30182006 በድሬ ደዋ ከተማ በጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውን
3019አካባቢዎች ሲጎበኙና አደጋ የደረሰባቸውን
3020ወግኖቻችንንም ሲያጽናኑ ነው በፎቶ ግራፉ ላይ
3021አብረዋቸው የምናያቸው ኢትዮጵያውይው አቶ አበራ
3022ቶላ ሲሆኑ እኚህ ሰው የኦክስፋም አሜሪካ የቀጠና
3023ዳይሬክተር ናቸው አቶ አበራ ቶላ ለኦባማ
3024ስለደረሰው አደጋ ገለጻ አድርገው ኦባማን
3025አስጎብኝተዋል ኦባማም ኦክስፋም አሜሪካ
3026በድሬደዋ በወቅቱ በደረሰው አደጋ ላደረገው
3027ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አድርሰዋል
3028ዛሬስ?
3029150 ሰው ያለቀበት ከ12ሺህ ሰዎች በላይ ጉዳት
3030ባደረሰው አደጋ ወቅት ኦባማ እንደደረሱት
3031በኢትዮጵያ መልካም አስተዳድር ሰፍኖ አንጨላጭሎ
3032የነበረው የዴሞክራሲ በር እንዳይዘጋ ምን ያግዙን
3033ይሆን?
3034በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ ብዙዎች የፖለቲካ
3035ተንታኞች እንደሚሉት ከምርጫው በፊት ኢሕአዴግ
3036ለዴሞክራሲ የከፈተው በር አሁን ጥርቅም ተደርጎ
3037ተዘግቷል ኦባማ ልክ በድሬደዋው አደጋ
3038እንደደረሱት ሁሉ ዛሬም በኢትዮጵያ ለሰብአዊ
3039መብቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለን
3040እንጠብቅ??
3041በነገራችን ላይ ድሬደዋ ከአዲስ አበባ 310 ማይልስ
3042ርቀት ላይ የምትገኝ ከታላላቅ የኢትዮጵያ የንግድ
3043ከተሞች መካከል አንዷ ናት በድሬደዋ አስተዳደር
3044ካውንስል ውስጥ ካሉት ሕዝቦች መካከል 40%
3045ኦሮሞዎች 277% አማሮች 139% ሶማሊዎች 45% ጉራጌዎች
304623% ሰባት ቤት 08% ሶዶ 14% ስልጤ እና 59% የሌሎች
3047ብሄሮች ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ
3048የድሬደዋ ዋና ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን 632%
3049የእስልምና; 345% የኦርቶዶክስ ክርስቲያን; 15%
3050የፕሮቴስታንት; 07% የካቶሊክ እና 01% የሌሎች
3051እምነት ተከታዮች ይኖራሉð
3052"አብረን ከሮጥን እርሱን አስቀድመዋለው"" ሲል
3053ጀግናው የኢትዮጵያ አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ
3054ያወደሰው በዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ከፍተኛ የክብር
3055ቦታ የሚሰጠው ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ""እውነትን
3056በዜማ የሚናገር የሕዝብ ልጅ"" ሲሉ ብዙሀኖች
3057ያወድሱታል ድምጻዊ የዜናማና የግጥም ደራሲ
3058በመሆን ተፈጥሮ ሁሉን አሟልታ የሰጠችው
3059የሚባልለት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ “ሰው ገድለሀል
3060ተብሎ በተጠረጠበት “ወንጀል” ቴዲ አፍሮ ጥፋተኛ
3061ተባለ።
3062ፍርዱ ዲሰምበር 5 የሚሰጥ ሲሆን እና የዲሴምበር
3063አንዱን ችሎት በገጽ 3 ላይ ይከታተሉ።
3064""የመለስ አስተዳደር ድራማ ሲሰራ አሰራሩን
3065አያውቅበትም"" ነበር ያለችው ችሎቱን
3066የተከታተለች አንዲት ወጣት ""ድራማቸው ሁሉ
3067የሕጻናት ስለሆነ ሁልጊዜ ይጋለጣሉ"" የምትለው
3068ይህችው ወጣት ከዲሴምበር አንዱ የቴዲ ችሎት
3069በፊት በሕዝቡ ላይ እየተደረገ የነበረው ነገር
3070ሁሉ በቴዲ ላይ ቀድሞ የተጻፈ ነገር
3071እንደሚፈረድበት ያስታወቀ ነበር ትላለችከጥቂት
3072ቀናት በፊት መሰብሰብ የተከላከለው ሕዝባችን
3073በመስቀል አደባባይ ለታላቁ ሩጫ በተሰበሰበት
3074ወቅት ''ቴዲ ኦባማ; መለስ አሳማ"" እያለ እየዘፈነ
3075ብሶቱን ሲያሰማ የቴዲን ቲሸርት የለበሰ; ስለቴዲ
3076ጮክ ብሎ የተናገረ አይን እና ጆሮ በሌላቸው
3077የፌደራል ፖሊሶች ተወግረው እስር ቤት አድረው;
3078ፈርመው መለቀቃቸው በአንድ ''ሰውን ገጭተሀል
3079ለተባለ እስረኛ'' የማይገባ ነገር ነበር ድራማው
3080ይህ ነው የምትለው ወጣት ከጥቂት ቀናት በፊት
3081በኢንጂነር ሀይሉ ሻውል የሚመራው የመኢአድ ፓርቲ
3082በአደባባይ በአይሱዙ መኪና የቴዲ አፍሮን 'ጃ
3083ያስተሰርያል" ሙዚቃ ከፍቶ ስለ ሰላማዊ ትግል
3084በመቀስቀሱ ዘፈኑን ከፍተው መቀስቀስ
3085እንደማይችሉ ፖሊሶች ገልጸው ቅሰቀሳውን ያፈኑ
3086ሲሆን ከቀናት በሗላ ያቺው ለቅስቀሳ የወጣችው
3087አይሱዙ መኪና የቴዲ ዘፈኖች ስለተከፈተና
3088ስለተቀሰቀሰባት ብቻ መኪናው ታስሯል እነዚህ
3089ሁሉ ሁኔታዎች እንዲሁም ቴዲ ችሎት በቀረበ ቁጥር
3090ችሎቱን የሚከታተል ሰው ካለፈቃዱ ቪዲዮ መቀረጹ
3091አሁንም በትራፊክ ሕግ መጣስ ለተከሰሰ የማይገባ
3092ነው ትላለች ይህችው ወጣት እነዚህ እና
3093ሌሎችምክንያቶች ተደማምረው በቴዲ ላይ የቀረበው
3094ክስ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው
3095ትናገራለችዲሴምበር 1 በዋለው ችሎት ላይ
3096የሕወሐት አባሉ ዳኛ አቶ ልኡል ገብረማርያም
3097ካለምንም ማገናዘብ ግልጽ የሆኑ ማስረጃዎችን
3098በቅንነት ባለመተርጎም በአርቲስቱ ላይ
3099የጥፋተኝነት ውሳኔ ወስነዋል እኚህ ዳኛ በቴዲ
3100ላይ ለመፍረድ ከተቀየሩበት ችሎት መምጣታቸው
3101ሌላው ድራማ ሲሆን ዳኛው ከዚህ ቀደም በመንግስት
3102ላይ ጥቂት ተቃውሞ ባላቸው ሰዎች ላይ በአንካሳው
3103ሕግ በመፍረድ ይታወቃሉ በውስጥ ገጾች ላይ
3104ይመልከቱ አርብ ዲሴምበር 5 ፍርድ የሚጠብቀው
3105ቴዲ በፍርድ ቤቱ የጥፋት ማቅለያ አቅርብ ቢባልም
3106""በሐቅ ለማይፈርድ ፍርድ ቤት ምንም አይነት
3107የቅጣት ማቀለያ ከዚህ በላይ የለኝም እውነት
3108ምንጊዜም ታፍና አትቀርም እኔ ንጹህሰው ነኝ'፤
3109ማንንም ሰው አልገደልኩም'; ብሏል በፖሊስ ታጅቦ
3110እየሄደ ባለበት ወቅትም ለተሰበሰበው ሕዝብ ‘ከ
3111እንግዲህ ያላችሁኝ እናንተ እና ፈጣሪ ብቻ ናችሁ”
3112ሲል መናገሩን ሪፖርተራችን ከአ
3113አ ዘግቧል።
3114ቴዲ አፍሮ ላይ ለመፍረድ በአንካሳው ሕግ
3115የተቀመጡት አቶ ልኡል ጥፋት ማቀለያ ቀረበም
3116አልቀረበም አርብ እለት የተጻፈላቸውን ፍርድ
3117ለቴዲ ማንበባቸው አይቀሬ ነው ብዙዎች ቴዲ ""17
3118መርፌ ብሎ ዘፍኖ 17 ዐመት ሊፈርዱበት ነው"" እያሉ
3119እንደቀልድ ቢጤ ጣል ቢያደርጉም ልጁ በተጠቀሰበት
3120አንቀጽ ከ5 እስከ 15 ዐመት ይፈርዱበታል ተብሎ
3121ይጠበቃል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል
3122ያነጋገራቸው የፖለቲካ ምሁራን እንደሚሉት በቴዲ
3123ላይ እየደረሰው ያለው ነገር ነገ ማንም ዘፋኝ
3124ተነስቶ ሰለፖለቲካ እንዳይዘፍን እና መንግስትን
3125በዘፈን እንዳይቃወም ታቅዶ የተደረገ ነው ሆኖም
3126ግን ይላሉ እነዚሁ ምሁራን ''ሆኖም ግን በልጁ ላይ
3127የተፈረደው ፍርድ ሕዝቡን የበለጠ በስርአቱ ላይ
3128እንዲነሳና የትግሉን መንፈስ ያጠናክራል"" ይላሉ
3129በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ ወንጀሉን ሰርቷል ብለው
3130የሚያምኑ ወገኖች ''የፈሰሰው የደሀ ነፍስ
3131እስከሆነ ድረስ ቴዲም እንደማንኛውም ሰው ፍርዱን
3132መቀበል አለበት'' ይላሉምስክሮች ሟች ደጉ
3133ይበልጣል አስከሬኑ ለምርመራ ምኒልክ ሆስፒታል
3134በጥቅምት 22 ቀን 1999 ዓም ገብቶ፣ በጥቅምት 23 ቀን
31351999 ዓም ምርመራ እንደተደረገለት የሚገልጸውን
3136ማስረጃ ቢሰጡም; አርቲስቱ ከውጭ ሀገር የገባው
3137ጥቅምት 23 ነው ፖሊስ ሰነዱን በሀይል ደጉ
3138ይበልጣል የሞተው ጥቅምት 23 እንደሆነና የሬሳ
3139ምርመራ የተደረገለትም በ24 እንደሆነ አስደርጎ
3140ሰነዱን ማስቀየሩ በግልጽ በፍርድ ቤት ቢመሰከርም;
3141ዳኛው ልኡል ነውና ጥፋተኛ ነህ ብሎታል ቴዲ
3142አፍሮ አርብ የሚፈርድበትን ፍርድ ለማወቅ ወደ
3143ዘ-ሀበሻ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ከአርብ ከሰአት
3144ጀምሮ ብትደውሉ መረጃ እንሰጣችሗለንበሌላ
3145በዘገባው አቃቤ ሕጉ ማነው?
3146ዳኛው ልዑል ገማርያምስ ማነው?
3147ከዳኛው የሚጠበቅ ፍርድ ተሰጠ ወይ?
3148የሚሉ ምርጥ እና ወቅታዊ ሁሉን አቀፍ ሚዛናዊ
3149ዘገባ ይዘናል ይከታተሉንየቴዲ አፍሮ ክስ አቃቤ
3150ሕግ ማነው?
3151በሻሸመኔ ከተማ ተወልዶ የመጀመሪያ ትምህርቱን
3152እዛው አጠናቆ ከ7ኛ እና 8ኛ ክፍል በሗላወደ አሩሲ
3153ያመራው ይህ ሰው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን
3154በአሰላ ከተማ ተከታትሏል ከዛም በ1992 ከአዲስ
3155አበባዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የተመረቀው
3156የቴዲ አፍሮን ክስ በአቃቢ ሕግነት የሚመራው
3157ፈቃዱ ጸጋ ነው አቃቤ ህጉ የቴዲ አፍሮንክስ ማን
3158ነው የሠራው??
3159በሚል በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ልዩ ዘጋቢ ለቀረበለት
3160ጥያቄ ''ክሱን እኔ አላዘጋጀሁትምክስ በፖሊስ
3161ተዘጋጅቶ ለአቃቤ ሕግ ይቀርባል አቃቤ ህግ
3162ያስከስሳል አያስከስስም የሚለውን መርምሮ
3163ለፍርድ ቤትያቀርባል'' ብሏልቴዲ አፍሮ
3164በተከሰሰበት ወንጀል ዓይነትከዚህ በፊት ታዋቂው
3165አትሌት ተስፋዬቶላ በዋስ ተለቆ ጉዳዩን በውጭ
3166ሆኖ ሲከታተል ነበር; አሁን ለምን ቴዲ አፍሮ ለምን
3167ታስሮ እንዲከታተልሆነ?
3168በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ አቃቤ ህጉ ''በሁለቱ
3169መካከል ያለው ልዩነት ተስፋዬ ቶላ መንጃ ፈቃድ
3170ነበረው'' በሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል ተባባሪ
3171ዘጋቢያችን ለአቃቤ ህጉ ከዚህ በፊት በዚሁ ክስ
3172ቴዲ አፍሮ በ15 ሺህ ብር ዋስ መለቀቁን አስታውሶ
3173ለምን ያን ጊዜ ተለቆ አሁን ይታሰራል?
3174የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር አቃቤ ህግ ፈቃደ ጸጋ
3175''አዎ ከዚህ በፊት በዋስትና ተለቆ ነበር ከአሁኑ
3176ጋር ልዩነት አለው ያኔ ገና የፖሊስ ምርመራ ላይ
3177ነበር ምርመራው ካላለቀና ጉዳዩ ተጠርጣሪውን
3178ያስከስሰዋል ወይስ አያስከስሰውም የሚለው ጥያቄ
3179ገና ካልተወሰነ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጥሮ ይሰጣል
3180በዚያ ጊዜ ተጠርጣሪው በዋስትና ይለቀቃል ወይም
3181አይለቀቅም የቴዲ ቁርጥቀን
3182ከገጽ 1 የዞረተብሎም በፍርድ ቤት ይወሰናል
3183ጉዳዩ በፖሊስ ነው የሚከናወነው በዋስትና
3184ተለቀቀ ማለት ጉዳዩ የሚያስከስስ ሆኖ ከተገኘ
3185ወደ ተከሰሰበት ቦታ እንዲቀርብ ዋስ ጠራ ማለት
3186ነው ከዚያ በሗላ ምርመራው አልቆ ወደ አቃቤ ሕግ
3187ይመጣል ፖሊሶች በምን እንደሚከሰስ
3188ስለማያውቁት ነው ዋስትና አስጠርተው የሚለቁት
3189አቃቤ ህግ ነው ሁሉን መርምሮ ከህግ ጋር አያይዞ
3190የሚከሰው በተጠቀሰው አንቀጽም አቃቤ ሕግ
3191ዋስትና እንዲከለከል ይጠይቃል'' ብለዋልአዲስ
3192የወጣው የኢትዮጵያ የትራፊክ ሕግ ከሁለት ሰው
3193በላይ ገጭቶ በመግደል የተጠረጠረ ወይም በመጠጥ
3194ሀይል ሲያሽከረክር ሰው የገደለ ሰው የዋስትና
3195መብቱ ይከለከላል ይላል ቴዲ የተጠረጠረው
3196በአንድ ሰው መግደል ነውና ለምን በዋስ
3197እንዲከታተል አልተደረገም ለሚለው ጥያቄ ''ዋስትና
3198የሚያስከለክለውም የሚፈቅደውም ሕጉ ነው እኛ
3199ቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ የጠቀስነው የወንጀል ሕግ
3200543 ንኡስ ቁጥር 3 ነው አራት ነገሮች ተጠቅሰዋል
3201ከአንድ በላይ ከገደለ ወይም ግልጽ የሆነ ደንብ
3202ተላለፎ ወንጀሉን ከፈጸመ ወይም የሚያሰክር ነገር
3203ወሶድ ወንጀሉን ከፈጸመ ወይም የሚያፈዙ እጾችን
3204ወስዶ ወንጀሉን ከፈጸመ የሚሉ ናቸው - 4ቱነጥቦች
3205ከእነዚህ መካከል አንዱን የሚያሟላ ከሆነ ዋስትና
3206ያስከለክላል በቴዎድሮስ ላይ የጠቀስነው
3207ወንጀል ግልጽ የሆነ ደንብ ተላልፏል ብለን ነው
3208መኪና ለማሽከርከር ከሚመለከተው ባለስልጣን መቤት
3209መንጃ ፈቃድ ሊሰጠው ይገባል ግን መንጃፈቃድ
3210አልተሰጠውም ተብለናል ስለዚህ ያለመንጃ ፈቃድ
3211ነው የትራፊክን ደንብ በማፍረስ የተከሰሰው ይህ
3212ወንጀል ከ5 እስከ 10 ዓመት ያስፈርዳል የሰው
3213ሕይወት ያለፈበት ደግሞ እስከ 15 ዓመት ያስቀጣል
3214ስለዚህ ዋስትና ያከለከለው ዳኛው; አቃቤ ህጉ
3215አይደሉም ህጉ ነው'' ሲሉ አብራርተዋልከፍርዱ
3216ቀን አስቀድሞ የቴዲ አፍሮ ፍርድ ደርሷል
3217ለመጨረሻ ቀጠሮ ተቀጥሯል ከፍርዱ ምን ይጠብቃሉ
3218የሚል ጥያቄ ለአቃቤ ህጉ ቀርቦላቸዋል ''አድናቂዎቹም
3219ሆኖ ሌሎች ሰዎች ማየት ያለባቸው ነገር አለ
3220ቴዎድሮስ ታዋቂ ነው; ግን ታዋቂ ሰው ወንጀል
3221አይሰራም የሚል ነገር የለም ይሄንን ወንጀል ሆነ
3222ብሎ ፈጽሞታል የተባለ አይደለም; በቸልተኝነት
3223ፈጽሞታል ነው የተባለው ቸልተኝነት ደግሞ ከሰው
3224ባህሪይ የሚመጣ ነገር ነው ነገር ግን ቸልተኛ
3225ላለመሆን መሞከር ነበረበት ነው; የክሱ ሀሳብ
3226በእርግጥ በሁሉም ነገር ቸልተኛ ስለሆነ አይቀጣም
3227ግን በቸልተኝነት ያደረሰው ጉዳት ይታያል ዋናው
3228ነገር ቴዎድሮስ ታዋቂ ስለሆነወንጀል ሊሰራ
3229አይችልም; ከሰራም ሊጠየቅ አይገባም ማለት ተገቢ
3230አይደለም እንደማንኛችንም የሰው ፍጡር ነው ብሎ
3231ማሰብ ነው የሚገባን በእኛ በኩል ወንጀሉን ሰርቶ
3232ከሆነ በደጋፊዎቹ እምነት ወንጀሉን አልሰራም
3233ከሆነ ሁሉን ነገር ማስረጃ ነው የሚወስነው'' ሲሉ ''የዳኛው
3234መቀየር በፍርዱ ላይ ምን ተጽእኖ ያመጣል; በተለይ
3235ዳኛው አቶ ልኡል የፖለቲካ ሰው ነው ተብሎ
3236ይነገራልና'' በሚለው ላይ አስተያየት ለመስጠት
3237እንደማይፈልጉና ተገቢው ፍርድ ይሰጣል፤
3238ፍርዱንም ማንም መቀበል አለበት ብለው
3239እንደሚጠብቁ ተናግረዋልዳኛው አቶ ልዑል ገማርያምበመጨረሻው
3240ሰአት ፍርዱን እንዲሰጡ ከሌላ ቸሎት ተቀይረው
3241የመጡት አቶ ልዑል ከዚህ ቀደም በኦነግ ጉዳይ;
3242በኡጋዴን ነጻ አውጪ ተከሳሾች ላይ; በቅንጅት
3243መሪዎች ላይ; በበርካታ ጋዜጠኞች ላይ እድሜ ልክ
3244እና የረዥም ዓመት ክስ የፈረዱ አንባገነን ዳኛ
3245ናቸው ይሏቸዋል እርሳቸውን የሚያውቁዋቸው አቶ
3246ልዑልን የሚያውቋቸው ሰዎች እንደሚናገሩት ገዢው
3247ፓርቲ የሚፈልገውን ሕግን አጣሞ የመፍረድ ሥራ
3248እንዲሰሩ በቦታው ላይ የተቀመጡ ናቸው አሁንም
3249በመጨረሻው ሰዓት የቴዲ አፍሮ ክስ እኚሁ ዳኛ እጅ
3250ላይ መውደቁ ትክክለኛ ፍርድ ይሰጣል ተብሎ
3251እንደማይጠበቅ ብዙሀን ይመሰክራሉ ከዚህ ቀደም
3252በአቶ ልዑል ዳኝነት 5 ዓመት እስር ቤት ቆይቶ
3253የወጣ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የነጻው
3254ፕሬስ ጋዜጠኛ 'በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት
3255የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተር ተመቶ መወድቁን መዘገቡን"
3256ተከትሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው "የሄሊኮፕተሩን
3257ስባሪ አምጣ'' እንዳሉት ገልጾ; በዚህ የተነሳ 5
3258ዓመት እስር ቤት ቆይቶ ወጥቷል በጣም የሚገርመው
3259ይህ ሂሊኮፕተር መወደቁ እውነት መሆኑንና
3260በጦርነቱ ወቅት አብራሪው በዛብህ ጴጥሮስ የፕሮፌሰር
3261በየነ ጴጥሮስ ወንድም እስካሁን በኤርትራ
3262መንግስት እጅ የት እንደተሰወሩ እንደማይታወቅ
3263በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ሁሉ ሲነገር
3264ነበር በበርካታ ሀገር ወዳድ ወገኖች ላይ አሰቃቂ
3265ፍርድ የሰጡት አቶ ልኡል በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና
3266አዘጋጅ ሔኖክ አለማየሁ ላይም በትራቸውን
3267አሳልፈዋል እኚህ ዳኛ ጋዜጠኛውን በኢትዮጵያ
3268እያለ በሚያሳትመው መዲና ጋዜጣ የተነሳ በጋዜጣው
3269ላይ 'የደህነንት ሚንስትሩን አቶ ክንፈ
3270ገብረመድህንን እነማን ገደሉት?
3271' በሚል ባወጣው ምስጢራዊ ዘገባ በዚህ ግድያ ላይም
3272የኢትዮጵያ ገዥ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት
3273በመጻፉና በማጋለጡ ለ3 ቀናት በማእከላዊ ወንጀል
3274ምርመራ በጨለማ ክፍል ከታሰረ በሗላ በ5ሺህ ብር
3275ዋስትና መለቀቁ; በፍርድ ቤት ቆይታውም የክሱ
3276አዝማሚያ ፖለቲካው ይዘትን እየያዘ በመምጣቱ
3277ከሀገር በዚህ እና በሌሎች 12 ክሶችየተነሳ
3278መውጣቱን ጋዜጠኛው ይናገራል በሌላ በኩልም
3279ሔኖክ ከሕወሓት ከተገነጠሉትና እስር ቤት
3280ተወርውረው ከነበሩት ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር
3281በማእከላዊ ምርመራ ማስተባበሪያ በታሰረበት
3282ወቅት እኚህን የቀድሞ ከፍተኛ የመንግስት
3283ባለስልጣን ከ እስር ቤት ቃለ-ምልልስ አድርጎ
3284በጋዜጣው ላይ በማተሙ በተከሰሰበት ክስ አቶ
3285ልኡል ሄኖክን በ5 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ ከእስር
3286እንዲወጣ አድርገዋል።
3287አንድን ሰው ኢንተርቪው አድርገሃል በሚል
3288መክሰስና ይህን በሚያህል ብር በዋስ መልቀቅ
3289አሳፋሪም አስገራሚም ነገር ነው።
3290ጨርሶም መክሰስ አይገባም።
3291አቶ ልዑል የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች በሙሉ ክስ
3292እርሱ በሚቀመጥበት ችሎት እንዲታይ ተደርጎ
3293በየጋዜጠኛው ላይ የቂም በቀል ፍርድ ሲሰጥ
3294የከረመ ሲሆን በዚህም በጋዜጠኞች ዘንድ አንድ
3295ክስ እርሱ ችሎት ከደረሰ ''አለቀልህ'' ተብሎ
3296ፍርዱን ቀድሞ ማወቅ እንደሚቻል ይነገራል
3297በጋዜጣ ላይ የጋዜጣ ቀን አልጻፍክም ብሎ
3298ካለምንም ማስጠንቀቂያ 2000 ብር የሚፈርደው አቶ
3299ልኡል እጅ የገባ ክስ የፈለገ ማስረጃ ቢቀርብ ነጻ
3300አይወጣም; ይልቁንም ስንት አመት ይፈረድብኝ
3301ይሆን?
3302ብሎ ማሰብ ይቀላል የሚሉ ብዙ ናቸውቴዲ አፍሮ
3303የምስክርነቱን ቃል ሲሰጥ- ”በጥቅምት 23 ቀን 1999
3304ዓም አዲስ አበባ ገባሁ።
3305ምትኩ ግርማ የተባለው ጓደኛዬ ከማናጀሬ ቀጥሎ
3306ጉዳዬን የሚፈጽምልኝ ሲሆን፣ በዕለቱ ከኤርፖርት
3307ከተቀበለኝ በኋላ ሚኪስ ፋሽን የተባለ ልብስ ቤት
3308ሄደን ልብስ ገዛሁ።
3309ምሳ ከበላን በኋላ ወደ ያሲን ቤት ሄድኩ።
3310ከዚያም እዚያ ውለን ወደ አራት ሰዓት አካባቢ
3311ማምሻውን ከያሲን ቤት ወጥተን መስቀል ፍላወር
3312አካባቢ ያለ ቤት አመሸን፣ በኋላ ሳምሶን የተባለ
3313ጓደኛዬ መጥቶ ነበር።
3314ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ከዛ ወጣን፣ እኔና
3315ሳምሶን ኦሎምፒያ ድረስ አብረን ሄድን፣ እኔ
3316የማሲንቆ ጨዋታ እወድ ስለነበር ወደ ካሳንችስ
3317ይወዳል ቤት እየነዳሁሄድኩ።
3318እዚያ ከደረስኩ በኋላ ሃሳቤን ቀየርኩና ወደ ቤቴ
3319ሲኤም
3320ሲ መንገድ ጀመርኩ፣ ምንግዜም ከውጭ ስመጣ
3321የሄድኩባቸው ሀገራትና የዚህ ሀገር የእንቅልፍ
3322ሰዓት ለማስተካከል ስለሚከብደኝ ነበር ቀኑን ውጭ
3323ያሳለፍኩት።
3324እንደሚታወቀውና ሐኪምም እንደሚለው እንዲህ
3325ዓይነት የእንቅልፍ መዛባት ሲገጥም መኪና መንዳት
3326አደጋ ሊያጋጥም ይችላል።
3327በዚህ ላይ ውጭ በነበርኩበት ግዜ ተጀምሮ
3328በምኖርበት ሲኤም
3329ሲ አካባቢ የመንገድ ኮንስትራክሽን ሥራ ተጀምሮ
3330ስለነበር አባጣና ጎርባጣውን መንገድ አላየሁትም
3331ነበርና ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባበቢ ከግዑዝ ነገር
3332ጋር ተጋጨሁ።
3333በሰዓቱ ብዙ ነገሮችን ወደሚረዳኝ ምትኩ ጋር
3334ደወልኩ፣ስልኩን ሊያነሳልኝ አልቻለም።
3335መኪናዬ ውስጥ ያሉትን ካሴቶቼንና ወረቀቶቼን
3336ሰብስቤ በላስቲክ ካደረኩ በኋላ ሠፈራችን ያለ
3337የፔፕሲ ሠራተኛ አግኝቶኝ በመኪናው ወደ ቤቱ
3338ወሰደኝ።
3339ጠዋት ምትኩ የደወልኩለትን ስልክ አይቶ ደወለለኝ።
3340የደረሰብኝን ነገርኩትና መኪናዋ መንገድ ዘግታ
3341ስለቆመች እንዲያስጎትትልኝ ነገርኩት።
3342በኋላ ላይ መኪናው በትራፊክ ጽሕፈት ቤት ሲያልፍ
3343ታርጋ የለውም ተብሎ መታሠሩን ሰማሁ።
3344ሌላ አንድ ላስገነዝብ የምፈልገው ነገር እኔ
3345ሀገር ውስጥ የገባሁት በጥቅምት 23 ቀን ነው፣
3346የምኒልክ ሆስፒታል ማስረጃ እንደሚያስረዳው
3347ደግሞ ሟች የሞተው በጥቅምት 22 ቀን ነው።
3348” ብሏል አቶ ልዑል የፈለገ ማስረጃ ቢቀርብ
3349ማስረጃውን እንደ እራሱ አመለካከት የሚመለከት
3350እንጂ የሚያገናዝብ እንዳልሆነ በቴዲ አፍሮ ፍርድ
3351ላይ አሳይቶአል የሚሉ ወገኖች አሉ።
3352ዳኛው በተለምዶ እንደታየው ነገሮችን በሙሉ
3353በቅንነት የመተርጎም ባህሪይ የለውም።
3354ዳኛ ለተከሳሽም ለከሳሽም እኩል እንደሆነ
3355የማይገነዘበው ከአቶ ልዑል እጅ መልካም ፍርድ
3356መጠበቅ፤ መለስ ዜናዊ የሚተርትባቸው እነዛ
3357ትላልቅ ግመሎች በመርፌ ቀዳዳ እንዲሾልኩ
3358እንደመጠበቅ ይቆጠራል የሚሉ በርካታ ናቸው።
3359ከአሁን በሁዋላ ምን ይጠበቃል?
3360በሚለው ጉዳይ ላይ አንድ የሕግ ባለሙያ ፕሮፌሰር
3361ይስሀቅ ኤፍሬም እና አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ
3362አርቲስቱን ከዚህ ቀደም እስር ቤት ድረስ ሄደው
3363ልክ ከዚህ ቀደም በቅንጅት መሪዎች ላይ
3364እንዳደረጉት ማነጋገራቸውን እንደ አንድ
3365ምክንያት; እንዲሁም ዳኛው አቶ ልዑል
3366ገብረማርያም የሕወሓትኢሕአዴግ አባል
3367መሆናቸውን በማውሳት ቴዲ ከፍርዱ በሗላ ልክ
3368እንደቅንጅት መሪዎች በይቅርታ ሰበብ ሊፈታ ይችል
3369ይሆናል የሚል ግምታቸውን ሲሰጡ; በርካቶች ቴዲ
3370አፍሮ የአንካሳው ሕግ ሰለባ ሆኖ ፍርዱን ጨርሶ
3371ነጻ ይወጣል የሚል እምነት አላቸው።
3372ይሄው ዳኛ ከ7 ዓመት በፊት በሞት እንዲቀጡ
3373የወሰነባቸው 44የኦነግ አባላት ሰሞኑን
3374በፕሮፌሰር ይስሃቅ እና ፓስተር ዳንኤል “አማላጅነት”
3375በይቅርታ ሰበብ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።
3376እነዚህ የኦነግ አባላት ሁለተኛ ወደፖለቲካ
3377አንገባም ሕዝብንም እንዳይሳሳት እንቀስቅሳለን
3378ብለው በመለስ ዜናዊ ሚዲያ ðላይ እየተናገሩ
3379ይገኛሉ።
3380እውን ይህች ቤተክርስቲያን የሁላችን አይደለችም
3381እንዴ?
3382ስለ ሃገራችን ሰላም፣ ስለ ቤተክርስቲያን ሰላም
3383እናልቅስ።
3384የሰላም አባት መድኅኒዓለም ክርስቶስ መልካሙን
3385ያሰማን
3386ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን ባለፈው
3387ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካን መዲና በሆነችው
3388ዋሽንግተን ዲሲ ላይ "የአገልጋዮች ጉባኤ" በሚል
3389ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ጉባኤ ጉባኤ
3390በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር ፕሮቴስታንት እምነቱ
3391ይህ ነው ሥርዓቱም ይህ ነው ለማለት አይቻለም
3392ይልቁንም በአብዛኛው የራሳቸው የሆነ ወጥ ሥርዓት
3393የሌላቸው በመሆናቸው ማንነታቸውን
3394ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ እኝህ ነበሩ
3395ላለፉት ፳ ዓመታ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ፕሬዘደንት
3396ከዛም ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት
3397ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ ላለፉት ሁለት
3398ወራት በሕዝብ መገናኛዎች አለመ
3399ሰሞኑን በአንድ የፌስ ቡክ ግድግዳ ላይ ተለጥፎ
3400ያየነው ነገር ዓይናችንን ስቦት ትንሽ ነበብ
3401ስናደርገው እንዲህ ይላል “ ኢየሱስ ሳያቆስል
3402የማረካቸው ” ይላል ዝርዝሩን ለመመል
3403ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንል ወላዲተ አምላክ
3404ዘይትነብብ በዕለተ ሠሉስ ለምስጋና ሁለተኛ
3405ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን
3406እመቤታችን ትመጣች የብርሃ ምንጻፍ ይነጸፋል
3407አቶ በጋሻው ዛሬም የውዝግብ ማዕከል ሆኗል ወደ
3408ሉንድ፣ስዊድን የገባበት ሰነድ በራሱ አወዛጋቢ
3409ሆኗል፣ ሉንድ፣ስዊድን የሚገኘው ቴዎሎጂ
3410ዩንቨርስቲ የግለሰቡን ወደ ስዊድን መምጣት
3411እንደሚ
3412አንድ የዘወትር አንባቢያችን ከላስቬጋስ አካባቢ
3413በተለይ በሐመረ ኖሕ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን
3414አስተዳዳሪ በመሆን እያገለገሉ ስላሉት መነኮስ
3415እና ሥራቸው መጠነኛ የሆነ መረጃዎችን ልኮልናል።
3416ምዕመን የማወቅ መብት አለ
3417 “ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በህወሃት
3418ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አሰሙ”
3419የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ህወሃት
3420በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ
3421ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት
3422የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ
3423ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ
3424በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ።
3425አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ
3426ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …?
3427” በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣
3428ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና
3429ወረዳዎች ካድሬዎችና ነዋሪዎች ውይይት
3430በተካሄደበት ጊዜ ነው።
3431በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3132007 ዓም በአቶ
3432ተስፋአለም ተወልደብርሃን የመቀሌ ከንቲባ፣
3433አቶ አሰፋ ተገኝ ምክትል ከንቲባ የተመራ ስብሰባ
3434የተካሄደ ሲሆን “የህወሓት ጉባኤ ምን ይመስላል?
3435” የሚል አጀንዳ ተሰጥቶት ነበር።
3436የትግራዩ አንጃ በጉባኤው ወቅት በፌስቡክና
3437በተባራሪ ወሬ የአቶ አባይ ወልዱ ስም ክፉኛ
3438ጠፍቷል በሚል እሳቤ የስም እዳሴ እያካሄዱ ነው።
34392 ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በትግራይ የሰጠው ቃለ
3440መጠይቆች ውሸት ናቸው።
34414 የጉባኤው ተሳታፊዎች ሚስጢር እንዲጠብቁ
3442ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም በቀጥታ ስርጭት ሊባል
3443በሚችል ደረጃ የስብሰባው መረጃ በፌስቡክ
3444ተዘግቧል።
34455 በአሁኑ ሰዓት ሁለት ዓይነት ጠላቶች አሉን።
3446ፊት ለፊት ወጥተው የሚታገሉን እንደ ዓረና
3447የመሰሉ እና በውስጣችን ሆነው የሚታገሉን ኪራይ
3448ሰብሳቢ ሃይሎች ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በፌስቡክ
3449ደረጃ ህወሓት መስለው ጀርባችን የሚወጉን ሃይሎች
3450ናቸው።
34516 አባይ ወልዱ ሙስናን የሚጠየፍ፣ ታግሎ
3452የሚያታግለን ጀግናና ብቁ መሪ ነው።
34537 በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ
3454እንወስዳለን።
34558 ጉባኤው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና በድል የተጠናቀቀ
3456ነበር ወዘተ
3457ተሰብሳቢዎቹ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በጥንቃቄ
3458የተመረጡ ቢሆኑም ያቀረቡት ሃሳብና ተቃውሞ ግን
3459ስብሰባው ላዘጋጀው አካል አስደንጋጭ ነበር።
3460ሀ አባይ ወልዱ በጉባኤተኛ በ20ኛ የፌስቡክ
3461ማህበረሰብ ከክፍል 20ኛ፤ ከዩኒት 1ኛ ብሎ
3462የቀለደበት ነው ደረጃ ተመርጦ እያለ
3463በሊቀመንበርነት እንዴት ሊመረጥ ቻለ?
3464እዚህ ላይ የጉባኤው ዲሞክራሲያዊነት የቱ ላይ
3465ነው?
3466ለ እነ አርከበ በድምፅ እንዲሳተፉ የተደረገበት፣
3467ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይወዳደሩ የተከለከሉበት
3468አሰራር በየትኛው ደንብ ይገኛል?
3469ሐ ዘመኑ ያመጣው የፌስቡክ ቴክኖሎጂ ህዝቡ
3470እንዳይጠቀም እርምጃ እንወስዳለን ማለታችሁ
3471ጊዜው የ21ኛ ክፍለ ዘመን መሆኑ ስላልገባችሁ ነው?
3472የሃይል እርምጃው ቴክኖሎጂውን ምን ያህል
3473ይቆጣጠረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?
3474መ አቶ ዳዊትና ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚነሱት ጉዳይ
3475በመሬት ያለና በየዕለቱ የሚያጋጥመን ሃቅ ሆኖ
3476ሳለ አትመኑት፤ ውሸት ነው፤ ማለታችሁ ችግሮቹን
3477ለመፍታት አቅም እንዳጠራችሁ አያመላክትም ወይ?
3478የሚሉትና ሌሎች ፈታኝ ጥያቄዎችና ሃሳቦች የቀረቡ
3479ሲሆኑ የመቀሌ ከንቲባና ምክትሉ የሚመልሱት
3480አጥተው አንገታቸው አቀርቅረው በሃፍረት
3481ከስብሰባው ወጥተዋል።
3482የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች የመሩት የመንግስት
3483ሰራተኞች ስብሰባዎች እየተካሄዱ ያሉ ሲሆኑ
3484ዘመቻው አቶ አባይ ወልዱ የደረሰባቸው
3485የይውረድልንና የስም ማጥፋት ዘመቻና የጠፋው ስም
3486እንደገና የማደስ ስራ ተጠምደው ይገኛሉ።
3487የዚህ ዘመቻ ትኩረት ተደርጎ ያለው ፌስቡክና
3488የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው።
3489ሰብሳቢዎች በተለያዩ መድረኮች ፌስቡክ ወጣቱ
3490ትውልድ በአሉታዊ ጎን እያበላሸው፣ የተቃውሞ
3491መንፈስ እየበረዘውና እየበከለው በመሆኑ
3492መንግስት እርምጃ ይወስዳል በማለት አዋጅ
3493እያስነገሩ ይገኛሉ።
3494እቺ ነገር መንግስቱ ሃይለማርያም “ትጥቅ
3495አቀረብን፣ ስንቅ አቀረብን፣ አሁን የቀረን ልብ
3496ማደል ነው።
3497እንደ ወያነ ጠንክራችሁ አትዋጉም ወይ…!
3498” ብሎ ያደረገው የተስፋ መቁረጥና የስርዓቱ
3499ማብቅያ አመላካች ንግግር በእጅጉ ይመሳሰላል።
3500የህወሓት አንጃዎች ክፍፍል ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ
3501እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በነዶር ሰለሞን
3502ዑንቋይ ለቀናት የፈጀ ሽምግልና ከመበተን
3503እንደዳኑ ፀሓይ የሞቀ ሃቅ ለመካድ ቢሞክሩም
3504ከህዝቡ የተሸፈነ ግን አልነበረም።
3505አሁን በመላ የትግራይ ወረዳዎች የአባይ ወልዱን
3506ስም ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት በመካሄድ ላይ
3507ይገኛል።
3508የአዲስ አበባው አንጃ ፊታውራሪ የሆኑት
3509ደብረፅዮን በ12ኛ ጉባኤ ላይ በፌስቡክ የሚነሱ
3510ሃሳቦች እንደ ትልቅ የሃሳብ ምንጭ ተቆጥረው
3511በጉባኤው ቀርበው እንደተወያዩበትና ለጉባኤው
3512እንደ ግብአት እንደተጠቀሙበት ለቪኦኤ
3513መግለፃቸው ይታወሳል።
3514የአባይ ወልዱን ስም ለማጥፋት አገልግሎት ላይ
3515ውለዋል የተባለው ፌስቡክና ተቃዋሚ ተጠቃሚዎች
3516አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።
3517የእርምጃው ዓይነት ምን ሊሆን እንደሚችል
3518እስካሁን በውል አልታወቀም።
3519ሆኖም የኢንቴርኔት ማእከላት ሊዘጉ ይችላሉ።
3520ማነው ትግራይ ሰሜን ኮርያ ያላት?
3521ያው ውድድራችን ከሰሜን ኮርያ መሆኑ ነው።
3522ትግራይ ለምትገኙ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች
3523ኢትዮጵያውያን አብዮታዊ እርምጃ
3524እንዳይወሰድባችሁ የመንፈስ ዝግጅት ብታደርጉ
3525እንመክራለን።
3526“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ
3527በ“ የኔ ሃሳብ ” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና
3528የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን
3529ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው
3530የአርትዖት ኤዲቶሪያል መመሪያ መሠረት ያለ
3531መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ
3532በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“ የኔ ሃሳብ ”
3533ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ®
3534አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
3535በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ከሚሆኑት አየር
3536መንገዶች ውስጥ አንዱ አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር
3537መንገድ በተቀዳሚነት እንዲታይ እና
3538መንገዶኞቻችን በይበልጥ የሀገራችንን አየር
3539መንገድ እንዲጠቀሙ በማሰብ ቅድሚያ የተሰጠው
3540ሲሆን፣ ሌሎችም እንደ ብሪትሽ አየር መንገድ
3541 ሉፍታንዛ እና ቨርጂን
3542እና ኬኤልኤም የመሳሰሉት አየር መንገዶችንም
3543ያቀፈ ነው፡፡
3544ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ትኬትዎን ከኢንተርኔት ላይ
3545ይቁረጡ
3546ባሁኑ ወቅት የቦ የጉዞ ወኪል ወብ ሳይት
3547ለደንበኞቹ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀን ክፍት
3548ሲሆን፣ ማናኛውም ተሳፋሪ የክሬዲት ካርድ
3549እና ኢንተርኔት መስመር ማግኘት እስከቻለ
3550ድረስ ካለምንም እንከን ጉዞውን ከሞቀ ቤቱ ቁጭ
3551ብሎ በፈለገው መልክና የተስማማውን ዋጋ እራሱ
3552መርጦ ትኬቱን መግዛት ሲችል፣ ለወደፊቱ
3553የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሌክትሮኒክ ትኬትን
3554 _ መጠቀም ሲጀምር አንድ ተሳፋሪ
3555ከአንድ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ትኬቱን
3556መቁረጥ እና የቀረውን ጊዜ ለሌላ ነገር ማዋል
3557ይችላል ይችል፡፡ እንዲሁም በብዛት ተሳፋሪዎች
3558ዋጋ ለማዋቅ ከተሌዪ የጉዞዎኪሎች በመደወል
3559የሚያተፉትን ጊዜ ይቆጥባል፡፡
3560እንዲሁም በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ሀገሮች ያሉ
3561ተሳፋሪዎች የሃገር ውስጥ በረራ ትኬት መቁረጥ
3562ከፈለጉ ከወብሳይታችን ላይ ከታዋቂ የኢንተርኔት
3563የጉµ ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት ስመሰረትን
3564በድህረ ገፃችን ላይ በመሄድ መቁረጥ ይቻላል፡፡
3565ለምሳሌ አውሮፕላን፣ መኪናና ሆቴል አሜሪንና
3566አውሮፓ ለመከራየት ከ ኦርቢትስ
3567፣ ከኤክስፒድያ
3568 እና ቺፕትኬትስ
3569 ከተባሉ ድርጅቶት ጋር ግንኙነት ስላለን
3570የሀገር ውስጥ በረራዎችን ከድህረ ገፃችን ላይ
3571ጎራ በማለት መቁረጥ ትችላላችሁ፡፡
3572ለወደፊቱም የቦ የጉµ ወኪል የደንበኞቻችን ጊዚ
3573ለመቆጠብ ተጓዡ በተመቸው ቀንና ሰዓት የመኪና፣
3574የሆቴልና የባቡር መከራዬትን የሚያስችል ድህረ
3575ገፅ ለማቅረብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
3576ከዚህም በተጨማሪ ከቢሯችን ጎራ ቢሉ ወይም
3577ከወብሳይታችን ቢሄዱ የፓስፖረት
3578ማመልከቻ ፎርም እንዲሁም ሰለ ጉዝዎ ከሀገር
3579ውስጥ ሰለተሰጡ የጉዞ ማሳሰቢያወችንማስጠንቀቂያወ
3580 ማንበብ ሲችሉ፣ ከቢሯችን
3581በመምጣት ደግሞ የፓስፖረት ፎቶ፣ የትርጉም ስራ፣
3582የኖቶሪ ኅትመት የማድረግ አገልግሎት
3583ሲኖረን፣ የፋክስ ማድረግ የኢሜል እና
3584የኢሚግሬሽን ማመልከቻዎችንም የመስጠት
3585አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
3586በበለጠ ለመረዳት እባክዎ ዛሬ ነገ ሳይሉ ድህረ
3587ገፃችንን ይጎብኙ፡፡ እንዲሁም የእርስዎ
3588አስተያየትም ሆነ ጥቆማ አገልግሎታችንን
3589ለማሻሻል ስለሚጠቅሙን እባክዎ በ @
3590ይፃፉልን፡፡
3591ነግር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ
3592እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን
3593የራሱን ፍቅር ያሳያል
3594ሴት መጋቢዎች ሰባኪዎች?
3595መጽሐፍ ቅዱስ በአገልግሎት ውስጥ ስለ ሴቶች ምን
3596ይላል?
3597መልስ፤ ምናልባት ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ
3598ሴቶች እንደ መጋቢዎችሰባኪዎች የማገልገላቸውን
3599ጉዳይ የበለጠ ሞቅ ያለ አከራካሪ ጉዳይ ሌላ የለም፡፡
3600ስለሆነም ይህን ጉዳይ ልክ ወንዶችን ከሴቶች ጋር
3601እንደ ማወዳደሩ አለማየቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
3602ሴቶች እንደ መጋቢዎች ማገልገል እንደሌለባቸው
3603እና መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶች አገልግሎት ላይ
3604ገደቦችን እንዳስቀመጠ ያን የሚያምኑ ሴቶች አሉ፤
3605እና ሴቶች እንደ ሰባኪዎች ማገልገል እንደሚችሉ
3606የሚያምኑ እና በአገልግሎት ውስጥ በሴቶች ላይ
3607ገደቦች እንደሌሉ ያን የሚያምኑ ወንዶች አሉ፡፡
3608ይሄ የመድልዎ ወይም የማግለል ጉዳይ አይደለም፡፡
3609መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ጉዳይ ነው፡፡
3610“ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤
3611ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም
3612በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።
3613” እያለ የእግዚአብሔር ቃል ያውጃል 1ኛ ጢሞቴዎስ
36142፡11-12፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔር
3615የተለያዩ ኃላፊነቶችን ለወንዶችና ለሴቶች
3616ሰጥቷል፡፡ ይህ የሰው ዘር የተፈጠረበት መንገድ
3617እና ኃጥአት ወደ ዓለም የገባበት መንገድ ውጤት
3618ነው 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡13-14፡፡ እግዚአብሔር
3619በሐዋሪያው ጳውሎስ በኩል ሴቶችን በማስተማሩ
3620ኃላፊነት ከማገልገል እናወይም በእነርሱ ላይ
3621መንፈሳዊ ሥልጣን እንዳይኖራቸው ይገድባል፡፡
3622ይህ ሴቶችን እንደ መጋቢነት ፤ በትክክል
3623መስበክን፣ ማስተማርን እና በወንዶች ላይ
3624መንፈሳዊ ሥልጣን ማግኘትን የሚያጠቃልለውን
3625እንዳያገለግሉ ይከለክላል፡፡
3626በዚህ አገልግሎት ውስጥ ሴቶችን በተመለከተ ብዙ
3627ተቃውሞዎች አሉ፡፡ የተለመደው ጳውሎስ ሴቶችን
3628ከማስተማር ይገድባል፤ ምክንያቱም በመጀመሪያው
3629ክፍለ ዘመን ሴቶች ያልተማሩ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን
3630በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-14 የትምህርት ደረጃን በየትም
3631ስፍራ አልጠቀሰም፡፡ ትምህርት ለአገልግሎት
3632መስፈርት ቢሆን ኖሮ ብዙኃኖቹ የኢየሱስ ደቀ
3633መዛሙርት ብቁ ባልሆኑ ነበር፡፡ ሁለተኛው የጋራ
3634ተቃውሞ ጳውሎስ ከማስተማር ያገደው የኤፌሶንን
3635ሴቶች ብቻ ነው 1ኛ ጢሞቴዎስ የተጻፈው በኤፌሶን
3636ለነበረች ቤተክርስቲያን መጋቢ ለነበረው
3637ለጢሞቴዎስ ነበር፡፡ የኤፌሶን ከተማ የግሪክሮማ
3638የሀሰት አማልክቶች በአርጤምስ ቤተ-መቅደስ
3639ይታወቅ ነበር፡፡ ሴቶች አርጤምስን በማምለኩ
3640ሥልጣን ነበራቸው፡፡ ሆኖም ግን የ1ኛ ጢሞቴዎስ
3641መጽሐፍም ሆነ ጳውሎስ በየትም ሥፍራ በ1ኛ
3642ጢሞቴዎስ 2፡11-12 ውስጥ የአርጤምስን አምልኮ
3643ለገደቡ እንደ ምክንያ አልተጠቀሰም፡፡
3644የተለመደው ሦስተኛው ተቃውሞ ጳውሎስ በአጠቃላይ
3645ለወንዶች እና ለሴቶች ሳይሆን ባሎችንና ሚስቶችን
3646ብቻ እያመለከተ ነው፡፡ በምንባቡ ውስጥ ያሉት
3647የግሪኩ ቃላቶች ባሎችንና ሚስቶችን ሊያመለክት
3648ይችላል፤ ሆኖም ግን የቃላቶቹ መሠረታዊ ትርጉም
3649ወንዶችና ሴቶችን ያመለክታል፡፡ በተጨማሪ
3650ተመሳሳይ የግሪክ ቃላቶች በቁጥር 8-10 ውስጥ ጥቅም
3651ላይ ውለዋል፡፡ ያለ ቍጣና ያለ ክፉ አሳብ
3652የተቀደሱትን እጆቻቸውን እያነሱ የሚጸልዩት
3653ወንዶች ብቻ ናቸው?
3654ቁጥር 8፤ እንደሚገባ የሚለብሱት፣ መልካምን
3655ሥራን በማድረግ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት
3656ሚስቶች ብቻ ናቸው?
3657ቁጥር 9-10፤ በእርግጥ አይደለም፡፡ ቁጥር 8-10
3658በግልጽ ባሎችና ሚስቶችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም
3659ወንዶችና ሴቶችን ያመለክታል፡፡ በቁጥር 11-14
3660በአገባቡ ውስጥ ወደ ባሎችና ሚስቶች መሸጋገርን
3661የሚያመለክት ምንም ነገር የለም፡፡
3662አሁንም ለዚህ ሴቶችን በአገልግሎት ውስጥ
3663በተመለከተ ለሚሰጠው ትርጓሜ ሌላው ተደጋጋሚ
3664ተቃመውሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመሪነትን ቦታ
3665ይዘው ከነበሩ ሴቶች ጋር በሚገናኝ መልኩ ነው፤
3666በተለይ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማሪያም፣ ዲቦራ እና
3667ሕልዳና ናቸው፡፡ ይህ ተቃውሞ ጥቂት ዋና
3668ጉዳዮችን ሳያካትት ቀርቷል፡፡ በመጀመሪያ ዲቦራ
3669ከ13 ወንድ ፈራጆች መካከል ብቸኛዋ ሴት ፈራጅ
3670ነበረች፡፡ ሕልዳና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
3671ተጠቅሰው ከነበሩ ብዙ ወንድ ነብያቶች መካከል
3672ብቸኛዋ ነብይት ነበረች፡፡ የማሪያም ከመሪነት
3673ጋር የተገናኘው ብቸኛው መንገድ የሙሴ እና አሮን
3674እህት መሆኗ ነበር፡፡ በነገሥታት ዘመን ሁለት
3675በጣም ስመ-ጥር ሴቶች፤ጎቶልያ እና ኤልዛቤል፤
3676ከእግዚአብሔር የሆኑ የሴት መሪዎች ምሳሌዎች
3677አልነበሩም፡፡ ምንም እንኳን በብሉይ ኪዳን
3678የነበረው የሴቶች ስልጣን በጣም በዋናነት ከጉዳዩ
3679ጋር ባይገናኝም፡፡ የ1ኛ ጢሞቴዎስ መጽሐፍ እና
3680ሌሎች የመጋቢው መልእክቶች የክርስቶስ አካል
3681ለሆነችው ለቤተክርስቲያን አዲስ ምሳሌዎችን
3682ያቀርባል እና ያ ምሳሌ ለእስራኤል ህዝብ ወይም
3683ሌላ የብሉይ ኪዳን አካል ሳይሆን ለቤተክርስቲያን
3684የስልጣን መዋቅርን ያካትታል፡፡
3685በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጵርስቅላን እና ፎኤብን
3686በመጠቀም ተመሳሳይ ክርክር ተደርጓል፡፡
3687በሐዋሪያት ሥራ 18 ውስጥ ጵርስቅላ እና አቂላ
3688እንደ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋዮች እንደሆኑ
3689ቀርቧል፡፡ ምናልባት ከባሏ ይልቅ በአገልግሎት
3690የበለጠ “ስመ-ጥር” እንደነበረች በሚያመለክት
3691የጵርስቅላ ስም በመጀመሪያ ተጠቅሷል፡፡ ሆኖም
3692ግን ከ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፤11-14 ጋር በተቃራኒ ጵርስቅላ
3693በየትም ስፍራ በአገልግሎት ሥራ ውስጥ ስትሳተፍ
3694አይገልጽም፡፡ ጵርስቅላ እና አቂላ አጵሎስን ወደ
3695ቤታቸው አምጥተው የእግዚአብሔርን ቃል በበለጠ
3696በትክክል እያብራሩ ሁለቱም ደቀ-መዝሙር አደረጉት፡፡የሐዋሪያት
3697ሥራ 18፤26
3698ወደ ሮሜ ሰዎች 16፡1 ውስጥ ፌበን ከ”አገልጋይነት”
3699ፈንታ እንደ “ዲያቆን” ብትታሰብም እንኳ ያ
3700ፌበን በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪ
3701እንደነበረች አያመለክትም፡፡ “ማስተማር መቻል”
3702ለመሪዎች እንደብቃት መለኪያ ተሰጠ እንጂ
3703ለዲያቆናት አይደለም 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፤1-13፣ ወደ
3704ቲቶ 1፤6-9፡፡ መሪዎች ወይም ጳጳሳት ወይም
3705ዲያቆናት “የአንዲት ሚስት ባል”፣ “ልጆቻቸው
3706ያመኑ” እና “የተከበሩ ሰዎች” እንደሆኑ
3707ተገልፆአል፡፡ ሀሳቡ በግልጽ እነዚህ ብቃቶች
3708ወንዶችን ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም በ1ኛ
3709ጢሞቴዎስ 3፤1-13 እና ወደ ቲቶ 1፤6-9 ውስጥ መሪዎችንጳጳሳትንዲያቆናትን
3710ለማመልከት ሙሉ ለሙሉ የተባዕታይ ጾታ
3711ተውላጠ-ስም ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡
3712የ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-14 አገላለጽ “ምክንያቱን”
3713በደንብ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ቁጥር 13 በ “ለ”
3714ይጀምርና ለጳውሎ ዐረፍተ ነገር በ11-12 ቁጥሮች
3715ውስጥ “መንስኤ” ይሰጣል፡፡ ሴቶች ወንዶችን
3716ማስተማር ወይም በእነርሱ ላይ ስልጣን ማግኘት
3717የሌለባቸው ለምንድነው?
3718ምክንያቱም “አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ ከዚያም
3719ሔዋን።
3720የተታለለውም አዳም አልነበረም፥ የተታለለችው
3721ሴቲቱ ነበረች፡፡” እግዚአብሔር መጀመሪያ
3722አዳምን ፈጠረ ከዚያም ለአዳም “ረዳት”
3723እንድትሆነው ሔዋንን ደግሞ ፈጠረ፡፡ ይኸ
3724የፍጥረት ተዋረድ በቤተሰብ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፤22-23
3725እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በየትም የሚሆን ነው፡፡
3726በተጨማሪም ሔዋን የመታለሏ እውነታ ሴቶች እንደ
3727መጋቢ እንዳያገለግሉ ወይም በወንዶች ላይ
3728መንፈሳዊ ስልጣን እንዳይኖራቸው እንደምክንያት
3729ተሰጥቷል፡፡ ይህ ጥቂቶችን ሴቶች በበለጠ በቀላሉ
3730በመታለላቸው ምክንያ እነርሱ ማስተማር
3731የለባቸውም የሚለውን ወደ ማመን ይመራቸዋል፡፡ ያ
3732ሀሳብ አከራካሪ ነው ነገር ግን ሴቶች በበለጠ
3733በቀላሉ የሚታሉ ቢሆኑ ልጆችን በቀላሉ
3734የሚታለሉትን እና ሌሎች ሴቶችን በጣም በቀላሉ
3735ይታለላሉ የተባሉትን እንዲያስተምሩ ለምን
3736ይፈቀድላቸዋል?
3737ምንባቡ የሚለው ነገር አይደለም፡፡ ሔዋን
3738በመታለሏ ምክንያት ሴቶች ወንዶችን ማስተማር
3739ወይም በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ስልጣን ሊኖራቸው
3740አይገባም፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር
3741በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጀመሪያውን
3742የማስተማር ሥልጣን ለወንዶች ሰጥቷል፡፡
3743ብዙ ሴቶች እንግዶችን በመቀበል ፤ በምህረት፤
3744በማስተማር እና በመርዳት ስጦታዎች ይልቃሉ፡፡
3745ብዙኃኑ የአጥቢያ ቤተክርስቲያናት አገልግሎት
3746በሴቶች ላይ የተደገፈ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን
3747ውስጥ ያሉ ሴቶች በወንዶች ላይ ከመንፈሳዊ
3748የማስተማር ሥልጣን ብቻ ተገድበዋል እንጂ በጉባኤ
3749ከመፀለይ ወይም ትንቢትን ከመናገር
3750አልተከለከሉም 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡5፡፡ መጽሐፍ
3751ቅዱስ ሴቶች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች
3752ከመለማመድ የከለከለበት የትም ሥፍራ የለም1ኛ
3753ቆሮንቶስ 12፡፡ ሴቶች ልክ የወንዶችን ያህል
3754ሌሎችን ለማገልገል፣ የመንፈስ ፍሬዎችን
3755ለማሳየት ወደ ገላቲያ ሰዎች 5፤22-23 እና ወንጌልን
3756ለጠፉት ለማወጅ የማቴዎስ ወንጌል 28፤18-20፣
3757የሐዋርያት ሥራ 1፤8፣ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15 ተጠርተዋል፡፡
3758እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈሳዊ
3759የማስተማር ኃላፊነቶች ቦታ ወንዶች ብቻ
3760እንዲያገለግሉ አዟል፡፡ ይኸ ወንዶች የግድ
3761የተሻሉ አስተማሪዎች ስለሆኑ ወይም ሴቶች የበታች
3762ወይም ያነሰ ችሎታ ያላቸው በመሆናቸው ምክንያት
3763አይደለም፡፡ በቀላሉ እግዚአብሔር
3764ቤተክርስቲያንን እንዴት እንድትሠራ ያበጀበት
3765መንገድ ነው፡፡ ወንዶች በህይወቶቻቸው እና
3766በቃሎቻቸው በመንፈሳዊ መሪነት ምሳሌን ማሳየት
3767ይገባቸዋል፡፡ ሴቶች ዝቅተኛውን የሥልጣን
3768ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባቸዋል፡፡ ሴቶች ሌሎች
3769ሴቶችን እንዲያስተምሩ ይበረታታሉ ወደ ቲቶ 2፤3-5፡፡
3770በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች ልጆችን
3771ከማስተማር አይከለክልም፡፡ ሴቶች የተከለከሉት
3772ብቸኛው ተግባር ወንዶችን ከማስተማር ወይም
3773በወንዶች ላይ ከሚኖራቸው መንፈሳዊ ሥልጣን ነው፡፡
3774ይኸ በተገቢው አስተሳሰብ ሴቶችን እንደ መጋቢ
3775ወይም ሰባኪ እንዳያገለግሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይኸ
3776በማንኛውም መንገድ ሴቶችን የማይጠቅሙ
3777አያደርግም ነገር ግን ይልቁን ከእግዚአብሔር
3778ዕቅድ ጋር የበለጠ የሚስማማውን እና ለእነርሱ
3779በሰጣቸው ስጦታዎች ላይ ትኩረት ያደረገውን
3780አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡
3781በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት
3782እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፉ እግዚአብሔር
3783አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን
3784እንዲሁ ወዶአልና
3785በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም
3786የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
3787ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም
3788ዓርብ ለቅዳሜ ምሽት፣ ጳጉሜን 52002 ዓ ም ማታ
3789በኢትየጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረውን
3790የአዲስ ዓመት ዋዜማ እያየሁ ነበር፡፡ ከአሜሪካ
3791የገባሁት በዚያው ቀን ነበርና ዕንቅልፌ
3792ሊስተካከልልኝ ስላልቻለ በደንብ ነበር
3793የተከታተልኩት፡፡ እኩለ ሌሊት ሊደርስ ሲል ግን
3794አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ፡፡ የማከብራቸው
3795አርቲስቶች ወደ መድረኩ ተሰባስበው ወጡና በዚያች
3796ታሪካዊት ቀን ታሪካዊ ቀን ታሪካዊውን ስሕተት
3797ሠሩት፡፡ እኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ሊሆን
3798ሽርፍራፊ ሰኮንዶች ሲቀሩ «አዲሱ ዓመት ሊገባ
3799ስለሆነ እንቁጠር» አሉና ወደ ኋላ አሥር፣ዘጠኝ፣
3800ስምንት፣ እያሉ እስከ ዜሮ ቆጠሩ፡፡ ከዚያም
3801ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ አዲሱ ዓመት ገባ ብለው
3802ዐወጁ፡፡
3803«ሊቃውንቱ ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል»
3804ይላሉ፡፡ በጥንት ጊዜ አውስትራልያ የገባ
3805አውሮፓዊ አይቷት የማያውቅ አዲስ ፍጡር ያይና
3806የሀገሬውን ነዋሪ «ይህቺ እንስሳ ማን ትባላለች?
3807» ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ያም የሀገሩ ነዋሪ «ካንጋሮ»
3808ብሎ መለሰለት፡፡ ያም ሰው «ካንጋሮ» የምትባል
3809እንስሳ አገኘሁ ብሎ ለዓለም ተናገረ፡፡ በሀገሬው
3810ቋንቋ ግን «ካንጋሮ» ማለት «አላውቅም» ማለት
3811ነበር፡፡ አንድ ሞኝ የተከለውን አምሳ ሊቃውንት
3812አይነቅሉትም እንዲሉ ይሄው ስሟ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህ
3813የአዲስ ዓመት መግቢያ ሰዓትም በየሚዲያው እና
3814በየአዳራሹ ብቅ ጥልቅ እያለ ሰነበተና ስሕተት «ሕግ»
3815ሆኖ በአደባባይ ታወጀ፡፡ ለመሆኑ ግን የስሕተቱ
3816መነሻው ምንድን ነው?
3817የመጀመርያው ቁርጥ ያለ ሕግ ካለመኖሩ የተነሣ
3818ይመስለኛል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 5120 ላይ
3819አንድ ወጥ ካላንደርን ማወጅ የፌዴራል መንግሥቱ
3820ሥልጣን መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሳላውቀው ታውጆ
3821ካልሆነ በቀር እስካሁን የተወካዮች ምክር ቤት
3822ካላንደርን በተመለከተ ያወጣው ሕግ የለም፡፡
3823ስለዚህም እንደ ዘመነ መሳፍንት «ሰው ሁሉ በፊቱ
3824መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ጀመር»፡፡ በሌላ
3825በኩል ደግሞ የሚመለከታቸውን ባለሞያዎች
3826በሚመለከታቸው ቦታ ያለማሳተፍ ልማዳችን
3827የፈጠረው ሊሆንም ይችላል፡፡ አንድ ሰው እድሉን
3828እና መድረኩን ካገኘ፤ ታውቃለህ ከተባለ፤
3829አጋጣሚውም ከተፈጠረለት ሁሉንም ይሆናል፡፡
3830ደራሲም፣ አዘጋጅም፣ ዳይሬክተርም፣ ተዋናይም፣
3831ይሆናል፡፡ ዘፋኝም፣ ኮምፖዘርም፣ ደራሲም፣
3832የድምፅ ባለሞያም ይሆናል፡፡ ይኼ ልማዳችን
3833የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተም በሞያው
3834የደከሙ፣ ከልክ በላይ የሠለጠኑ፤ ነገሩን
3835ከነምክንያቱ ሊያስረዱ የሚችሉ ሊቃውንት እያሉ
3836ሞያውን የማያውቁት እና ለሞያውም ትኩረት
3837የማይሰጡ አካላት ገቡበትና ሁሉም የየራሱን
3838መንገድ ፈጠረ፡፡
3839እንደገናም ደግሞ ፈረንጅ ያደረገው ሁሉ ትክክል
3840ነው የሚለው ክፉ ልማዳችንም ለዚህ ሳያጋልጠን
3841አልቀረም፡፡ ፈረንጆቹ አዲሱን ዘመናቸውን
3842የሚቀይሩት በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ያም እንኳ
3843ቢሆን ትክክል ሆኖ አይደለም፡፡ የዘመን መለወጫ
3844በሽርፍራፊ ሴኮንዶቹ የተነሣ በየጊዜው
3845ይለዋወጣልና፡፡ ነገር ግን በልማድ ሕግ
3846መሠረት በእኩለ ሌሊት ሰዓታቸውን በመጀመራቸው
3847ከሰዓታቸው ጋር እንዲገጥም አድርገው
3848ተጠቀሙበትና በዚያው ጸና፡፡ ታድያ እኛም
3849ለመሠልጠን እንደ እነርሱ በእኩለ ሌሊት አዲሱን
3850ዓመት መቀበል አለብን ተብሎ ሳይታሰብ አልቀረም፡፡
3851ፈረንጆቹ በእኩለ ሌሊት አዲስ ዓመታቸውን ቢቀበሉ
3852እውነታቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም የእነርሱ የቀን
3853አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት አንድ ሰዓት አልፎ
3854ይጀምርና በእኩለ ሌሊት ያልቃል፡፡ አዲሱ
3855ዓመታቸውም 00 ብሎ የሚጀምረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡
3856ኮፒ በሚጠቅም መንገድ ከተደረገ አንዳንድ ጊዜ
3857መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኮፒ ሲደረግ ለገልባጩ
3858እንዲያመቸው አድርጎ ካልሆነ ከመኮረጅ የባሰ
3859ስሕተት ይሠራል፡፡
3860ትምህርት ቤት እያለን የሚቀለድ አንድ ቀልድ
3861ነበረ፡፡ አንድ ሰነፍ ተማሪ ነበረ ይባላል፡፡
3862ይኼ ተማሪ አራተኛ ክፍል ይደርስና እንዴት
3863እንደሚያደርግ ግራ ይገባዋል፡፡ በመጨረሻም
3864በፈተና ሰዓት አነጣጥሮ ተኳሽ መሆን
3865እንደሚያዋጣው ራሱን አሳምኖ ፈተና ክፍል ይገባል፡፡
3866ከዚያም እያነጣጠረ ከጎበዙ ተማሪ መኮረጅ
3867ይጀምራል፡፡ አንዲትም ጥያቄ ሳታመልጠው
3868ይኮርጃል፡፡ በመጨረሻም ፈተና በሚመለስበት ቀን
3869ግቢው ሁሉ በሳቅ አወካ፡፡ ለካስ ያ ሰነፍ ተማሪ
3870ከጎበዙ ተማሪ ሲኮርጅ ከነ ስሙ እና ከነ ቁጥሩ
3871ኑሯል የኮረጀው፡፡
3872የኛም አኮራረጅ የዚህን ሰነፍ ተማሪ ዓይነት ሆነ፡፡
3873ቢያንስ ቢያንስ የአዲስ ዓመት በዓል
3874አከባበራቸውን ወስደን የኛ አዲስ ዓመት
3875በሚከበርበት ሰዓት ብናደርገው ከሰነፉ ተማሪ
3876አኮራረጅ የተሻለ በኮረጅን ነበር፡፡ ምናልባትም
3877ደግሞ ነገሮችን በአራቱም አቅጣጫ ካለማየት
3878የመጣም ይሆናል፡፡ ዕውቀት ማለት ነገሮችን
3879ከአራት አቅጣጫ ማየት መቻል ነው፡፡ ማንበብ፣
3880መጠየቅ፣ መመራመር፣ ማነፃፀር፣ ማወዳደር፣
3881መተንተን የሚባሉት ነገሮች የሚመጡት ነገሮችን
3882ከአራቱም አቅጣጫዎች ለማየት ሲሞከር ነው፡፡
3883በእኩለ ሌሊት ተነሥተው አዲስ ዓመት ገብቷል
3884ብለው የሚያውጁ አካላት ሌላው ቀርቶ የእጅ
3885ሰዓታቸውን እንኳን ቢያዩት በታረሙ ነበር፡፡ «ከሌሊቱ
3886ስድስት ሰዓት» ነበር የሚለው፡፡ በዚያ ሰዓት
3887ስድስት ሰዓት ካለ ደግሞ ሌሎች አምስት ሰዓታት
3888ከፊቱ ሄደዋል፤ ወይንም ደግሞ ሌሎች ስድስት
3889ሰዓታት ከኋላው ይቀሩታል ማለት ነው፡፡ በዚያ
3890ሰዓት ስድስት ሰዓት ከተባለ ደግሞ ያ ሰዓት
3891ያለፈው ቀን ቅጣይ እንጂ የአዲስ ቀን መጀመርያ
3892አለመሆኑን መረዳት ይገባ ነበር፡፡ አንዳንዶች
3893ይህንን የአዲስ ዓመት ጉዳይ ከገና እና ፋሲካ
3894በዓላት ጋርም ያያይዙታል፡፡ በገና እና ፋሲካ
3895በዓላት ጊዜ በዓሉ የሚበሰረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡
3896ከዚህ አያይዘውም አዲስ ዓመትም በእኩለ ሌሊት
3897ይበሠራል ይላሉ፡፡ ገና እና ፋሲካ በእኩለ ሌሊት
3898የሚበሠሩት በበዓላቱ ታሪካዊ ምክንያት የተነሣ
3899እንጂ የበዓሉ ቀን በእኩለ ሌሊት ስለ ገባ
3900አይደለም፡፡ ክርስቶስ የተወለደውም ሆነ ከሙታን
3901የተነሣው በእኩለ ሌሊት ነው ተብሎ በቤተ
3902ክርስቲያን ስለሚታመንበዓሉ በእኩለ ሌሊት
3903ተከበረ እንጂ ዕለታቱ በስድስት ሰዓት
3904ስለሚገቡአይደለም፡፡
3905በቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት አቆጣጠሮች አሉ፡፡
3906የፀሐይ አቆጣጠር እና የጨረቃ አቆጣጠር፡፡
3907የፀሐይ አቆጣጠር ከጠዋቱ አሥራ ሁለት በኋላ
3908ጀምሮ እስከ ሌሊቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ይደርሳል፡፡
3909አብዛኛውን የሕዝቡ በዓላት እና አቆጣጠር
3910 የተመሠረተው በዚህ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ
3911የጨረቃ አቆጣጠር ነው፡፡ ይህም በምሽቱ አሥራ
3912ሁለት ሰዓት ጀምሮ በማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት
3913ያልቃል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የቤተ ክርስቲያኒቱ
3914በዓላት፣ በተለይም ዐበይት በዓላት የሚወጡት
3915ይህንን አቆጣጠር ከፀሐይ አቆጣጠር ጋር በማጣመር
3916ስለሆነ ተብይጠራል፡፡ በሥርዓተ
3917ጸሎት ምሽት ሲገባ የቀጣዩን ቀን ጸሎት
3918የምናደርሰው የጸሎት አቆጣጠራችን የጨረቃን
3919አቆጣጠር ጭምር ስለሚከተል ነው፡፡
3920ቤተ ክርስቲያን ሁለቱንም
3921አቆጣጠሮችእንደየአስፈላጊነታቸው
3922ትጠቀምባቸዋለች፡፡ አንዳንድ መፍቀርያነ በዓል
3923ደግሞ በዓሉ የሚያምረው እና የሚደምቀው በእኩለ
3924ሌሊት ሲሆን ነውና በእኩለ ሌሊት ብናከብረው
3925ምናለ ይላሉ፡፡ በዓሉን በእኩለ ሌሊት ማክበርና
3926አዲሱ ዓመት በእኩለ ሌሊት ገባ ብሎ ማወጅ
3927ይለያያሉ፡፡ የበዓሉን ዋዜማ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ
3928እስከ ንጋት ድረስ ማክበር ይቻላል፡፡ የሺ
3929ዘመናትን ሥርዓት እና አቆጣጠር በአንድ ሌሊት
3930በማወቅ እና ባለማወቅ መናድ ግን በታሪክ እና
3931በትውልድ የሚያስጠይቅ ነው፡፡
3932ሰለጠንን የምንል ሰዎች ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ
3933ሆነን በጎርጎርዮሳዊው ቀመር ሰዓታችንን
3934እንሞላዋለን፡፡ በኛ የሰዓት አቆጣጠርም ዕለቱ
3935የሚጀምረው በኛ ከሌሊቱ ስድስት በእናንተ ደግሞ
3936ከሌሊቱ 00 ሰዓት ነው፡፡ የኢትዮጵያን የዘመን
3937አቆጣጠር እያከበሩ በአውሮፓ ሰዓት መጠቀም ግን
3938በዶሮ ወጥ ላይ ማርማላታ እንደ መጨመር ነው፡፡
3939ሁለቱንም አያይዞ ማጥፋት፡፡
3940ታድያ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚብተው ስንት
3941ሰዓት ነው?
3942ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንችል ዘንድ አራት
3943ነገሮችን እናንሣ፡፡ የመጀመርያው በኛ አቆጣጠር
3944ዕለት የሚባለው ምንድን ነው?
3945የሚለው ነው፡፡ ዕለት ሁለት ነገሮችን ይይዛል፡፡
3946ቀን እና ሌሊት፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ዕለት
3947የሚባለው ከመንፈቀ ሌሊት እስከ ማለዳ ያለውን
3948ግማሽ ሌሊት፣ ከዚያም ከማለዳ እስከ ማታ ያለውን
3949ቀን እና ከማታ እስከ እከየለ ሌሊት ያለውን ግማሽ
3950ሌሊት የያዘው ክፍል ነው፡፡ በኛ ግን አንድ ቀን
3951እና አንድ ሌሊትን ብቻ የያዘ አቆጣጠር ነው፡፡
3952ስንክሳሩ መስከረም አንድን ሲጀምር «ይህ
3953የመስከረም ወር የተባረከ ነው፤ እሱውም የግብጽ
3954እና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመርያ ነው፡፡ የዚህ
3955ወር ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው» ይላል፡፡
3956ይህ የሚያመለክተን በመስከረም አንድ ቀኑ እና
3957ሌሊቱ እኩል የሆነ አንድ ቀን እንጂ በግማሽ ሌሊት
3958እና በሙሉ ቀን የሚቆጠር አይደለም ማለት ነው፡፡
3959ምንም እንኳን በየወራቱ የቀኑ እና የሌሊቱ
3960ርዝመት ልዩነት ቢኖረውም ሰዓቱ ግን እኩል አሥራ
3961ሁለት ሰዓት ቀን እና ሌሊት ነው፡፡
3962ለምሳሌ አሜሪካውያን በዓመት ሁለት ጊዜ የሰዓት
3963ማስተካከያ ወደፊት እና ወደ ኋላ ያደርጋሉ፡፡
3964አውሮፓውያን፣ በተለይም ሰሜኖቹ ደግሞ ከአንድ
3965ሰዓት ሌሊት እስከ ሁለት ሰዓት ቀን የሚደርሱበት
3966ጊዜ አለ፡፡ በኛ ግን የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት
3967ብዙም ልዩነት የለውም፡፡
3968ይሆናሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን ቀኑም ሆነ ሌሊቱ
3969ከአሥራ አምስት እንደማይረዝም፤ ከዘጠኝ
3970እንደማያንስ ነው፡፡ እንግዲህ አዲስ ዓመት
3971በመስከረም ወር እንዲብት የተደረገበት አንዱ
3972ምክንያት ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል የሚሆንበት ጊዜ
3973ስለሆነም ነው፡፡
3974ሁለተኛው ነገር ደግሞ የዓመቱን ወራት የምናወጣው
3975በምን አቆጣጠር ነው የሚለው ነው፡፡ ቀደም ብለን
3976እንዳየነው የዓመቱን ወራት የምንቆጥረው በፀሐይ
3977አቆጣጠር ነው፡፡ በፀሐይ አቆጣጠር ደግሞ መዓልቱ
3978ሌሊቱ ይስበዋል፡፡ ምክንያቱም ፀሐይ
3979የሚሠለጥነው በቀን ነውና ዘፍ 1፤14፣16፡፡ ያ
3980ከሆነ ደግሞ በአቆጣጠራችን ቀኑ ቀድሞ ይጀምራል
3981ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የኛ አንድ ሰዓት ማለዳ
3982ላይ እንጂ እኩለ ሌሊት ላይ ሊጀምር አይችልም፡፡
3983ሦስተኛው ደግሞ የሰዓት አቆጣጠራችን ነው፡፡
3984በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር አንድ ብሎ
3985የሚጀምረው መቼ ነው?
3986አዲሱን ዓመት በእኩለ ሌሊት የሚያውጁት ሚዲያዎች
3987እንኳን መልሰው ጠዋት ይነሡና «መስከረም አንድ
3988ቀን ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ነው» ይሉናል፡፡
3989የፈረንጆቹ ሰዓት ግን በዚያ ሰዓት 7 ሰዓት ነው
3990የሚለው፡፡ ምክንያቱም እኩለ ሌሊት ላይ አንድ
3991ብሎ ጀምሯልና፡፡ አንድ ሰዓት ደግሞ ስድሳ
3992ደቂቃዎች እና 3600 ሰኮንዶች ነው፡፡ ስለዚህም
3993አንድ ሰዓት ለማለት እነዚህ ተቆጥረው ማለቅ
3994አለባቸው፡፡ እነዚህ መቆጠር የሚጀምሩት ደግሞ
3995ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አሥራ
3996ሁለት ሰዓት የሌሊቱ ማጠናቀቂያ ነውና፡፡
3997አውሮፓውያንም ቢሆኑ ይህ በየዓመቱ ያለውን
3998የወንጌላውያን መለያየት ያውቁታል፡፡ ነገር ግን
3999የአዲስ ዓመት መግቢያቸውን በእኩለ ሌሊት
4000ያደረጉት አንድ ወጥ ለማድረግ ነው፡፡እኛም
4001በዚያው በእኩለ ሌሊቱ ብንቀጥለው ምናለ?
4002የሚሉ ሃሳብ አቅራቢዎች አሉ፡፡ ቀደም ብለን
4003እንዳየነው የእነርሱ የዘመን መለወጫቸው ከሰዓት
4004አቆጣጠራቸው ጋር አብሮ ይሄዳል፡፡ የኛ ግን
4005ዘመን ለወጥን ብለን መልሰን ሰባት፣ ስምንት
4006እያልን መቁጠሩ መምታታት ነው፡፡
4007እንግዲህ እነዚህን ነጥቦች ስናያቸው የኢትዮጵያ
4008አዲስ ዓመት በእኩለ ሌሊት ሊጅምር የሚችለው
4009የወንጌላውያንን መግቦት ከተከተልን በዘመነ
4010ማርቆስ ብቻ ነው፡፡ ያም ቢሆን ከሰዓት
4011አቆጣጠራችን ጋር ይጋጫል፡፡ ከሰዓት
4012አቆጣጠራችንም ሆነ ከባህላችን ጋር፣ ብሎም
4013ከመስከረም የቀን እና ሌሊት እኩል መሆን ጋር
4014የሚገጥመው አዲሱን ዓመት በማለዳ አሥራ ሁለት
4015ሰዓት ላይ መቀበሉ ነው፡፡
4016በዚህ ጉዳይ ላይ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች ጳጉሜ
4017አምስት እና ስድስት ሌሊት ተነሥተው መከራ
4018ከሚያሳዩን ሰነድ ማገላበጥ እና ምሁራኑን መጠየቅ
4019አለባቸው፡፡ ሊቃውንቱም ቢሆኑ ደፍረው ወጥተው
4020ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የውይይት መድረክ
4021የሚያዘጋጁ አካላትም አንዱ የመወያያ ጉዳይ
4022አድርገው ፈር እንድንይዝ ቢያደርጉ
4023ይመሰገኑበታል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ያለ ምርምር
4024በዘፈቀደ እየተፈጸመ ያለው ስሕተት ሕግ ሆኖ
4025እንዳይቀጥል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 5120 መሠረት
4026ፓርላማው አንዳች ነገር ማድረግ አለበት፡፡
4027በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የመወሰን
4028ሥልጣን የተሰጠው የፌዴራሉ መንግሥት ሊቃውንቱን፣
4029ባለሞያዎችን እና ሕዝቡን አማክሮ፤ ሰነድ
4030አገላብጦ እና ታሪክ መርምሮ ይህንን ዝብርቅርቁ
4031የወጣውን የአዲስ ዓመት የመባቻ ሰዓት ጉዳይ
4032አንዳች እልባት የሚሰጥ ዐዋጅ ማወጅ ይጠበቅበታል፡፡
4033መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ!
4034?=891
4035በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣
4036በዕለተ እሑድ ነው፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን
4037እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው
4038በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ የግዕዝ
4039ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ
4040ማለት-መነሳት ማለት ነው፡፡” ሞትን ድል አድርጎ፣
4041ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው፡፡ “ሕይወት
4042ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት
4043ነው፡፡ በዓሉ ጌታችን የተሰቀለበትን ዕለት መጋቢት
404427ን እና ሞትን ድል አድርጎ “ለይኩን ትንሣኤ
4045ለሙታን!
4046” ብሎ የተነሳበትን መጋቢት 29ን ቀን ጠብቆ
4047እንዳይከበር ያደረገው ትልቅ ምክንያት አለ፡፡
4048እርሱም፣ በየዓመቱ መጋቢት 29 ቀን እሑድ-እሑድ
4049አለዋሉ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ከዘመናት በኋላ
4050መጋቢት 29ን እየጠበቁ፣ አንዴ ሰኞ፣ ሌላም ጊዜ
4051ማክሰኞ ወይም ረቡዕና ኀሙስ፣
4052ወዘተርፈ ይከበር የነበረውን የጌታ ትንሣኤ
4053በዕለተ-እሑድ ለማክበር የሚያስችለውን ድንጋጌ፣
4054በ13ኛው ክፍለ ዘመን ላይ-አቡሻህር ኢብን ቡትሩስ
4055ራሒብ ወይም ዮሐንስ የተባለው የእስከንደሪያ
4056ካህን ገለጠው፡፡ በዚህም ድንጋጌ መሠረት
4057የትንሣኤ በዓል ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ባሉት
4058እሑዶች ውስጥ እየተዘዋወረ ይከበር ጀመር፡፡
4059በመሆኑም፣ የጾመ ነነዌና የዐብይ ጾም
4060የሚጀርባቸው ዕለታት ሰኞ-ሰኞ እንዲሆኑ ተደነገገ፡፡
4061የሆሳዕና እና የትንሣኤም ዕለቶች ከእሑድ ውጪ
4062እንዳይሆኑ ደንብ ተሠራ፡፡ የጸሎተ
4063ኀሙስም-በዕለተ ኀሙስ፤ የስቅለት ዕለትም በያመቱ
4064አርብ-አርብ እንዲሆን ተደረገ፡፡ የቅዳሜ
4065ሥዑርም-ከቅዳሜ ውጪ እንዳይሆን ተደረገ፡፡
4066ጌታችን መድኃኒታችንም የሞትን ቅኝ-ግዛት ድል
4067የተቀዳጀበት ዕለት እሑድ ስለነበረ፣ የትንሣኤ
4068በዓል ከእሑድ ውጪ እንዳይሆን ተደረገ፡፡
4069በዕለተ ኀሙስ ግን ሁለት የማይታለፉ ተግባራትን
4070አከናወነ፡፡ የመጀመሪያው ወደ ተራራው ጫፍ ወጥቶ
4071ያደረገው ጸሎት ነው፡፡ ደም እንደላብ እየወረደው
4072በተመስጦ ሲጸልይና ሲተጋ ሳለ፣ ሦስቱ ነብያት ነብዩ
4073ሄኖክ፣ ነብዩ ሙሴ፣ እና ነብዩ ኤልያስ
4074የሰማየ-ሰማያትን አድማስ ጥሰው ከተፍ አሉ፡፡
4075እንዲጸናም አዘዙት፡፡ የእግዚአብሔርም ድምጽ
4076እያስገመገመ መጣ፡፡ ፈጣሪያችን መጽናናትንም
4077ለዓለም ላከ፡፡ ከተራራው ከወረዱ በኋላ
4078የመጨረሻውን ራት ለመብላት ሄዱ፡፡ በዚህም ምሽት
4079ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ
4080እንዲህ አላቸው፡፡ “ነገ በመልዕልተ መስቀል ላይ
4081የሚፈተተው ሥጋዬ እና የሚፈሰውም ደሜ ይህ ነው!
4082” ስለዚህም፣ በምሴተ-ኀሙስ ሥጋውን-በስንዴ፣
4083ደሙንም-በወይን አምሳል አድርጎ ለደቀ መዛሙርቱ
4084የሠጠበት ምሽት ነው፡፡ ከዚህም ሌላ የደቀ
4085መዛሙርቱን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትም
4086ሰዓት ነው፡፡ እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ
4087እንደዚህ አድርጉላቸው!
4088ብሎም ያዘዘው በዚሁ ጊዜ ነበር፡፡ የጌታንም
4089አርዓያነት በመከተል የኢትዮጵያ ተዋሕዶ
4090ቤተ-ክርስቲያን ምእመናን ዕለተ-ኀሙስን ጸሎት
4091በማድረግና የጌታንም ራት ለማሰብ ተብሎ
4092የሚዘጋጀውን ጉልባን በመመገብ ታከብረዋለች፡፡
4093ከዚህም የመጨረሳ ራጽ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ
4094ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እስከሚነሳበት ለእሑድ
4095አጥቢያ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ድረስ ምእመናን ምንም
4096ነገር ከመመገብ ይታቀባሉ፤ ይጾማሉ፡፡
4097የአዱዋውን ድል የተጎናፀፍንበት ዕለት፣
4098በአለማችን ላይ ከተከሰቱት 15ቱ ታላላቅ ቀናት
4099መካከል የምናስቀምጠው ነው፡፡ በአዲስጉዳይ
4100መጽሔት ላይ 20120615
4101በሁለት ተከታታይ መጣጥፎች እንደገለጽኩት፣
4102የሰውን ልጆች ሰብዓዊ ክብርና የመንፈስ ሙላት
4103ላቅ በማድረግ ከሚወሱትከሚጠቀሱት ቀናት መካከል
4104አንዱ፣ “የአዱዋው ድል” ነው፡፡ የድሉ አብነትተምሳሌት፣
4105ብሎም የዘር-መድሎን በመፈወስ ሃይሉና
4106የእኩልነትን አዋጅ በማወጅ አቅሙ አዱዋን
4107የሚስተካከል የለም፡፡ ድሉ፣ የስልጡኗ
4108አውሮፓንና የኋላ-ቀሯን አፍሪካ ጦርነት ነው
4109የአሸናፊዎች አሸናፊ መለያም ነው፡፡ አንዳንድ
4110ተንታኞች ደግሞ አልፈው-ተርፈው “ የጥቁሮችና
4111የነጮች ፍልሚያ” አድርገው ተመልክተውታል፡፡
4112የሃይማኖትን ታሪክ አጥኚ የሆኑት ምሁራን
4113በበኩላቸው፣ የካቶሊካዊቷ ሮማና
4114የኦርቶዶክሳዊቷ ኢትዮጵያ ፍልሚያ አድርገው
4115አስበውታል፡፡ እርግጥ ነው፣ የጊዮርጊስ ጽላትታቦትና
4116አቡኑና እጨጌውም በጦርነቱ ሥፍራ ነበሩ፡፡ በሌላ
4117በኩል፣ በአድዋው ጦርነት ወቅትና ከአርባ ዓመታት
4118በኋላ በተደረገው የአምስት ዓመቱ የወረራም ዘመን
4119ጅማሮ ላይ የሮማ ሊቃነ-ጳጳሳት በአደባባይ
4120ተገኝተው የፋሺስትን ጦር በካቶሊክ
4121ቤተ-ክርስቲያን ስም ባርከው ልከዋል፡፡ በመሆኑም፣
4122ጦርነቱ የጊዮርጊስ ጽላትታቦት ተሸክመው
4123የዘመቱት “ኦርቶዶክሳዊያን” እና
4124በሊቀ-ጳጳሳቶቻቸው ቡራኬ አገር እንዲያቀኑ
4125ተባርከው የተሸኙት “ኮተሊኮች ጦርነት” ሆነ፡፡
4126ውጤቱም ለኦርቶዶክሳውያኑ ያደላ ሆነ፡፡
4127የአዱዋ ጦርነት መንስኤ የታወቀው የውጫሌ ውል
4128ነው፡፡ ውጫሌ በአንባሰልና በየጁ መካከል
4129የሚገኝ፣ ለሐይቅ እስጢፋኖስ ቀረብ ያለ ቦታ ስም
4130ነው፡፡ ይህ ስምምነት ሃያ አንቀፆች ያሉት ሲሆን፣
4131በሚያዝያ 25 ቀን 1881ዓም ተፈረመ፡፡ ለውዝግቡም
4132ጉልሁን ድርሻ የሚወስደው “አንቀጽ 17” የተባለው
4133አንቀጽ ነበር፡፡ ውሉን ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ
4134የተረጎሙት ወይም የአማርኛውን ዘር ያረቀቁት
4135ሰው፣ ግራዝማች ዮሴፍ ንጉሤ ይባላሉ፡፡
4136የጣሊያንኛውንም ቅጂ ያሰናዳው አንቶንሌ ነበር፡፡
4137አንቶንሌ ከአስር ዓመታት በላይ አንኮበርና
4138በእንጦጦ አብያተ-መንግሥታት አካባቢ ስለኖረ
4139አማርኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ ስለሆነም
4140የሕጋዊ ዘይቤና አገባብ ያላቸውን ቃላትና
4141ፍቺዎቻቸውንም አብጠርጥሮ እስከማወቅም ደርሶ
4142ነበር፡፡ በዚህም እውቀቱ ተጠቅሞ በአማርኛና
4143በጣሊያንኛ የተለያዩ ትርጓሜዎች ያሉትን አንቀጽ
414417ን አሰናዳ፡፡ የአማርኛው እንዲህ ይላል፤ “የኢትዮጵያ
4145መንግሥት ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር መገናኘት
4146ከፈለገ የኢጣሊያንን መንግሥት አገልግሎት
4147ሊጠቀም ይችላል፤ ” ሲል-የጣሊያንኛው ቅጂ ደግሞ
4148“የኢትዮጵያ መንግሥት ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር
4149መገናኘት ከፈለገ የኢጣሊያንን መንግሥት በኩል
4150ይገለገላል፤ ” ይላል፡፡
4151በአዱዋው ጦርነት ዋዜማ ላይ ከሰኔ 1885 እስከ
4152ጥቅምት 1888ዓም ድረስ ኢትዮጵያና ጣሊያን
4153በየፊናቸው ዝግጅቶቻቸውን ሲያድርጉ ከረሙ፡፡
4154በጣሊያን በኩል የተለመደውን ተንኮልና
4155ማጭበርበር ቀጠለ፡፡ ዋነኛው ተንኮል የከብት
4156በሽታን ወደኢትዮጵያ ማስገባት ነበር፡፡ በዚህም
4157ሰበብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶች አለቁ፡፡
4158ገበሬው ለእርሻ የሚጠቀምባቸው በሮችም አለቁ፡፡
4159በመሆኑም፣ ዋነኛው የእርሻ ግብዓት በበሽታው
4160በመጠቃቱ፣ የገበሬው ምርታማነት እጅግ
4161አሽቆለቆለ፡፡ ረሃብና ጠኔ በመላ ሀገሪቱ
4162ተንሰራፋ፡፡ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ
4163በኢትዮጵያ ምድር ተከሰተ፡፡ አዝማሪው እንዲህ
4164ሲል አዜመ፤ “የበሬዎቹ ስም ጠፍብኝ ነበረ፤
4165አሁንስ ባስታውስ ከብት ዓለም ነበረ፡፡” አለ፡፡
4166እጅግ የታወቀው “ሞጣ ቀራኒዮ ምነው አይታረስ፤
4167በሬሳ ላይ መጣሁ፣ ከዚህ እስከዚያ ድረስ፡፡”ም
4168የተባለው በዚያ ወቅት ነበር፡፡ በዚያ ዘመን
4169ያለቁትን ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ፀሐፌ
4170ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “ይኼ
4171ዘመን የእግዚአብሔር መዓት ከሰማይ የወረደበት”
4172ዘመን ነው ብለውታል፡፡ ይህንን ዘመን ሕዝቡ፣ “የክፉ
4173ቀን” እያለ ሲጠራው፣ ሰብዓዊ ቀውሱ የትየሌሌ
4174ነበር፡፡ ገጣሚው እንዲህ ሲል ገልፆታል፤
4175በዚህ ወቅት ነበር የሞጃ ቤተሰብ ግንባር ቀደም
4176መሪ የነበሩት ደጃች ገርማሜ ለክፉ ቀን ብለው
4177ያከማቹትን እህልና የዘር ሰብል ለሕዝቡ በነፃ
4178የደሉት፡፡ በትውልድ አጥቢያቸው የነበሩትም
4179አለቃ ገብረሃናም ፍትሐ ነገሥቱ በሚያዘው
4180መሠረት፣ ቤተ-ክርስቲያኗ ያከማቸችውን እህልና
4181ገንዘብ አውጥተው ለምዕመናኑ ያደሉት በዚህ ወቅት
4182ነበር፡፡ የደሰው ቀውስና በኢትዮጵያ ንጉሠ
4183ነገሥት መንግሥት ጠቅላላ አቋም ላይ የፈጠረው
4184ጫና እጅግ መራራ ነበር፡፡ ነገር ግን በንጉሠ
4185ነገሥቱ ቆራጥ አመራርና በነበሯቸው ቆፍጣና
4186ባለሟሎች ብርቱ ትጋት 1886 እና 87ዓም እንዳያልፉት
4187የለምና አለፈ፡፡ ጣሊያንም በነዚህ ሁለት ዓመታት
4188ውስጥ እንደፍልፈል እየተሳበ ከመረብ ምላሽ
4189ወደሰሜንና ደቡብ ትግራይ አቅጣጫ መስፋፋት ጀመረ፡፡
4190ይህንን ዘመን በአኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ
4191ጥንካሬያችን እጅግ የተፈተንበት ጊዜ ነበር፡፡
4192ከዚህ ዘመን ጋር የሚስተካከሉ ታሪካዊ ወቅቶች
4193ካሉም የአህመድ ግራኝ ዘመንና የ1928-1933ዓም
4194የነበረው የወረራ ዘመናት ናቸው፡፡
4195ያም ሆኖ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እልህ
4196አስጨራሽ ትግልና የአደጋ መከላከል ሥራ ሲከናወን
4197ቆየ፡፡ በመሆኑም፣ ያለማንም ወዳጅ አገር ርዳታና
4198ምጽዋት የሞተው ሞቶ፣ ያለቀውም ከብትና እንሰሳት
4199ሁሉ በየፈፋው ቀርተው በ1887ዓም የበረከት ተስፋ
4200ፈነጠቀ፡፡ በሚያዝያ 1887ዓም ንጉሠ ነገሥቱ
4201ራሳቸው ዶማና አካፋ ይዘው ለበልግ እርሻ ወጡ፡፡
4202ባለሟሎቻቸውና መሳፍንቱም የእረሳቸውን
4203አርዓያነት ተከተሉ፡፡ በ1887ዓም ገበሬው አረሰ፤
4204ነጋዴው ነገደ፤ ሸማኔውም ሸመነ፤ ቀጥቃጩም
4205ብረቱን አዘበጠ፤ ወታደሩም ወኔው ተንተገተገ፡፡
4206የኢትዮጵያውያን የአትንኩኝ ባይነት መንፈስ
4207እንደገና ታደሰ፡፡ “ክፉ ቀን” ኢትዮጵየውያንን
4208ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ
4209አንድ አደረጋቸው፡፡ የጣሊያን መንግሥት
4210ሊጠቀመው የሞከረውን ያረጀና ያፈጀ የሮማውያን
4211ከፋፍለህ-ግዛ ስልት መልበስ ተጀመረ፡፡ ለዚህ
4212ደግሞ የግንባር ቀደምነቱን ሚና የተጫወቱት የአፄ
4213ዮሐንስ ልጅ ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው፡፡ ቀጥ
4214ብለው አዲስ አበባ አፄ ምኒልክ ዘንድ መጥተው
4215በብሔራዊ ጥቅምና በሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ ወዛና
4216ፈዛዛ እንደማያሳዩ አረጋገጡ፡፡ ቪቫ ራስ
4217መንገሻ!
4218ቪቫ-ቪቫ!
4219
4220ሌላም መታወስ ያለበት ነጥብ አለ፡፡ የአድዋን
4221ድል ተከትሎ ስለመጣው የኢትዮጵያ ወሰን ጉዳይ
4222ነው፡፡ በግንቦት 1889ዓም ጣሊያኖቹ ከአፄ ምኒልክ
4223ጋር ስለወሰን ጉዳይ እንዲነጋገር ኔራዚኒ
4224የተባለውን መልዕከተኛ ላኩት፡፡ አፄ ምኒልክ
4225ራሳቸው፣ በአንድ ካርታ ላይ የኢትዮጵያን ወሰን
4226አስመልክተው መስመር አሰመሩና ማስመሩም ላይ
4227ማኅተማቸውን አድርገውበት ሲያበቁ፣ “የኢትዮጵያ
4228ወሰን ከዚህ እስከዚህ ድረስ ነው፤” ብለው
4229ለኔራዚኒ ሰጡት፡፡ ከሁለት ወራት በኋላም
4230የጣሊያን መንግሥት የአፄ ምኒልክን የወሰን ካርታ
4231እንደተቀበለው አስታወቀ፡፡ ሆኖም፣ አፄ ምኒልክ
4232አንድ ትልቅ ስኅተት ሠሩ፡፡ ለኔራዚኒ ካርታውን
4233ሲሠጡት ለራሳቸው ቅጂ አላስቀሩም ነበር መክሸፍ
4234እንደኢትዮጵያ ታሪክ ፤ ገጽ 148፡፡ ከዚህም ጊዜ
4235ጀምሮ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ወሰን
4236በሰሜን-ከኤርትራ፣ በምስራቅ ከሶማሊያ እና
4237በምዕራብም ከሱዳን ጋር እንደላስቲክ እንዳንዴ
4238ሲሳብ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲሰበሰብ አንድ መቶ አስራ
4239አምስት አመታት ተቆጠሩ፡፡
4240የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በ1999 ዓም
4241ባሳተመውና፣ ፊሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም
4242“የሕይወቴ ታሪክኦቶባዮግራፊ ” ብለው በጻፉት
4243መጽሐፋቸው በገጽ-73 ላይ እንደገለጹት፣ “ራስ
4244መኮንንና አፄ ምኒልክ በዘመናቸው የሠሩት ሥራ
4245የሚደነቅ ነው፡፡ ነገር ግን፤ ስህተታቸውን
4246አውሮፓ ለትምህርት ከሔድኩ በኋላ እየገመትኩት
4247መገረሜ አልቀረም፡፡ ይሁን እንጂ፣ የዚያን ጊዜ
4248ዕውቀትና ኃይል በማነሱ ይቅርታ ሊደረግላቸው
4249የተገባ ነው፡፡ እነሱ በደከሙበት ሥራ ብዙ
4250ተጠቅመናል፡፡ በስህተታቸውም አደጋ
4251ተቀብለንበታል፡፡ …የጣሊያን መንግሥት በዐዱዋ
4252ጊዜ ዕውቀቱም ኃይሉም ትንሽ ነበር፡፡ …በእኛ
4253ስህተት አገር-በጁ እንደሆነ ስለቀረ ኤርትራን
4254ማለታቸው ነው፤ ሃምሳ ዓመታት ያህል ቆይቶ
4255ተሰናዳና አጠቃን፤…
4256” ሲሉ እርር ድብን ይላሉ፡፡ ከፍ ብለውም፣ “ዐዱዋ
4257ላይ ያን ያህል ሰዎች ተላለቁና፣ ጣሊያን
4258የወሰደብንን አገር ሳናስለቅቅ ሄድን፡፡…የድሉን
4259ዋጋ ዐዱዋ ከራስ መኮንን ጋር በዘመትኩ ጊዜ
4260ለመገመቻ የሚሆን ዕውቀት አልነበረኝም፡፡ ኋላ፣
4261በአውሮፓ መማር ከጀመርኩ በኋላ ግን
4262እያስታወስኩት እንደ እሳት ያቃጥለኝ ጀመር፡፡”
4263እያሉ ስለዐዱዋ ድልና ጥሎት ስላለፈው ጠባሳ
4264ይገልጻሉ፡፡
4265ከዚህ ቀደም የፃፍኩት ቢሆንም፣ በውስጥም ሆነ
4266በውጪ የምኒልክን ያህል መስፈሬ-ግርማ የተጎናጸፈ
4267መሪ የለም፡፡ የፈረንጅን ጦር በአዱዋ ጦር ሜዳ
4268ላይ ድል መትቶ፣ ከፈረንጅ መንግሥት ጋር
4269በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የዕርቅና የሰላም ውል
4270የተዋዋለ አፍሪካዊ መሪ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ብቻ
4271ናቸው፡፡ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ ጥበብም
4272ያስመዘገቡት ድል ከአዱዋው ድል ያልተናነሰ ነው፡፡
4273አራቱ የአውሮፓ ኃያላን ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣
4274ጀርመንና እንግሊዝ ኢትዮጵያን ሊቀራመቷት
4275አሰፍስፈው በነበረበት በዚያ ቀውጢ ወቅት፣
4276ከቅኝ-ግዛት ቅርምት የታደጋት የአዱዋው ድል ብቻ
4277አይደለም፤ የንጉሡ የዲፕሎማሲና የፖለቲካም
4278ጥበብ ነው፡፡ አንዱን በማባበል፤ ሌላውን
4279በማስፈራራት፤ የአንዱን የጥቅም ዝንባሌ አጢኖ
4280ከሌላው ግብዝ ጋር በማጋጨት እርስ-በርስ
4281እንዲፋጠጡ በማድረግ የአራቱንም ኮሎኒያሊስቶች
4282ፖሊሲ እንዳይስማማ አድርገውታል፡፡ ዘንድሮም
4283ደግመን፣ ቪቫ ኢትዮጵያ!
4284ቪቫ ምኒልክ!
4285ልንል እንወደለን፡፡…መልካም የአዱዋ የድል
4286በዓል ይሁንልን፡፡
4287 በ አዲስጉዳይ መጽሔት፣ በቅጽ 8 ቁጥር 205፣ ቅዳሜ
4288የካቲት 22፣ 2006 ዓም ዕት ም ላይ የወጣ ነው፡፡
4289የኢትዮጵያና የአፍሪካ አኅጉር መናገሻ ከተማ
4290በሆነችው በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ሃውልቶች
4291መካከል፣ አምስቱ በኢትዮጵያና በኢጣሊያን
4292መካከል በ1886ዓም እና በ1928-1933ዓም ለተደረጉት
4293ጦርነቶች የድልና የግፍ መታሰቢያ የታነጹ ናቸው፡፡
4294አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘው “የአዱዋን ድል”
4295የምንዘክርበትና አራት ኪሎ አደባባይ ላይ የቆመው
4296“የሚያዝያ 27ን የነፃነትና የድል በዓል”
4297ለመዘከር የቆሙ ሁለት ሃውልቶች ናቸው፡፡ ከዚህም
4298ሌላ ለገሀር የሚገኘው “የይሁዳ አንበሳ” ሃውልት
4299ደግሞ በፋሺስት ኢጣሊያን በ1928ዓም ዘርፎ ተወስዶ
4300የነበረና፣ በጥቅምት 231955ዓም እንደገና ተመልሶ
4301የቆመ ነው፡፡ አሁን በባቡር መስመር ግንባታ
4302ሰበብ የተነሳውና በአምስት ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም
4303ውስጥ የቆመው የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልትም
4304አራተኛው ማሳያ ነው፡፡ አምስተኛውና በቁመት
4305ከሁሉም ጠሚበልጠው ደግሞ፣ በ1951ዓም
4306በዩጎዝሎቫያው ፕሬዝዳንት ማርሻል ዴኒስ ቲቶ ልዩ
4307ድጋፍ እንደገና የቆመው የስድስት ኪሎው “የየካቲት
430812ቱ ሰማዕታት” መታሰቢያ ሃውልት ነው፡፡ ሁለት
4309የድል ማብሰሪያ ሃውልቶች፣ እና ሦስት የመከራና
4310የእልቂት መዘከሪያ ሃውልቶች ቆመዋል፡፡ በዛሬው
4311መጣጥፋችንም ስለዚህ ስለአምስተኛው ሃውልትና
4312ሊዘክራቸው ስለቆመው በመቶ ሺዎች ሲለሚቆጠሩት
4313ሰማዕታት ይሆናል፤ መልካም ንባብ
4314እንደሚሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
4315የካቲት 12 ቀን 1929ዓም የዋለው በዕለተ ዓርብ ነበር፡፡
4316ሩዶልፎ ግራዚያኒ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ረፋድ 4፡00
4317ሰዓት ላይ፣ ከቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ መልስ
4318በገነተ-ልዑል ቤተ መንግሥት ፊት-ለፊት የዛሬው
4319የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ካምፓስ ፏፏቴው
4320ጋር ነው፤ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፡፡ ለነዲያንና
4321ለችግረኞችም ለእያንዳንዳቸው ሁለት-ሁለት ሊሬ
4322እንደሚሰጥ ጭምር አስለፈፈ፡፡ ነገር ግን፣ “ልክ
4323በ4፡00 ሰዓት ይጀምራል” የተባለው ፕሮግራም እስከ
43244፡55 ድረስ ሳይጀመር ቀረ፡፡ ሰበቡም የግብፃዊው
4325አቡን፣ አቡነ ቄርሎስ፣ “ታምሜያለሁ!
4326” ብሎ በመቅረቱበመዘግየቱ የተነሳ ነበር፡፡
4327እስኪመጣም ድረስ የዕለቱ መርሃ-ግበር ለአንድ
4328ሰዓት ያህል ዘገየ፡፡ ወታደሮች ተላኩና አበኑ
4329ልክ 4፡55 ሲሆን ቤተ መንግሥት ደረሰ፡፡ ወንበር
4330መጣለትና ከግራዚያኒ በስተቀኝ በኩል፣
4331ከከፍተኛዎቹ የፋሺስት ባለስልጣናትም ጎን
4332ተቀመጠ፡፡ ከግራዚያኒም በስተግራ በኩል ጄኔራል
4333ጋሪባልዲ፣ ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ የአፄ
4334ዮሐንስ የልጅ-ልጅ፣ ራስ ኃይሉየጎጃሙ ንጉስ
4335ተክለ ሃይማኖት ልጅ እና ከሌሎች ባንዶችም ጋር
4336ተጎልቶ ነበር፡፡ ልክ 5፡00 ሲል ግራዚያኒ ሻኛው
4337እንዳበጠ ኮርማ ቁና-ቁና እየተነፈሰ
4338ኢትዮጵያውያንን ያበሻቅጥ ጀመር፡፡ “ይኼው
4339አለሁ!
4340
4341ሞቷል እያላችሁ የምታወሩትና የምታስወሩት ኹሉ
4342ከንቱ ሟርት ነው፡፡” እያለ የኢትዮጵያን ሕዝብ
4343በገዛ አገሩና በገዛ መሬቱ ላይ ያዋርደው ጀመር፡፡
4344ግራዚያኒና ተባባሪዎቹ የነበሩበት ቦታ ወደ ራስ
4345መኮንን አዳራሽ መግቢያ በር ላይ ያለው-የቤተ
4346መንግሥቱ በረንዳ ላይ እንደነበር ልብ ይሏል፡፡
4347ልክ 5፡15 ሰዓት ገደማ ሲሆን አብራሃ ደቦጭና ሞገስ
4348አስገዶም የተባሉት ሁለት የኤርትራ ክፍለ-ሀገር
4349ተወላጆች ከበረንዳው በላይ ባለው ፎቅ ላይግራዚያኒ
4350ከቆመበት ሥፍራ ላይ ጥቁር ሸሚዝ ፋሺስቶች
4351ለባንዶች ያለብሱት የነበረውን ወታደራዊየአስካሪስ
4352ልብስ ለብሰው፣ ኩታቸውን ተከናንበው ታዩ፡፡
4353ዓይኖቻቸው በንቃት ይንተገተጋሉ፡፡ ልክ 5፡30
4354ሲሆንም ለነዲያን ምጽዋት መሠጠት ተጀመረ፡፡
4355በሥፍራው ከሦስት ሺህ ሁለት መቶ 3,200 በላይ
4356ነዲያን ተሰብስበው ነበር፡፡ እንዲሁም
4357ግብር-ሊበሉ የመጡ በርካታ የአዲስ አበባ
4358ነዋሪዎችም ግራዚያኒና ግብረ-አበሮቹ ከቆሙበት
4359ስፍራ በአሥር ወይም አሥራ ሁለት ሜትር ርቀት ላይ
4360ከበው ቆመዋል፡፡ ከሰዎቹም ፈንጠር ብለው ከዘጠና
4361የማያንሱ መትረየሳቸውን የደገኑ ሶላቶዎችና
4362አስካሪዎች በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ነዲያኑን
4363ከበረንዳው አካባቢ ራቅ እንዲሉ ይገፏቸው ጀመር፡፡
4364ጫጫታና ውካታው ከፍ ብሎም ለአስር ደቂቃዎች
4365ያህል ተሰማ፡፡
4366ነገር ግን፣ ኢያን ካምፔል ; “
4367” ብሎ በ2003ዓም ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ
4368እንደዘገበልን ከሆነ፣ በግምት ከ5፡40 እስከ 5፡45
4369ድረስ ባሉት አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ተከታትለው
4370ቦንቦች እነአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም
4371ካሉበት ደርብ ላይ ቁልቀል ተወረወሩ፡፡
4372የመጀመሪያው ቦንብ እንደተመረወረ፣ ብዙዎቹ
4373ታዳሚዎች ለስብሰባው ማድመቂያ መድፍ የተተኮሰ
4374ነበር-የመሰላቸው፡፡ ሁለተኛው ሲወረወር ግን፣
4375አቡነ ቄርሎስና ግራዚያኒ መሬት ያዙ፡፡
4376በስተ-ግራ በኩልም ያሉት ሁለት ጥበቃዎች
4377ወዲያውኑ ሞቱ፡፡ ሦስተኛውም ሲወረመር፣
4378ግራዚያኒ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሊገባ ፊቱን አዙሮ
4379መሸምጠጥ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም፣ የሦስተኛው
4380ቦንብ ፍንጣሪዎች አቆሠሉት፡፡ ዳኒሎ ብቢሪንዴሊ
4381የተባው የካሜራ ባለሙያም እየደማና እያቃሰተ
4382የነበረውን ግራዚያኒን ከወደቀበት አንስቶ፣ ከ5፡50
4383እስከ 6፡00 ባሉት አስር ደቂቃዎች ውስጥ ወደ
4384መኪናው ከተተው፡፡ በፍጥነት ወደ “ኦስፒዳሌ
4385ኢታሊያኖ” “የጣሊያ ሆስፒታል” ለማለት ነው፤
4386የዛሬው “ራስ ደስታ ሆስፒታል” መሆኑን ልብ
4387ይሏል፤ ወሰዱት፡፡
4388ከየካቲት 12 ቀን 1929ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓትም ጀምሮ
4389እስከ የካቲት 14 ቀን 1929 ዓም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት
4390ድረስ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በግፍ
4391ተፈጁ፡፡ የሚነገረው ቁጥር በአዲስ አበባ ብቻ
4392የተፈፀመውን ግድያ የሚያሳይ ብቻ ነው፡፡ በደብረ
4393ሊባኖስ ገድምና በዝቋላ አቦ የተረሸኑትም
4394መነኮሳትና ምዕመናን እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በ1934ዓም
4395የመጀመሪያው የየካቲት 12ቱ ሰማዕታት መታሰቢያ
4396በዓል በተከበረበት ዕለት የወጣው የአዲስ ዘመን
4397ጋዜጣ ክስተቱን እንዲህ ሲል ነበር የዘገበው፤ “ያቺን
4398ቀን እናስባት፤ አንርሳት፡፡ የኢትዮጵያ
4399ሰማዕታት የክብር አክሊል የተቀበሉባትን፣
4400ደማቸው እንደጎርፍ በግፍ የፈሰሰባትን፣ ሥጋቸው
4401እንደክትፎ የተከተፈባትን፣ አጥንታቸው
4402እንደገል የተከሰከሰባትን፣ ዕለተ-ዓርብን፣
4403ያቺን ቀን አንርሳት!
4404
4405መቼም የዕለተ-ዓርብ መከራና ሃዘን ማለቂያ
4406የለውም!
4407አስቀድሞ፣ ንጹሑ ክርስቶስስ በዕለተ-ዓርብ በ33ዓም
4408አልነበር የተሰቀለው!?
4409የካቲት 121929ዓም ደግሞ ሁለተኛው የንጹኃን ደም
4410በከንቱ የፈሰሰበት ዕለት ኾነ፤” እያለ ይቀጥላል፡፡
4411ይህ በእንዲህ ሳለም፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት
4412መንግሥት፣ በፋሺስት ኢጣሊያ ስላለቁት
4413ወገኖቻችንና ስለደም ካሳቸው በተመለከተ ጥያቄ
4414ማቅረብ የጀመረው ከ1936ዓም ወዲህ ነው፡፡
4415ጥያቄውን የበለጠ ፖለቲካዊና ዓለማቀፋዊ ይዘት
4416እንዲኖረው አድርጎ፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ
4417ወደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተቀየረበት
4418የመጀመሪያው ዓመት ላይ፣ በ1938ዓም የኢትዮጵያ
4419መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ሦስት ጥያቄዎችን
4420አቅርቦ ነበር፡፡ “አንደኛ፣ ለኢጣሊያ ፋሺስታዊ
4421መንግሥት ወረራ መነሻ የሆኑት ጥንታዊ
4422ክፍለ-ሀገሮች ኤርትራና ሱማሊያ፣ ለኢትዮጵያ
4423እንዲመለሱላት፤ ” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛ፣ “ለተቃጠሉት
4424አብያተ-ክርስቲያናት፣ ለተበረበሩትና
4425ለተዘረፉት ንዋየ-ቅዱሳት፣ ለተደመሰሰው
4426የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብትና ንብረት፤ ከሁሉም በላይ
4427ደግሞ በግፍ ለተሰውት ከ750ሺህ በላይ ንጹኃን
4428ኢትዮጵያውያን ሕይወት፣ የኢጣሊያን መንግሥት
4429ካሳ እንዲከፍል ፤” የሚጠይቅ ነበር፡፡ ሦስተኛው
4430ጥያቄ ደግሞ፣ “በኢትዮጵያ ለተፈጸሙት ወንጀሎች
4431ኹሉ ዓብይ አርእስት ሆኖ የሚገመተው በግራዚያኒ
4432መሪነት የተፈፀመው የየካቲት 121929ኙ ዓም ዕልቂት፣
4433ከማናቸውም የፋሺስት የግፍ ሥራዎች ኹሉ
4434ከፍተኝነትና ኢ-ሰብዓዊነት ስላለውም፣ ጭፍጨፋው
4435እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት የጦር አዛዦችና
4436ግብረ-አበሮቻቸው በሙሉ፣ ፍርዳቸውን ግፉን
4437በሰሩበት ቦታ እንዲቀበሉና ግፉ
4438ስለተፈፀመባቸውም ወገኖቻችን የደም ካሳ
4439እንዲከፈል ፤” የሚጠይቅ ነበር፡፡ በኹሉምበሦስቱም
4440ጥያቄዎች ውስጥ ገኖ የሚታየው ጥያቄ፣ “የጥቁሮቹ
4441ሰማዕታት” ጩኸት ነው፡፡
4442ሆኖም ግን፣ በሚያዝያ 191940ዓም ኢትዮጵያ ያ ን
4443ጊዜ፣ በምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ
4444በነበሩት-ክቡር አቶ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ
4445አማካይነት ያቀረበችው አቤቱታ ተቀባይነት
4446አግኝቶ ነበር፡፡ ይህንም ውሳኔ
4447እንደኔዘርላንድና ኢራን የመሳሰሉት አገሮች
4448በፓርላማዎቻቸው አቅርበው አጸድቀውታልም፡፡
4449ነገር ግን፣ የኢጣሊያና የሮማንያ መንግሥታት
4450ባቀረቡት ይግባኝ መሠረት፣ ለመንግሥታቱ ዋና
4451ፀሐፊ ባስገቡት ማመልከቻ መሠረት፣ ጉዳዩ
4452እንደገና እንዲመረምር ተደረገ፡፡ ከዚያንም ጊዜ
4453ጀምሮ፣ እስካለንበት ዘመን ድረስ እንደተዳፈነ
4454ነው፡፡ ይባስም ብሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ጭፍጨፋው
4455እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት የጦር አዛዦችና
4456ግብረ-አበሮቻቸው በሞላ የጦር ወንጀሉን
4457በፈጸመበት ቦታሀገር ፍርዳቸውን መቀበል
4458ይገባቸዋል፤” ብሎ ያመለከተውን እግዚኦታ
4459ከቁብም ሳይቆጥሩ፣ ለዚያ የተኩላ ልጅ የሚላኑ
4460መስፍን ብለው ሃውልት አቆሙለት፡፡ ይህ አባዜ፣
4461የነጩ ዓለም ለጥቁሮች ያለውን ከፍተኛ ንቀትና
4462መዘባበት የሚያሳብቅ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት
4463ግዙፍ እውነት ከፊታችን ተገትሯል፡፡ እርሱም
4464የያንኪዎቹና የያፌታውያኑ ናላ፣ ለእኛ
4465ለካማውያን ወንድሞቹ ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ
4466ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ በተከታዮቹ አንቀፆች
4467አማካይነት ላብራራው እወዳለኹ፡፡
4468ነገር ግን፣ የቦሲኒያውና የሄርዞ-ጎቪኒያው ጉዳይ
4469ሲመጣ ሌላ ሽፋን ይሰጡታል፡፡ የሃይማኖት
4470መለያየት የፈጠረው ጣጣ እንደሆነ ሊሰብኩን
4471ይጣጣራሉ፡፡ አለያም ደግሞ የርዕዮተ-ዓለም
4472ግጭቶች ጣጣ ውጤት እንደተፈጠረ አድርገው
4473ሊያሳምኑን ይፍጨረጨራሉ፡፡ ይህ ዘረኛና
4474ከያፌታዊ ትምክህት የመነጨው አስተሳሰብ ነው፤
4475በተለያየ ዘመን በከንቱ የተሰውትን ጥቋቁር
4476ሰማዕታት ደመ-ከልብ ያደረጋቸው፡፡ በየትም ቦታ
4477ጥቁሮች ለያፌታውያንና ለአንዳንድ ቡርዣ
4478ሴማውያን አሽከርና አገልጋይ ሆነው የምጽዓት ጊዜ
4479እንዲደርስ ይፈለጋል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችልበት
4480መጠነኛ እድልም አለው፡፡ የካም ቤት ተከፋፍሎና
4481ተበታትኖ ነው ያለው፡፡ ታላቁ ንጉሠ ነገሥታችን
4482አፄ ኃይለ ሥላሴና እነአቶ ከተማ ይፍሩ
4483የተለሙትን አፍሪካንና መላውን የጥቁር ህዝብ
4484አስተባብረን እንዲረዳዳ ማድረግ ካልቻልን
4485ያፌታውያኑ እንደልባቸው ይፈነጩብናል፡፡
4486አንዳንድ ሴማዊ ቡርዣዎችም፣ እንደባሪያ ፈንጋይ
4487እየሆኑ፣ ሴቶቻችንን ለጭን-ገረድነት፣
4488ወንዶቻችንንም ለዘበኝነት ይዳርጓቸዋል፡፡ እንዳጋጣሚ
4489ሆኖ፣ በአሜሪካንም-ይህ ወር የጥቁሮች ወር ነው፡፡
4490በአፍሪካ ደግሞ ትልቁ የጥቁር ህዝብ ድል
4491የተበሰረበት የአዱዋም ድል የሚከበረው በዚሁ ወር
4492ነው፡፡ በተጨማሪም ትልቁ የጥቁር ሕዝቦች
4493ኢ-ሰብዓዊ ጭፍጨፋም የተካሄደበት ወር ነው፡፡
4494በመሆኑም፣ በመላው ዓለም ያሉትን ጥቁሮች፣
4495በከንቱ ስለቀሩት “ጥቋቁር ሰማዕታት” ጋራ
4496ልንጮኽላቸው ይገባናል፡፡
4497በሀገራችን የኖረ አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል
4498ነው፣ “በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል፤
4499ወይም እኩል ነው፤” ይባላል፡፡ የባርነትን ዋጋ
4500ባንቀምሰው ኖሮ፣ የነፃነትን ዋጋና ጣዕምም
4501አናውቀውም ነበር፡፡ በነፃነት ደጃፍ መኖርን
4502የለመደ ሰው፣ ከባርነት ይልቅ ሞትን ይመርጣል፡፡
4503ለኢትዮጵያውያንንና ለመላው የአፍሪካ ጥቁር
4504ህዝቦች የባርነትን ብርቱ ስቃይ ከሚያሳዩት
4505ቀኖችም አንዱ “የየካቲት 12ቱ የጥቋቁር ሰማዕታት”
4506በዓል ነው፡፡ ከሰባ ስምንት ዓመታት በፊት
4507በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመው ግፍ ያዩት
4508ሰዎች እጅግ ነው የሚያንገፈግፋቸው፡፡ የብሔራዊ
4509ነፃነታችን ምልክት የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን
4510በኢትዮጵያና በአፍሪካ አኅጉር መናገሻ ከተማ
4511በማይውለበለብብት በዚያ የባርነት ወቅት፣
4512በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ እንኳን ከሰላሳ ሺህ በላ
4513ይ ዜጎች አልቀዋል፡፡ ሰንደቅ ዓላማችን በግፍ
4514ወርዶ የፋሺስት ባንዲራ ከተካው አስር ወር
4515እንኳን ሳይሞላው፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ኃዘን
4516ሰፍኖ ነበር፡፡ ህዝቡ አቀርቅሮ መሄድ ጀምሯል፡፡
4517ኩራት የለም!
4518እራትም አልነበረም፡፡ አለኝታ የለም፤ ገበያና
4519አደባባይም ወጥቶ በሰላም ለመመለስ ዋስትና
4520አልነበረም፡፡
4521የጥቁር ህዝብ የድል-ብስራት ማወጃ የሆነችው
4522ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በባርነት ሥር ሆነው
4523እጅግ ተሳቀዋል፡፡ በባርነት ስር ያለ ህዝብ
4524ማናቸውም ነገር ሊደርስበት ይችላል፡፡ ቢታሰር፣
4525ቢረገጥ፣ በሰደብ፣ ቢደበደብም ሆነ ቢገደል ለምን
4526ብሎ መጠየቅ አይችልም፡፡ ምክንያቱም፣ በባርነት
4527ቀንበር ሥር ያለ ህዝብ ማናቸውም መዓት
4528ይደርስበታላ!
4529በባርነት ሥር ያለ ህልውና በእርግጥ ምንም
4530ትርጉም የለውም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በነፃነት
4531መኖር ሕይወታችን ነው፡፡ ኑሯችን ነው፡፡
4532በነፃነት መሥራት፣ በነፃነት ማሰብ፣ በነፃነት
4533መማርና በነፃነት መብትን የማስከበር ልዩ
4534ትዕምርት አለን፡፡ ልዩ ባሕልም አለን፡፡ እነዚህ
4535ከሌሉ ሕይወታችን የለችም፡፡ “ያለነፃነት
4536የምንኖር ከሆንን፣ እንደሮቦት የምንንቀሳቀስ
4537ሕቁራን ፍጡሮች ነን፤” ማለት ነው፡፡
4538ከዚህ ሕቁርነት ሰውሮን፣ የጥቁሮቹን ሰማዕታት
4539ደም ሕያው ለማድረግ ያብቃን!
4540
4541የኢትዮጵያ ወጣቶች በሦስት መስቀለኛ መንገዶች
4542ላይ ቆመዋል፡፡ የመጀመሪያው መንገድ ከባህልና
4543ከልማድ የተወረሰ ነው፡፡ ዘፈን፣ ቀረርቶና
4544ሽለላም አለው፡፡ አፋሩ፣ “ዳሀር ቦር ናሬ!
4545” ይላል፡፡ “ግመሎቼና ከብቶቼ፣ እውጪ ማደር
4546ልማዳችሁ ነው፤ እኔም እንደናንተ ጠላቴን
4547ሳመነዥገው ደጅ-አድራለሁ!
4548” እያለ ይዘፍናል፡፡ ኦሮሞውም፣ “አቢቹ ነጊያ
4549ነጊያ!
4550” የሚል ዜማ አለው፡፡ የወንድሞችህን ገዳዮች
4551አሰቃይተህ እስከምትገላቸው ድረስ፣ እንቅፋትም
4552አይንካህ!
4553ድል-በድል ያድርግህም!
4554” የሚል መልዕክት አለው፡፡ የአማርኛ ተናጋሪውም
4555ቢሆን፣ “ጥራኝ ደኑ!
4556ጥራኝ ዱሩ!
4557
4558ላንተም ይሻልሃል ብቻ ከማደሩ!
4559” እያለ ይሸልላል፡፡ ይህ የሚሆነው እንግዲህ
4560ወጣቱ ያኮረፈ ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱ ሊለያይ
4561ይችላል፤ ነገር ግን፣ ወጣቱ ኩርፊያውን ለመግለጽ
4562የሚጠቀምበት ባህላዊ መንገድ “ሽፍትነትን”
4563ነበር፡፡ አብዛኞቹም ሽፍቶች በአካንዱራ በባህላዊ
4564የጦር ስልት የተካኑና የተፈጥሮ አደጋዎችን
4565መቋቋም የሚችል ተክለ-ሰውነት ነበራቸው ፡፡
4566የቤተ-ክህነትም ሆነ የዘመናዊ ትምህርት የላቸውም፡፡
4567ዛሬ ላይ፣ ይሄን ባህልና ልማድ ጠብቆ ለመሄድ
4568የሚያመች ነባራዊ ኹኔታ የለም፡፡ ደኖች
4569ተጨፍጭፈዋል፤ ተቃጥለዋልም፡፡ በሌላም በኩል፣
4570የዘመናዊ ትምህርትና የዘመናዊ አኗኗር ዘይቤዎች
4571ወጣቱ ባህልና ልማዱን ተከትሎ እንዳይሄድ ደንቃራ
4572ሆነውበታል፡፡
4573ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች በሚ ሰ ባሰቡባቸው
4574የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ኮሌጆች፣ እንዲሁም
4575በሀገር ውስጥና በውጪም ሀገራት ጎዳናዎች ላይ
4576ተቃውሞአቸውን የማሰማት አማራጭን መጠቀም
4577ጀምረዋል፡፡ ነገሩ፣ በ19456 ዓም ከኮሪያ ዘመቻ
4578በተመለሱ የክብር ዘበኛ ወጣት መኮንኖችና በቀ
4579ኃሥ ዩኒቨርሲቲ-ኮሌጅ ተማሪዎች አማካይነት
4580እንደተጀመረም ይታወቃል፡፡ ዛሬ ላይ ግን፣
4581ከኢትዮጵያ ዳር ድንበሮችም አልፎ በወጪ አገራት
4582በሚገኙ የአትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትም ዘንድ
4583ተንሰራፍቷል፡፡ “ጥራኝ ደኑ!
4584ጥራኝ ዱሩ!
4585” በሚለው ሽለላ ምትክ፣ “ጥራኝ ጎዳናው!
4586ጥራኝ መንገዱ!
4587” ወደሚል ተሸጋግሯል፡፡ ለምን?
4588ከላይ እንደጠቀስነው፣ የደኑ መጨፍጨፍና መቃጠል፣
4589የወጣቱ በዘመናዊ ትምህርት እያደገ መሄድ፣
4590የዓለም አቀፉ ተጽዕኖ እያደገ መሄድ፣ የግለኝነት
4591ንቃተ-ህሊና መጎልበትና የተከታታይ ሥርዓቶች
4592ያሰረፁት ፍርሃት ቦቅቧቃነት-
4593ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገጣሚው ኃይሉ ገብረ ዮሐንስን ከ1958-66ዓም
4594ድረስ፣ “ኧረ!
4595የወንድ ያለህ!
4596” እያለ ያስጮኸው ይኼው የወንድየወኔ ዕጦት ጣጣ
4597ወጣቱ አካባቢ “ስላጣ” ነበር፡፡ ያም ሆኖ፣
4598ዛሬ-ዛሬ፣ “ጥራኝ ጎዳናው!
4599ጥራኝ መንገዱ!
4600” የሚለው የወጣቶች እንቢተኝነት፣ ከአረቦቹ
4601የፀደይ አብዮት በኋላ የሚጠበቅ ነው ፡፡
4602በሦስተኝነት የሚመጣው አማራጭ የወጣቶች ብሔራዊ
4603እንቢተኝነት የሚገለጽበት መንገድ ደግሞ
4604ሽብርተኝነት ነው፡፡ ይህንን መንገድ ለመከተል
4605የሚያመች ነባራዊ ሁኔታ የለም የሚሉ በርካታ
4606ኢትዮጵያውያን አጋጥመውኛል፡፡ በግንባር
4607ቀደምትነት የሚመጡት ፕር መስፍን ወማርያም
4608ናቸው፡፡ የእርሳቸውን ንግግሮችም የሚጋሩ
4609በርካታ የግል መገናኛ ብዙኃን ፀሐፍትና
4610አዘጋጆችም አሉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ባላጋራ
4611መሪዎችምተቀናቃኝ የፖለቲካ ማኅበሮችም ከፕር
4612መስፍን አባባል ጋር ይስማማሉ፡፡ “የገዢው ፓርቲ
4613መሪዎችና ካድሬዎች፣ ይኼንን ከኢትዮጵያውያን
4614ባህልና ልማድ ጋር የማይሄድ ቋንቋ የሚጠቀሙት
4615የተቃዋሚ አባላትንና የግል ጋዜጠኞችን ለማሰርና
4616ለማሸማቀቅ እንዲያመቻቸው ብለው ነው፤” ሲሉም
4617ይከራከራሉ፡፡ በእርግጠኝነትም፣
4618የእነአንዱዓለም አራጌንና የርዮት ዓለሙን እስር
4619ከዚህ ጋር ያገናኙታል፡፡ በ198990 ላይ ተደርገው
4620የነበሩትንም የነዶር ታዬ ወሰማያትና የሌችንም
4621የፖለቲካና የሙያ ማህበራት መሪዎች የእስር ሂደት
4622ያወሳሉ፡፡ በብያኔውና በትርጓሜው ላይ
4623ብንስማማም-ባንስማማም “ሽብርተኝነት”
4624የኢትዮጵያ ወጣቶች ሊሳቡበት ከሚችሉበት
4625የእንቢተኝነት መንገዳቸው አ ን ዱ ነው፡፡ በእርግጥ!
4626አለ ወይስ የለም?
4627የሚለውን ክርክር ለየቅላን ብንተወው ይሻላል፡፡
4628እስካሁን የተነጋገርንባቸውን ሦስት ሃሳቦች
4629በሌላ ቋንቋ መነጋገር አስፈላጊ ነው፡፡ ከቅርብ
4630ጊዜ ወዲህ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች የተቃውሞና “የአልገዛም
4631ባይነት” እንቅስቃሴዎችን በተጠናከረ ኹኔታ
4632እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ እንቅስቃሴዎቻቸውም ሦስት
4633ዓይነት መልኮችን በመያዝ ላይ ናቸው፡፡
4634የመጀመሪያው የጎዳና ላይ ትዕይንተ-ተቃውሞ ነው፡፡
4635መነሻውም-መድረሻውም ሰላማዊ እንደሆነ
4636እናውቃለን፡፡ በዋናነት በከፍተኛ የሁለተኛ
4637ደረጃ ትምህርት ቤቶችና፣ በከፍተኛ የትምህርት
4638ተቋማት ውስጥ ይታይ ነበር፡፡ ከዓመት ከመንፈቅ
4639ወዲህ ደግሞ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥ
4640የማይናቅ አቅም አጎልብቷል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፣
4641የሽምቅ ውጊያ ይዘት አለው፡፡ ላለፉት ሠላሳ
4642ዓመታት ገደማ የኦሮምኛ፣ የሶማሊኛና የአፋርኛ
4643ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በእጅጉ
4644ሲለፉበትና ሲደክሙበት ቆይተዋል፡፡ የትግራይና
4645የኤርትራ ወጣቶችም በዚሁ ዓይነት መንገድ “ናጽነት”
4646አገኘን ብለዋል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ፣
4647ይሄው የሽምቅ ውጊያ የርስ-በርስ ጦርነት
4648አዝማሚያ ወደ ጋንቤላ፣ ወደ ደቡባዊት ኢትዮጵያና
4649ወደ አማርኛ ተናጋሪ-ወጣቶችም ዘንድ ተዛምቶ
4650ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ባብዛኛው የኢትዮጵያ
4651ገጠራማ ክፍሎች ውስጥ መታየት ጀምሯል፡፡ የአኙዋክ
4652ወጣቶች ንቅናቄ አወን፣ የደቡብ ወጣቶች የጋራ
4653ንቅናቄ ደወጋን፣ እና የአማራ ወጣቶች የጋራ
4654ንቅናቄ አወጋን የሚባሉት ካለፉት ሦስት ዓመታት
4655ወዲህ የተመሠረቱ “ወጣት-ተኮር” ድርጅቶች ናቸው፡፡
4656በሦስተኛው ዓይነት የኢትዮጵያ ወጣቶች
4657ተቃውሞአቸውንና “ያልገዛም ባይነታቸውን”
4658የሚገልጹበት መንገድ በኅቡዕ የመደራጀት አማራጭ
4659ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አደረጃጀት
4660መነሻውም-ሆነ-መድረሻው ምስጢራዊ ነው፡፡
4661ሄዶ-ሄዶም፣ የራሱን የመገናኛ ኮድና የራሱን
4662ጠንካራ የሰው ኃይል አደራጅቶ ወደ
4663ሽብርተኝነት ያድጋል፡፡ በርግጥ!
4664ብዙዎች “የኢትዮጵያ ህዝብ የባህል፣
4665የሃይማኖትና የማኅበራዊ ኹኔታ ለዚህ አደረጃጀት
4666ለሽብርተኝነት ኔትዎርክ የሚመች አይደለም”
4667ይላሉ፡፡ ከዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች መካከልም ፕር
4668መስፍን ወማርያም ይገኙበታል “አደጋ
4669ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” የሚለውን
4670መጽሐፋቸውን መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል
4671ደግሞ፣ ኢትዮጵያን የሽብርተኝነት አደጋ
4672እየተጋረጠባት ነው በማለት፣ ገዢው ፓርቲ
4673ወያኔ-ኢህአዴግም ሁለት አዋጆችን አውጥቷል፡፡
4674አንደኛው “የፀረ-ሽብር ሕግ” አዋጅ ቀጥር 6522001
4675እየተባለ የሚታወቀው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ “ሽብርተኝነትን
4676በገንዘብና ቁሳቁስ መደገፍን የሚከለክል ሕግ” አዋጅ
4677ቁጥር 7802005 ነው፡፡
4678እዚህ ላይ ሊጤን የሚገባው ትልቅ ቁምነገር አለ፡፡
4679እርሱም፣ ሽብርተኝነት ከባህልና ከሃይማኖት፣
4680ብሎም ከፖለቲካ-ኤኮኖሚ ጋር አያይዞ አለመመልከቱ
4681ጥሩ ነው፡፡ ከ1957 ዓም ወዲህ እንዳየነው ከሆነ፣
4682የኢትዮጵያ ወጣቶች አይሮፕላን የመጥለፍም ሆነ
4683የአቬሽን እንቅስቃሴዎችን የማስተጓጎል ባህልና
4684ዝንባሌ አልነበራቸውም፡፡ ግና፣ ከዚያን ጊዜ
4685ጀምሮ እስከ ኮሞሮስ ደሴቶች አካባቢ በግዳጅ
4686እስካረፈው አይሮፕላናችን ድረስ ኢትዮጵያውያኑ
4687ጉዳት የማድረስ አቅምም ክህሎትም እንዳላቸው
4688ታይቷል፡፡ ነገሩ የዓለም ዓቀፉ ትኩሳትም ማሳያ ነጸብራቅ
4689አካል ነው፡፡ በቀላል አማርኛም የየዘመኑን ፋሽን
4690የመከተልም ዝንባሌ ስበት ተደርጎም ሊወሰድ
4691ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን፣ ወደ
4692ሽብርተኝነትና ወደ ኅቡዕ መዋቅሮች ውስጥ ሊገቡ
4693የሚችሉት ወጣቶች ከአንድ ከተወሰነ ሃይማኖት፣
4694የኤኮኖሚ መደብ፣ ከሆነ ዘርብሔር፣ አለያም
4695ደግሞ ከአንድ የማኅበራዊ መድሎ ከደረሰበት ክፍል
4696ብቻ አድርጎ ማሰላሰሉ አያዋጣም፡፡
4697ወደ ሽብርተኝነቱ ጎራ ለመቀላቀል የሚፈልጉ
4698ወጣቶች ካሉ የሚከተሉት ሦስት አማራጮች ምቹ
4699መደላድሎች ይሆኗቸዋል፡፡ 1ኛ
4700የፖለቲካ-ኤኮኖሚው የሚፈጥርባቸው ኩርፊያ ነው፡፡
4701በዚህ በኩል ደግሞ፣ ገዢዎቻችን እንደሚነግሩን
4702ሳይሆን ስር-የሰደደ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ዱካክ
4703ወጣቱን አስኮርፎታል፡፡ መሥራት ከሚችሉት
4704መካከል 45% በመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ወጣቶች
4705ሥራ-አጥ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ
4706ችሎታውና አቅሙ እያላቸው በክልል መንግሥታትና
4707ሹመኞች ፖለቲካዊ በሆነ አድሎና መድሎ
4708ለሥራ-የደረሱ እጆቻቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ
4709ናቸው፡፡ ጉዳይ ፖለቲካዊ በመሆኑና ኢኮኖሚያዊ
4710ተጽዕኖውም ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ ከፍተኛ
4711ኩርፊያን አስከትሏል፡፡ ኩርፊያውም እያደገ ወደ
4712ከባድ የተስፋ መቁረጥን ደረጃ በመድረስ ላይ
4713ይገኛል፡፡ 2ኛው ችግር ደግሞ ከወጣቱ ንቃተ-ኅሊና
4714ጋር የማይሄድ የገዢዎቹ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡
4715ገዠዎቹ “ወጣቱ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢ ነው፤”
4716እያሉ ሲሸነግሉት ኖረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ወጣቱ
4717“የአሁኒቷም ኢትዮጵያ ባለድርሻ ነኝና
4718የሚገባኝን ድርሻዬን አምጡ፤” በማለት ላይ
4719ይገኛል፡፡ የገዢዎቹ “ወደፊት ጠብቁና”
4720የወጣቶቹ “አሁኑኑ አምጡ” ንትርክ ማቆሚያም
4721ያለው አይመስልም፡፡ ስለሆነም አስገድዶ ድርሻን
4722ለመንጠቅ የሽብር አማራጭ ሊከተል ይችላል፡፡
4723ዛሬ፣ ተደራጅተው የልጃገረዶችን ተንቀሳቃሽ
4724ስልኮችና ጌጣጌጦች ከመንጠቅ አልፈው፣ ትልልቅ
4725የኮንተራባንድና የዕጽ-ማዘዋወር ተግባራት ላይ
4726ኔትወርክድ ሆነው ሊደራጁ ይችላሉ፡፡
4727ሦስተኛ3ኛው ነጥብ ደግሞ፣ የወጣቶቹ በዘመን
4728አመጣሽ አስተሳሰቦች መማረክና በባዕዳን ኃሎች
4729የመጠለፍ እድላቸው እያደገ የመሄዱ ጉዳይ ነው፡፡
4730በ1960ዎቹ የነበሩት የኢትዮጵያ ወጣቶች በኮሚኒዝም
4731አስተምህሮዎችና መሪዎች እንደተሳቡት ሁሉ፣
4732ያሁኖቹ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅና በሩቅ
4733ምስራቅ አካባቢ ባሉ የኅቡዕ ድርጅቶችና መሪዎች
4734ሊማረኩ የማይችሉበት ምንም ምክንያት የለም፡፡
4735ይህ የስሜት የ ጉዳይ ነው፡፡ በዚያ ላይ
4736ደግሞ፣ በአሁኑ ሰዓት ድንበር-ዘለል የኅቡዕ
4737ድርጅቶ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጉርሻና ጠቀም ያለ
4738ክፍያን ለወጣቱም ሆነ ለቤተሰቡ ይከፍላሉ፡፡ ይህ
4739ማበረታቻም ከስሜት ድጋፍ ሰጭነታቸው ባሻገር፣
4740ሳቢና ማራኪ ነው፡፡
4741ይህንን የሽብር አማራጭ ሳይጠቀሙ የተሻለና እጅግ
4742አመርቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለው መንገድ
4743የትኛው ነው በሚለው ላይ የበለጠ መነጋገር፤
4744መወያየትም የተገባ ነው፡፡ ከ“ጥራኝ ደኑም ሆነ
4745ከሽብሩ መንገድ” ይልቅ “የጥራኝ ጎዳናው!
4746የጥራኝ መንገዱ!
4747” አማራጭ እጅግ አዋጪ ነው፡፡ የህንን የምለው
4748የግብጽን፣ የቱኒዚያንና የሌሎችን አረብ አገር “የፀደይ
4749ወራት!
4750” ብሔራዊ እንቢተኝነት እንድገም ለማለት
4751አይደለም፡፡ በዚህ አመለካከቴም፣ ከልጅ
4752ተመስጌን ደሳለኝና ከተወሰኑት ባልደረቦቹ
4753የተለየ አቋም ነው ያለኝ፡፡ እነርሱ፤ “መስቀል
4754አደባባይን የጣህሪር አደባባይ እናደርጋታለን”
4755የሚል ሃሳብ ያንፀባርቃሉ አዲስ ታይምስ መጽሔት፣
47562005ዓም፣ ቁጥር-3ን ይመልከቱ፡፡ የምለው፤ በ1966እና
4757በ1983ዓም እንዳደረግነው፣ ሕዝባዊ
4758እንቢተኝነታችንን ለታጣቂ ኃይሎች ላለማስከብ፣
4759በቅድሚያ ጠንክረን መሥራት ይገባናል ነው፡፡
4760የመጀመሪያው ሥራ፣ ወጣቱንና ሕዝቡን በተሳካ
4761ኹኔታ በማደራጀት ነው፡፡ ከገጠር እስከ ከተማ
4762ድረስ ጠንካራና ሰላማዊ የሆነ ድርጅት መሥራት
4763የግድ ይላል፡፡ ከገዢው ፓርቲ ጋር የሚደረገውም
4764ትንቅንቅ ቀላል አይሆንም፡፡ ያንን ተቋቁሞ
4765የተሳካ አደረጃጀትና ታዓማኒነት ያለው የፖለቲካ
4766አመራር ማዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡
4767“ሥልጣን” የምትባለውን ጉደኛና አደገኛ “ሰይጣንም”
4768ለመያዝ፣ በወታደሩና በፀጥታ ኃይሎች አካባቢ
4769የሰላማዊ ታጋዮቹ አላማና ርዕይ ተቀባይነት
4770እንዲያገኝ ያለመታከት መሥራትን ይጠይቃል፡፡
4771የወጣቶቹ ሰላማዊ አደረጃጀትና ተዓማኒነት ያለው
4772አመራር ዕውን ከሆነ፣ በወታደራዊውም ሆነ
4773በፀጥታና በደኅንነቱ አካላት ዘንድ ያሉትን በመቶ
4774ሺ የገመቱ ወጣቶችን ልብ ለማሸፈት አቅም
4775ይኖረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ፣ በሰላማዊ መንገድ
4776የሚዳጁት ወጣቶች ያሏቸውን የተለያዩ የመገናኛና
4777የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች ይበልጥ
4778ጠንካራና የማይታወኩ አድርገው መሥራት አለባቸው፡፡
4779ለዚህም ተግባር የሚያግዙ በርካታ በጎ
4780ፈቃደኞችንና የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞችን የሚያገኙ
4781የቴሌ፣ የፖስታ፣ የመንገድ ትራንስፖርት፣
4782የአቬሽንና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ከወዲሁ
4783ማዘጋትም የግድ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉትንና
4784በተለያዩ ኤጀንሲዎች ተጽፎ የሚሰጣቸውን
4785መግለጫና ዜና ለእጀራቸው ብለው የሚያቡትን የሚያነበንቡትን
4786ጋዜጠኞች መጥላቱም ሆነ ማጥላላቱ ጊዜ ማጥፋት
4787ነው፡፡ ከእነርሱ ይልቅ፣ ከኋላ ሆነው
4788የሚያቅዱትና ስልቶችን የሚነድፉት “ጎበዞችና
4789ጎበዛዝት” ላይ ማተኮሩ ተገቢ ነው፡፡
4790ይህ ሃሳብ ወደ አንድ አቅጣጫ ይመራናል፡፡ ወጣቱ
4791ያለውን ውሱን ጥሪትና የሰው ሃይል በሚገባው
4792ቦታና ሰዓት አውሎ፣ ትግሉን አስተማማኝና እጅግ
4793ሰላማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ከፈለገ፣
4794የሚያተኩርባቸውን “ጎበዞችና ጎበዛዝት”
4795ማንነት፣ አድራሻ ቦታ፣ የዘወትር
4796እንቅስቃሴያቸውንና የእነማን ወዳጅና ጠላት
4797እንደሆኑ ኹሉ አብጠርጥሮ ማወቅ አለበት፡፡
4798እነማን የንግድ ሸሪኮቻቸው እንደሆኑ፣ እነማንስ
4799ቂመኞቻቸው እነደሆኑ ከወዲሁ ለይቶ ማወቅ
4800ይገባዋል፡፡ ይህንን ማድረጉ ለሁለት ነገሮች
4801ይጠቅመዋል፡፡ አንደኛ፣ እባብ ተይዞ በትር
4802ስለማይፈለግ ነው፡፡ በእርግጥም፣ ለፍርድ
4803መቅረብ ያለባቸውን ከሌለባቸው ለመለየት
4804ስለሚበጅ ነው፡፡ ሁለተኛ፣ “መረጃ አይናቅም፣
4805አይደነቅም!
4806” ከሚለው መርሆም በመነሳት ነው፡፡ ለብሔራዊ
4807እንቢተኝነት የሚዘጋጁትን ወጣቶችና
4808ደጋፊዎቻቸውን እነማን እያሳደዷቸው እንደሆኑና
4809እነማንስ ያላግባብ በህዝብና በሀገር ክብር ላይ
4810እየቆመሩ እንዳሉ ማወቁ በራሱ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡
4811ክፍል-2ን ሳምንት ይጠብቁ፡፡
4812ባለፈው ሳምንት በወጣው የአዲስ ጉዳይ ቅጽ 7፣
4813ቁጥር 150 የካቲት 2 ቀን 2005 ዓም ዕትማችን ላይ
4814ወይም ደግሞ 201306-
4815ስለሐረርነት እና ስለጎንደርነት ተናግረን ነበር፡፡
4816በዚህ ዕትማችን በቁጥር 150ኛው ላይ ደግሞ ስለ“ጎንደርነት
4817እና ሐረርነት” እንጽፋለን፡፡ ባለፈው ዕትማችን
4818ላይ እንደገለጽነው ስለጎንደርነትና
4819ስለሐረርነት ማውራት ማለት ስለጎንደሬዎች እና
4820ስለሐረሮች ማውራት ማለት አይደለም፡፡ ልናወሳ
4821የምንፈልገው፣ ስለጎንደር እና ስለሐረር ስለቦታዎቹ
4822ነው፡፡ በመሆኑም፣ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ
4823በምናነሳቸው አንኳር- አንኳር ነጥቦች፣
4824የዛሬዎቹን ሐረሮች እና ጎንደሮች እያሰብን
4825አልጻፍነውም፡፡ እንዲያውም ፍላጎታችን፣
4826ከደርግ መራሹ ወያኔ-ኢህአዲግ መምጣት በፊት
4827ስለነበሩት ጎንደር እና ሐረር ለመዘከር ነው፡፡
4828በመሆኑም፣ አንዳንድ ነጥቦችን ስታገኙ በቀጥታ
4829ከዚህ ዘመንና ከዚህ ወቅት ጋር ባታናጽሩት
4830ይመከራል፡፡ ካነጻጸራችሁትም፣ የእናንተ
4831የአንባቢያኑ ነፃነት እንጂ የጸሐፊው ፍላጎት
4832አለመሆኑን ልብ ይሏል፡፡
4833የ“ጎንደርነት” ኩራት በዋናነት የነገሥታቱ
4834አብያተ-መንግስታት እና ከጢስ ዐባይ አጠገብዝቅ
4835ብሎ ያለው፣ “የአፄ ፋሲል ድልድይ” ወይም “የዕንቁላል
4836ድልድይ” ነው፡፡ ያሬድ ግርማ ኃይሌ የተባሉ
4837ፀሐፊ በ1999 ዓም ባሳተሙት “ የጎንደር ታሪክ፣
4838ከኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር” በሚለው መጽሐፋቸው
4839እንደገለጹት፣ “አፄ ፋሲል፣ የተለያዩ የእደ
4840ጥበብ ሙያ ያላቸውን፤ የሽመና፣ የግንብ ሥራ፣
4841የብረታ ብረት ሥራ፣ የአንጥረኝነት፣ የኖራ አቡኪ፣
4842ሸክላ ሠሪዎችን፣ ኮርቻ ሠሪዎችን፣ እና ወዘተ…
4843ከተለያዩ ቦታዎች አሰባስበው በቤተ መንግሥቱ
4844ዙሪያ አስፍረው ማሠራት ጀመሩ፤” እያለ ይቀጥላል፡፡
4845ደራሲው ያሬድ ግርማ ዋናውን ምስጢር አልተናገረም፡፡
4846ዋናው ቁምነገር፣ እነዚህ የስነ ሕንጻና
4847የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች “ከየትኞቹ የተለያዩ
4848ቦታዎች ነው አሰባስበው ያመጧቸው?
4849” የሚለው ነው፡፡ “ከተለያዩ ቦታዎች” የሚለው
4850ሃረግ አሻሚ ነው፡፡ “ከሀገር ውስጥ ነው ወይስ
4851ከውጭ አገር?
4852” የሚለውን አያሳይም፡፡ “ፋሲል ይንገስ!
4853ሃይማኖት ይመለስ!
4854” ተብሎ ፋሲል ሲነግስና አባቱ አፄ ሱስንዮስም
4855በአዋጅ ቀይሮት የነበረው ካቶሊክነት ተወግዶ
4856የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሲመለስ፣ “አፄ ፋሲል ሙሉ
4857ለሙሉ ፖርቹጋሎቹን ከኢትዮጵያ አስወጥቷቸዋልን?
4858” ወይስ “የተወሰኑ የስነ-ሕንጻ ባለሙያዎችን
4859መርጦ አስቀርቶ ነበር?
4860” “የፋሲልየእንቁላል-ድልድይ” የሚባለውንስ
4861ከጢስ ዐባይ ዝቅ ብሎ የሚገኘውን ድልድይስ ማነው
4862የገነባው?
4863” በዕርግጥ፣ ኢትዮጵያውያን ናቸውን ወይስ
4864ከክርቶፎር ዳጋማ ጋር የመጡት 400ዎቹ ፖርቹጋሎች
4865መካከል የስነ-ሕንጻና የድልድይ ሥራ መሃንዲሶችም
4866መጥተው ነበር?
4867” እነዚህንና እነዚህን መሠል ጥያቄዎች ደህና
4868አድርገን እንዳናገኝ ያገደን፣ የአፄ ፋሲል ዜና
4869መዋዕል ያለመገኘቱ ጉዳይ ነው ሥርግው ኃብለ
4870ሥላሴ 1957፤ አፄ ምንሊክ የአዲሷ ኢትዮጵያ
4871ስልጣኔ መስራች ፤ ገጽ 47-8፡፡
4872በተመሳሳይ መልኩም፣ የ“ሐረርነት” ኩራት
4873የሆነው የጀጎል ግንብና በውስጡም ያሉት መኖሪያ
4874ቤቶች ናቸው፡፡ አረብ ፋቂህ የተባለው ፀሐፊ
4875በፃፈውና ሬኔ ባሴት በተረጎሙት “ፍቱሕ አል
4876ሀበሽ” በተባለው መጽሐፍ ላይ በገጽ 168
4877እንዳሰፈረው ከሆነ፣ “በ1540-42 ባሉት ሦስት
4878ዓመታት ውስጥ አሚር ኑር ኢብን ሙጃሂድ፣ 481,812
4879ሜትር ካሬ ያለውን የጀጎል ግንብ፣
4880ከክርስቲያኖችና ከኦሮሞዎችም እየተከላከለ
4881ሐረርጌ ተቀምጦ በሚያስተዳድርበት ጊዜ፣ ከተማዋ
4882ሐረር የወረራ አደጋ እንዳይደርስባት ዙረያዋን
4883በግንብ አሳጠራት” ይላል፡፡ ባሳየውም መልካም
4884አስተዳደርና ባሠራውም በዚህ ግንብ የተነሣ
4885በዘመኑ በነበሩ የእስልምና ተከታዮች ዘንድ
4886እንደጻድቅ የሚቆጠር መልካም አሚር መስፍን
4887እንደነበረ፤ በዘመኑ ከነበሩት ታሪክ ፀሐፊዎች
4888መኻከል እነአቡበከር ኢብን መሐመድ አልዊ
4889ሰንባልም ያረጋግጣሉ፡፡ ነገር ግን፣ በግራኝ
4890ዘመን የመጡትና ከልብነ ድንግል እንዲሁም
4891ከገላውዲዮስ ጋር ለአህመድ ግራኝ ወግነው ይዋጉ
4892የነበሩት የቱርክ ወታደሮች፣ በአሚር ኑር ዘመን
4893ሙሉ ለሙሉ ከሐረር ይውጡ ወይስ አይውጡ፣ አረብ
4894ፋቂህም ሆነ እነአቡበከር መሐመድ አይገልጹም፡፡
4895ምናልባትም፣ መድፍና ዐረር ይዘው ከቱርክ የመጡት
4896ሙጃሂዲኖች መካከል የተወሰኑት የስነ-ሕንፃና
4897የግንባታ ባለሙያዎች የነበሩ ሊሆን ይችላል፡፡
4898ይኼንን የሚያሰኘውም፣ ከአሚር ኑር በኋላ፣ ሌላ
4899ተመሳሳይ ጀጎል ወይም ግንብ በቅርብ እርቀት ላይ
4900ወይም የወላስሞች መናገሻ በሆነችው ሰመራ ወይም
4901ሚሌ አካባቢ እንኳን አለመሰራቱን ስለምናውቅ ነው፡፡
4902የጎንደርንም ሆነ የሐረርን ግንባታዎች ማንም
4903ሠራቸው ማንም፣ ትልቁ ቁምነገር ያለው “ማን
4904አሰባቸው?
4905” የሚለው ጥያቄ ላይ ነው፡፡ የጎንደርን እና
4906የሐረርን ግንቦች ከሠሯቸው ግንበኞች ይልቅ፣ “ሐረር
4907እና ጎንደር በግንብ መታጠር አለባቸው!
4908” ብለው ያሰቡትና ያቀዱት አሚር ኑርና አፄ ፋሲል
4909ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ለመገንባት ሲነሱም
4910ከጎናቸው ሌሎች ሕዝቦችና ወገኖች ነበሩ፡፡
4911ጎንደርነት የተገነባው የሸዋን፣ የወሎን፣
4912የጎጃምንና የጎንደርን እንዲሁም የትግራይንና
4913የባሕረ-ነጋሽን ሕዝብ ግብር በመቀበል ነው፡፡ “ፃዲቁ
4914ዮሐንስ” እየተባሉ ከሚጠሩት፣ ከአፄ ዮሐንስ 1ኛ 1659-1674
4915እና ከመናኒው ንጉሥ አድያም ሰገድ እያሱ
4916በስተቀር፣ ሌሎች ነገስታት ከፍተኛ ግብር
4917ይሰበስቡ ነበር፡፡ ያንንም ግብር
4918ለአብያተ-ክርስቲያናትና ለአበያተ-መንግሥታት
4919መሥሪያ አዋሉት፡፡ በተለየ መልኩም፣ አሚር ኑርና
4920ቀዳሚው ኢማም አህመድ ግራኝ፣ ከሸዋ፣ ከወሎ፣
4921ከጎጃም፣ ከጎንደር፣ ከትግራይና ከደቡብ
4922ኢትዮጵያ አብያተ-ክርስቲያናትና የነገሥታት
4923አምባዎች በበዘበዙት ሀብትና ቅርስ የራሳቸውን
4924ግንብ፣ ለራሳቸውና ለሕዝባቸው ሠሩበት፡፡ ዞሮ
4925ዞሮ፣ “የጎደርነት ኩራት” የሆነውም የፋሲል
4926ግንብ ሆነ፣ “የሐረርነት ኩራት” የሆነው የጀጎል
4927ግንብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብትና ንብረት እንጂ
4928የጎንደሬዎች ወይም የሐረሬዎች ብቻ አይደሉም፡፡
4929ሊሆኑም አይችሉም፡፡ የሚያሳዝነው
4930የኢትዮጵያውያን ሀብትና ንብረት በግብርም ሆነ
4931በዘረፋ ሲበዘበዝ ኖሮ፣ ላለፉት አራት መቶ ሃምሳ
4932ዓመታትና ከዚያም በላይ ለሚሆኑ ዘመናት፣ ሌላ
4933የመሳፍንትና የሕዝብ መኖሪያ የሆነ “የጀጎል
4934ግንብ” እና ሌላ የነገሥታት መናገሻ የሆነ የ“ፋሲል
4935ግንብ” አለመሥራታችን ነው፡፡
4936በጥር 1879 ዓም የእስልምና መናኸሪያዋ ሐረር፣
4937በክርስቲያኖች መዳፍ ውስጥ ገባች፡፡ በአፍጋኒስታን
4938ታሊባንን መራሹ የአሜሪካን ጦር ሐሚድ ካርዛይን
4939ፕሬዝዳንት ብሎ እንዳነገሰው ሁሉ፣ በሐረርም
4940ግፈኛውን አሚር መሐመድ ኢብን ዐሊን በሕዝቡ
4941ትብብር ያስወገደው የግብፁ ቄሳራዊ ጦር ሐረርን
4942ለቆ በ1878 ሲወጣ አሚር አብዱላሂን አንግሦ ወጣ፡፡
4943ከሸዋ በዘመተው ጦር የተሸነፈው የአሚር አብዱላሂ
4944“ፈሪ የናቱ ልጅ ነው!
4945” ብሎ ወደሶማሊያ ፈረጠጠ፡፡ አፄ ምንሊክም፣
4946ሁሉም የያዘውን ሃይማኖት ሳይቀይር “ሃይማኖት
4947የግል፣ አገር የጋራ ነው!
4948” ብለው አዋጅ ስላስነገሩ፣ እስልምና የሐረርነት
4949የተከበረ ሃይማኖት ሆኖ ቀጠለ፡፡ አንዲትም
4950መስኪድ ያለዲፕሎማሲያዊ ድርድርና ታክቲክ
4951አልፈረሰም፡፡ በጀጎል ውስጥ ያለውን ዋና መንገድ
4952“አንደኛ መንገድ” ይባላል ለማውጣት ሲስማሙ
4953የአሚር አብዱላሂ አጎት አቡበከርና ሌሎች የሐረር
4954ሽማግሌዎች ከምንሊክ ጋር ፊት-ለፊት “በሰጥቶ
4955መቀበል መርህ” ተደራድረዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን፣
4956በጥር 1880 ዓም ወደ ጎንደር የገሠገሠው ጂሃዳዊው
4957የደርቡሽ ጦር፣ የጎጃሙን ንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን
4958አሸንፎ፣ ጎንደርን በዘበዛት፤ አቃጠላት፡፡
4959ከአርባ-አራቱ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አራቱ
4960ብቻ በተዐምራት ተረፉ፡፡ አርባዎቹ ሙሉ ለሙሉ
4961ወደሙ፡፡ በርካታ ክርስቲያኖች ተማርከው በመተማ
4962በኩል ወደሱዳን ተወሰዱ፡፡ “ አይታሰስም ምጣድ
4963በግምጃ፤ ዘንድሮ ደርቡሽ መጽረፉን እንጃ!
4964” ብሎ ፎክሮ ሄዶ የነበረው የጎጃም ጦር ክፉኛ
4965ተመታ፡፡ ወታደሩም ተፈታ፡፡ የሞተው ሞቶ፤
4966የሸሸውም ፈርጥጦ፣ የተያዘውም ተማረከ፡፡ ንጉሥ
4967ተክለ ሃይማኖትና ጥቂት አዛዦቹም ምንትዋብ
4968የምትባለውን የተክለ ሃይማኖትን ሁለተኛ ሚስት
4969እንኳን ሳይዙ ሸሽተው አመለጡ፡፡ ለዚህም ነው፣
4970ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት በጎንደሬዎች ዘንድ “አትከልክልሞይ
4971ተክለ ሃይማኖት፣ ይዘህ አለንጋህን፤ አሞራ ደርቡሽ
4972ሲበላው የገዛ ገላህን ምንትዋብህን!
4973” ተብሎ የተወቀሰው፡፡ ሐረርነት ውስጥ “ሃይማኖና
4974ሀገር” የተለያዩ መሆናቸው ተስተውሎ ሐረር
4975ከጥፋትና ከቃጠሎ ስትድን፤ ጎንደርነት ውስጥ ግን
4976“ሃይማኖትና ሀገር አንድ ናችሁ!
4977” ተብለው፣ በአንድነት ተገደሉ፤ ተቃጠሉ ተክል
4978ጻድቅ መኩሪያ 1982 አፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ
4979አንድነት ፣ ገጽ 292 እና 450-451 ላይ ይመልከቱ፡፡
4980ሌላው ጎንደርነትን እና ሐረርነትን
4981የሚያመሳስላቸው የጣሊያን ወረራ ነው፡፡ ጣሊያን
4982ከወረራው ሦስት ዓመታት ቀደም ብሎ በሐረርና
4983በጎንደር ላይ ቆንስላ ከፍቶ ነበር፡፡ ሕዝቡንም
4984በስኳርና በሳሙና፣ በፓስታና በሹታ እርዳታ ስም
4985መደለል ጀምሮ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎችንም ልብ
4986አሸፍቶ ነበር፡፡ በተለይም የወጣቶችን ልብ
4987አማልሎ ነበር፡፡ መንግሥቱ ለማ፣ “ኧረ ሄደ-ሄደ፣
4988ሄደ ኮበለለ፤ በስኳር ብስኩት እየተደለለ!
4989” ያሉት ነገር ለዚህም ጊዜ ይሠራል፡፡ ጥሊያን
4990ሲኒማ ቤቶችን ያሠራው ከ1927 በፊት ነበር፡፡
4991ለወጣቶቹም የፋሺስትን መርዘኛ ፊልሞች ማሳየት
4992ጀምሮ ነበር፡፡ “ባሊላ” የተባሉትም የፋሺስት
4993ትምህርት ቤቶች በሐረርና በጎንደር ተከፍተው
4994ነበር፡፡ የሐረሩ ልዑል ራስ መኮንን ትምህርት
4995ቤትን ለወንዶቹ ልጆች፤ የወይዘሮ የሺ እመቤትን
4996ትምህርት ቤትንም ለሴቶች ያሠራው በወረራው ወቅት
4997ነበር፡፡ ዛሬ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች በሌላ
4998መጠሪያ ስም ነው የሚታወቁት፡፡ በጎንደርም፣
4999የፋሲለደስ ትምህርት ቤትን ሕንጻ ገንብቶ በርካታ
5000ወጣቶችን ለፋሺስታዊ እኩይ ተግባሩ እያዘጋጃቸው
5001ነበር፡፡ ጣሊያን ከሐረር 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
5002የሚገኘውን ጠመዝማዛ የደንገጎ መንገድ
5003ለወታደርና ስንቅ ማመላለሻ በ182728 ሲሠራው፤
5004ከደባርቅ ወረድ ብሎ ያለውንም የሊማ-ሊሞን
5005ጠመዝማዛ መንገድ ለተመሣሣይ ዓላማ ከ1927-1929 ዓም
5006ባሉት ጥቂት ዓማታት ውስጥ አጠናቋቸዋል፡፡
5007ጎንደርነት፣ በደርግ ዘመን ክፉኛ በቀይ ሽብር
5008ቸነፈርና አለንጋ ተመቶ ነበር፡፡ ግፈኛው መላኩ
5009ተፈራ የጎንደርን ወጣቶች ለሶሻሊዝም ባዕድ
5010ርዕዮት-ዓለምአምልኮው ሲል አስፋልት ላይ
5011ረፈረፋቸው፡፡ የጎንደሩ ሰው መላኩ ተፈራ በገዛ
5012ወገኖቹ ላይ ከኔሮና ከግራዚያኒም የማይተናነስ
5013ጭካኔ አሳየ፡፡ ጎንደርነት ከፍተኛ አደጋ
5014ተጋረጠበት፡፡ የጎንደር ወጣቶች በበረሃ
5015እያሳበሩ ወደሱዳን ተመሙ፡፡ አንዲት ጎስቋላ
5016እናት “መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም፤
5017የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም!
5018” ያለችው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ በአንፃሩ፣
5019ሐረርነት በብዛት በቀይ ሽብር አልተጎደም፡፡
5020በመጠኑም ቢሆን ግን በተለይ የአማርኛና የኦሮሚኛ
5021ተናጋሪ ወጣቶችን ገሏል፡፡ በኮሎኔል ዘለቀ በየነ
5022ይመራ የነበረው የቀይ ሽብር ገዳይ ግብረ-ሃይል
5023በርካታ ወጣቶችን ያለ ፍርድ ገድሏል፡፡ ብቻውን
5024አልነበረም፡፡ የሐረር ተወላጆቹን እነአዲል
5025አሊን ይዞ ነበር፡፡ አዲል አሊ፣ ኢህአዲግ
5026በግንቦት 26 ቀን 1983 ዓም ሐረርን ሲቆጣጠር ፈርጥጦ
5027ሶማሊያ ሞቃዲሾ ተቀመጠ፡፡ የሐረር ወጣት
5028የሚሰደደውም በጅቡቲ በኩል ነበር፡፡ ብዙ ወጣቶች
5029እግሬ አውጭኝ ብለዋል፡፡ ብልጦቹም፣ “ቪቫህ
5030ደርጎ-ቪቫህ ደርጎ!
5031ይገባሃል ወተቲና ኢርጎ!
5032” ብለው ዘፍነው ዘመኑን አጎንብሰው በጥበብ
5033ተርፈዋል፡፡ ሐረርነት እና ጎንደርነት ብዙ ልጆች
5034በውጭ ሀገራት ስላሏቸው፣ ከውጭ የሚላክ ዶላር ና
5035ወርቅ አላጡም፡፡ ዛሬ አቦከርና አዘዞ የሚገነቡት
5036ምርጥ ምርጥ ቪላዎች ከውጭ አገር በሚላኩ
5037ገንዘቦች መሆኑን ማስታወስ ይገባል፡፡
5038ከሼክ አባድር ዘመነ ጀምሮ እስልምና በጎንደር
5039እና በሐረር ፀንቶ የቆየ ነበረ፡፡ የሼክ
5040አባድርን በረከት ለማግኘት ለመዘየር አንድ ሺህ
5041ኪሎ ሜትሮች በላይ ተጉዘው የጎንደር እስላሞች
5042ሐረር ይመጡ ነበር መርደቻይ አብር፤ ኢትዮጵያ፤
5043በዘመነ መሳፍንት ባለው መጽሐፉ እንደገለፀው
5044፡፡ አንድ ቀን ታዲያ በነዚህ ጎንደሬዎች ድካም
5045ያዘኑት ሼክ አባድር፣ የብረት ዘንጋቸውን አርቀው
5046ሲወረውሩት ተሰወረ፡፡ ከጎንደር ለመጡት በረከት
5047ፈላጊዎችም እንዲህ አሏቸው፤ “ሂዱ፣ ይሄንን
5048ዘንጌን ከአንገረብ ወንዝ ማዶ ታገኙታላችሁ፡፡
5049እዚያ ሆናችሁ ጸልዩ፡፡ እዚህ ሐረር ያለውን
5050በረከት ሁሉም እዚያው ጎንደር ታገኙታላችሁ!
5051” አሏቸው፡፡ መንገደኞቹም ዝየራቸውን ፈጽመው
5052ተመልሰው ጎንደር ሲገቡ ዘንጉን ፈለጉት፡፡
5053ከአንገረብ ወንዝ ማዶም ተሰክቶ አገኙት፡፡
5054ዘንጉም ሲነቀል ቅዱስ ውሃ ፈለቀ፡፡ በአው
5055አባድርም ትዕዛዝ ሐረርነትና ጎንደርነት አንድን
5056በረከት እየተካፈለ፣ በ1,101 ኪሜትር ርቀት ላይ
5057በየፊናው ሥልጣኔውንና ባሕሉን ሲከተል ለዘመናት
5058ኖረ፡፡ ያንን ቦታ ከ1966 ዓም በፊት ልዕልት ተናኘ
5059ወርቅ፣ የአባድር እርሻ ልማት ብላ ለበጎአድራጎት
5060ስራ ታሳርሰው ነበር፡፡ ደርግ መጣና በ1967 ዓም
5061ለሕብረተሰቡ ጥቅም ወረሰው፡፡
5062በጎንደርነት እና በሐረርነት መካከል ያለውን
5063ዋነኛ የመንፈስ ልዩነት ማውሳት ያሻል፡፡
5064ልዩነታቸውም የተገነባው አው አባዲር አትመላለሱ
5065ስላሏቸው ሳይሆን፣ ከግንቦቻቸው እና
5066ከቅጥሮቻቸው አሠራር ጋር በተገናኘ ነው፡፡
5067የሐረርነት እና የጎንደርነትም ፖለቲካዊ
5068ፍልስፍና የሚያጠነጥነው እዚህም ላይ ነው፡፡
5069ሐረርነት በአሚር ኑር አማካይነት የሐረርን ጀጎል
5070ሲገነባ፣ ለአሚሮቹ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡም
5071ደኅነነትና ሰላም መጨነቁንና መጠበቡን ያሳያል፡፡
5072“በአሚርነት ክብርና” በተራው “የሐረር ሕዝብ
5073ክብር” መካከል የሠፋ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ
5074ልዩነት እንዳይኖር አድርጎ ወጠነው፡፡ በዚህም
5075የተነሳ እስከ ዘመናችን ድረስ እንደምናየው፣
5076ሐረርነት ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና
5077የሕዝቡ የስነ-ልቦና ትስስር በጣም የተራራቀ
5078አይደለም፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ በቀላሉ በአይን
5079ጥቅሻ ፍጥነት ከፍተኛ መግባባትና መተማመን
5080ይታያል፡፡ መስኪዶች እና ሕንጻዎች በያመቱ
5081በረመዳን ወር ይታደሳሉ፡፡ የፈረሰና
5082የተደረመሰም ካለ በሕዝቡ ትብብር ይገነባል፡፡
5083ይህም ነገር ለመጤዎችና ለአንዳንድ ጉዳዩን በቅጡ
5084ለማይረዱት ሰዎች “ዘረኝነት ወይም ጠባብነት”
5085ይመስል ይሆናል፡፡ ግን አይደለም፡፡ ላለፉት 450
5086ዓመታት ያህል “ለሐረርነትና ለደኅንነት
5087አስፈላጊ ነው” ተብሎ የተያዘ የኑሮ ዘዴ ነው፡፡
5088ሐረርነትን ከኦሮሞዎችና ከሌሎችም የጦርና
5089የባህል ወረራዎችም የታደጋትም ይኼው ሕዝባዊነቷ
5090ነው፡፡
5091በአንፃሩ፣ ጎንደርነት በአፄ ፋሲል አሳቢነት
5092ስትገነባ የነገሥታቱን እና የሕዝቡን ልዩነት
5093በጉልህ አስምሮበት ነው፡፡ ነገሥታቱ በረጃጅም
5094ግንብ በታጠረውና በምቹ ሁኔታ በተሠራው ቅንጡ
5095ቤተ-መንግሥታቸው ሲኖሩ፣ ሕዝቡ ግን ከግንቡ ውጭ
5096በጎጆ ቤት እንዲኖር ተደርጓል፡፡ ነገሥታቱ
5097ከሕዝባቸው ደኅንነት ይልቅ የራሳቸውን ክብር
5098አስበልጠዋል፡፡ በዚህም የተነሳ፣ በ1880 የመጣውን
5099የደርቡሽ ጦር ሕዝቡ በትጋት ሳይከላከለው ቀርቶ
5100ከፍተኛ ጉዳት በአብያተ-መንግሥቱ ላይና
5101በአብያተ-ክርስቲያናቱ ላይ ደረሰ፡፡ አሁንም
5102ቢሆን፣ የጎንደርነት ኩራት የሆኑትን የፋሲልን
5103ግንብና አብያተ-ክርስቲያናቱን ለማደስ ሲፈለግ
5104ለጋሾች ተለምነው ነው፡፡ ሕዝቡ የእኔነት ስሜት
5105እንዳይሰማው ስለተደረገ፣ የጎንደርነት ኩራቶች
5106በአግባቡ አይጠበቁም፤ በወቅቱም አይታደሱም፡፡ ቸር
5107እንስብት!
5108
5109እግዚአብሔር እኛን ለመሥራት በተለያዩ የሕይወት
5110ጎዳናዎች ያሳልፈናል፡፡የልቅሶ ዘመን አለ፤የመከራ
5111ዘመን አለ፤የጭንቅ ዘመን አለ፤የእጦት ዘመን አለ፤ደግሞም
5112የዕረፍት እና የበረከት ዘመን ይኖራል፡፡የእግዚአብሔር
5113ቃል የልቅሶ ዘመን በሕይወታችን እንደሚኖር
5114ሲያበስረን እንዲህ ይላል፡-
5115እግዚአብሔር ሊሠራንና ሊያበጃጀን መዝ 119፡73
5116ብሎም ከእኛ ላይ እልህን፣በገዛ ፈቃድ መሄድንን፣ትዕቢትን
5117ሊያራግፍ እና ሊያለዝበን በብዙ ነገሮች ውስጥ
5118ያሳልፈናል፡፡አዎ!
5119እርግጥ ነው የፈተና፣የንቀት፣የስድብ እና
5120የመከራ ዘመን አለ፡፡የጌታ ጊዜ ሲደርስ ደግሞ
5121ግሩም የሆነ የዕረፍት ዘመን ይመጣል፡፡የፈተናው
5122እና የመከራው ዘመን ያማል፣አንገትን ያስደፋል፣ያስለቅሳል፣ግራ
5123ያጋባል ወዘተ፡፡በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ከእሱ
5124ጋር ተጣብቀንና አጥብቀን የጌታን ፊት የምንፈልግ
5125ከሆነ፣እግዚአብሔር እንደሚደግፍ፣እንደሚያጽናና፣እንደሚረዳ
5126በተግባር ደረጃ የምናውቅበት ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡
5127‹‹ከዚያም የወይን ቦታዋን የተስፋ በርም
5128እንዲሆንላት የአኮርን ሸለቆ እሰጣታለሁ፤በዚያም
5129ከግብጽ ምድር እንደ ወጣችበት ቀን እንደ
5130ህጻንነትዋ ወራት ትዘምራለች፡፡በዚያ ቀን ባሌ
5131ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ በኣሌ ብለሽ
5132አትጠሪኝም ይላል እግዚአብሔር፤የበአሊምን ስም
5133ከአፍሽ አስወግደዋለሁና በስማቸውም እንግዲህ
5134አይታሰቡምና›› ሆሴዕ 2፡17-19
5135ከዚህ ምንባብ እንደምንረዳው፣ያ ምድረ በዳ እና
5136የመከራ ቦታ፣ለእስራኤል ትልቅ መንፈሳዊ
5137ለውጥንና በረከትን እንዳመጣ እንገነዘባለን፡፡ሕብረታቸው፣አምልኮአቸውና
5138ከጌታ ጋር ያላቸው ግንኑነት እንደታደሰና
5139እንደጠለቀ እናያለን፡፡የሚጓጓለት አስደናቂ
5140ለውጥ!
5141በመከራ ዘመን ከድሎት ዘመን ይልቅ ብዙ ጸሎትና
5142የጌታን ፊት መፈለግ ይስተዋላል፡፡ና አይባልም
5143እንጂ የመከራ ጊዜ የመማሪያና የመሞረጃ ጊዜ
5144መሆኑን ብዙ ሰዎች ይስማማሉ፡፡ጊዜው መርዘሙ
5145ቢያታክተንና ጉስቁልናው ተጭኖ ቢያስጨንቀንም፣ለመንፈሳዊ
5146ዕድገት ትልቅ አጋጣሚ መሆኑ የሚያስማማን
5147ይመስለኛል፤ለዚህ ነው ሐዋርያው ያዕቆብ እንዲህ
5148ብሎ የሚመክረው፡-
5149‹‹ወንድሞቼ ሆይ የእምነታችሁ መፈተን
5150ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ
5151ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፡፡ትዕግሥትም
5152ምንም የሚጎደላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን
5153ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም›› ያዕ 1፡1-4
5154አገር ቤቱ ዳያስፖራ፤ ዳያስፖራው ደግሞ አገር
5155ቤት እየሆነ በመጣበት በዚህ ህልሙም፤ ቅዠቱም፤
5156ባህሉም፤ ኑሮውም ተወራራሺ በሆነበት ዘመን የሥነ
5157ጥበብ ሰዎች አስጎምዥ የትረካ አውድማ እንደተቸሩ
5158ሳውቅ ሰንብቻለሁ።
5159የምሕረት ደበበ ልቦለድ ታሪክ ስድሰት ሺህ ማይል
5160አራርቋቸው በሚኖሩ ያበሻ ሕበረተስቦች
5161ሁለንተናዊ ባሕርይና ዕጣ-ፈንታ ላይ የተመሠረተ
5162ነው።
5163የደራሲው አንድ እግር አሜሪካ፤ ሌላኛው እግር
5164ደግሞ ኢትዮጵያ መሆን የሁለቱንም ሕብረተሰቦች
5165ውጫዊና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ ባሕርይ፤ እንዲሁም
5166የየቤቱን ውሎና ከራሞ በቅርብ ለማስተዋል ዕድል
5167እንደሰጠው ከትርካዎቹ ማስተዋል ይቻላል።
5168ሁለቱም ሕብረተሰቦች ውስጥ እየተከሰተ ያለው
5169ፈጣንና አንዳንዴም አስፈሪ የሆነ ማሕበራዊ ለውጥ
5170የብዙ ደራሲያንን እንዲሁም በየሙያ ዘርፉ ያሉ
5171ጠቢባንን የሰላ አእምሮና ብዕር የሚጋብዝ ነውና
5172እንደ ምሕረት ደበበ ያሉ ብዕር ሲያነሱ ደስ ይላል።
5173የመጽሐፉ ጭብጥ በዘመናችን ሕብረተሰብ
5174አመለካከቶች፤ የኑሮ ምርጫዎችና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ
5175ለውጦች ላይ ያተኮረ ነው - አገር ውስጥም ውጭም
5176ባለነው ላይ።
5177ገጸ-ባህርያቱ ተአማኒነትና መልካም ስብጥርም
5178አላቸው።
5179አሜሪካ ተሻግራ ሃብታም ለመሆን ባላት ምኞት
5180የድሜ አቻዋ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር
5181ያገባችው ስንክሳር አገር ቤት ግድግዳ አስደግፋ
5182የተወችውን የወጣትነት ፍቅረኛዋን የመላኩን
5183ልብ መልሳ ለማሸነፍ የምታደርገው ሴራ ውስብስብና
5184እጅግ መሠሪነት የበዛበት ሰለሆነ ስንክሳርን
5185በጣሙን ትጠሏታላችሁ፤ ትፈሯታላቸሁ፤
5186ልታንቋትም ይከጅላችሁ ይሆናል።
5187መጨረሻ ላይ ደግሞ እርሷ ራሷ በደረተችው ተንኮል
5188ተጠልፋ ዙሪያ ዓለሟ እየፈራረሰባት ስታዩ “ሰው
5189ተፀፅቶ ከልብ የሚወደውን ቢሻ ይህን ያህል ፍርድ
5190ሊቀበል ይገባዋል ወይ?
5191” የምትሉም አትጠፉ።
5192መላኩ ባንዲት ሴትዮ ትሩፋት ምንጥ ካለ ድህነት
5193የተረፈና በውጭ አገር ጭምር ትምህርቱን ተከታትሎ
5194“ባገሬ
5195ውስጥ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ” ብሎ በምግባረ
5196ሰናይ ድርጅት ውስጥ ሀቀኛ ጥረት የሚያደርግ ሰው
5197ነው።
5198በመልካም ባህርዩም፤ በጥልቅ አስተሳሰቡም፤
5199በፍቅረኛው በስንክሳር በመገፋቱም ለመላኩ ስስ
5200ልብ ይኖራችሗል።
5201አብሮ ያላደጋቸውን ዘመዶቹን ፈልጎ በማግኝት
5202ከድህነት መቀመቅ ለማውጣት ያደረገውን ጥረትና
5203ይህ ዘመቻው ፍሬ እንዲያገኝ መሣሪያ የሆነችውን
5204ግን በትምህርት ያልገፋችውን ያክስቱን ልጅ
5205በጣሙን ትወዷታላቸሁ።
5206ደራሲ ምሕረት ደበበ የሥነ-አዕምሮ ጠበብት
5207ስለሆነ በገጸ-ባሕርያቱ ውይይት ውስጥ በርካታና
5208ጥልቀት ያላቸው የአዕምሮ አሠራር ሁነቶችን
5209እየሰነገ ያስገባል።
5210ለዋቢ ያህል ስለ “ኦቲዝም” እና ስላገር አመራር
5211የተካሄዱትን ውይይቶች ማንሳት ይቻላል።
5212አንዳንዶች “የትረካውን ፍሰት አደናቀፈብኝ”
5213ሊሉ እንደሚቸሉ እረዳለሁ።
5214ወይንም የሰበካ ያህል ሊቆጥሩት እነደሚችሉ
5215እገምታለሁ።
5216በበኩሌ ግን በደራሲው የዕውቀት ደረጃ ያሉና
5217የነበሩ ሰዎች ፀጋቸውን በልቦለድ ትረካ አጊጠው
5218ሲያካፍሉን አይቸ አላውቅምና ሥራውን እጅግ በጣም
5219ነው የወድኩት።
5220አድናቂውም ሆኛለሁ።
5221ይህን አስተያዬት ስሰነዝር የማተሚያ ቤት
5222ልምዴንና ከደራሲያን ጋር ለመዋል ያጋጠምኝን ሰፊ
5223እድል ዋቢ ጠርቸ ነው።
5224“የተቆለፈበት ቁልፍ” ባወቃቀርም በሴራም ደረጃ
5225የተዋጣለት ሥራ ስለሆነ ነው ባንድ ዓመት እድሜ
5226ለሶስተኛ እትም የበቃው።
5227በቀድሞዎቹ ዘመናት ለሁለተኛና ሦስተኛ እትም
5228የበቁ ደራሲያን በጣት መቆጠራቸውን ግንዛቤ
5229ስናስገባና ባሁኑ ዘመን ደግሞ እንደነ ይስማእከ ዴርቶጋዳ
5230ያሉ ደራሲያን ላሥረኛ እትም መብቃታቸውን ስናይ
5231የመግዛት አቅም ያለውና የተማረው ሕበረተሰባችን
5232መስፋቱን እንረዳለን።
5233ይህ ታዲያ ደራሲያንን ሊያበረታታ ይገባል።
5234ደራሲ ተጨንቆና ተጠቦ የሚጽፈው ሥራው ይነበብለት
5235ዘንድ ባለው ምኞት ተገፋፍቶ ነው።
5236ሌሎች እንደ ዓላማ የሚጠቀሱ አነሳሾች በኔም
5237በብዙዎችም ዘንድ ሚዛን አይደፉም።
5238በዚህ ረገድ ደራሲ ምሕረት ደበበ ባገኘው
5239ተቀባይነት በጅጉ መደሰት አለበት።
5240የሚቀጥለው ሥራው በዚህኛው ስኬት ተበረታትቶና
5241ባገኘው ልምድ ይበልጡን በልጽጎ እነደሚቀርብ
5242አልጠራጠርምና “በርታ!
5243” እለዋለሁ።
5244“ድሮም ሆኖ አያውቅም፣ ትናንት ሆነ ዛሬም አንድ
5245የንብ አውራ ነው- ከሺህ ሰራዊት ጋር ውጤትን
5246የሚያሳይ- የሚጋግረው ማር፡፡” ዳግማዊ ዳዊት -
5247ጥቅምት 2002 @
5248እንደ ግምገማ - ኩችዩ “መጽሐፍ!
5249” ሲሉት ሰፍ የሚል ከራማ ቢጤ አለብኝ መሰል ስዬ
5250አብርሃ ደረሱ የተባለው መድብል እጄ እስኪገባ
5251ቸኩዬ ነበር።
5252ባገራችን የቅርብ ዘመን ታሪክ ላይ አሻራቸውን
5253ካተሙት ጥቂት ስዎች መሀል ናቸውና እኒህ ሰው
5254የሚሉትን ለማወቅ ብተጋ አይፈረድኝም።
5255ጀመርሁ የሚሉት የሁለተኛው ምዕራፍ ጉዟቸው
5256የምንፈልገው ዓይነት መሆኑን የሚያመላክቱ
5257ፍንጮች ያዘለ ሊሆን ስለሚችልም መጽሐፉን
5258ለማንበብ በቂ ምክንያት አለ።
5259ላወቀበት በመስመሮቹ መሀል የተሰነጉትን ሁሉ
5260መመርመር ነው።
5261የትኛውም የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ከወቅት ጋር ባለው
5262ተዛምዶ መነበብ አለበትና ደራሲው ለምንና አሁን
5263መናገር ፈለጉ?
5264የሚለውን ለመመለስ ሞክሬያአለሁ።
5265አንድም የጎደፈ ስምን ለማጽዳት፤ አንድም የገዘፈ
5266ችግር አገራዊ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድርግ፤
5267አንድም ላዲስ የፖለቲካ ግብ መደላድል ለመፍጠር፤
5268አንድም ደግሞ ለበቀል ሊሆን ይችላል አልኩ።
5269የጠቀስኳቸው አነሳሾች ነውር ወይንም መሰሪነት
5270አላቸው ለማለት አይደለም።
5271ያ እያንዳንዱ አንባቢ በየበኩሉ የሚደርስበት
5272ድምዳሜ ነው።
5273ሌላው ታሳቢ ደግሞ ከደራሲው ጀርባ-አጥንት ጋር
5274ተያይዞ ብቅ የሚለው የጥርጣሬ መንፈስ ይመስለኛል።
5275በዚህ ረገድ ብዙዎቻችን እንደ ጎጃሙ ገበሬ እንደ
5276ተክለዬስ የፖለቲካ ሰዎችን የምናየው በጎሪጥ ነው።
5277እንኳንስ እኛ የሶስተኛ ዓለም ሰዎች ያንደኛ
5278ዓለሙ ያሜሪካ ሕዝብ 70% ያህሉ በፖለቲከኞች ላይ
5279ዕምነት አጥቶ የለም እንዴ?
5280የነስዬ ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ ነገሩ በመጠኑ
5281ወሰብሰብ ይላል።
5282ከብሔር ፖለቲካ ካምፕ ወደ ሕብረብሔር ፖለቲካ
5283ካምፕ የዘለለን ሰው ባንዴ ሊያቅፉት ያሰቸግራልና
5284ለተወሰነ ጊዜ በጥርጣሬ ዳመና ተከበው መሥራታቸው
5285የማይቀር ነው።
5286የጨዋታው ሕግ ስለሆነ ይህን አይስቱትም በዬ
5287እገምታለሁ።
5288ይሁን እንጅ፤ የኔዋ የጥርጣሬ ዳመና ተግባራዊ
5289እንቅስቃሴዎችን እየመዘነች፤ ደረጃ በደረጃ
5290እየጠራች ለመሄድ የተዘጋጀች ናት።
5291እንደምንም ብዬ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረስኳት
5292ይምስለኛል።
5293ሚዛናዊነቷ ደግሞ ለየትኛውም ወገኔ ነው።
5294ተስፋ በትናንት ላይ ሳይሆን በዛሬውና በወደፊቱ
5295ውሎ ላይ የሚገንባ እሴት ነውና ዝንተ-ዓለም
5296የጥርጣሬ ተገዥ ልንሆን አይገባም ከሚሉት ወገን
5297ነኝ።
5298ቁም ነገሩም፤ ብልህነቱም ያለው አዕምሮን አትግቶ
5299ልብን ከፍቶ ማዳምጡ ላይ እንጂ ማለቂያ ለሌው የ “ጠርጥር!
5300” ባህል ተገዥ እመሆን ላይ አይደለም።
5301ይህን ማድረግ ያልቻለ ህሊና ራሱን ቢታዘብ
5302ይሻለዋል።
5303“በደል ደርሶብኛል!
5304ንጽህናዬ ሊታወቅልኝ ይገባል!
5305ማስረጃዬም ይኸው!
5306” ብሎ ወደ ህሊና አደባባይ የሚመጣ ሰው በመሠረቱ
5307ሊከበር ይገባል - በታሪካችን ውሰጥ ይህን ያደረጉ
5308ብዙ አይደሉምና።
5309ካላችሁስ ጥርጣሬን ማጠንከር ተከሶና ታምቶ ፀጥ
5310በሚለው ላይ ነው።
5311ደራሲው ስዬ ነገሮችን እንደማያደባልቁ በመጽሐፉ
5312ምርቃት ላይ አሳውቀዋል።
5313ህዝብ ከርሳችው የሚጠብቀው “የሕወሀትን ታሪክ፤
5314ወሰጠ-ነገሩን፤ ውጣ-ውረዱን፤ ሹም-ሺሩን… ወዘተ
5315እንድተርክለት መሆኑን አውቃለሁ” ብለዋል።
5316ዕድሜውን ከሰጣቸው ለታሪክና ለተመክሮ ቅርስ
5317የሚሆኑ ፅሁፎች እንደሚያቀርቡም ቃል ገብተዋል።
5318ሰለሆነም ለጊዜው ልንተቻቸው የምንችለው
5319ለህትመት ባበቁት “ነፃነትና ዳኝነት በኢትዮጵያ”
5320በሚለው አቅርቦት ላይ ብቻ ነው።
5321እንደኛ ባለ አገር ዳኝንት በገዥው ፓርቲና
5322በመንግሥት ተጽእኖ ውስጥ ለመሆኑ ክርክር
5323የሚያስፈልገው አይመስለኝም -
5324የሁዋላ-ቀርነታችንም ሆነ የንዝንዛችን መነሻ
5325ይኽው ነው።
5326ያቶ ስዬ መጽሃፍ የችሎቱንና የእሥር ቤቱን ድራማ
5327የሲኒማ ያህል ነው ቀርጾ የሚያሳየን።
5328የደራሲው ተማጽኖ “በኔ ላይ የደረሰው የፍትህ
5329መዛባት በመላ አገሪቱ ወስጥ ባሉ ወገኖቼ ላይ
5330እየደረሰ ያለ ለመሆኑ ቋሚ ምስክር ነኝ!
5331” የሚል ይመስላል።
5332ከሌሎች ጋር ተዳምሮ፤ ይሄ ግንዛቤ በሰውዬው
5333የፖለቲካ አስተሳሰብ ለውጥ ላይ ተጽዕኖ
5334አላደረገም ማለት የሚቻል አይመስለኝም።
5335በሁለተኛ ደረጃ ያጤንሁትና ደራሲው በጽኑ
5336እንዲታወቅላቸው የፈለጉት ጭብጥ ደግሞ በርሳቸው
5337ቡድንና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ቡድን መሀከል
5338የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን አስመልክቶ የተፈጠረው
5339ያቋም ልዩነት ሰለባ እንዳደረጋቸው ነው።
5340“በህወሐት ውስጥ ለተከሰተው መሰነጣጠቅ ዋናው
5341መንስኤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዙሪያ የተከሰተው
5342ጦርነት ነበር” በማለት ፈርጠም አርገው
5343ይከራከራሉ።
5344የነስዬ ወገን “የወራሪውን ጦር አከርካሪ መስበር
5345የተያዘውን መሬት እርግጠኛ በሆነ መልኩ
5346እንዲመለስ ያደርጋል፤ በኤርትራ የሚኖረው
5347መንግሥት ለዘለቄታው በኢትዮጵያም ሆነ
5348ባካባቢያችን የስጋት ጠንቅ ያልሆነና ልኩን ያወቀ
5349እንዲሆን ያደረጋል…በሁለቱ አገሮች መሀከል
5350በእንጥልጥል ያሉ ችግሮች ተፈትተው የሁለቱም
5351ግንኙነት በጠንካራ መደላድል ላይ የሚገነባበት
5352ሁኔታ ይፈጠራል” የሚል አቋም እንደነበረው
5353ደራሲው ያስረዳሉ።
5354ባንጻሩ ደግሞ ያቶ መለስ ቡድን፤ በተለይም አቶ
5355መለስ ይህን የመከላከያ ጦርነት ዓላማ
5356እነዳልደገፉና፤ ዓላማው በኢሕአዴግ ምክር ቤት
5357ከጸደቀ በሗላም ለተፈጻሚነቱ መሰናክል እንደሆኑ
5358ነው ጠንክረው የሚያትቱት።
5359የገጽ ማዕቀቤ ብዙ እንዳትት አይፈቅድልኝምና
5360ዝርዝሩን ከመጽሐፉ ብታገኙ ይሻላል እላለሁ።
5361መጽሐፉ እጅግ በርካታ በሆኑ ያገራችን ጉዳዮች
5362ላይ ጮራ ይፈነጥቃል።
5363በፖለቲካው፤ በማህበራዊው፤ በመንግሥት ቁንጮና
5364በዙሪያው ስለተቀመጡት ሰዎች ምንነትና ማንነት፤
5365በረጅም ዘመን መከራ የተፈተነ ወዳጅነት
5366ለህልውናና ለጥቅም እንዴት ተኖ እንደሚጠፋ፤
5367እነዚህን ሁሉ በመጽሀፉ ውሰጥ ከዳር እሰከዳር
5368ተርከፍክፈው ታገኟቸዋላቸሁ።
5369ከላይ እንደጠቆምሁት ደግሞ በመስመሮቹ መሀል
5370የተሰነጉትን ፍንጮች በቅጡ መመርመር የሚችል ብዙ
5371ያገኝበታል።
5372በውጭ የሚኖረው ወጣት ባገሩ ፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ
5373አለመሆኑ ያሳዝነኛል።
5374አንዳንዴማ ከዚያም ያለፈ ነው የሚያደርገኝ።
5375ሰሞኑን ታዲያ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ የተባለ ኦሮሞ
5376ወገኔ ተስፋ ዘራብኝ።
5377ዲሲ በተካሄደው ዓውደ ጥናት ላይ ነው የ24 ዓመቱ
5378ጃዋር “ዱድ” ሥራውን ሲያቀርብ ያዳመጥሁት።
5379የነጠሩ ሊቆች የሚወጡበት የስታንፈርድ
5380ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ነውና የዋዛ 24 ዓመት
5381እንዳይመስላችሁ።
5382ባንፃሩ ደግሞ ከጃዋር ጋር መድረክ የተጋሩት
5383ምሁራን ባገራችን ፓለቲካ ውስጥ ቆይታ ያደረጉ፤
5384የቤታችንን ግድግዳ ጌጦች ያህል የምናውቃቸው
5385ባለውለታዎቻችን ነበሩ።
5386እዚህ ላይ በጃዋርና በሌሎቹ መሀከል የነበረው
5387የዕድሜ ልዩነት ከልክ በላይ እንዳስደመመኝና
5388ጥያቄዎች እንደጫረብኝ ልደብቃችሁ አልችልም።
5389ያነሳቸው ነጥቦች ጆሮዬ ላይ ሲዘምሩብኝ ነው
5390የከረሙትና ላከፍላችሁ ብዕሬን አነሳሁ።
5391ሦስት ቀን ስለፈጀው ዓውደ ጥናት ባንዲት አንቀጽ
5392ውስጥ ጥቂት ልበልና ጃዋር በምሳሌነት
5393እንዲያገለግለኝ ወደመረጥሁት ወደ ወጣቱ ጉዳይ
5394እመለሳለሁ።
5395ያለጥርጥር እጅግ የተሳካ ስብሰባ ነበር።
5396አዘጋጆቹ ብዙ ጉልበት እንዳፈሰሱበት የሚመሰክሩ
5397አሻራዎች ስላየሁ አብዝቼ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
5398አቅራቢዎቹም፤ ታዳሚውም ሀላፊነታቸውን ሲወጡ
5399ያየሁት ፍጹም በሰከነ ቋንቋና በደርባባ ባህርይ
5400ስለነበር ስልጡን ፖለቲካ ተገቢ ቦታውን እያገኘ
5401ነው አልሁ።
5402ታዲያ በባህላችን “ግን” ካልተጨመረበት ምስጋና
5403ምስጋና አይሆንምና ለወደፊቱ ይታሰብበት ዘንድ
5404ላዘጋጆቹ ትንሺ ቅር ያለኝን ነገር ላካፍላቸው
5405እወዳለሁ።
5406የኢትዮጵያ ችግር በርካታ ሆኖባችሁ ይመስለኛል
5407ሁሉን ርዕስ ለመሸፈን ባደረጋችሁት ሙከራ ዓቢይ
5408ጉዳዮች ላይ ሊያወያዩን የመጡ ምሁራን ሰዓት
5409እያነሳቸው ነገራቸውን እንዲቆራርጡ መገደዳቸው
5410አሳቆኛል።
5411ያቅራቢዎቹን ቁጥር ሰብሰብ ማድረግ ቅያሜ
5412የሚያስከትል ሆኖባችሁ ይሆን?
5413የጃዋር አቀራረብ የወጣት ለዛና የወጣት ነፃ
5414አስተሳሰብ የተንጸባረቀበት ነበር።
5415በዝግጅት ደረጃም የተሻለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ -
5416ፓወር-ፖይንት ተክኖሎጅን ተጠቅሟል፤ የኢትዮጵያ
5417ፖሊቲካ ምን ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ
5418ለማስረዳት በቃላት ጋጋታና በ “እጠቅሳልሁ” “አልጠቅስም”
5419አባዜ አልታሰረም።
5420በአዕምሮ ውስጥ ታትሞ በሚቀር ቪዡዋል ቻርት
5421አማካይነት በሁለት የፖለቲካ ጠርዞች ላይ
5422የሚገኙትን አስተሳሰቦች ደህና አድርጎ ተንትኖ
5423መፍትሔው መሀል ላይ መገናኘት ብቻ መሆኑን
5424በሚገባ አስረድቷል።
5425በርሱ ስሌት በ “ብሔርተኛውም” ሆነ “ኢትዮጵያዊነት”
5426በሚለው ካምፕ ውስጥ አክራሪ ዓይነት አቋም
5427ያላቸው ከ 20% አይበልጡም።
5428ቀሪው 80% ፍጹም ሠላማዊ ኑሮ ፈላጊና የብሔር
5429ቅርሱን ለማዳበር የሚያስችል ሥርዓት እስካገኘ
5430ድረስ በኢትዮጵያዊነት መለያው የሚኮራ ነው።
5431“ሆኖም ግን በየመድረኩና በየቤቱ ከሚመነዘሩት
5432የመልካም ምኞት መግለጫዎች ባሻገር ተጨባጭ ሥራ
5433መሠራት አለበት” አለ።
5434“ፈተናው እዚህ ላይ ነው ወገኖቼ!
5435አዲሱ ትውልድ ለዙሪያ ጥምጥም ፍልስፍና፤
5436ለዲስኩርና ለቃላት ማንጠር ትዕግሥትም አንጀትም
5437የለውም” ሲል አስጠነቀቀ ጃዋር ድምጹን ከረር
5438አድርጎ።
5439አውራ ጣቱንና የታጠፈች ሌባ ጣቱን ሕዝቡ
5440እንዲያይለት ከፍ አድርጎ ደጋገሞ እያፋተገ “ይህ
5441ትውልድ የ ሾው-ሚ-ዘ መኒ!
5442ትውልድ መሆኑን መቀበል አለብን!
5443” አለ።
5444ጭብጨባውና ቻቻታው መለኪያ ከሆነ በዚያች ወቅት
5445የታዳሚውን ቀልብ ሙልጭ አድርጎ ኪሱ እንዳስገባ
5446አልጠራጠርኩም።
5447ለዚህም ነው “ዱድ!
5448ብሩን አሳዬኝ!
5449” የምትለዋን የጽሑፌ ርዕስ ያደረግኋት።
5450ጃዋር “ሾው-ሚ-ዘ መኒ!
5451” ሲል ወጣቱ ትውልድ እንደሸቀጥ በገንዘብ
5452የሚገዛ ነው ለማለት አልነበረም።
5453“ባዶ ቃላት አትመግበኝ!
5454ከዚህ የጥርጣሬ ዘመን ወደመተማመን ዘመን እንዴት
5455እንደምንሸጋገር ያለህን ተጨባጭ የመፍትሄ ሀሳብ
5456እፊቴ ቁጭ አድርግልኝ” ማለቱ ነበር።
5457የጃዋር ትውልድ ባጠቃላይ፤ የአማራትግሬ ዝርያ
5458የሌለው ክፍል ደግሞ በተለይ፤ አዲሱ
5459የኢትዮጵያዊነት ገጽታ በማያሻማና ቅሬታን
5460በሚያጠፋ መልኩ ተነድፎ ሲተገበር መሳተፍ
5461እንደሚፈልግ ጃዋር አሳውቋል።
5462ይህን ዕውን ለማደረግ የሚወሰዱ ርምጃዎችም
5463በዕለት-ተለት ግንኙነቶቻችን ሳይቀር
5464የሚንጸባረቁ መሆን እንደሚገባቸው በአጽንኦት
5465ነበር ያስረዳው።
5466ነጥቡን ለማስረገጥ መሰለኝ፤ መድረኩ ላይ ከርሱ
5467ጋር የተሰየሙትንና ዞር ብሎም ታዳሚውን ሕዝብ
5468በዓይኑ ቃኘት አድርጎ “ይህ ፎቶግራፍ
5469ኢትዮጵያዊነትን በቅጡ ስለማንጸባረቁ እርግጠኛ
5470አይደለሁም” አለ።
5471በዚህ ጊዜ ነበር የጉባዔው አዘጋጆች ወደ መድረኩ
5472ብቅ ብለው በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያገባቸውን ሁሉ
5473መጋበዛቸውን የገለጹት።
5474በድረ ገፆች አማካይነት ከተደረገው ግልጽ ግብዣ
5475በተጨማሪ ካንዳንዶቹ ጋር ቀጥታ ግንኙነቶች
5476ተደርጎ አመርቂ ምላሺ እንዳልተገኘ አስረዱ።
5477እዚህም ላይ “ሕምምም!
5478” ያሰኘ ቅጽበት ተፈጥሮ ነበር።
5479ጃዋር ያዘጋጆቹን ጥረት አድንቆ እርሱ ራሱ
5480ጉባኤው ላይ ቢገኝ ምን ዓይነት ምቾት
5481እንደሚሰማው ጥርጣሬ አድሮበት እንደነበረ
5482ተናዘዘ።
5483ሆኖም ግን ላቀረባቸው ነጥቦች ሕዝቡ ይሰጠው
5484የነበረውን ከበሬታ ካዬ በኋላ በውሳኔው እንደኮራ
5485አልሸሸገም።
5486በመቀጠልም “የቀሩት ወገኖቻችን ካልመጡ
5487ከመንገዳችን ወጥተን የምናደርገው የማግባባትና
5488የማረጋጋት ሥራ በቂ አልነበረም ማለት ነው” ብሎ
5489በዚህ ረገድ ብዙ እንደሚቀረን አስተማረ።
5490ይህ ሰው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ገና ብዙ ሚና
5491እንደሚኖረው፤ በዕድሜም በብሔሩም በዕምነቱም
5492እርሱን መሰል ዜጎችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ
5493አስተዋጻኦ እንደሚያደርግ ፍንትው ብሎ ነው
5494የታየኝ።
5495በዚህ ስብሰባ ላይ ወጣቱን ትውልድ ወደፊት
5496የማምጣቱ አስፈላጊነት አንገብጋቢ እንደሆነ
5497በብዛት ተወስቷል።
5498የ 24 ዓመቱ ወጣት 55+ ሶች ጋር መቅረቡ ነው ጥያቄውን
5499ከምኔውም በበለጠ ትርጉም የሰጠው።
5500አንዳንዶቹ አቅራቢዎች ይህን ጉዳይ ሲያወሱ ጥፋት
5501እንዳጠፋ ሰው መሸማቀቅ አይቸባቸዋለሁ።
5502በዚህ ፈጽሞ አልስማማም።
5503የቀድሞዎቹ ብዙ መሥዋዕትነት ለመክፈላቸውና ብዙ
5504ለማስተማራቸው አጠያያቂ አይደለም።
5505በወቅቱ ተረካቢ አለማፍራታቸው፤ አንዳንዶቹ
5506ደግሞ ወንበር የሙጥኝ ማለታቸው፤ ከሁሉም በላይ
5507ደግሞ ወጣቱን የሚስብ ራዕይና የሚጥመው አሠራር
5508አለመንደፋቸው ጥፋት ነው።
5509አባጣ ጎባጣ ያልበዛበት የትውልድ ሺግግር
5510ሳያደርጉ በየጓዳቸው ቢከተቱ ግን የጥፋትም ጥፋት
5511ይሆንባቸዋል።
5512ስለዚህ እስቲ ፈረንጆቹ “ሜንተርሺፕ” የሚሉትን
5513ነገር ይሞክሩት።
5514ያንዳንድ ወጣት እጅ ይያዙ።
5515እንግዲህ ያልሆነ ትርጉም ለመስጠትና አጉል
5516ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አትጣደፉ!
5517ጃዋር በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን፤ የነገው እንጅ
5518ያለፈው ብዙም ፋይዳ እንደሌለው የተረዳ፤ ነገር
5519ግን አዲሱ የኢትዮጵያዊነት ራዕይ አንዱን እላይ
5520ሌላውን እታች በማያደርግ መልኩ በድፍረትና
5521በስልት መቀረጽ እንዳለበት ነው ያሳወቀው።
5522ዜጎችንና ብሔረሰቦችን የሚያቀራርብ፤
5523መተማመንን የሚያሰርጽ ድልድይ በያቅጣጫው
5524ተዘርግቶ ባዲስ ጥርጊያ መንገድ ጉዟችንን
5525እንድንጀምር ነው የሚመኘው።
5526ችግራችንን በሠላማዊ ትግልና ተጨባጭ ርምጃዎች
5527በመውሰድ እናስወግድ ነው የሚለው።
5528ለኔም ለናንተም ጆሮ ከዚህ የተሻለ ጥዑም ሙዚቃ
5529አለ?
5530የጃዋርን ዋና ቁምነገር አትርሱ።
5531ወደድንም ጠላንም አዲሱ ትውልድ መድረክ ላይ ብቅ
5532እያለ ነው።
5533የተፈጥሮ ግዴታ ጭምር ነውና።
5534አዲሱ ትውልድ ደግሞ የ “ሾው-ሚ-ዘ መኒ!
5535” ትውልድ ነው።
5536ከተስፋ ይልቅ ተጨባጭ ርምጃ፤ ከጥላቻ ይልቅ
5537ፍቅር፤ ከቃላት ጋጋት ይልቅ ቅልጥፍ ባለ ቋንቋ
5538እንድናወጋው ነው የሚፈልገው።
5539ለሚንዛዛና ለቃላት አንጥረኛ ጊዜ የለውም።
5540ለርሱ ጊዜ ወርቁ ነው።
5541በሕዝብ አዕምሮ ውስጥ ጥርጣሬ የመፍጠርን ያህል
5542የፕሮፓጋንዳ ድል የለም።
5543ለዚህ ማስረጃ ከፈለጋችሁ የሂትለር ቀኝ-እጅና
5544የፕሮፓጋንዳ ጠበብት የነበረውን ጎብልስን
5545ጠይቁት።
5546ዓለም ሲፈጠር የት ነበርክ ትሉኛላችሁ እንጅ
5547ከያን ጊዜ ጀምሮ ይመስለኛል ጥርጣሬ መፍጠር
5548የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆነው።
5549ቀልጠፍ ብዬ ወደተነሳሁበት ርዕስ ልመለስና “በርግጥ
5550ተቃዋሚው አገር የመምራት ብቃት አለው?
5551” የሚል ጥያቄ መናፈስ የጀመረው በ‘97 ምርጫ
5552ማግስት እንደነበር ትዝ ይለኛል።
5553ቅንጅት ውስጥ በተፈጠረው ውዝግብ ቆሺታቸው ያረረ
5554ደጋፊዎች ሳይቀሩ ነው አባባሉን የብስጭታቸው
5555መወጫ ያደረጉት - ትልቅ ስህተት!
5556በጣም ትልቅ ስህተት!
5557ኢሕአዴግ ደግሞ እንኳንስ ይችን ያህል ቀዳዳ
5558አግኝቶ እንዲያውም እንዲያው ነው በሕዝቡ ውስጥ
5559የተፈጠረውን የጥርጣሬና የብሺቀት መንፈስ ደህና
5560አድርጎ አራገበው።
5561እዚህ ላይ ባንድ ነገር እንስማማ።
5562የሰው ልጅ በፍጥረቱ ተጠራጣሪና የ7 ቀን 24 ሠዓት
5563ኑሮው በስጋት የታጠረ መሆኑን አትክዱኝም።
5564ለዚህ አይደል እንዴ ኢንሹራንስ የሚገዛው?
5565አጥር የሚያጥረው?
5566ብቻውን የሚያወራውና የሚቃዠው?
5567ልብ ብላችሁ ከሆነ ፖለቲከኞች ይህን ሰብዓዊ
5568ደካማ ጎን ደህና አድርገው ነው የሚበዘብዙት
5569“ነውጠኞች የቀድሞውን ሥርዓት ሊያመጡብህ ነው!
5570እኛ ከሌለን አገር ትበተናለች!
5571ሠላማዊ ኑሮህ ይናጋል!
5572የብሔረሰቦች ነጻነት ይገፈፋል!
5573የርስ በርስ ጦርነት ይነሳል!
5574የስልምና አክራሪዎች አገርህን ይወሩታል!
5575ተቃዋሚው አገር የማስተዳደር አቅም የለውም!
5576
5577ታዲያ ሁለት ዓቢይ ችግሮች ይታዩኛል።
5578አንደኛው ችግር ተቃዋሚው ወገን የዚህን
5579ፕሮፓጋንዳ አደገኛነት ተገንዝቦ ቀጣይነት ያለው
5580አምካኝ ፕሮፓጋንዳ በፈረንጁ ሰፈር ጭምር
5581አለማካሄዱ ሲሆን ሁለተኛው ችግር ደግሞ
5582የተቃዋሚው የፖለቲካ ገጽታ በመንግሥት
5583እንዲነደፍ መፈቀዱ ነው።
5584በሁለቱም ላይ ያለኝን የተሙን ሀሳብ
5585አካፍላችኋለሁ።
5586በደፋር አስተያየት ልጀምርና ይህ ዘመን
5587ኢትዮጵያን ወደከፍተኛ የዕድገት ደረጃ
5588ለማሸጋገር ከምን ጊዜም የበለጠ ተነሳሺነት
5589የገነነበት፤ የሰለጠነ የሰውና የማቴሪያል ኃይል
5590የተከማቸበት ነው እላለሁ።
5591በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚው ክፍል፤ በተለይም “መድረክ”
5592ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያለው ብቃት ከየትኛውም
5593ፓርቲና ስብስብ የላቀ ነው እላለሁ።
5594እንዳላሰለቻችሁ በሦስት ዋቢዎች ብቻ ልወሰን።
5595የፖለቲካ ፕላትፎርም።
5596የአንድነትመድረክ ፖለቲካ ፕሮግራም የዜጎችን
5597ችግር አበጥሮ የተረዳ ብቻ ሳይሆን ያጭርና
5598የረጅም ጊዜ መፍትሄዎቻቸውንም የሚዘረዝር ነው።
5599ያልተገደበ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት
5600እንደሚኖር፤ የግል መሬትና ንብረት የሕገ
5601መንግሥት ጽኑ ድጋፍ አግኝተው የኤኮኖሚና
5602የማሕበራዊ እድገት አንቀሳቃሺ ሞተር እንደሚሆኑ፤
5603የኢትዮጵያ አንድነትና ልኡዋላዊነት ለድርድር
5604የሚቀርብ እንደማይሆን፤ ብሔረሰቦችን
5605የሚከፋፈል ፖሊሲ ተወግዶ ያንድ አገርና ያንድ
5606ታላቅ ራዕይ ልጆች በሚያደርግ ፖሊሲ እንደሚተካ፤
560785ሚሊዮን ሕዝብ ህልውናውንና ስትራቴጅያዊ
5608ጥቅሙን አደጋ ላይ በማይጥል መልክ ወደ ባሕር
5609የመውጣት መብቱ እንደሚከበር፤
5610ወዘተ ያስቀምጣል።
5611ትናንት የቅንጅት ዛሬ ደግሞ ያንድነት የሆነው
5612ራዕይ ገዥው ፓርቲ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ከሚለው
5613ራዕይ በዓይነትም በጥራትም የተሻለ፤ እጅግ በጣም
5614የተሻለ ለመሆኑ ሕዝብ በቅጡ ያውቃል።
5615ለዚህ ነበር በ ‘97ቱ ምርጫ ቅንጅትን የሾመው።
5616ለዚህም ነው ዛሬ በአንድነትና በመድረክ ዙሪያ
5617በሚያስደንቅ ቁርጠኝነት እየተሰባስበ ያለው።
5618ሌላውን ለጊዜው እንተወውና በትግራይ ክልል
5619እየተገለጸ ያለው የፓራዳይም ለውጥ
5620አላስደነቃችሁም?
5621ጥልቅና የምሥራች ትርጉም እንዳለው
5622አልተረዳችሁም?
5623በቢሮክራሲ ልቀጥል።
5624ማንኛውም ለሥልጣን የሚበቃ መንግሥት ሀገሪቱ
5625አዳብራ ባቆየችው ያስተዳደር መዋቅር ቢሮክራሲ
5626መገልገሉ ሀቅ ነው።
5627ይህ የጦር ሠራዊቱን ይጨምራል።
5628ምኒልክ ከዮሐንስ፤ ኃይለ ሥላሴ ከምኒልክ፤ ደርግ
5629ከኃይለ ሥላሴ፤ ኢሕአዴግ ከደርግ በተረከቡት
5630ቢሮክራሲ ነው አገር የመሩት።
5631ሌላው ሀቅ ደግሞ እያንዳንዱ መንግሥት
5632የተረከበውን ቢሮክራሲ አሻሽሎና አዳብሮ
5633ለሚቀጥለው መንግሥት የማስረከቡ ዕውነታ ነው።
5634በዚህ ስሌት እንደ ኢሕአዴግ ጠንካራ መሠረት
5635ያለው፤ በተማረ የሰው ኃይልና በዘመናዊ
5636የማኔጅመንት ዘይቤዎች የዳበረ ቢሮክራሲ የወረሰ
5637መንግሥት አልነበረም።
5638ኢሕአዴግ ራሱ ምን ዓይነት
5639የመንግሥት-አስተዳደርና የማኔጅመንት ልምድ ይዞ
5640በ1991 አዲስ አበባ እንደደረሰ የያኔ ሬዙሜውን
5641ማዬት ይበቃል።
5642በራሴ ላይ የጣልኩት የገጽ ማዕቀብ ከለከለኝ
5643እንጅ ከአፄ ዮሐንስ እስከ ኢሕአዴግ ያሉት
5644መንግሥታት ሥልጣን ሲይዙ የነበረባቸውን ፈተና
5645አነጻጽርላችሁ ነበር።
5646ላለፉት መንግሥታት ከልብ ታዝኑላቸዋላችሁ።
5647እዚህ ላይ ያች ልማዴ እንዳትቀር አንዳፍታ
5648ከመሥመር ወጣ ልል ነው።
5649ስለ ቢሮክራሲ ካወጋን ዘንድ “ቢሮክራሲ” ከፍተኛ
5650የሥም ማጥፋት ዘመቻ የተካሄደበት ያገር ኃብት
5651ነውና ይህን የተዛባ አመለካከት ማቃናት አለብን
5652እላለሁ።
5653ካጭር ትርጉሙ ብንነሳ “ቢሮክራሲ” ያንድ ትልቅና
5654ውስብስብ መዋቅር አስተዳደራዊ አቅም ነው።
5655በሹመት እየመጡ አናት ላይ ጉብ ከሚሉት አላፊዎች
5656በስተቀር ሌላው ሕዝበ-ሠራዊት በሙያ ሚዛን
5657እየተለካ እንደሚቀጠርበት ግዙፍ አገራዊ ፋብሪካ
5658ተደርጎ ሊታይ ይችላል።
5659መንግሥት ቢለወጥ፤ ሹም ከርቸሌ ቢወርድ፤ ጎርፍ
5660ቢያጥለቀልቅ፤ ቢሮክራሲ ከቦታው ንቅንቅ አይልም።
5661እንደ ዝቋላ ተራራና እንደ አዋሺ ወንዝ
5662ካስቀመጡት ቦታ የሚገኝ ውሉን የማይስት ያገር
5663ኃብት ነው ማለት ነው።
5664ቢሮክራሲን ያልሆነ ጥላሸት የቀባው ባላባቱን፤
5665ከበርቴውን፤ ካፒታሊስቱንና ኢምፔሪያሊስቱን
5666የሕዝብ ጠላት በማድረግ አንጀቱ ያልራሰለት
5667የኮሚኒስት ሥርዓት ነበር።
5668እንዲያው በሞቴ ኮሚኒስቶች የሚሉትን ከቁብ
5669የሚጥፍ ሰው ተርፎ ይሆን?
5670በፓራዳይም ለውጥ ላጠቃል።
5671ሦስተኛው ቁምነገር ደግሞ ለመድረክ መፈጠር
5672ምክንያት የሆነ የፖለቲካ ክስተት መኖሩ ነው።
5673የብሔር ፖለቲካ ከመሣሪያነት አልፎ ማቴሪያላዊም
5674ሆነ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንደማያስገኝለት ሕዝቡ
5675መረዳት ከጀመረ ሰንበት ብሏል።
5676መቼም ፖለቲከኞች ብልጥ አይደሉም?
5677- የፓራዳይም ለውጥ ሕዝብ ውስጥ ሥር መስደዱን
5678ከማረጋገጣቸው በፊት የአቋምና ያሰላለፍ ለውጥ
5679አያደርጉም።
5680ለዚህ ነው እንገነጠላለን ከሚሉት ጀምሮ ለዘብተኛ
5681እስከሚባሉት ድረስ በብሔር ፖለቲካ ላይ ያላቸውን
5682አቋም ሲከልሱ እያየን ያለነው።
5683ዓለም ወደ አንድ ትንሺ መንደርነት እየተለወጠች
5684በምትገኝበት በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የብሔር ፖለቲካ
5685የሚያራምዱ ሰዎች ከሌላ ፕላኔት እንደመጡ ፍጡሮች
5686ይቆጠራሉና መለወጣቸው እሰዬ የሚያሰኝ ነው።
5687የብሔር ፓለቲካ ያራምዱ የነበሩ ፓርቲዎች
5688በመድረክ ውስጥ መሰባሰባቸው፤ በብሔር ፖለቲካ
5689ዓለም ውስጥ ስማቸው የተጠራ እንደነ ስዬ አብርሃ፤
5690ነጋሶ ጊዳዳ፤ ገብሩ አሥራት፤ አረጋሺ አዳነና
5691ቡልቻ ደመቅሳን የመሳሰሉ በመድረክ ውስጥ
5692መሰባሰባቸው አንዳንዶች ሊያምኑ ከሚፈልጉት
5693በላይ ጥልቅ መልዕክት ያዘለ ነው።
5694ባጋጣሚና በድንገት የተከሰተ ፓራዳይም ሳይሆን ከ
569545 ዓመት ተመክሮ የተወለደ ነው።
5696እዚህ ላይ “ተቃዋሚው ኢትዮጵያን ለመምራት ብቃት
5697አለው?
5698” ከሚል ጥያቄ ጋር ምን አገናኘው ብትሉ
5699አልፈረድባችሁም።
5700አያችሁ!
5701ኢሕአዴግ ባለሙያና ደጋፊ የሚጨልፈው የብሔር
5702ፖለቲካን በውድም በግድም ከሚያራምዱ ቁጥራቸው
5703እየቀነሰና ወርዳቸው እየጠበበ ከሚገኝ
5704የህብረተሰብ ኩሬዎች ነው።
5705ባንጻሩ ደግሞ መድረክ ደጋፊና ባለሙያ የሚቀዳው
5706እጅግ ሰፊ ከሆነ የህብረተሰብ ሃይቅ ነው።
5707ለዚህ ነው ተቃዋሚው ክፍል፤ በተለይም “መድረክ”
5708ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያለው ብቃት ከየትኛውም
5709ፓርቲና ስብስብ የላቀ ነው ያልኩት - እመነሻዬ ላይ።
5710የለየልኝ ቅን-አሳቢ መሆኔን ደጋግሜ ተናዝዣለሁና
5711ቀሪዎቹ በብሔር ፖለቲካ ጠርዝ ላይ የሚገኙ ያገሬ
5712ልጆች ከፊታቸው የተጋረደውን መጋረጃ እየቀደዱ
5713አንድነትን፤ ኢትዮጵያዊነትንና ትልቅነትን
5714እንዲያቅፉ እመኛለሁ።
5715ሹም መሆን ብዙ ፈተና አለው ወዳጄ!
5716አንዲት አነስተኛ ወረዳ ውስጥ አስተዳዳሪ ሆኖ
5717የተመረጠ ሰው የህዝቡን ተሳትፎ ለማግኘት ቁርጥ
5718ሀሳብ ያደርጋል።
5719የነጋዴው፤ ያስተማሪው፤ የተማሪው፤ የገበሬው
5720በር አልቀረውም።
5721የሁሉንም አንኳኳ።
5722አንዱን ቀን እግሩ ካንድ ገበሬ ቤት ይጥለውና
5723“የዛሬው አመጣጤ አንድ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት
5724እንዲሳተፉልኝ ለመጠዬቅ ነው” ይላል
5725አስተዳዳሪው።
5726ይችን ጨዋታ ያካፈለኝ አንዱ እጁ ከመጽሐፍ አንዱ
5727ደግሞ ከላፕቶፕ ገበታ ላይ የማይነሳ ሌላው ወዳጄ
5728ነው።
5729ይንግሊንግ ቢራችንን ይሄኔ እኮ ያሜሪካ ቀዳማዊ
5730ቢራ መሆኑን የማታውቁ ትኖራላችሁ!
5731 ጨብጠን በሌላ ርዕስ ላይ ገራ-ገር ጨዋታ
5732ስንሰልቅ ነው አንቀጹን ያነበበልኝ።
5733አጉል ልማድ አይለቅምና ሀሳቤ እንደገና ወደኛው
5734ጉዳይ አቀና
5735ስንቶቻችን ነን የዶሮዋን ያህል አስተዋጽኦ
5736እያደረግን ያለነው?
5737ስንቶችስ ናቸው የበሬውን ያህል ራሳቸውን
5738አሳልፈው ለመስጠት የቆረጡ?
5739“ሠላማዊ ትግል” በሚለው አንቀጽ ውስጥ “ሠላም”
5740የምትለዋ ቃል አዘናጊ ሆና ትታየኛለች - በዚህ ጎራ
5741የሚታገሉ ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው ያለችግርና
5742በሠላም ውለው የሚያድሩ ታስመስላለችና።
5743ዕውነቱ ግን ይህ አይደለም።
5744በሙሉም ይሁን በከፊል አዱኛቸውን እርግፍ አርገው
5745የሚጥሩ ሁሉ ችግር ይኖራቸዋል።
5746ፓርቲዎቹስ ቢሆኑ ከየት በመጣ ገንዘብ ነው
5747ከክልል ክልል ተዘዋውረው በምርጫው የሚወዳደሩት?
5748ሕዝቡስ ጋር የሚገናኙት?
5749በርግጥ ከመንግሥት የሚሰጥ በጀት እንዳለ
5750ሰምቻለሁ።
5751ግን ዘጠኝ ሺህ የኢትዮጵያ ብር የት ታደርሳልች?
5752አባባሌ አገር ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን መደገፍ
5753የዜግነትና የህሊና ግዴታ አለበት ለማለት ነው።
5754የዚህ ወይንም የዚያ ፓርቲ ደጋፊ መሆናችን
5755አይደለም ቁምነገሩ።
5756ለሀገራችን ዴሞክራሲንና ሠላምን የምንመኝ
5757እስከሆነ ድረስ ለዚህ ለግንቦት 2002ቱ ምርጫ
5758የሚረዳ አሥርና ሃያ ብር ለሚመስለን ፓርቲ
5759ማዋጣቱ ላይ ነው ቁምነገሩ።
5760እርስ በርስ የሚጋጭ ሃሳብ ያዘለ ስለሚመስል “የባላንጣዎች
5761ቡድን” ብሎ ነገር ግር ሊል ይችላል።
5762ስመ ጥሩዋ የታሪክ ተመራማሪ ዶሪስ ጉድዊን “
5763” በሚል ርዕስ ስለ አብርሃም ሊንከን
5764ያቀለመችው ድንቅ መጽሀፍ ነው ። ከዛሬ ነገ
5765አነበዋለሁ በሚል አባዜ ውስጥ መጠመዴን የታዘበ
5766ወዳጄ ነው ሰበብ ለማሳጣት ጭምር ይህን መጽሐፍ
5767ጀባ ያለኝ።
5768“ስለ አብርሀም ሊንከን አሥር ሺህ የሚደርሱ
5769መጻህፍትና መጽሔቶች ታትመው ሳለ ዶሪስ ምን
5770ይሁን ብላ ነው ሌላ መጽሐፍ የምትጨምረው?
5771” ያሉ ሁሉ አፋቸውን በጨው አጥበዋል።
5772ዶሪስ ታሪክን የምታበጥረው ለርሷ ብቻ በተቸረ
5773ዓይነት የተመራማሪነት ስልት ነውና መጽሐፉ
5774በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንብብያን አገኘ።
5775“በሥልጣን ላይ ያሉትና ለሥልጣን የሚዘጋጁት
5776መሪዎቻችን ይህን መጽሐፍ በጥሞና ቢያነቡ ምን
5777ያህል ትምህርት ባገኙበት?
5778” አልሁ።
5779“ባንባቢነት ለሚታሙት ለጠቅላይ ሚንስትር መለስ
5780ዜናዊ ቀበቶዬን አስሬም ቢሆን ገዝቼ ልላክላቸው?
5781” የሚል ነገርም ዳዳኝ።
57821855-1865 አሜሪካ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በአጭር
5783ትረካ ልጀምር።
5784ዘመኑ ባሜሪካው ሰሜናዊና ደቡባዊ ስቴቶች መሀከል
5785የጥቅም፤ የተደማጭነትና ያስተሳስብ ፉክክር
5786የጎላበት ነበር።
5787ሁለቱን ወገኖች ያንድ ታሪክ ሕዝብና ያንድ ትልቅ
5788ራዕይ ማሕበርተኛ አድርገው የሚያስተሳስሩ ድርና
5789ማጎች የመብዛታቸውን ያህል ክልል-ተኮር ስሜቶችና
5790የኤሊቶችን ጥቅም ለማስከበር ሲባል የተፈለሰሙ
5791የፖለቲካ እንዝርቶች የጦዙበትም ዘመን ነበር።
5792የሰሜኑ ኤሊት በሁለት ዓቢይ ምክንያቶች ባርነት
5793እንዲያከትም ፈለገ።
5794አንደኛው ምክንያት የባሪያዎች ነጻ መውጣት
5795በታሪካዊው ያሜሪካ ሕገ መንግሥት ውስጥ በጉልህ
5796የተቀረጸውን የሰው ልጆች እኩልነት ዕውን
5797የሚያደርግ ሲሆን ሁለተኛዋና ስውሯ ምክንያት
5798ደግሞ የባርነት መወገድ ሰሜኑ ክፍል ለልማትና
5799ለፋብሪካዎች መስፋፋት የሚያስፈልገውን የሰው
5800ኃይል ስለሚያፈልስለት ነበር።
5801ብሔራዊ አንድነትን የሚፈታተን፤ የሕይወትና
5802የንብረት ጥፋትን የሚያስከትል ጥቁር ዳመና
5803ባንዣበበበት በዚያ ቀውጢ ዘመን አብርሃም ሊንከን
5804በፕሬዚደንትነት ተመርጦ ካቢኔ ለማቋቋም
5805ይንደፋደፍ ነበር።
5806ዕውቀቱም ልምዱም ሁሉም አላቸው የሚባሉት ምሁሮች
5807እርስ በርስ ሲናቆሩ ነበርና ሊንከን ሹልክ ብሎ
5808ፕሬዚዳንት የሆነው ባገሪቱ ውስጥ የጥርጣሬ አየር
5809ሰፈነ።
5810በዚያው ልክም የሊንከን ጣጣ በረከተ
5811የሕዝቡንና አብረውት የሚሠሩትን ሰዎች አመኔታ
5812ባጭር ጊዜ ውስጥ ማሸነፍ ነበረበት፤ የበርካታ
5813ተጻራሪ ሃይሎችን የጥቅም ግጭት ማስታረቅ
5814ነበረበት፤ የርስ በርስ ጦርነቱ የሚጠይቀውን
5815የሰውና የማቴሪያል ኃይል ስለማግኘቱ እርግጠኛ
5816መሆን ነበረበት፤ ባሪያዎች ነፃ መውጣት አለባቸው
5817በሚለው ጥያቄ ላይ በራሱ ፓርቲ ውስጥ እንኳ ወጥ
5818አመለካከት አልነበረምና እንዲጣጣም ማድረግ
5819ነበረበት፤ በዲፕሎማሲው መስክ ደግሞ
5820አውሮፓውያን “ሕዝባዊ መንግሥት” የሚሉት ነገር
5821እያፈረጠመ መሄዱ ያባንናቸው ነበርና
5822ኮንፌደርሬቱን ቢደግፉ የኃይል ሚዛን ወደደቡብ
5823ያጋድላል የሚል ስጋትም ያስጨንቀው ነበር።
5824አሜሪካ እንዲህ ያለ ፈተና ገጥሟት አያውቅም።
5825ጥርጣሬ የነገሰበትና ልጆቿ ፊትና ጀርባ የሆኑበት
5826ጊዜ አልነበረም።
5827በብዙ መስዋዕትነት የተገነባው ብሔራዊ አንድነቷ
5828እንዲህ የተፈተነበት ወቅት አልነበረም።
5829የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም ብዙ ፈተናዎች አልፎ
5830ነው የአብርሃም ሊንከን ቡድን ዛሬ የምናውቃትን
5831የዴሞክራሲ ቀንዲል፤ የሁሉ መጠጊያና መጠለያ
5832የሆነችውን አሜሪካን ያቆየን።
5833“የባላንጣዎች ቡድን” ሊንከን አሜሪካ
5834የገጠማትን ታላቅ ፈተና በድል መወጣት የምትችለው
5835በዕውቀትም በልምድም የነጠሩ ሰዎችን ማሰባሰብ
5836ከቻልሁ ብቻ ነው ብሎ በጹኑ ያምን ነበር።
5837አስተዳደሩ ሁሉንም ስቴቶች እንደመስታወት
5838የሚያሳይና ሁሉንም በሀቅ የሚወክል፤ ስጋቶችንና
5839ምኞቶችን ያገናዘበ እንዲሆን ይፈልግ ነበር።
5840ከዚህ ዕምነቱ ተነስቶ ነው በምርጫ ላይ
5841ያሸነፋቸውን ባላንጣዎቹን ጭምር በካቢኔው ውስጥ
5842እንዲያገለግሉ ቅድሚያ ጥሪ ያደረገላቸው።
5843“ገና የሺንፈቱ ምሬት ሳይጠፋላቸው፤ አንዳንዶቹ
5844ደግሞ እንደሚንቁት እያወቀ ባላንጣዎቹን
5845አብረውት እንዲሠሩ መጋበዙ የለየለት የዋህነት
5846ነው!
5847” አሉ ያደባባይ ተችዎችና ጋዜጠኞች።
5848ሊንከን በራሱም በዜጎቹም ላይ ያለው ዕምነት
5849ጠንካራ ነበርና ተፎካካሪዎቹን እቤታቸው ድረስ
5850እየሄደ ከማግባባት ወደኋላ አላለም።
5851አሜሪካ የገጠማት ፈተና የያንዳንዳቸውን
5852እውቀትና መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ አሳሰባቸው።
5853ጥሪውን ከተቀበሉ ደግሞ በሙሉ ነጻነትና ከሙሉ
5854ድጋፍ ጋር እንደሚሠሩ ቃል ገባላቸው።
5855አገሪቱ ያለችበትን ችግር በፖለቲካው ውስጥ
5856ከሰነበቱት ባላንጣዎች ይበልጥ የሚረዳ
5857አልነበረምና፤ እንዲሁም ደግሞ በሊንከን
5858ያልተፈተነ ያመራር ችሎታ ሀሳብ ገብቷቸው ነበርና
5859ባላንጣዎቹ ጥሪውን ተቀብለው ካቢኔውን ተቀላቀሉ።
5860ዊሊያም ሲዋርድን፤ ኤድዋርድ ስታንተንን፤
5861ሳልመን ቸስን፤ ኤድዋርድ ቤትስን፤ እነዚህን
5862ከባድ ባላንጣዎች አጠገቡ ሳያደርግ መረጋጋትና
5863ድል አጠራጣሪ ይሆኑበት ነበርና ሊንከን በጣሙን
5864ነበር የዘየደው።
5865በሳል፤ ታዋቂና ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ያላቸውን
5866ፖለቲከኞች ባንድ ካቢኔ ውስጥ ማሰባሰቡ በጣሙን
5867ጠቀመው።
5868የካቢኔው ተቀዳሚ ተግባር ጦርነት እንዲቆምና
5869እርቅ እንዲወርድ የሚያደርጉ ሀሳቦችን
5870በጥልቀትና በድፍረት ማማንጨት ነበር።
5871ከሀገር መገንጠል በመለስ ሊደርጉ የሚችሉ
5872ሰጥቶ-መቀበሎችን መመዘን ነበር።
5873የሠላም አማራጮች ፋይዳ ባይሰጡ ደግሞ ጦርነቱ
5874በሰው ኃይል፤ በፋይናንስ በዲፕሎማሲና በሌላው
5875ዘርፍ የሚጠይቀውን አቅም ማጥናትና እንዴትስ
5876እንደሚሰባሰብ ስትራቴጅ ማውጣት ነበር።
5877የሠላም አማራጭች ገዥ ቦታ ይኖራቸው ዘንድ
5878የሊንከን ዓይነ-ልቦና ምንጊዜም ክፍት ነው።
5879የተለያዩና አንዳንዴም የማይዋጡ የሚመስሉ
5880የክልል ፍላጎቶችን ለማስተናገድ ወኔ አንሶት
5881አያውቅም።
5882ትናንት በፉክክርና በጥርጣሬ መጋረጃዎች
5883ተለያይተው የነበሩ ባላንጣዎች በአንድ ሰው ጥረት፤
5884አስተዋይነትና የማስተባበር ችሎታ አንድ-አካል
5885አንድ-አምሳል ሆነው አገርና ወገንን በመታደግ
5886ክቡር ሥራ ላይ ተሰማሩ።
5887ባላንጣነት በልብ ወዳጅነትና በወንድማማችነት
5888ስሜት ተተካ።
5889ቀጥሎ ደግሞ ሊንከንን ታላቅ መሪ፤ የባላንጣዎችን
5890ቡድን ደግሞ የቻምፒዎን ቡድን እንዲሆኑ የረዱትን
5891ባህርዮች በጭር ባጭሩ ላነጥብላችሁ እሞክራለሁ!
5892• የራዕይ ጥራት ~ የሰሜን-ደቡብ ቅራኔ ለብዙዎች
5893ባርነትን የማጥፋትና ያለማጥፋት ጥያቄ ይሁን
5894እንጅ ለሊንከን ከዚያ የበለጠ ትርጉም ነበረው።
5895“ያሜሪካ መፈራረስ የሕዝቦች-በሕዝቦች-ለሕዝቦች
5896የተሰኘው አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ራሱን ችሎ
5897መቆም የማይችል ቅዠት ነው ለሚሉ ወገኖች
5898የፖለቲካ መሣሪያ ይሆናልና ያንድነት ኃይሎችን
5899መሸነፍ እንደ አማራጭ አንቀበለውም” አለ።
5900የዚያ ትውልድ ኃፊነት ዓለማቀፋዊ እንድምታ
5901እንዳለውም አሳየ።
5902ከዚህም ሌላ “ባሜሪካ መገነጣጠል የሚጠቀሙት
5903ዜጎች ሳይሆኑ እዚህና እዚያ በሚፈጠሩ ትናንሺ
5904ግዛቶች መንበር የሚፈልጉ የሥልጣን ጥመኞች”
5905መሆናችውን አበክሮ ተከራከረ።
5906• ስሜታዊነት ጠላት ነው ~ አገርን የማስተዳደር
5907ያህል ውቅያኖስ ውስጥ የተነከረ ሀላፊ
5908የሚያበሳጨውና አንዳንዴም የሚያሳብደው ነገር
5909ያጣል ማለት ዘበት ነው።
5910ሊንከን ለዚህ ጥሩ ዘዴ ነበረው።
5911ደብዳቤ ይጽፍና በይደር ያቆየዋል።
5912ታዲያ በማግስቱ ብስጭቱም ስሜታዊነቱም ሲረግብ
5913የሚልከው ደብዳቤ የሚቆጭበት አይሆንም።
5914በስሜታዊነት ድባብ ውስጥ እንዳለ ያመለጡ
5915ዳብዳቤዎች ቢኖሩ እንኳ ሰውየውን የሚያረጋጋና
5916ቂም ያልያዘበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ተከታይ
5917ደብዳቤ ይልክለታል።
5918ፀያፍ ቃል ካፉ ወጥቶ አያውቅም።
5919• ርሕራሄና ታላቅነት ~ ሊንከን ፍጹም ሩህሩህ፤
5920ከቅጣት ይልቅ ምሕረት ሰዎችን ወደበጎ የመመለስ
5921ኃይል አለው ብሎ የሚያምን ሰው ነበረ።
5922በጦር ሜዳ ያሸነፋቸው ጀኔራሎች ላይ ውርደት
5923እንዳይደርስ፤ የተፈታው ጦር ሠራዊት ደግሞ
5924ከነፈረሱና ከነመሣሪያው ቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሎ
5925ኑሮውን እንዲቀጥል መፍቀዱ የወዳጆቹንም
5926የባላንጣዎቹንም ከበሬታ አስገኘለት።
5927ሀገሪቱን ወደ እርቅና ስምምነት ጎዳና አፋጥኖ
5928ወሰዳት።
5929ለዚህ ነው ሊንከን “አባታችን” የሚለውን
5930የፍቅርና የአቅርቦት ቅጽል ሥም ከወገኖቹ
5931የተቸረው።
5932 እርቅና ስምምነት ~ ጦርነቱ አብቅቶ ሊንከን
5933ለሁለተኛ ጊዜ ተመረጠ።
5934ባስመዘገባቸው ድሎች ከመኩራራት ይልቅ ታሪካዊ
5935ንግግሩን ብሔራዊ እርቅ አንዲሰፍንና የአንድነት
5936ስሜት እንደገና እንዲነግስ መንገድ መክፈቻ
5937አደረገው።
5938ብሔራዊው የትኩረት አቅጣጫ ምን ሊሆን እንደሚገባ
5939ማመላከቻ አጋጣሚ አደረገው።
5940ያ አቅጣጫ በብሩህ ተስፋ የተቃኘ፤ በዕርቅና
5941በሠላም መዓዛ የታጀበ ነበርና አገሪቱን
5942ከዳር-እዳር አወዳት።
5943• በምሳሌነት መምራት ~ ሊንከን ከሕዝብ መሀል
5944የወጣ ስለሆነ ከሕዝብ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት
5945ማድረግን ይወድ ነበር።
5946ስለሆነም ቤተመንግሥቱን ለጎብኝዎች ክፍት
5947አደረገ።
5948ዜጎችን ወደ ጦር ሜዳ ከማሰማራት የከበደ ውሳኔ
5949የለምና ሊንከን ራሱን ከጦር ሜዳ ለይቶ አያውቅም።
5950ከወታደሩ ጋር ይወያያል፤ ብሶታቸውን ያዳምጣል፤
5951ያበረታታቸዋል፤ ያስተምራቸዋልም።
5952ይህን በማድረጉ ከታሸና ከተኳኳለ የሹሞች ሪፖርት
5953ራሱን መከለል ቻለ።
5954የሊንከን የጦር ሜዳ ጉብኝት የወታደሩን ሞራል
5955ለማነቃቃት ጠቃሚ ቢሆንም አደጋ ይደርስበታል
5956ብለው ለሚሰጉ ጀኔራሎቹ ግን ራስ ምታት ነበር።
5957• ዘና ማለትማ ተፈጥሯዊ ነው ~ በሥራ ብዛት
5958የተወጠረች ነፍስ ዕረፍት እንደሚያስፈልጋትና
5959የተሟጠጠ ጉልበት በሳቅና በጨዋታ መታደስ
5960እንዳለበት ሊንከን ከልቡ ያምን ነበር።
5961እርሱ ራሱ የተዋጣለት ቀልድ አውሪ ብቻ ሳይሆን
5962አስተዳደሩ በውጥረት ቅንፍ ውስጥ ተወጥሮ
5963እንዳይሠራ የተቻለውን ሁሉ አድርጓል።
5964የቱን ያህል ጫና ቢበዛበት ለቲያትር ቤት ጊዜ
5965አያጣም ነበር።
5966ሊንከን ማስመስልና መኮፈስ የማይወድ ውነተኛ ሰው
5967ነበር።
5968እዚህ ላይ ባጠቃልለው ደግ መስለኝ።
5969ያሜሪካው የርስ በርስ ጦርነት 620 ሺህ ያህል
5970ሕይወት የጠፋበት እጅግ አስከፊ ጦርነት ነበር።
5971ከሚሊዮን በላይ ዜጎች አካለ ስንኩል ሆነውበታል፤
5972ሠላማዊ ኑሮ ተናግቶ ዕድገት የኋልዮሺ ተመልሳለች።
5973ይህ ጦርነት ሊወገድ ይችል ነበር ወይ የሚለው
5974ጥያቄ “ሙት” ጥያቄ ነውና ፋይዳው አስተማሪነቱ
5975ላይ ብቻ ነው።
5976ራሳችንን በማታለል አባዜ ውስጥ ተተብትበን
5977ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ማሕበራዊ ቀውስ
5978የመከሰቱ አደጋ የማይታሰብ ነው የሚባል አይደለም።
5979ያንዱ አስተዋጽኦ ከሌላው ይለይ እንደሁ እንጅ
5980ባገሪቷ ፖለቲካ ውስጥ ሚና ያላቸው ድርጅቶች ይህ
5981ቀውስ እንዳይከሰት ኃላፊነት የተሞላው ርምጃ
5982ሲወስዱ አለመታየታቸው ያሳስበናል።
5983የፖለቲካ ቅራኔዎች እየተንገዋለሉ እንዲቆዩ
5984ማድረግ ባልታወቀ ሠዓት የሚፈነዳ ቦምብ አቅፎ
5985የመተኛት ያህል ነውና ስንባንን መኖር የለብንም።
5986ልዩነቶቻችንን ማቀራረብ አለመቻላችን፤ የጠባብ
5987ብሔር ስሜት እንዲስፋፋ ማድረጋችን፤ ሕዝቦች
5988እየተራራቁ እየተፈራሩና መግባቢያ ቋንቋ እያጡ
5989እንዲሄዱ ማድረጋችን የራሳችንን እግር ደግመንና
5990ደጋግመን በጥይት የማቁሰል ያህል ቂልነት አለው።
5991ወለጋ ስባተኛን ክፍል ጨርሳ ከቤተሰቦቿ ጋር
5992አዲሳባ ስትዛወር ከሦስተኛ ክፍል ጀምሪ
5993የተባለችዋ ወጣት የሥርዓታችንን ድህነት
5994ታስረዳችኋለች።
5995ያዲሳባውና የወለጋው ወጣት የሚግባቡበት ቋንቋ
5996ተደልዟላ!
5997አሜሪካ አንድ ታላቅ መሪ ባስፈለጋት ሰዓት
5998ሊንከንን አግኝታለች።
5999የሊንከንን የባላንጣዎች ቡድን አዋቅራ ከመዓት
6000ድናለች።
6001እኛ ደግሞ ሳይውልና ሳያድር የራሳችንን ሊንከን
6002መፍጠራችን ወሳኝ ነው።
6003ማለቂያ በሌለው ጉስቁልና የሚማቅቀውን
6004ሕዝባችንን የሚታደግ የባላንጣዎች ቡድን
6005ለማደራጀት ከዚህ የተሻለ የታሪክ አጋጣሚ የለም።
6006አስፈላጊነቱም እንዲህ አንገብጋቢ ሆኖ አያውቅም።
6007መቼም ዳጎስ ያለ ቁርስ ጎርሶና ትከሻውን ቼብ-ቼብ
6008ተደርጎ የወጣ ወንድ የልብ ሳያደርስ አይመለስምና
6009ወርደ-ሰፊ አካፋየን እያውለበለብሁና ውርድ ከርሱ
6010እንደሚሆን እያስጠነቀቅሁ በረዶ ላይ ጦርነት
6011ከፈትሁ።
6012አጀማመሬን በጣሙን ወደድሁት።
6013በዚህ አያያዝ በራሴ ቀዬ ላይ የሚደነፋው ብቻ
6014ሳይሆን ጎረቤት መበለቷ ደጃፍ ላይ የተከመረውም
6015እንደማይተርፈኝ አወቅሁት።
6016የልብ ልብ ተሰማኝና አካፋውን ካፍ-እስከገደፉ
6017እየሞላሁ አቶ በረዶን በትከሻየ ላይ እያሻገርሁ
6018አሺቀነጥረው ጀመር።
6019እንዲህ ያካፋውን ስነፈትና የትከሻየን ልግመት
6020በመታዘብ ላይ እንዳለሁ ነው ከመበለቷ ቤት
6021አቅጣጫ “ርርርርርርር!
6022” የሚል የሞተር ድምጽ ሰምቼ ዞር ያልሁት።
6023እመቤቲቱ በረዶ መንፊያ መንኮራኩራቸው ላይ ቂጢጥ
6024ብለው ቀያቸው ላይ በድፍረት የተጋረጠውን በረዶ
6025ይመነጥሩታል።
6026እጃቸውን አውለበለቡልኝ።
6027እኔም አውለበለብሁላቸው።
6028“እናም ሀይሉ ሻውል 2010 ምርጫ ውስጥ ለመግባት
6029መወሰኑ ከምን መጣ?
6030በእሥር የተንገላታበት የቅንጅት ባለ ስምንት
6031ነጥብ ቅድመ ሁኔታስ ምን ጅብ በላው?
6032ከትናንት በስቲያ የብርቱካን መፈታት ቅድመ ሁኔታ
6033ነው አላለም ነበር ወይ?
6034በርግጥ ሀብቱንና ንብረቱን ካደጋ ለመጠበቅ ሲል
6035ያደረገው ሰጥቶ-መቀበል ነው?
6036በ2005 ምርጫ ያሳዘናቸውን ደጋፊዎቹን እንደገና
6037ማሰባሰብ እችላለሁ ቢል የለየለት እብደት
6038አይደለም ወይ?
6039” እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ወዳጄ ላይ
6040ያራገፍሁት እንደመትረዬስ ነበር።
6041በንዲህ ያለ ስሜታዊነት ጨዋታ በጀመርኩ ቁጥር
6042ምንጊዜም ዓይኑ ወደጣራው እጁ ወደ ቡናው ስኒ ነው
6043የሚያመራው።
6044በርጋታ ፉት ብሎ እስኪያጣጥም ድረስ የኔ ስሜት
6045ሳይወድ-በግዱ እንደሚበርድ ያውቃል።
6046ሰው የዚህን ያህል ውስጣችሁን ሲያነብ እህ!
6047አትሉም?
6048ቀጥልኩ ደግሞ ስለምርጫው - “የኢሕአዴግ ስሌት
6049ምን ይመስልሀል?
6050ምን ያህል ያገር ውስጥና የውጭ መንግሥታት
6051ተጽዕኖ አለበት?
6052ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም ያለው አቅምስ?
6053የኦባማስ አዲስ ፖሊሲ?
6054ኢዩስ?
6055የብርቱካንስ ጉዳይ?
6056መድረክ ምርጫው ውስጥ የሚሳተፍ ይመስልሀል?