የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን መስዋዕት አድርጎ በማቅረቡ የክህነት አገልግሎት ዋና ይዘት ፍቅር፣ ራስን ለቤተ ክርስቲያን አሳልፎ መስጠት መሆኑን አሳየን። ከጌታችን የባሕርይ ምንጭነት የተገኘው የአዲስ ኪዳን ክህነት ሐዋርያትን አረስርሶና አርክቶ በቂ የሆነ ክህነታዊ ተግባርም አሳይቶ አሁን ባሉ አባቶች ላይ ይገኛል። አምላካቸውን ያገኙ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን የምትፈጽማቸው ምሥጢራት ስላሏት፣ ምሥጢራቱ የሚፈጸሙትም የግድ በካህናት ስለሆነ ክህነት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ አስፈላጊና የማይቀር ነው። ይህም በዓለም ያለው በእግዚአብሔር አርዓያና ምሳሌ የተፈጠረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን እንዲያይበትና ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በዓመታዊ የንግስ በዓላት ወቅት የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ማትያስ፣ የቪክቶሪያ ዳግማዊ ቆልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ የሲያትል ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናት እየመጡ ያገለግላሉ። በዓመት እስከ አራት ጊዜ ያህል ካናዳና አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትንመምህራንን በመጋበዝ ለተወሰነ ጊዜ እየቆዩ ምዕመናንን ወንጌል እንዲያስተምሩ በመደረግ ላይ ነው። ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን መንፈሳዊ አገልግሎትና እየጨመረ የሄደውን የካህናትና የምዕመናን ቁጥር እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ ይጠብቅልን። በአሁኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት ካህናትና ዲያቆናት በፎቶው ላይ የሚታዩት ናቸው። በሀገራችን በኢትዮጵያ የዘመን ስሌት አዲሱን ዓመት በወርኃ መስከረም አንድ ብለን መቁጠር እንደጀመርን ከምናስተውላቸው ዓበይት ክስተቶች መካከል የውኃውን መጉደል፣ የሰማዩን መጥራት እንዳለ ሆኖ ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው የምድር በአበቦች ማጌጥ ነው፡፡ ዝርዝር ንባብ የመዝሙረ ዳዊት አራት ዋና ዋና ጥቅሞች - ስብከት በዲን ዶር ቴዎድሮስ በለጠ ፤ ፔርኒስ - ሮተርዳም የገዳማት ቀን ሃምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ። ም 2, 2015 የሊቀ መልዐኩ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በዓል አምስተርዳም በሚገኘው ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብረዔል ቤተ ክርስቲያን በእለቱ እሁድ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓም ከሆላንድ፣ ከቤልጄም፣ ከፈረንሳይ እንድዚሁም ከጀርመን ሃገራት የመጡ የኢትዮጵያ የኤርትራ እና የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤክርስቲያናት ካህናት አባቶች ዲያቆናትና ምዕመና በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ። የበዓሉን አከባበር ከዚህ በታች ባሉት ቪዲዮች ይመልከቱ- ባሕታዊ አባ ገጊዮርጊስ የተባሉ በሆላንድ ሃገር በተለያዩ ከተሞች የስብከትና ሀብተ ፈውስ አገልግሎት እንደሚሰጡ በመግለጽ ምእመናን በጉባዔው እንዲሳተፉ የሚጋብዝ ጥሪ እየተሠራጨ ይገኛል ። እኝህ ሰው የመጡት በሆላንድ የኢኦተ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካው መንፍሳዊ ኮሚቴም ሆነ በአምስተርዳም፣ በሮተርዳም፣ በአይንድ ሆቨን እና በአምስፎርት ከተሞች በቤተ ክርስቲያናችን ስር የሚገኙት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተወካዮች የማያውቁት ስለሆነ ምእመኑ ጠንቅቆ እንዲገነዘብ ፅህፈት ቤቱ ያሳውቃል። ይህንን በሚመልክት ተቀማጭነቱ በጀርመን ሃገር የሆነው የኢኦተ ቤተ ክርስቲያን የምእራብ፣ የምስራቅና የድቡብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጽቤት፥ በፌስ ቡካቸው ላይ ያወጡትን መልእክት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ። የ፳፻፰ ዓም መስቀል በዓል አከባበር ፔርኒስ-ሮተርዳም በፎቶ ይህንን ይመስል ነበር የ፳፻፰ ዓም መስቀል በዓል አከባበር አምስተርዳም በፎቶ ይህንን ይመስል ነበር አንድ መጽሐፍ ጠፍቶብኝ መደርደሪያው ላይ ያሉትን ሳገላብጥ አንድ መጽሐፍ አገኘሁና አንዳንድ ትዝታዎችንም ሀሳቦችንም ጫረብኝ፤ ክንፈ አብርሃም ለፒኤችዲ የጻፈውና በኋላ ያሳተመው መጽሐፍ ነው፤ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ክንፈን በስዊድን አግንቼው ቤቱ ጋብዞኝ ከእሱና ከባለቤቱ ጋር ስንጫወት አመሸን፤ ስንሰነባበት ይህንን መጽሐፍ ሰጠኝ፤ለመጽሐፉ መግቢያ የጻፈለት ዶር ኃይሉ አርአያ ነው፡፡ የመጽሐፉ ርእስ በአማርኛ ምናልባት ከዘር ወደመደብ ልንለው እንችል ይሆናል፤ ወያኔ ጎሣን እንዳስተማረን ለደርግ ምስጋና ይድረሰውና በበኩሉ መደብ የሚለውን ቃል አስተምሮናል፤ ሁለቱም የቸገረው እርጉዝ ያገባል እንደሚባል ሆኖባቸው ነው፤ ይህ መጽሐፍ ግሩም የእውነተኛ ምሁር መጽሐፍ ነው፤ እንዳጋጣሚ ሆኖ አሁን ባላስተውሰውም ከዚህ በፊት በአንዱ መጽሐፌ ውስጥ ጠቅሼዋለሁ፡፡ ዛሬ ላነሣ የፈለግኋቸው ሁለት ነጥቦች ናቸው፤ አንዱ በጎሣ ስሜት ተገፍተን ከአየናቸው ዶር ክንፈም አብርሃምም፣ ዶር ኃይሉም ትግሬዎች ናቸው፤ ነገር ግን ክንፈ መጽሐፉን ሲጽፍና ኃይሉ መግቢያውን ሲጽፍለት የተገናኙበትና የተስማሙበት በአንድ ጎሣ አባልነታቸው ሳይሆን በሰውነታቸውና በምሁርነታቸው ነው፤ በዚያን ጊዜ ሁለቱም ከጎሣ ደረጃቸው ከፍ ብለው በአንድ የሰውነት ደረጃ ላይ ነበሩ፤ ሁለቱም ከዘረኛ አስተሳሰብ ወደመደብ አስተሳሰብ መሸጋገር እድገት መሆኑን የተገነዘቡ ሰዎች ነበሩ፡፡ ሁለተኛው ነጥብ በድኅረ-ወያኔ የመጣው ለውጥ ነው፤ ክንፈ በእውቀቱና በሰውነቱ ሳይሆን በጎሣው ተመልምሎ የወያኔ መኳንንት አገልጋይ ሆነ፤ እንደክንፈ አብርሃም ያለ ምሁር ለሎሌነት አይመችም፤ ጠርሙሱን ወዳጅ ያደረገውም ይህንን ለመርሳት ይሆናል፤ በአንጻሩ ኃይሉ አርአያ ለጎሣው ሥርዓት በተቃዋሚነት ሲፈረጅ ቆይቷል፤ እስከዛሬም እንደዚያው ነው፡፡ በሠላሳ አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ይህንን ያህል ልዩነት በመሀከላቸው የተፈጠረው እንዴት ነው? ክንፈ ወደጎሣ ሎሌነት ወርዶ እግዚአብሔር ጠራው፤ ኃይሉ አሁንም ከሰዎች ተራ አልወጣም፡፡ ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው! ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡ ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ --- 1 የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤ 2 በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁ ማኅበር ታዛቢ አባል ነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤ በዚህ ሁሉ መሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን ነች፤ 3 የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤ ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤ ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ›› ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼ ታስሬአለሁ፤ ስለዚህ አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤ ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው፡፡ አሁን…! አሁን…! ባለፈው ሰሞን ነው። ወሮ አዜብ መስፍን መኪና እያሽከረከሩ የትራፊክ ፖሊስ ያስቆማቸዋል። ስህተት ሰርተሻል በማለት ያስቆማቸው ትራፊክ ጥፋቷን ይገልጽላታል። ወሮዋ ጥፋታቸውን አልሸመጠጡም። አዎ አጥፍቻለሁ አንዱን ግን ስታስቆመኝ ተደናግጨ ነው ስህተት የሰራሁት ይላሉ። የትራፊክ ፖለሱም የቅጣት ትኬቱን ጽፎ በጃቸው አስረክቦ የመንጃ ፈቃዳቸውን ይወስዳል። ይሄ በኢትዮጵያ የትራፊክ አሰራር የተለመደ ነው። እናም መንጃ ፈቃድ የሚወሰደው የትራፊክ መምሪያ ተኪዶ፤ ቅጣት ተከፍሎ ነው። ወሮ አዜብም መንጃፈቃዳቸውን ለትራፊክ ፖሊስ አስረክበው የማንነታቸውን ሳይገልጹ ወደ ቤታቸው ያመራሉ። እጅግ ይበል ሊያሰኝ ይችላል። የትራፊክ ፖሊሱ የመንጃ ፈቃዱ ባለቤት የማን መሆኗን በሰማ ሰአት ወደላይ ይበለው ወደታች፤ ስኳር ይነሳበት፣ ደም ብዛት አላህ ይወቅ። ችግሩ… አዜብ አይደለችማ!? ። ወሮ አዜብማ ያለ መለስ ምንም ናት። አዜብ ያለመለስ ከአስናቀች፣ ከትብለጽ፣ ከጸዳለ በምንም አትለይም። እትየ አዜብ የሚለዩት የህወሀት መሪ፣ የኢህአዴግ ተጠሪ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር የሚባል ባል ስላላቸው ብቻ አይደለም። ከቅርብ ጓደኞቹ እስከ ሩቅ ወዳጆቹ፤ ከ10 አመት ህጻን ልጅ እስከ ሰማኒያ ኣመት አዛውንት በእጁ ያስጨረሰ፣ እጁ በማይነጥፍ የሰው ደም የጨቀዬ አረመኔ ባል ስላላት ጭምር እንጂ። አዜብ ስፔን ሄዳ ሚሊየን ዶላር ብታጠፋ ምን አለበት!? በአሁኑ ጊዜ እንኳን እሷ ሌላ ተራ የተባሉ የሀብታም ሚስቶችስ ያን ያህል ገንዘብ ያጠፉ የለም እንዴ? ችግሩ ያለው ህዝብ በርሀብ እንዲሰቃይ እና በስራ እጦት እንዲማስን ዋና ተጠያቂ የሆነ ባል ስላላት እንጂ? ጣጣ የሚመጣው እኮ ወሮ አዜብ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል መሆን አለባት ስላለ የምትሆንለት። ያሻውን የሚያደርግ ባሏ መለስ ላይ እንጂ… መለስ ባይኖር እነ አቶ በረከት ተነስተው አዜብየ ግቢ ለሚቀጥለው ስልጣን ስለምንፈልግሽ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል መሆን አለብሽ የሚሏት ይመስላችኋል? ። ለዚያም ነው ያ ትራፊክ ማንነቷን ሳይሆን የማንነቷን ሲያውቅ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመማጸን ወደላይኛው እንድናጋጥጥለት የምለምነው። ስንት ልጆች ይኖሩት ይሆን…? በነገሬ ላይ ወያኔ ባዶ ሶስት የሚሉት የወሬ ጎስም ቡድን ነበረው። መለስ ምላሱን መላእኮች ሌሊት ሌሊት ክንፋቸውን ዘርግተው ይባርኩለታል ብላችሁ ወሬ ንዙ ከተባሉ ወይም ደግሞ ኢህአዴግ በኤሌክትሪክ የሚሰራ መሳሪያ ሊያስገባ ነው። ከአሁን በኋላ በጦርነት ሞት የሚባል አይኖርም፤ የኢትዮጵያ ወታደር ከግብጽ ጋር ቢዋጋ ከመሀል አዲሳባ ሆኖ በኮምፒውተር ነው ጦርነት የሚያደርገው… ብዙ ብዙ አይነት ወሬዎችን ተቀብለው የሚያቀባብሉ። ባዶ ሶስቶች። የሚመለመሉት ከመንደር ቡና አንጫላጭ ወሬኛ እናቶች እስከ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ድረስ ባሉ “አደገኛ”ወሬኞችን በማካተት ነው። ወይንም ደግሞ ምንም ጉዳት የማያደርስ የዋህ ካለ ወሬው ለሱ እንዲደርስ ይደረጋል። እናም ወሬውን ከኋላ ያባርሩታል። ወሬው ጆሯችን ገብቶ እስኪያበቃ አይለቁትም ያባርሩታል። እነኝህ ሰዎች ኢትዮጵያ በነበርኩ ሰአት አንድ ወሬ ማስወራት ጀምረው ነበር። አቶ መለስ ተደብቀውና ራሳቸውን ቀይረው ገበሬ መንደር በመግባት ሰዎችን ያነጋግራሉ የሚል። ድንቅ ወሬ ነበር። ሸጋ። ግን ግን አቶ መለስ በአደባባይ ሰው ስለሚገድሉ፣ ሰው እንዳሻቸው ስለሚያስሩ፣ ሀገርን በጎሳ ከፋፍለው ስለሚያስተዳድሩ ያ ገበሬ ሳያውቃቸው አስተናግዷቸው ይሆናል። ችግሩ ያለው አቶ መለስ ጭምብል አጥልቀው ገበሬ መሀል መግባታቸው ሳይሆን ራሳቸውን አቶ መለስን ሲሆኑ ነው። አቶ መለስ ራሳቸውን ደብቀው እንጂ ራሳቸውን ሆነው ህዝብ መሀል ቀርቶ ግለሰብ ዘንድ አይቀርቡም። ስራቸው ነዋ! ስራቸው ዋጋቸውን ሰጥታቸዋል ተከቦ መኖር። ምን እሳቸው ብቻ ልጆቻቸው ዘመዶቻቸውም ጭምር እንጂ…። እንደ አቶ መለስ ያሉ አምባገነኖች ለራሳቸው እንጂ ለልጆቻቸው እንኳን ግድ የማይሰጣቸው ፍጥረቶች መሆናቸውን በአርባ አመቱ መንበር ጋላቢ ጋዳፊ አየን። ሳዳምንም ተመለከትን፣ ቢን አሊም ታዩ፣ የኛኑ መንግስቱንም ማየት መልካም ነው። በነገራችን ላይ በቅርቡ የኮሎኔል መንግስቱ ልጅ ትምህርት መንግስቱ መሰለችኝ እዚህ ውቧ መንደር ቫንኩቨር ነበረች። ማንንም ሳታይ ማንም ሳያያት በአባቷ ሀጢያት የኋልዮሽ እያየች ትኖራለች። … አምባገነኖች አሁን ባለ ደስታ የኋላ ኋላ ልጆቻቸውን ጭምር ያሳቅቃሉ። እየተሹለከለኩ በየት ልግባ በየት ልውጣ ሲሉ፣ የቅርቡን የኛኑ መንግስቱን አይቶ መማር ምን ያቅታል ጎበዝ፡፤ የመንግስቱ ልጆች በምንም አይነት መለኪያም ያጠፉት ቅንጣት ጥፋት የለም። በምንም አይነት መልኩ ቀናብለው መሄድ ግን አይችሉም። ጥፋት ቢኖርባቸው እንኳን ከነፍሰ በላው አባታቸው መፈጠራቸው ብቻ ነው። ያለሀጢያታቸው አሁንም ወልደው ከብደው እንኳን ከመሽሎክሎክ አላመለጡም። የቢን አሊም… የጋዳፊም… የሙባረክም… ሁሉም አንድ ነው የሚገጥማቸው። የአቶ መለስ ሴት ልጅ ያኔ ቅንጅት በህዝብ ድጋፍ አይሎ በነበረ ጊዜ ተስፋዋ ጨልሞባት ለአንድ መምህሯ “የአባየ ነገር አለቀለት” ማለቷን ከመምህሯ ጓደኛ ሰምቼ ነበር። የመለስ ልጅ አድጋለች፣ ነፍስ አውቃለች፣ የአባቷን መጨረሻ ስታይ ምን ትል ይሆን? አሁንማ ለንደን አለላት፣ ዛሬማ ኦሀዮ የራሷ ነው። ሁሉ በእጇ የሆነላት ግንግን የራሷ የግሏ ያልሆነ ህይወት የምትኖር ፍጥረት። ታዲያ የዚህች በአምባገነን የምትማቅቅ ሀገር ተስፋ በማን ላይ ነው? ሀገር ቤት ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ላይ ተስፋውን ጥሎ ወደ ላይኛው ማንጋጠጥ ይዟል። እኛ እዚህ የተደላደለ ኑሮ እያሳደድን የምንገኘው ዲያስፖራዎች ግን ነጋ ጠባ በማይረቡ ጉዳዮች ጭቅጭቅ ይዘናል። አቤት የንትርክ መአት፣ አቤት የስድድብ ብዛት…! አቤት አቤት የሚነሱ ሰንካላና የማይረቡ ንዝንዞች መአት። እነኝህ ንዝንዞች ታዲያ ኦስሎ ወይም ለንደን እንዳሉት ሁሉ አለያም ታላቋ የሀበሻ መናገሻ ዋሽንግተን ዲሲ ወይ ቶሮንቶ እንዲያም ካለ አትላንታም ሆነ ሎስ አንጀለስ እንዳለው ሁሉ በተመሳሳዩ እዚህ ቫንኩቨርም አለ። ውቧ መንደር ቫንኩቨር። ሸጋዋ… ደጓ ምድር ቫንኩቨር። ውጭ ሀገር መኖር ትልቁ ጥቅም ነጻነት ነው። እዚህ ስንኖር በምርጫችን ነው። አባ ጳውሎስንም ሆነ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀርዮስን ለመምረጥ መብቱ ያለን እዚህ በመኖራችን ብቻ ነው። እዚያ ነጻነት የለም እዚያ… ኢትዮጵያ ያለው ምርጫ አባ ጳውሎስ ወይም ስደት ገፋ ካለም ሞት ነው። እዚህ ግን እንደ ቫንኮቨሯ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ካልተሰረክና ካልተጭበረበርክ በስተቀር ነጻነት አለህ። የቫንኩቨሯ ማሪያም ታሪክ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ መነጋገሪያ ነበረች። በገለልተኛ ሽፋን በተሸሸጉ የአባ ጳውሎስ አሽከሮችና በአቡነ መርቀሪዮስ በሚመራው ሲኖዶስ ስር መተዳደር በሚፈልጉ ሰዎች መሀል ሰፊ ክርክር ነበር። የፈረንጅ ዳኛ ገላጋይ የገባበት። ማውራት የፈለኩት ስለቤተ ክርስቲያኗ ጣጣ አይደለም። የሱ ምእራፍ ተዘግቷል። ልናገር የፈለኩት ስለነዚያ ልጅ ተክሌ እንደሚላቸው የኢትዮጵያን ፖለቲካ በዚህም በዚያም ተጠቅመው የወጡ ይህንን አገዛዝ አጥብቀው ስለሚቃወሙና በነጻዋ ምድር ቫንኩቨር ላይ ድብብቆሽ ስለሚጫወቱት እንጂ። አንዱ ስሙን ቀይሮ በስልክ ሊያናግረኝ ቀጥሮኝ ብሄድ ስሙ ሌላ ወሬው ሌላ… ገለልተኛ ነን! እኛ ቤተክርስቲያኗ ወደ አባ ጳውሎስ እንድትሄድ አንፈልግም… በማለት ሲደሰኩርልኝ የነበረ ሰው ዛሬ ቤተክርስቲያኗ በጳውሎስ እጅ ወድቃ የቤተክርስቲያኗ አመራር ሆኖ ሲያየኝ ምን እንደሚሰማው አላውቅም። እኔ እሳቀቅለታለሁ። ቤተ ክርስቲያኗ ወደ አባ ጳውሎስ እያመራች ነው ሲባል… እኛ እያለን? … እንዴት ይደረጋል…? በኢንተርኔት ላይ ሲባል ነው የምሰማው እንጂ በፍጹም አይደረግም። ሲል የነበረ የማከብረው ትልቅ ሰው ዛሬ በጳውሎስ ስር ለመተዳደር ብቻ ሳይሆን የህወሀት ካድሬ መሆኑ የሚታማ ቄስ ተሹሞ ሲባርከው በምን አይነት ሞራል እንደሚቀበለው እግዜር ይወቅ። ቫንኩቨር ታዲያ ትችለዋለች ሁሉም አለ ሁሉም የለም። በቫንኩቨር። ልክ እንደ ኔዘርላንዱ ልክ እንደ ሲድኒው… እናንተየ ይሄ በየ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ጉድ ጉድ የሚል ሰው ወይንም አንዴ ለሰበካ ጉባኤ የተመረጠ ሰው ስልጣን አልለቅም ብሎ የሙጥኝ የሚለው ለምን ይሆን? … እዚያ አካባቢ ምን አይነት ጥቅም እንዳለ አላውቅም። ግን ግን ብዙ የሚሸት ነገር አለ! … በገንዘብ የማይጠረጥረው ግልሰብ ቦታዋ ላይ ሲደርስ የሙጥኝ ይላል… የምታከብሩት ሰው በየደብሩ ሲገባ የስራ ዘመኑ ቢያልቅ እንኳ መልቀቅ አይሻም! ምን ጉድ ነው እዛ ውስጥ ያለው? … ገንዘብ? አይመስለኝም… ስልጣን እንዳይባል ትርፉ እንዘፍ እንዘፍ ነው… የሰው መውደድ እንዳንለው… ሰው በቃ አዲስ ሰበካ ጉባኤ ይምጣ ሲል ትሰማላችሁ… ሌላ ምን ይሆን? ይሄንንም ቫንኩቨር ታያላችሁ ልክ እንደ ካልጋሪው ልክ እንደ ዳላሱ… በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እልህ ታያላችሁ ቡድንም አለ… ጎጥም እንዲሁ… ቫንኩቨር ደጋግ ሰዎች አሉባት ከኔ ቢጤ ኮስማና እስከ ታታላቅ በግልና በቡድን እስከሚሮጡ ጎበዛዛት፤ ቤተክርስቲያንን በጽናት ለማቆም ከሚሮጡት ጀምሮ ለማፍረስና በቡድን በመቧደን እስከሚሽከረከሩ… እነዚያ የዋሆቹ ሀገር ቤት ያሉ አባቶችና ምእመናን ነጻ ያወጡኛል ብለው የሚተማመኑባቸውና የሚጸልዩላቸው እዚህ ውጭ ሀገር ያሉ የቤተክርስቲያን ሰዎች እዚህና እዚያ ሆነው እንደሚናቆሩ ቢያዩ ልባቸው ምን ያህል ያዝን። በቫንኩቨር ታዲያ ፖለቲካም አለ። እንደሌሎቹ ሀገራት ሁሉ። እንደ ኖርዌይ እንደ ሲዊዘርላንድ እንደ ዊኒፕግ ሁሉ። ቫንኩቨርም ፖ…ለ… ቲ…ካ… አለ። በጽኑ ሞራልና ሰብእና ከተገነቡት እስከ ደፋርና እዩኝ እዩኝ ባዩ። ፖለቲካን ወኔ ብቻ ወንዝ አያሻግረውም። ብልህነት ይጠይቃል። የዲያስፖራው ፖለቲካ ችግሩ ወኔ አይደለም ባለ ወኔያሞችማ ሞልተውታል። ብልሀትና መከባባር ማጣት ጠፉ እንጂ… በቫንኩቨር ብልሀት የለም። ነፋሱ እንደነፈሰ ነው። መሮጥ… መሮጥ… ቀጥ ሲል ደግሞ ቀጥ ነው። ከእንደገና መሮጥ… ያው ወያኔ በየስድስት ወሩ እየነቀሰ ሚያስረውና የሚገለው ወይም የሚሰራው ትርኢት ሲኖር እዚህም ሩጫ ነው። በመሰረቱ ፖለቲካ በሜዳው ነው የሚያምረው። እዚያው። እዚህ ሲመጣ ስራችን ትንሽ ነው። ሁላችንም እንደምንስማማው ውጭ ሀገር የሚኖረው ህዝብ ሀገር ቤት ለሚደረግ ፖለቲካ የገንዘብ ድጋፍ መስጠት ወይም እዚህ ያለንበት ሀገር ላሉ ዜጎችና መንግስታት የዚያን አረመኔ መለስ አገዛዝ ምንነት ማሳወቅ። ይህችን ትንሽ ስራ ለመስራት ንትርኩ ብዙ ነው። ሀገር ቤት ያሉትን ፖለቲከኞች ወያኔ ድራሻቸውን ለማጥፋት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም አንዴ በሀገር ክህደት ሌላ ጊዜ በዘር ማጥፋት፤ ሲለው ህገመንግስቱን ለመናድ ሲያሻው በአዲሱ ትኬት… ሽብርተኛ ወንጀል ድራሻቸውን እያጠፋ ነው። ለነገሩ እኛ ራሳችንም እዚህ ያለን ዜጎች ከመጠየቅ አንድንም። አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2008 ኤፍ ቢሲ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎችን ህገወጥ ዝውውር ለመከላከልና የጥራት ደረጃውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሶፍትዌር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የምግብ አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 13 ፣ 2008 ኤፍ ቢ ሲ በቢሾፍቱ ከተማ በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የኮኖርያ አፍሪካ የጨርቃ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2008 ኤፍ ቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ጥሎት የቆየውን የጦር መሳሪያ ግዢ ማእቀብ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2008 ኤፍ ቢሲ ለረዳት ምሩቅ የዩኒቨርሲቲ መምህርነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ፈተና ከወሰዱ እጩ ምሩቃን አብዛኛዎቹ ማለፍ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2008 ኤፍ ቢሲ የስዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ሲሞኔታ ሶማሩጋ በኢትዮጵያ ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ለሶሰት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13 ፣ 2008 ኤፍ ቢ ሲ ከጋና አቻው ጋር ለ2016ቱ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የተጫወተው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2008 ኤፍ ቢሲ የሰው ልጅን አካላዊ ሁኔታ በማየት ስለስብዕናው መናገር የተጀመረው ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት እንደሆነ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2008 ኤፍ ቢሲ በአየርላንድ በኩል ወደ አሜሪካ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ተመልሶ ወደ አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2008 ኤፍ ቢሲ የፎቶ እና የተንቀሳቃሽ ምስል ቪዲዮ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚያስችል መተግበሪያ አፕሊኬሽን ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ከስላሴ በዓል ላይ ተባረሩ • ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡›› የየካ ክፍለ ከተማ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ • ‹‹ገዥው ፓርቲ ጥላውን የማያምንበት ደረጃ ላይ ደርሷል! ›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ጥር 72007 ዓም የዓመቱን የስላሴ በዓል ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ እንደተባረሩ የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል! ›› የሚል ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ ማባረሩን እማኞቹ ገልጸዋል፡፡ ከተባረሩት ወጣቶች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚገቡትንና የሚወጡትን አማኞች በማስተባበር ላይ እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን የተባረሩት ወጣቶች ይታሰሩ አይታሰሩ የታወቀ ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመጡ ከፍተኛ ኃላፊዎች ለጥምቀት በዓል ሰማያዊ ቲሸርት ያዘጋጁትን የጃንሜዳ አካባቢው የጥምቀት በዓል አስተባባሪዎች፣ ያዘጋጁት ሰማያዊ ቲሸርት በዓሉ ላይ እንዳይለበስ በተደጋጋሚ እያስጠነቀቁ እንደሚገኙ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በፖሊሶችና በደህንነቶች ተደጋጋሚ ጫናም ለጃንሜዳ አካባቢ ወጣቶች የተዘጋጀው ሰማያዊ ቲሸርትና ‹‹ያመነ፤ የተጠመቀ ይድናል›› የሚለውን ጥቅስ በነጭ ቲሸርት እና በሌላ ጥቅስ እንድንቀይር ተገደናል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ የፈረንሳይና ቤላ አካባቢ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርቱን እንዲቀይሩ ጫና ቢደርስባቸው አንቀይርም በሚል አቋማቸው መጽናታቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ጥር 6 የአዲስ አበባ መስሪያ ቤቶችና ወረዳዎች ኮሚኒኬሽን ኃላፊዎች አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ባደረጉት ስብሰባ የየካ ክፍለ ከተማ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል ሰማያዊ ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡›› ሲል ሪፖርት ማቅረቡን የስብሰባው ተሳታፊዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ደህንነት፣ ፖሊሶችና ካድሬዎች እያንዳንዱን የህዝብ እንቅስቃሴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በማገናኘት ወቀሳ የሚያቀርቡት ህዝብ ውስጥ ብሶት እንዳለ፣ ሰማያዊም የህዝብን ብሶት እንደሚያሳማ ስለሚያውቁ፣ ከምንም በላይ ገዥው ፓርቲ የራሱን ጥላ የማያምንበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ባነሱባቸው ጊዜያት ሁሉ ገዥው ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲን ‹‹የሙስሊም ፓርቲ ነው›› በሚል ሀሰተኛ ወሬ ሲያሰራጭ እንደነበርና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲን ሲወቅስ እንደከረመ ያስታወሱት ኃላፊው አሁንም ፓርቲውን ከእያንዳንዱ የህዝብ እንቅስቃሴ ጋር እያገናኘ ቢበረግግ አያስገርምም ብለዋል፡፡ የብፁዕ አባታችን የአቡነ መልከ ጼዴቅ ፪ኛ ዓመት የዕረፍት መታሠቢያ ቀን ነገ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓም በመላው ኢትዮጵያ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎተ ፍትሐትና በቅዳሴ ታስቦ ይውላል። በይበልጥ ደግሞ በምሑር ኢየሱስ ገዳም ብዙ የመንፈስ ልጆቻቸው፣ አረጋውያን መነኮሳትና ተማሪዎች አስበዋቸው ይውላሉ። የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተስቦች አሁንም ቢሆን በመላው ዓለም የምትገኙ ሁላችሁም የብፁዕ አባታችን በርካታ ሥራዎችን ዳር ለማድረስ በምትችሉት ሁሉ እንድትራዱ እናሳስባለን። እግዚአብሔር አምላክ ደጋግ አባቶችን ያብዛልን፤ የብፁዕ አባታችን ነፍስ በገነት መንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን። የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ ገቢው ብጹዕነታቸው ለሰበሰቧቸው ልጆች ማሳደጊያ እና ለጀመሯቸው ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚሆን ተንቦላ እያከፋፈለ ይገኛል። እጣው በጥቅምት ወር እንደሚወጣ የተገለጸው ተንቦላን በየእስቴቱ ለማከፋፈል በጉ ፈቃደኛ የሚሆኑ የብጹዕነታቸውን ወዳጆች ጥሪ እያቀረበ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰቦች በ 202-656- 202-656-9268 በመደወል ኮሚቴውን ማነጋገር እንደሚችሉ ገልጻል። በተያያዘ ዜናም በአንድ አንድ ኢትዮጵያዊያን በሚበዙበት የአሜሪካ ግዛቶች በዲሲ እንደተደረገው አይነት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለማዘጋጀት እያሰቡ ያሉ ምዕመናን እንዳሉ የተገለገ ሲሆን ለዚህ ዝግጅት ማስተባበር ፈቃደኛ የሆኑ ካህናት አባቶች ሰንበት ተማሪዎች እና ምዕመናን በንዑስ ኮሚቴ ለማደራጀት ይቻል ዘንድ ከላይ በተገለጸው ስልክ በመደወል ኮሚቴውን ማነጋገር የሚቻል መሆኑን አሳስበዋል። ነገ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፫ ዓም ብፁዕ አባታችን ያረፉበት አንደኛ ዓመት መታሠቢያ ቀን ነው። በመላው ኢትዮጵያ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎተ ፍትሐትና በቅዳሴ ታስበው ይውላሉ። በይበልጥ ደግሞ በምሑር ኢየሱስ ገዳም ብዙ የመንፈስ ልጆቻቸው፣ አረጋውያን መነኮሳትና ተማሪዎች አስበዋቸው ይውላሉ። አምላካችን እግዚአብሔር የብፁዕ አባታችንን ነፍስ በገነት መንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን አሜን። ሚያዚያ 23 2003 ከቀኑ 5፡30 ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ ለተገኘ ሰው ዛሬ ምን ተፈጥሮ ነው ሰዉ ሁሉ እንዲህ ተፍ ተፍ የሚለው ያስብላል። እናቶችና እህቶች የምግብ ማዘጋጃ ክፍሉን ተቆጣጥረውታል። ከፊሉ ወጣቶች አዳራሹን ሲያስውቡ ከፊሎቹ ደግሞ የቪዲዮ ፣ የድምፅ ፣ የፕኦጀክተር እንዲሁም ዝግጅቱን ለመላው አለም ለማስተላለፍ የሚረዷቸውን ኮምፒተሮች መልክ መልክ ያሲዛሉ። የመርሐ ግብሩ ሰዓት ደርሶ ከዲሲ እና አካባቢው የተጋበዙ እንግዶች ሲገኙ አዳራሹ አምሮና ሰምሮ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ብዙ ሩጫ የነበረበት አይመስልም። ብፁዓን አባቶች፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ካሕናት አባቶችና ዲያቆናት ቦታቸውን ከያዚ በኃላ ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፀሎት ተከፍቶ በኮሚቴው ሰብሳቢ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፓርት ቀረበ ፤ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መላከ ሕይወት ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ባህሩና በብፁዕ አቡነ አብርሃም የዲሲና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ መልከ ጼዴቅ በሕይወት በቆዩበት ጥቂት አመታት ለቤተክርስቲያን ስላበረከቱት መንፈሳዊ፣ ማሕበራዊ እና የልማት እንቅስቃሴዎች ትንታኔ ከተሰጠ በኋላ የገቢ ማሰባሰቢየ ዝግጅት በቀሲስ ዘበነ እና በመምህር ሕዝቂያስ ተከናውናል። በጉባኤው ላይ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ እጅግ የሚያስደንቅ እና እውነትም ብጹዕነታቸው አንድ ጠይቀው ሁለት የሚያገኙ ናቸው የተባለውን ቃል እንድናስታውስ አርጎናል። የዝክረ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የሆኑት ቆሞስ አባ ፈቃደ ኢየሱስ ዝግጅቱን አስመልክቶ አነጋግረናቸው እንደገለጹልን ዝግጅቱ እጅግ ከተጠበቀው በላይ የተሳካ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በወንድማቸው በብጹዕነታቸው እረፍት እጅግ በጣም እንዳዘኑ በማስታወስ አሁን ከዚህ ዝግጅት በኋላ ምን ተሰማዎት ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሲመልሱ በፊትም ብጹዕነታቸው በአካል ስለተለዩን ሳይሆን በየቦታው ተሰርቶ የማያልቅ የሚመስል ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ጀምረው ፤ ልጆችን ለማሳደግ በየቦታው ሰብስበው በመሔዳቸው የተሰበሰበው ይበተናል፤ የተስተካከለው ይበተናል ነበረ ሀዘኔ። አሁን ብጹዕነታቸው “እኔ እግዚአብሔር ያመለከተኝን እጀምራለሁ የሚያስፈጽሙትን ደግሞ እሱ ያስነሳል” እንዳሉት ይኸው ብዙዎችን አስነስቷል ከእንግዲህ ወዲህ ሀዘን የለም ሥራዎችን በአግባቡ ማስፈጸም እንጂ ብለዋል። በመጨረሻም በዝግጅቱ አስፈላጊውን ሁሉ ላበረከቱ ምዕመናን በእግዚአብሔር ስም ምስጋና አቅርበዋል። ዝክረ መልከ ጼዴቅ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በአካል በነበሩበት ጊዜ የጀመሩዋቸውን መንፈሳዊ ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ በመንፈሳዊ ልጆቻቸው የተቋቋመ ማኅበር ነው። ዋና አላማውም ብፁዕነታቸው ያስጀመሯቸውን አያሌ መርሃ ግብሮች ከግብ ለማድረስ ገንዘብ ማሰባሰብ ነው። ማኅበሩ ዋሽንግተን ዲሲ ማዕከል በማድረግ በአለም ዙሪያ ያሉ መንፈሳዊ በጎ አድራጊዎችን ለማቀፍ የተቋቋመ ነው። በአለም ዙሪያ ያላችሁ የብፁዕነታቸው ወዳጆች እና ልጆች አስፈላጊውን የገንዘብ ፣ የጊዜ ፣ የባለሙያ እርዳታ ታደርጉ ዘንድ እንዲሁመ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዛችኋል። 1 - 2 በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤ 3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። 4 ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ። 5 ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። 6 በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ 7 እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። 8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። 9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። 10 ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። 11 ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤ 12 ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም። 13 በአይሁድ ሥርዓት በፊት እንዴት እንደ ኖርሁ ሰምታችኋልና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያለ ልክ አሳድድና አጠፋ ነበር፥ 14 ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ በዘመኔ ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ ነበር። 15 - 16 ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ 17 ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። 18 ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ፤ 19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም። 20 ስለምፅፍላችሁም ነገር፥ እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት አልናገርም። 21 ከዚያ ወዲያ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ አገር መጣሁ። 22 በክርስቶስም ያሉት የይሁዳ ማኅበሮች ፊቴን አያውቁም ነበር፤ 23 ነገር ግን። ቀድሞ እኛን ያሳድድ የነበረ፥ እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ነበር፤ 24 ስለ እኔም እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር። ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ይጫኑ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መዝ67፤31 ኢትዮጵያ በጥንት የግብጻውያን ቋንቋ ጱንጥ፤ “ቶ” ኔቶር፤ ኩሽ፤ እየተባለች ትጠራ ነበር። ጱንጥ የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ካለው ፉጥ ከሚለው ስም ጋራ ይመሳሰላል። ዘፍ 10፤7 “ቶ”ኔቶር ማለትም ሀገረ እግዚአብሔር ማለት ነው ይላሉ የቋንቋው ባለቤቶች፤ ሙሴ ብሉይ ኪዳንን ሲጽፍ ይህችን ቅድስት ሀገር የኩሽ ምድር እያለ የጻፈው በግብጽ ተወልዶ ያደገ እንደመሆኑ መጠን የ ግብጻውያንን ቋንቋ ያውቅ ስለነበር ነው፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኩሽ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የካም የመጀመሪያው ልጅ እንደሆነ ነው። ዘፍ 10፤1-7 1ኛ ዜና 1፤810 ኩሽ የሚለው ቃል ሀገርን ሲያመለክት ኢትዮጵያ ተብሎ ተተርጉሟል። ዘፍ 2፤13 ኢትዮጵያ የሚለው የቃሉ ትርጉም የሕብር፤ የመልክ፤ የሀገር ስም ሲሆን የትውልዱ ማንነት ሲመዘን ቁመቱ እንደአዛሄል ቀውላላ፤ እንደድንክም በጣም አጭር ያልሆነ መጠነኛ ቁመት ያለው ዜጋ ነው፡፡ በጣምም ነጭ ያልሆነ ከመጠን በላይም እንደቁራ ያልጠቆረ፤ እንደለምጻምም ያልተንቦገቦገ፤ዓሣ የሚመስል ጠይም መልክ ያለው ነው፡ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ40 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ዘፍ 2፤13 ኤር 12፤23፤ ኢሳ 18፤1 ሶፎ3፤102፤12 2ኛ ዜና 14፤9-45 2ኛ ነገ 19፤9፤ ናሆ 3፤8-10 ወዘተ ኢትዮጵያ የኩሽ ምድር ለመባል የበቃችበት ዋናው ታሪካዊ ምክንያት ቀደም ሲል ከላይ እንደተገለጸው የካም የመጀመሪያ ልጅ የኩሽ ዘሮች ስለሰፈሩባት ነው የካም ልጆች ኩሽ ምጽራይ ፉጣ እና ከነዓን ናቸው። ዘፍ10፤1-8 የኩሽ ልጆችም ሳባና አቢሳሰብታ ይባሉ ነበር ዘፍ 107-8 ይህችው ሀገር በሌላ አጠራር የሳባ ምድር በተለይም በምዕራባውያን ዘንድ አቢሲኒያ እየተባለች ስትጠራ ቆይታለች ምናልባትም ይህን ስያሜ ያገኘችው እነዚህ የኩሽ ልጆች ሳባና አቢሳ ሰብታ ስለሰፈሩባት በስማቸው አስጠርተዋታል ማለት ነው ብለው ምሁራን አባቶቻችን ይተርካሉ፡ ያስተምራሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ከላይ የጠቀስናቸው ሁለቱ ታላላቅ የታሪክ ባለቤቶች ሮምንና አሌክሳንደርያን ከመሰረቱ በኋላ በራሳቸው ስም እንዳስጠሯቸው ኢትዮጵያም በ አቅኒዎቿ ስም ማለትም በሳባ የሳባ ምድር፤ በአቢሳ አቢሲኒያ እየተባለች ለብዙ ዘመናት ስትጠራ ቆይታለች አሁንም ትጠራለች። ሆኖም ግን የእኛ አላማ ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ ከየት እንደመጣና አቕኒዎቿም እነማን እንደነበሩ በመጠኑ ለትውልዱ ለመግለጽና ለማስተዋወቅ ያህል እንጂ ስለሮምና ስለአሌክሳንደርያ አመሰራረት ግድ ብሎን አይደለም አቢሲኒያ የሚለውን ቃል ዐረቦች ብዙ ጊዜ ሀበሽ በማለት ይጠቀሙበታል፡ ይህውም ድብልቅልቅ፤ ውጥንቅጥ ለማለት ነው፡ ነገር ግን የታሪክ ተመራማሪዎች በቂ መረጃ የለውም ይላሉ፡፡ በ3600 ዘመን አካባቢ ከጌታ ልደት በፊት በየመን ይኖሩ የነበሩ ከነገደ ሴም የተከፈሉ ነገደ ዮቅጣን በባብ አልመንድብየመከራ በር ማለት ነውአካባቢ ገብተው ሰፈሩባት በዚህች ሀገር ከሚኖሩ የኩሽ ማለትም ከኗሪዎቹ ጋራ ተጋብተው እየተበራከቱ ሄዱ ሀገሪቱንም ምድረ አግዓዚት ምድረ አግዐዝያን፤ ትርጉም ነጻ ሀገር፤ ነጻነት ያላቸው ስዎች ፤መኖሪያ ብለው ጠሯት በመጨረሻም ለዚች ሀገር የተሰጣት ስያሜ ኢትዮጵያ የሚል ነው፡፡ በሀገራችን እንደሚተረከው “ኩሽ” ሁለት ስም ነበረው። ሁለተኛው ስሙ “ኢትዮጲስ” ይባል ነበር በዚህ መነሻነት አቅኒዎቹ ባባታቸው ስም ሀገሪቷን ኢትዮጵያ ብለዋታል። እነርሱም ኢትዮጵያውያን ይባላሉ እየተባለ ይተረካል። ነገር ግን በጽርዕግሪክ ቋንቋ “ኢትዮጲስ” የተባለው በዕብራይስጥ “ኩሽ” የተባለው የመጀመሪያው የካም ልጅ ነው። ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገጽ 248 ”ኢትዎፕስ” ማለት በጽርዕ ግሪክ ሁለት ዓይነት ትርጉምን ያሳያል። የስው ስም ሲሆን ጥቁር፤ የሀገር ስም ሲሆን ደግሞ ቆላ በረሃ፤ ምድረ-በዳ ማለት ነው፡፡ስምነቱም ኩሽ ከሞተ በኋላ በ2450 ዓመት ሰብዓ ሊቃናት ያወጡት ስም ሲሆን በሱዳን ዙሪያ ያለችውን ክፍል የኩሽ ልጆች የሚኖሩባት ሀገር ስለሆነች በሰብዓ ሊቃናት ትርጉም መሰረት ኢትዮጵያ ተብላለች፡፡ ዘፍ 2፤13 በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን የተጻፈው መደበኛው ኢትዮጵያ ግን ታላቁን የሳራን በረሃ ጨምሮ ያለው ክፍል ነው። 2ኛ ዜና 14፤9 12፤13 16፤8 ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገጽ 248 “ይዌልጥኑ ኢትዮጵያዊ ማዕሶ ወነምር ሕንብርብሬሁ” በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ኤር 13፤23 አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪኮች የተወረሰ ነው “ኢቶስ” ዋዕይሙቀት “ኦፕ” “ሲስ” ገጽ አርአያ ማለት ነው እነዚህ ሁለቱ ቃላት ሲጣመሩ “ኢቲኦፕያ”ወይም“ኢቲኦፕስ” የሚል ይወጣል፡ ይህም እንደመጀመሪያው “ኤቴኦፕያ” ቢል የሀገሪቱን ቆላነት ያመለክታል “ኢቲኦፕስ” ቢል የሕዝቧን ምንነት የሚገልጽ ይሆናል፡ የግሪኮች የቅኔ ገጣሚ በሆነው በሆሜር መጽሐፍ ደግሞ ቀዩንም ኢትዮጵያ ብሎት ስለሚገኝ ኢትዮጵያ ማለት ጥቁር ብቻ ሳይሆን ቀይ ፤የቀይ ዳማ ቀለም ያለው ሕዝብ ማለት ነው፡የኢትዮጵያውያን ቅድመ አያት ኩሽ የነበረው በ2734 አካባቢ ሲሆን እርሱ በሞተ በ2450 ማለት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ284 መሆኑ ነው መጻሕፍተ ብሉያትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕግሪክ የመለሱየተረጎሙ ሰብዓ ሊቃናት ነቢዩ ሙሴ ኩሽ እያለ በብሉይ ኪዳን የጻፈውን ኢትዮጵያ በሚል ቃል ለውጠውታል። ባለቅኔው ሆሜርም ስለኢትዮጵያ ሲናገር ኢትዮጵያውያን በጉልበት ኃያላን፤ በውበት የተደነቁ፤ የዋሆች በጠባይ ጭምቶች፤ ትህትናን ፍቅርን የተመሉ ናቸው ብሏል። ከዚህ የተነሳ ከግሪኮች 12 አማልክት አንዱ የመጀመሪያ ታላቁ እንደ-አባት የሚቆጠረው ዜውስ የተባለው ኢትዮጵያውያንን ለማየት፤ ከእነርሱ ጋራ ለመብላት ወደውቅያኖስ ወረደ ብሏል። ኢትዮጵያ በላስፎችና በታሪክ ሰዎች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ የታወቀች ሀገር፤ የሕዝቧ ማንነት በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸ፤ የጂኦግራፊ አቀማመጧ እና ከባቢ አየሯ ለፍጥረታት ሁሉ ተስማሚ የሆነ ነው፡፡ ሙሴ የስነ-ፍጥረትን ዝርዝር ሲጽፍ በአባይና በተከዜ የተከለለች መሆኗን ያወሳት በኢትዮጵያና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ፍቅር አስመልክቶ ነቢዩ ዳዊት ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ሲል በግልጽ የተነበየላት ቅድስትና ውብ ሀገር ናት። መዝ 67፤31 ስለ ኢትዮጵያ የሃይማኖትና የሞራል ክብር የተናገረ ሶፎንያስ ኢትዮጵያ በአንድ አምላክ የምታምን ሀገር መሆኗን ሲገልጽ “እምነ ማዕዶተ አፍላገ ኢትዮጵያ ያመጽኡ ሊተ መሥዋዕተ ከኢትዮጵያ ወንዝ ማዶ የሚሰግዱልኝ የተበተኑት ልጆቼ መባዬን ይዘው ወደኔ ይመጣሉ” ብሏል ሶፎ 3፤10 ሃይማኖቷም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትባላለች ኦርቶዶክስ ቃሉ የጽርዕግሪክ ሲሆን ጥምር ቃል ነው” ኦርቶስ” ቅጽል፤ ርትዕት ቀጥተኛ ማለት ነው። “ዶክስ” ማለት ደግሞ “ዶኮ” ካለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙ ማሰብ መገመት ማመን ማለት ነው “ኦርቶዶክስ” እንደ አንድ ስም ሆኖ ተጠቃሎ ሲፈታ ቀጥተኛ ሃሳብ፤ በሃይማኖትም የቀናች ቀጥተኛ ሃይማኖት ማለት ነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 1974 ዓም ሪቪል፡ ከመንፈሳዊነት ጋር ተያይዞ መዝፈን አቁመሻል? ዘሪቱ፡ መንፈሳዊነት ሁለገብና የሁለንተናችን ለውጥ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ደግሞ ከአለማዊነት ስንወጣ የማይነካ የህይወታችን ክፍል የለም፡፡ ሁሉም ነገር እኔ እንደምለውና ዓለም እንደምትሰብከው ሳይሆን እግ ዚአብሄር እንደሚለው የማድረግና የመሆን ሂደት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ታዲያ እንደ ሁሉ ነገሬ የጥበብ ስራየም ሳይፈተሸ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሙዚቃም ይሁን ፊልም፤ ብቻ ምንም ነገር ልስራ የማደርገው ነገር እግዚአብሄር የሚፈልገውን መለዕክት ያደርሳል ወይ? ሰዎችን ይጠቅማል ወይ? ደሞስ እንደሱ ፍቃድና ልክ ሰዎችን ያሳዝናል? ያስደስታል ወይ ብዪ በመጠየቅና ይልቁንም ከሱ ከራሱ መለዕክትን በመቀበል ወደ መስራት መንፈሳዊነት እያደኩ ነው፡፡ መዝፈን ይሁን መዘመር አላውቅም፡፡ የማውቀው እግዚአብሄር እንደሚከብርበት ነው፡፡ ሪቪል፡ ግን ዝናና ገንዘብን መስዋትነት ማድረግ የሚከብድ አይደለም? ዘሪቱ፡ እኔ ለመተው የሚከብድ የገንዘብ ክምችት የለኝም፡፡ዝናንም በተመለከተ ዘማሪዎች ከዘፋኞች ባልተናነሰ ዝነኞች የሆኑበት ዘመን እንደሆነ ነው የማስበው፡፡ ከዝና ወደ ዝና ብሸጋገር አሁን ከምከፍለው ዋጋ የበለጠ እንደምከፍል አውቃለሁ፡፡ ሪቪል፡ ቤት መኪናና ሌሎች አያስፈልጉም ብለሽ ነው የምታምኚው? ዘሪቱ፤ እኔ የማምነው ከሆነ ቦታ ተነስተህ የሆነ ቦታ ለመድረስ ትራንሰፖርት እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ መኪናው ያንተ ከሆ ጥሩ፤ ካልሆነም መኖርህን ለማታውቅበት ለዛሬ ባለቤትነትህ ያለው ፋይዳ ውስን ነው፡፡ የቤትም አስፈላጊነት መጠለያነቱ፤ትርጉሙም አብረውህ በሚኖሩት ሰዎች እንጂ በባለቤተረነት ካርታው አይደለም፡፡ የባለቤተረነት ዋስትና ለእኔ ትርጉም የለሽ ነው፡፡እግዚአብሄር ወዶ ለሚጨምርልኝ ለእያንዳንዱ ቀን የሚያስፈልገኝን ሁሉ እንደሚያዘጋጅልኝ አምናለሁ፡፡ ሪቪል፤ እንደዚህ ያለ ህወት ግን ላገባችና በተለይም ልጆች እናት ለሆነች ሴት አይከብድም? ዘሪቱ፤ እንደዚህ ያለ ህይወት ለማንም ቀላል አይደለም፡፡ በተለይም እንዳልከው፤ቤተሰብ ላለን ሰዎች ደግሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በስጋዊ አቅማችን ስንሞክረው ነው፡፡ ሰው የመሆንን ትርጉም ለመረዳት በፈቀድን መጠን ግን ራሱ እግዚአብሄር በእና ውስጥ ይችለዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ማለት፤ ሰው በሀጢያት ከመውደቁ በፊት ወደ ነበረው ማንነት የመመለስ ጉዞ ማለት ነው፡፡ ያ ማንነት ደግሞ ከእግዚአብሄር የመሆንና ማንነቱን የማንፀባረቅ ህይወት ነው፡፡ በመሬታዊ ገደብ እሱን ማንፀባረቅ አይቻልም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አሰልጣኝነት ከመሬታዊ ገደብ ወደ እሱ ማንነት የሚያሻግረን መመሪያ ሁሉ ደሞ በቅዱስ ቃሉ ወስጥ አለ፡፡ ኢየሱስ ለምን አይነት ክብር እንደጠራን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ከንግዳችን፣ ከቤተሰባችንና ከራሳችን ጭምር በላይ እሱን እንድናስቀድም ነው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ ደቀመዛሙርቶቹ ልንሆን እንምንችል በግልፅ አስቀምጦልናል፡፡ ስለዚህ እሱን በመከተል ውስጥ ምንም አይነት አቋራጭ አልፈልግም፡፡ ሪቪል፤ ባለቤትሽ በዚህ ደስተኛ ነው? ዘሪቱ፤ በጣም ደስተኛ ነው እንጂ፡፡ የምተገዛ ሚስት አድረጎለታል፡፡ ከዚህ ህይወት ጋር በተዋወኩባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በእኔ ላይ ባስከተለው የማንነት መናጋት ተከትለው በመጡ ጥፋቶች ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ ሚስትህ ፈርሳ እስክተሰራ መታገስ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ከመጀመሪያዋ የተሻለች ሚስት እንዳለችው እሱ ምስክር ነው፡፡ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2008 ኤፍ ቢ ሲ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት በእነ ሶሊያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ዛሬ ብይን ሰጥቷል። ጦማሪያን እየተባሉ የሚጠሩት እነዚህ ግለሰቦች ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተከሰሱ ነበሩ። በዚህ የክስ መዝገብ ውስጥ ከሚገ አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2008 ኤፍ ቢሲ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አምስተኛ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር መረጠ። በዚህም መሰረት አቶ አባይ ወልዱን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ ሲመርጥ፥ አምባሳደር ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተ ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ መስከረም 3 ቀን 2008 ዓም ================================================= በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓትኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠ ያኔ ስትዘፍን እና በየመሸታ ቤቱ ሰካራም ስታዝናና ምንም ያላላችኃት ሁላ ዛሬ ኢየሱስን ነው የምከተለው ስትል ምነዋ ለስድብ አፋቹ ተከፈተ? ነውር እንወቅ እንጂ ጎበዝ! አበዛቹት እኮ ሰው ዘፈን አቆምኩ ባለ ቁጥር ምንድን ነው መዘርጠጥ? ማንም እኮ የፈለገውን እምነት የመከተል ሙሉ መብት አለው። ደግሞስ ዘፈን ማቆም በየትኛው እምነት ነው ስህተት የሆነው? በየደብተራ መተተኛ ጠንቋይ መንደር ስር በበኣላት ስም ስታፈነድዱ ማን ሰደባቹ? እስኪ በቅድሚያ የገዛ እምነታቹን እወቁት ከዛ ኑሩት። ዝም ብሎ መቦርተፍ ያስገምታል። ምን ያሉ ጉድ ናቸው ባካቹ የኢትዮጵያ ሕዝብም ይፈታ! ለ484 ቀናት በር በሌለው እስር የቆየው ድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ በር ያለው እስር ቤት የመፈታቱ ዜና አስደስቶናል የኢትዮጵያዊው የሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ መፈታት ጥቅሙ አብሮ ታስሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሙዚቃንም ይፈታዋል ሲሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሲተነትኑ ተደምጧል አዎ ቴዲ አፍሮ ከታሰረ ወዲህ፤ የ2 ኤፍ ኤም ራድዮዎች መኖርም ታክሎበት በሀገራችን የሲዲ እና የካሴት ሽያጭ ወርዶ በርካታ የሙዚቃ አሳታሚዎች ሲያማርሩ ተደምጠዋል ካሁን በሗላ ቴዲ ተፈቶ የሚሰራው የሙዚቃ አልበም ገበያውን ያንቀሳቅሰዋል የሚል እምነት አለ ቴዲ ከእስር ቤት ከተፈታ በሗላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-ምልልስ ወቅት የተናገረው ነገር ቢኖር 'በቃሊቲ በርከት ያሉ ጥሩ ጥሩ ሰዎች እንዳጋጠሙትና መልካም ጊዜን እንዳሳለፈም ተናግሯል ከእነዚህ መልካም ሰዎች መካከል ደግሞ በኢሕአዴግ የታሰሩ የሕሊና እስረኞች እንደሚገኙበት አንጠራጠርም በኢሕአዴግ ዘመን ከታሰሩ የሕሊና እስረኞች መካከል ‘’በደህና" ሲለቀቅ ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያው ነው ለማለት እንደፍራለን በእርግጥ በደህና መፈታቱን ወይም ምን አይነት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተሰጡት ወደፊት ጊዜ የሚፈታቸው ሲሆን ቢያንስ ቢያንስ ግን ቴዲ እንደ ፕሮፌርሰር አስራት ሊሞት ሲል አለመውጣቱም ተመስገን ነው ቴዲ አፍሮን ለማስፈታት በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲጮኹ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ቴዲ የፖለቲካ እስረኛ እንደሆነ በመመስከር እንዲፈታ ጭምር ሲታገሉ ነበር አሁን ቴዲን ካስፈታን ደግሞ ሌሎች የሕሊና እስረኞችን ለማስፈታትና 'ተቃወምከኝ ብሎ የማሰር" ፖለቲካ በኢትዮጵያ ቀርቶ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን መታገል አለብን ከነዚህ ውስጥ አንዷ ደግሞ በግፍ የታሰረችው ብርቱካን ሚደቅሳን ጀምሮ፤ ሰሞኑን ለኢሕአዴግ ሚዲያዎች የወሬ ወፍጮ የሆነው የኦነግ አባል ናቸው ተብለው የታሰሩት እነ በቀለ ጅራታና ሌሎች በኢሕአፓ፣ በአርበኞች ግንባር፣ በግንቦት 7፣ በቅንጅትና በሌሎችም ምክንያት የታሰሩ ንጹሀን የዲሞክራሲ ታጋዮች እንዲፈቱ ትግላችንን የበለጠ ለማጠናከር ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል የመለስ ዜናዊ አስተዳደር የሕሊና እስረኞችን በአጠቃላይ አዲሱን የኢትዮጵያን ዓመት በማስመልከት ይፈታል ብሎ ማሰብ ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ቢሆንም ይህንን እንዲያደርግም ግፊት የማድረጉ ሀላፊነት በእኛው እጅ ያለ ይመስለናል የሕዝብ ልጅ የሆነውን ቴዲ አፍሮን ፈትቶ ሌሎች ሺሕ ቴዲ አፍሮዎችን በእስር ቤት ያጎረው ኢሕአዴግ በማናለብኝነት የሚያደርጋቸውን የሰብአዊ ጥሰቶች እንዲያቆም ቢመከር አልሰማ ካለ ሰንብቷል አምባገነን ሥርአት መሆኑና የሕዝብ ድምጽን የማያከበር መሆኑም ሲነጋ ሁሉም አውቆታል ለዚህም ነው አሜሪካኖቹ ፊት የነሱት እንደ አፍሪካ ሕብረት መቀመጫነቷ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም ሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት ሲዟዟሩ ኢትዮጵያን ሊያዩዋት ቢገባም ሳያይዋት የቀሩትና መንግሥቱን እርቃኑን ያስቀሩት በዚሁ በአምባገነንታቸው ነው ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ደግሞ እኛ በውጭ ያለነው ወገኖች በየቀኑ በምናደርገው በሰልፍ፣ በፒቲሽንና በሌሎችም መልኩ ማጋለጦች መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል ዛሬ በኢትዮጵያ ከሀገር ወዳድ ፖለቲከኞች ውጭ በሀገራችን መዋዕለ ነዋያችንን አፍስሰን፤ እኛም ተጠቅመን ወገናችንም የሥራ እድል ያግኝ ብለው የንግድ ድርጅት ያቋቋሙ ባለሀብቶች በገበያ ተወዳድረው በሀዜብ መስፍን የሚመራውን የኢሕአዴግ ግዙፍ የንግድ ተቋም በመጣላቸው እየታሰሩ ለመሆኑ ለዚህ መልእክት አንባቢዎች መንገር ለቀባሪው እንደማርዳት ይሆናል ሆኖም ግን ለወገናችን የሥራ እድል የፈጠሩ ባለሀብቶችም ካለ አግባብ 'የሙስና" ታፔላ ተለጥፎላቸው ሲታሰሩም ዝም ማለት የለብንም የመንግስት ባለስልጣናት እንደፈለጓቸው የፈለጉትን ሲያስሩ፣ ሲፈቱ፣ ሰብአዊ መብቱን ሲጥሱ እኛ ጋር ካልደረሰ ምን ቸገረን ብለን በቸልተኝነት መመልከት የለብንም የሀገራችን ሰው ሲተርት "ባልጀራህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ" ነውና ዛሬ የምናውቀው ሲታሰር የነገው ባለተራ እኛም እንደሆንን ማሰብና ከወዲሁ በቃችሁ ልንላቸው ይገባል በቀጣዩ ዓመት ይደረጋል በሚባለው "ምርጫም" ትክክለኛ እንደ ጋና ያለ የሚያስቀና ምርጫ ተደርጎ የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ስልጣኑን በሕዝብ ለተመረጠ ፓርቲ አስረክቦ ከእስር እንደማንወጣ የታወቀ ነው ይህ ከሆነ ደግሞ በቀጣዩ 5 አመታት በርከት ያሉ ቴዲ አፍሮዎችና በርከት ያሉ ብርቱካን ሚደቅሳዎች እንደሚታሰሩ አንጠራጠር ስለዚህ መብታችንን አውቀን ስለመብታችን እንጠይቅ ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው ሲደፈር፤ ሲንኳሰሱ፤ ሲገለሉ ለምን? ማለት እንጀምር ዛሬ ቴዲ አፍሮ በር ከሌለው እስር ቤት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደታሰረበት እስር ቤት ነው የተዛወረው እንጂ እሱም አልተፈታም ማለት እንችላለን ላለፉት ዓመታት ታስሮ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብም በነጻ የመናገርና የማሰብ እንዲም የፈለገውን አመለካከት እንዲያራምድ፤ የፈለገውን የፖለቲካ አቋም እንዲይዝ፣ በአጠቃላይ የዲሞክራሲ መብቱ 100% ተክብሮ ይፈታ ዘንድ እንታገል® ኢትዮጵያውያን ጀማሪ እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም የሚለውን ለመሻር በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ብዙ የጻፍን ወቅታዊ መረጃዎችን ስናደርስ የከረምን እውነትን ስለያዝን የታሰርን ታስረን የተፈተንን የእስር ፈተና ሳይበግረን ስደት የገባን ስደት ብዙ ፈትንኖን ብዙ አስተምሮ ብዙ አሳይቶ እዚህ ያደረሰን የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ኢነጋማ አባል የሆንን ጋዜጠኞች ነን በተለይ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ እና አሳታሚ የሆነው ሔኖክ አለማየሁ በስደት ከሀገር ወጥቶ በሱዳን በሊቢያ ብዙ ግፎችንና መከራዎችን የተቀበለና ያሳለፈ ሲሆን በሀገረ ሶሪያ እና በቱርክ ብዙ ሕይወቶችን አሳልፎ እዚህ የደረሰ ነው እነዚህ የስደት ታሪኮች አምድ ተሰጥቷቸው በጋዜጣችን ላይ ሕይወት እንዲህ መራራም ጣፋጭም እንደሆነች የሚያሳይ ጽሑፍ ከዚህ እትም ጀምሮ ቀርቧል ይከታተሉት ብዙ ጊዜ የውጭ ሀገር ሰዎች ''ኢትዮጵያውያን ጀማሪዎች እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም"" ሲሉ ይተቹናል ይህን የሚሉበት ምክንያት ጥንት ከዓለም በፊት ሥልጣኔን ወደ ሀገራችን አስገብተን ዛሬ ዓለም የቀደመንን እንደምሳሌ በማንሳት ነውእናም እናንተም የማንበብ የውዴታ ግዴታችሁን ከተወጣችሁ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ጀማሪ ብቻ ሳትሆን ታሪክ ሠሪም መሆን ትችላለች በነገራችን ላይ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ጀማሪ እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም የሚለውን ለመሻር ሁላችንም በተሰማራንበት የሥራ መስክም ሆነ የኑሮ አቅጣጫ መታገል አላማችንን ከግብ የማድረስ የአባቶቻችንን የቆራጥነት መንፈስ እላያችን ላይ ማሳረፍ ይኖርብናል እኛም ጀማሪ ብቻ ሳይሆን ጨራሽም ለመሆን ዛሬ አንድ ብለን የጀመርናትን ጋዜጣ እንድታነቡልን ስንጋብዝ በጋዜጣው ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ የአዘጋጁን አቋም እንደማያንጸባርቁ እንድታውቁልን እንፈልጋለን የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር በሚያዘን መንገድ ወገኖቻችንን በማንኛውም መልኩ ለማገልገል መጥተናል እንኳን ደህና መጣችሁ በሉን በመስከረም በቀለ እኛ ሴቶቹን ለሰላምታ ስንስም እንደው ባህሉን ለመጠበቅ ያህል ቦረሽ ቦረሽ አርገውን ነው የሚሄዱት። ሴትና ሴት ሲሳሙ ግን ዳኮታ የሚኖሩ አበሾች አብዛኛዎቹ የሚሰሩት በሬ እየታረደ የሚከፋፈልበት የሥጋ መሸጫ ፋብሪካ ውስጥ ነው። አንደኛው ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት ተለቅ ያሉ ሰውዬ ስለ ስራቸው ጠይቄያቸው ደስተኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። “እንደውም” አሉ ሲያጫውቱኝ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ ሚስታቸውን “ምሳ ቋጥሪልኝ” ሲሏት በብልቃጥ አዋዜ እንደምትሰጣቸው አጫውተውኛል። ሁሌ ፋሲካ ማለትም አይደል? የአሜሪካ አገር የሥራ ባህል ከኛ አገር ጋር በጣም የተለየ ነው ። ከሁሉም ነገር ለኛ የሚከብደን ግን የሽያጭ ሥራ ስንቀጠር ገብያተኛ ሲመጣ “ፈገግ በሉ” የሚሉን ነው። ትዝ ይለኛል የመጀመሪያ ሥራዬ አለቃዬ “ጎበዝ ጎበዝ” ሲለኝ 8፡00 ሰዓት ሙሉ ጥርሴን አግጥጩ ማታ ቤት ስገባ ጉንጩን ስትራፖ ይዞኝ እንደ ቦክሰኛ ጉንጬን ቫዝሊን ተቀብቼ ነው ያደርኩት። ጮክ ብሎ ማውራትም ሌላው ችግር ነው። አሜሪካኖች ጮክ ብሎ አለማውራትን እንደድክመት ያዩታል። እኛ በባህላችን ጮክ ብሎ የሚያወራ ሰው ገገማ ወይም ባለጌ ነው የሚባለው፤ እኛ ቤት ጮክ ብለን የምናወራው ከአሜሪካ ስልክ ሲደውል ወይም ፈተና ወድቀን ስንገረፍ ብቻ ነው። አንድ ቀን አንድ እብድ የሚያክል አለቃዬ… በነገራችን ላይ እኛ ሰፈር ያሉት እብዶች እንደአጋጣሚ ቀጫጮች ናቸው። ስለዚህ ለምሳሌ ያህል የናንተን ሰፈር እብዶች ተጠቀሙ። አፍንጫዬ ሥር ቆሞ ምራቁን ግንባሬ ላይ እያፈናጠቀ ጆሮዬን በጩኸት ሲቀደው ለሱ ሲያወራ አንድ ሰውዬ ትዝ አሉኝ። ሰውዬ ጆራቸውን ደከም ብሏል። እዚሁ አሜሪካ ለሚኖረው ልጃቸው “እባክህ ጆሮ ላይ ተሰክቶ የሚያሰማ መሳሪያ አለ አሉ “ሄሪንግ ኤድ” የማይሰራውን ገዝተህ ላክልኝ”፤ ልጁም ግራ ተጋብቶ ለምንድን ነው የማይሰራውን የምልክልህ? ቢላቸው እሳቸውም “አይ ልጅ እኔ የ 85 ዓመት ሽማግሌ ነኝ ከአሁን በኋላ ስንት ጊዜ እንደምኖር አላውቅም። አንተንም ባለቀ ሰዓት ከማከስርህ የማይሰራውን ላክልኝና ላርገው እሱን ጆሮዬ ላይ ሲያይ ይሄ ሽማግሌ ጆሮው ችግር አለበት ብለው ጮክ ብለው ያወራሉ አሉ። እኔም ታዲያ ድሮ አንዴ ይሄ ግለሰብ ድምጼ ቀጠን ስላለ ጆሮዬ የማይሰማ መስለው እንዴ ስል ነበር። ካሊፎርኒያ ደግሞ ከ600 በላይ የሚሆኑ አበሾች የሚሰሩበት ካምፓኒ አለ። ጠዋት ጠዋት አበሾች ወደ ሥራ ሊገቡ ሲሉ ካምፓኒው በር ላይ ሰላምታ እየቀያየሩ እየተሳሰሙ ፈረንጆች አላስገባ ስላሏቸው ባለፈው ዓመት የካምፓኒው በር ላይ “ ” መሳሳም ክልክል ነው የሚል ሳይን “ ” ከሚለው ጎን ፈጥረዋል። እንደው የከንፈር ሊስትሮ አትበሉኝና ሰላምታ ላይ መሳሳም ከሚወዱት ውስጥ አንዱ ነኝ። የካምፓኒው ችግር ከወንዶች የመጣ አይመስለኝም። እኛ ሴቶቹን ለሰላምታ ስንስም እንደው ባህሉን ለመጠበቅ ያህል ቦረሽ ቦረሽ አርገውን ነው የሚሄዱት። ሴትና ሴት ሲሳሙ ግን በተለይ አንዳንዶቹ በእያንዳንዱ መሳሳም መሃል የፉገራ ወሬ ያወራሉ። “የጠፋ ሰው” ሳም ዛሬ ደግሞ በጠዋቱ ፏ ብለሻል፤ ሳም… ፀጉርሽ ደግመሽ ተቀባሽው እንዴ? ”… ሳም… የኔ ስልክ ነው ወይስ ያንቺ የሚጮኸው? ” ሳም። … ® ከሊሊ ሞገስ ያንን ዋሽንት አምጡት ዋ ባይ ትካዜው ቢለቀኝ መቼም ያለ ሀሳብ ዋ ባይ ምንም ዘመድ የለኝ ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋስንቱ ልበል በዋሽንቱ ''ኩኩ መለኮቴ'' ከተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ላይ ''ዋ ስንቱ'' የተሰኘችዋን ምርጥ ዜማ ነበር ግጥሟን የቆነጠርኩላችሁ የእድሜን እና የትውልድ አመተ ምህረተ ምህረቱን ነገር ለእናቱ ወይም ለአባቱ እንተወው እና ይሁኔ በላይ በአጭሩ የተወለደው በጎጃም ክፍለ ሀገር በፍኖተ ሰላም ከተማ ነው ዛሬ የትራንስፖርት ችግሩ በመጠኑም ቢሆን የተቃለለበት ወቅት ይሁን እንጂ በዛ ዘመን ወደ ባህር ዳር አልያም ጎንደር ሲሄዱ አዳር ፍኖተሰላም ነበር በፍኖተ ሰላም ግሮሰሪዎች መንገድ ላይ እና በአጠቃላይ ሆቴል ቤቶች ማስንቆ ያነገቡ ብዙ አዝማሪዎችን አላያችሁም? ታለንትድ ከሆኑት እነዚህ ሕጻናት አዝማሪዎች መካከል አሁን ብዙዎቹ ወደሙዚቃው አለም ገበተዋል - ጥቂቶቹ እንደ ይሁኔ በላይ ተሳክቶላቸዋል ከቤተሰቦቹ 3 ልጆች የመጨረሻው የሆነው ይሁኔ ከላይ ብዙዎች እንደሚመሰክሩለት ማንነቱን አይረሳም የሙዚቃ ፍቅሩና ታለንቱ ወደ ጥብበ የመራችው ብዙዎቹ ''የጎጃም አምባሳደር'' የሚሉት ይሁኔ በላይ ግሽ አባይ ባንድ ውስጥ በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራት የሙዚቃ ክሊፕ ሙዚቃዊ ድራማውን ለሕዝብ አደረሰ ''አንቱዬዋ'' የተሰኘችው ድራማዊ ሙዚቃ ሰማህኝ በለውን ሳይቀር ያካተተች ስትሆን ለይሁኔ በላይ መታወቅ በሩን የከፈትችለት ዜማ ነበረች ግሽ አባይ ባንድ በርካታ የባህል ሙዚቀኞችን ለሕዝብ ያደረሰ ለባህል ሙዚቃችን እድገት ትልቁን ሚና የተጨወተ ስብስብ ነበር ''በልጅነታችን በግሽ አባይ ውስጥ የምንሰራቸው ሥራዎች የሚገርሙ ነበሩ'' የሚለው ይሁኔ ስለ አንቱዬዋ የሙዚቃ ድራማ አውርቶ አይጠግብም ''ፈጠራውን እስከአሁን ድረስም አደንቃለሁ'' የሚለው አርቲስቱ ''ከሕዝብ ጆሮ ዜማዋ ከደረሰች ጊዜ ጀምሮ የእኔ ሕይወት አንድ በአንድ እየተለወጠ መጣ'' በማለት የሕይወት መስመሩን ይህ ስራው እንደጠቆመው ተናግሯል ''የእኔ የሙዚቃ ሕይወት የሚጀመረው ከአካባቢ ነው ቆላ ደጋ ዳሙት የሚል ፍላጎት ያላቸው ልጆች ስሜታቸውን የሚያስደስቱበት የወረዳ የሙዚቃ ቡድን ነበረ እዚያ እየተሰባሰብን ራሳችንን ከማስደሰት አልፎ በአንዳንድ ዝግጅቶች ላይ ሥራዎቻችን ማቅረብ ጀመርን'' የሚለው ይሁኔ የሙያ መሰረቶቹን አንድ በአንድ ያስረዳል ''ከዚህ በፊት ግን በትምህርት ቤት ለጓደኞቼ ስዘፍን አስተማሪዬ አይተው አንተ በኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ ዘፋኝ ትሆናለህ ብለው የሰጡኝ ማበረታቻ ለዛሬው መሰረት ሆኖኛል ይላል ''እረ ነይ ግቢ ግቢ ግቢ አረ ነይ ግቢ ግቢ አንቺ ልጅ ግቢ ግቢ እረ ተይ ግቢ ግቢ በኔ ሞት ግቢ ውጡና አነጋግሯት አንድ ሁለት ሆናችሁ የቆመችበትን ምክንያት ጠይቃችሁ እሷ ውጭ ቆማ በር ተቀምጣ ማን እህል ሊበላ ማን ማን ውሀ ሊጠጣ የታለች በር ቆማለች ; አስገቧት አልገባም አለች!! '' ‘’ሙሉቀንን ማዳመጥ፤ ማድነቅና የእርሱን መድረክ ውሎን ፊት ለፊት እያየሁ ከሥር ከሥሩ የእርሱን ፈለግ ልከተል፤ እርሱ በዋለበት መድረክ ለመሰማራት ልቤ ተሰቅሎ ደፋ ቀና ስል ከመቅስፈት ከዘፈኑ ዓለም ተሰወረ ይሁንና ጋሼ ሙሉቀን አዘፋፈኑ ማለቴ ድምጽ አወጣጡ፤ ግጥምና ዜማ መርጦ በማዋሀድ ያቀርባቸው የነበሩት ዘፈኖቹ ዛሬም፤ ነገም ለእኔም ሆነ ለመላው አድናቂዎቹ መጽናኛ ሆኖናል በተረፈ ግን ድምጻዊ ሙሉቀንን የሚተካ ዘፋኝ ይፈጠራል የሚል ግምት የለኝም’’ ለድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ አድናቂዎች የኢንተርኔት መረብ ይሁኔ በላይ የሰጠውን አስተያየት ነው የቆነጠርኩላችሁ ከዚህ የይሁኔ በላይ ንግግር የምንረዳው ለሙዚቃ መሰረቱ ሙሉቀን መለስ እንደሆነ ይሁን እንጂ የይሁኔ የሙዚቃ ሕይወት ስኬት በር ከፋቹ መምህሩ እንደሆኑ በአንድ ወቅት በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አትቷል ‘ ' ! ’ ጆስ የተሰኘው የመረጃ መረብ ስለ ይሁኔ የተናገረው ነው ከሙዚቃ ቡድኑ አልፎ የመጀመሪያ አልበሙን ለሕዝብ ያቀረበው ይሁኔ የአዘፋፈን ስታይሉ ሙሉ በሙሉ ባህል የተላበሰ እና እንቅስቃሴውም ከዘፈኑ ጋር አንድ አይነት በመሆኑ ቶሎ ሕዝብ ሊቀበለው ችሏል ''ያገሬ ልጅ ባለጋሜ ትውልዷ ጎጃሜ'' የተሰኘችው የይሁኔ የመጀመሪያ አልበም በመላው ኢትዮጵያ የተደመጠ ሲሆን በባህል ሙዚቃ የካሴት ሽያጭም የወቅቱ አንደኛ እንደነበር ይነገራል ይህ ሥራው ስኬትን ያጎናጸፈው በትክክልም የጎጃም ''አምባሳደር'' ቢባል የማያንሰው ይሁኔ ''አሎ ሉሎ''ን አልበም አከለ ይህም አልበም እንደወጣ የሕዝብ ጆሮ ለመግባት ጊዜን አልፈጀበትም ''ብዙዎች እድለኛ ነህ ይሉኛል በእርግጥም እድለኛ ነኝ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ቶሎ ሕዝብ ጋር ለመድረስ ችያለሁ'' የሚለው ይሁኔ ለዚህ ሁሉ ስኬቱ ግን ያሳለፈውን ችግር እና መከራ አይዘነጋም ''ብዙ ነገሮች በሕይወቴ ውስጥ ደርሰውበኛል ሁሉም በእግዚአብሄር ሀይል አልፌ ለዚህ በቅቻለሁ'' ሲል ፈጣሪውን ከምንም በላይ ያመሰግናል ይሁኔ 3ኛ አልበም ሲወጣ ስታይሉም እያደገ እንደመጣ አሳየ ከባህል ሙዚቃዎች ወጣ ብሎም ወደ አፍሪካ ስልት ሙዚቃዎችም የኢትዮጵያን ባህል አስገብቶ መስራት ጀመረ ''ብ ብ ከፊላው ስር'' የምትባለው አልበሙ የብቃቱን ደርጃ እጅግ አድርጋ ማደጉን ያሳየች አልበም ነበረች ይሁኔ ከዛም ኩኩ መለኮቴ የተሰኘውን አልበሙን ሲያወጣ ከአሜሪዋ የወቅቱ ፕሬዚዳንት ከነበሩት የቢል ክሊንተን ባለቤት ሚስ ሂላሪ ክሊንተን ጋር ለመገናኘት እና ካሴቱን በስጦታ ለማበርከት ችሏል የሙዚቃ ሥራውን በመጠኑም ቢሆን ከቃኘን ወደ ግል ሕይወቱ ስንመለስ ይሁኔ ከባለቤቱ የሺመቤት ቱቱ ጋር በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ውስጥ ከአንድ ወንድ ልጁ እና ሴት ልጁ ጋር በፍቅር ይኖራል ይሁኔ ለልጆቹ የኢትዮጵያን ባህል እንዳይዘነጉ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አስታውቆ ብዙ ጊዜ ልጁን የጎጃም ሕጻናት የሚለብሱትን የባህል ካኪ ልብስ እንደሚያለብሰው እና ምንነቱን ጠንቅቆ እንደሚያሳውቀው የቅርብ ወዳጆቹ ይናገራሉ ይሁኔ በላይ የልጆቹ ስሞች ፍቅር ይሁኔ እና ሰላም ይሁኔ ይባላሉ በአሁኑ ወቅት ይሁኔ ከዘፋኝነቱ ሌላ የተሳካለት ነጋዴም ሆኗል በአሜሪካን ሀገር የሚታተም የሎ ፔጅስ አለው ይህ የሎ ፔጅስ ታርጌት የሚያደርገው በአብዛኛው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብን ነው ሻሎም!! ® ኢትዮጵያውያን ቆንጃጅት በዓለም ላይ ነገሡ ሚስ ሚሊኒየም ተብላ በኢትዮጵያ አሸንፋ የነበረችው ሞዴል ኪዳን ተስፋሁን የአለማችን ምርጥ የሴቶች ሞዴል 2009 በመባል በስፔን ተመረጠች የተባለው ድርጅት ስፔን ላይ ባዘጋጀው ውድድር ላይ ያሸነፈችው ኢትዮጵያዊቷ ኪዳን 18 ሜትር የሚለካ ቁመት አላት የ24 አመቷ ኪዳን ካሸነፈች በሗላ በሰጠችው ቃል በሀገራችን እምብዛም ያልተለመደውን የሞዴልነት ሞያ በደንብ ለማጠናከር ጠንክራ እንደምትሰራ ተናግራለች ከዚህ ቀደም 2008 ተብላም ያሸነፈችው ኪዳን በስፔን ማሸነፏ ሀገራችንን ስሟን በመልካም ጎኑ ያስጠራል ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጥቂት ወራት በፊት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችው ሳራ ኑሩ በጀርመን የሞዴል ውድድር ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን ቆንጆዋ ለሥራ ወደ ኒውዮርክ መዘዋወሯን ኮስሞፖሊታን የተሰኘው ታዋቂው የሴቶች የውበት መጽሄት ዘግቧል የጀርመን ቁጥር አንድ ሞዴል ሆና የተመረጠችው ሳራ ኑሩ ዝናዋ ባመጣላት ጸጋ ከእጅ ስልክ አምራቹ ሶኒ ኤሪክስን ኩባንያ ጋር የማስታወቂያ ውልአድርጋለች፣ በዚሁ መሰረት የሶኒ ኤሪክስን ስልኮች ሲወጡም ሆነ በየቦታው በሚደረገው ማስታወቂያ ሥራ ኑሩ ፈገግ እንዳለች የሚያሳየው ፎቶዋአብሮ ይወጣል። አዲሱ የሶኒ ኤሪክሰን ስልክ ፎቶ የሚያነሳው ሳቅ ሲሉለት ብቻ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ሳራም ፈገግታዋን እያሳየች ስልኩን ታስተዋውቃለች ማለት ነው። ® ወጋየሁ ደግነቱ አረፈ "የሰው የእንስሣት የአራዊት… እናት እኮነች መድኃኒት”" በሚል ዜማው የምናውቀው ተወዳጁ ድምጻዊ ወጋየሁ ደግነቱ አረፈ ከአባቱ ከአቶ ደግነቱ ጅማ ከእናቱ ከወሮአበራሽ ወዳጆ ጥር 12 ቀን 1940 ዓም በሀረርጌ ክሀገር በወበራ አውራጃ በጐሮ ጉቱ ወረዲ ልዩ ስሙ መካኒሳ በተባለው ስፍራ ተወልዶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በሀረር ልዑሌ መኮንን አንደኛ ደረጃ ትቤት ተከታትሎ በነበረው ልዩ የሙዚቃ ፍቅር የተነሳ መጋቢት 1 ቀን 1955 ዓም በሀረርጌ ክሀገር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል በታዳጊነት ዕድሜው ተቀጠረ፡፡ ከ1957 ዓም ጀምሮ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪ ድምፃዊ ለመሆን የበቃው ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ፤ በ1959 ዓም ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ የሀረር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል የተወዛዋዥ ቡድን አሰልጣኝ፣ የዜማና የግጥ ም ደራሲ ሆኗል ስለእናት በዘፈነው ዘፈን እና 'ፈንዲሻ" በተባለው ሙዚቃው የሚታወቀው ወጋየሁ ከሙዚቃው ጎን በተማረው የህግ ሙያ በጥብቅና ሙያ እስከአረፈበት ጊዜ ድረስ ሲያገለግል ነበር ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ለነብሱ ገነትን ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ትመኛለች® ሕይወት ሽንኩርት ናት ስትላጥ ብታስለቅስም ስትበስል ግን ትጣፍጣለች ከሕይወት ስንክሳሮች መካከል ደግሞ አንዱ ስደት ነው የሰው ልጅ የተሻለ ኑሮን ወይንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ሲሰደድ እንደሽንኩርቷ በችግር ሲላጥ አልቅሶ; የተፈተነበት ውጤት ሲያልፍ ደስተኛ ይሆናል የዛሬዋ እንግዳችን በሚኒሶታ ብቸኛዋ የታክሲ ሹፌር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ቅድስትም በሕይወት ስንክሳር ብዙ ተፈትና ዛሬ እዚህ ደርሳለች የዚህችን ሴት ታሪክ ሰማንና የጋዜጣችን እንግዳ ለማድረግ ወደ ስልኳ በተደጋጋሚ ደወልን ከስልኳ የምናገኘው የሚለውን አናዳጅ ምላሽ ነበር ሆኖም ግን በነዚህ ቃላት መካከል "ኪኪ" የሚል ድምጽ ስናገኝ ስልኳ የእርሷ መሆኑን አረጋግጠን ድወላችንን ቀጠልን ምላሽ ስናጣም የድምጽ መልዕክት አስቀመጥን; ቅድስት ወይም ኪኪ ወዲያውኑ ስልካችንን መለሰች ከዛም የሚከተለውን እዛው የምትሠራበት ፖስት ሮድ ተቀጣጥረን የታክሲዋን መስኮት ከፍተን አወራን ዘ-ሐበሻ- ተጀመረ! ቅድስት- ምኑ? ዘ-ሐበሻ- ቃለ ምልልሱ! ቅድስት- ሳቅ ዘ-ሐበሻ- ምነው? አልተዘጋጀሽበትም እንዴ? ቅድስት- ኸረ እንደውም! ዘ-ሐበሻ- የፈራሽ ትመስያለሽ? ቅድስት- እንዴ እኔ ለኢንተርቪው አዲስ አይደለሁም እኮ! ድሮ እኔም ራሴው ኢንተርቪው አደርግ ነበር ዘ-ሐበሻ- ኦው! ጥሩ ታዲያ ራስሽም ቃለ-ምልልስ ታደርጊ ከነበረ; እንዲሁም ብዙ ሰው ቃለ-ምልልስ ሲደረግለት አይተሻልና ጋዜጠኞች ብዙ ጊዜ አስቀድመው የሚጠይቁት ነገር ስለምንድን ነው? ቅድስት- ስለማንነት! ከራሳቸው ላይፍ ስታይል ከስማቸው ያሉበትን የመጡበትን ዘ-ሐበሻ- ታዲያ እኛም ከእርሱ እንጀምር? ቅድስት- እንደፈለክ! ዘ-ሐበሻ- ይሄንን በቅድሚያ ብጠየቅ የምትይው ነገር ካለ? ቅድስት- ይሄን ብጠየቅ? ዘ-ሐበሻ- አዎ! ቅድስት- ሳቅ! የሥራ ሁኔታ እንዴት ነው? አንቺ ሴት ሆነሽ እንዴት እዚህ ቦታ እንዴት መጣሽ? ብቻሽን ነሽና እንዴት ልትመጪ ቻልሽ ምናምን ነው መስለኝ ጥያቄው የሚመስለኝ ሳቅ እና ተደሰቺበታለሽ ወይ በሥራው? ይመስለኛል ዘ-ሐበሻ- እሺ ቅድስት ማናት ብለን እንጀምር! ቅድስት- ቅድስት ታዬ ዘ-ሐበሻ- ይህን ጋዜጣ ለሚያነቡ ሰዎች ራስሽን አስተዋውቂ ብትባይ እንዴት ራስሽን ትገልጪዋለሽ? ቅድስት- የመጣሁት ከኢትዮጵያ ነው ተወልጄ ያደግኩትም ጅማ ውስጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተማርኩና ከሰራሁ በሗላ ወደ አውሮፓ ሄድኩኝ ከአውሮፓ ወደ እዚህ መጣሁ ወደዚህ ሙቭ ሀገር የቀየርኩት ያደረግኩት በ1998 ነው ዘ-ሐበሻ- አውሮፓ የት ነበርሽ? ቅድስት- ስዊድን ነበርኩ! ዘ-ሐበሻ- እንዴት ነበር ወደ አሜሪካ የመጣሽው? ቅድስት- መጀመሪያ ያው በደርግ ጊዜ ነው ከሀገር የወጣሁት ስዊድን ሀገር ሄጄ ከዛ በሗላ 10 ቆየሁ እዛ እያለሁ; እኔ እንኳን አልሞላሁም ጓደኞቼ ዲቪ ሞልተው ላኩልኝና መልሱ ሲመጣ በእኔ አድራሻ መጣ ዘ-ሐበሻ- ስዊድን ሆነሽ ማለት ነው? ቅድስት- አዎ! ዘ-ሐበሻ- ኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነበር ሞያሽ? ምንድን ነበር የምትሰሪው? እዛም እንደዚሁ ታክሲ ትነጂ ነበር? ቅድስት- ሙያ የሚባል ነገር ያው ሀይስኩል ከጨረስኩ በሗላ ባንክ ትንሽ ሰርቻለሁ ዘ-ሐበሻ- ቅድም የጋዜጠኝነት ሙያው አለኝ; በራዲዮ ሰርቼ ነበር ስትይኝ ነበር? ቅድስት- ጋዜጠኝነት እንኳን ሳይሆን በራዲዮ ነው የራዲዮ ፕሮግራም እናዘጋጅ ነበር - በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኢቫንጀሊካል ቤተክርስቲያን ፕሮግራም እያዘጋጀን ስዊድን ሀገር ለ5 አመታት ሰርቼበታለው ዘ-ሐበሻ- አሜሪካ ከመጣሽ በሗላ የታክሲ ሹፌርነቱ ሥራ የመጀመሪያ ሥራሽ ነው? ቅድስት- አይደለም መጀመሪያ ኤርፖርት ውስጥ እሠራ ነበር ለ2 ወራት በኤርፖርት ሥራዬ ሴክዩሪቲ ሆኜ ነበር የሠራሁት ከዛ በሗላ ደግሞ የአፍሪካ ሕጻናት እና ሴቶች እንክብካቤ ቡድን ውስጥ ሰርቻለሁ በዚህ መሥሪያ ቤት ውስጥ በሰዎች "አብዩዝ" የተደረጉ ልጆችን እና ሴቶችን መርዳት ነበር ሥራችን ከ6 እስከ 8 ወር ለሚሆን ጊዜ ሰርቻለሁ ዘ-ሐበሻ- በሀገር ቤትም; በስዊድን ቆይታሽም የታክሲ ሾፌር ካልነበርሽ እንዴት አሜሪካ መጥተሽ ይህንን የሥራ ክፍል ልትመርጪው ቻልሽ? ቅድስት- ባንክ ሰርቼ ነበር በዌልስ ፋርጎ ባንክ ውስጥ እየሰራሁ አብሬያቸው ቸርች የምሄዳቸው ልጆች እነርሱ ታክሲ ይነዳሉ እና ብዙ ጊዜ አንዳንድ ቦታ ለመሄድ አንድ ነገር ለማድረግ; በሕብረት የሆነ ነገር ለማድረግ እነርሱ ፍሪ ጊዜ አላቸው ናቸው እኔ ማስፈቀድ ምናምን ስላለብኝ አይመቸኝም ከዛም ለምን እኔም እንደነርሱ አልሰራም ብዬ አስብ ነበር ይህ ሀሳብ በአእምሮዬ ውስጥ እንዳለ አንድ ቀን መንገድ ላይ ስሄድ አንዲት ሶማሌ የባሏን ታክሲ ይዛ ነው መሰለኝ ስትነዳ አየሗትና እንዴት የሱማሌ ሴት ታክሲ የነዳች እኔን ያቅተኛል ብዬ ካልጀመርኩኝ ሞቼ እገኛለሁ አልኩ ዘ-ሐበሻ- ከዛስ? ቅድስት- ከዛማ አብረውኝ ቸርች የሚሄዱትን የታክሲ ሹፌሮች አነጋግሬያቸው ታክሲ ሥራ ለመጀመር እንዴት እንደማደርግ ፕሮሰሱን ነገሩኝ እና ጀመርኩት ዘ-ሐበሻ- አንዴ ኢንተርቪውን ላቋርጠው ጉንፋን ይዞኛልና አፍንጫዬን ማጸዳዳት ይኖርብኛል ቅድስት- ሶፍት ልስጥህ? ዘ-ሐበሻ- አይ ተይው! ግን ጉንፋኔን እንዳላጋብብሽ? ቅድስት- ! ሳቅ ዘ-ሐበሻ- ከጥቂት ቆይታ በሗላ እሺ አሁን መቀጠል እንችላለን እና ያቺ ሱማሌ ነች መነሻ የሆነችሽ ማለት ነዋ! ቅድስት- አዎ ሱማሌዋ ናት መጀመሪያ አእምሮዬ ውስጥ የነበረውን ሀሳብ በደንብ አጠናክሬ እዚህ ሥራ ውስጥ ያደረገችኝ ማለት ይቻላል በጣም ሞራል ሰጠችኝ የሶማሌ ሴት የነዳች እንዴት ያቅተኛል ብዬ ገባሁበት ዘ-ሐበሻ- የታክሲ ሾፌር ከሆንሽ በሗላ ሥራውን እንዴት አገኘሽው? ቅድስት- በጣም ቀላል ሥራ ሆኖ ነው ያገኘሁት ስለእውነት ለመናገርም የሚከብድ ሥራ አይደለም ደግሞ ከእኔ በፊትም የሚገርምህ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሴት የታክሲ ሾፌሮች ነበሩ ሆኖም ጥቂት ጊዜ ሰርተው ጥለው ወጡ ወዲያው ዘ-ሐበሻ- አሁን ግን እዚህ የኤርፖርት ታክሲ ላይ አንቺ ብቻ ነሽ ሴት? ቅድስት- ያው ከሀበሻ እኔ ብቻ ነኝ ከነጮች ግን አንድ ሴት አለች 5 ይሆናል ብቸኛዋ ሴት የሀበሻ የታክሲ ሾፌር እኔ ነኝ ያለሁት ዘ-ሐበሻ- ከብዙ የታክሲ ሾፌሮች እንደምሰማው ሥራውን የምትሰሪው ትንሽ ሀላፊነት ወስደሽ ነው ወንጀለኛ ሊያጋጥም ይችላል ሰካራምና በአደንዛዥ እጽ የደነዘዘ ሰው መጫን አለ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰው ጭነሽ መንገድ የመጥፋት ነገር አለ እና አንቺ በዚህ ሥራ ውስጥ ያጋጠመሽ ነገር ምንድን ነው? ቅድስት- ጥሩ ጥያቄ ነው ወንጀለኛ እንኳን አጋጥሞኝ አያውቅም በጣም የሚያጋጥመኝ ያው መንገድ መጥፋት ነው በታክሲ ስራ ውስጥ መንገድ መጥፋት ነው ይሄ እ እ እንደማሰብ አለችና አንድ ጊዜ እንደውም ምን አጋጠመኝ መስለህ? አንዱን ደንበኛዬን ሆቴል እየወሰድኩት እያለ ሰውዬውም እኔም ሆቴሉ ያለበትን ቦታ አናውቀውም እየነዳሁ ሆቴሉ ጋር ስልክ ደውለን አድራሻውን ጠየቅኳቸው በየት በየት እንደምሄድ የነገሩኝ በትክክል አልገባኝም በቃ ሰውዬውን ይዤው ጠፋሁ ይገርምሀል ሰውዬው ምንም ነገር አይናገርም ዝም ብሎ ብቻ ነገሩን ይከታተላል ከተማውን ዞሬ ዞሬ እንደገና ሆቴሉ ጋር ስደውል የሚነግሩኝ መንገድ አይገባኝም ቢቸግረኝ ስልኩን ለተሳፋሪው ሰጠሁት ከዛ በሗላ በይ ከዚህ በኩል ተመለሺ ብሎኝ በተሳፋሪዬ እየተመራሁ ሆቴሉ አደረሰኩት ካሁን ካሁን ጮኸብኝ ብዬ ስፈራ እሱ እንደውም ቲፕ አድርጎ ሲከፍለኝ እኔ 'ይሄን ያህል ገንዘብ አይመጣም; እንደውም ጊዜህን ሁሉ ስላጠፋሁብህ አላስከፍልህም' ስለው እርሱ ጥሩ ሰው ስለነበር ከነቲፑ ሰጥቶኛል ሆኖም ግን ወንጀል ምናምንም አጋጥሞኝ አያውቅም ዘ-ሐበሻ- አንቺ የታክሲ ስራ አስከፊ ጎን የምትይው ምንድን ነው? ቅድስት- መቼም በእኔ አስከፊ አድርጌ የምወስደው መንገድ መጥፋትን ነው ሰው ይዞ መጥፋት በጣም በጣም የሚያስፈራ ነው ሌላው ደግሞ ማታ መሥራት ትንሽ አደገኛ ሊሆን ይችላል አንዳንድ ጊዜ የሰከረ ሰው ሊያጋጥም ይችላል ማታ መሥራት ጥሩ አይደለም በተለይ ወደ ኖርዝ ሚኒያፖሊስ ማታ ከሆነ ሰው ይዞ መሄድ ብዙም ጥሩ አይደለም ዘ-ሐበሻ- አንቺ ማታ ማታ አትነጂም ማለት ነው? ቅድስት- ማታ በጣም አላመሽም ዘ-ሐበሻ- በሴትነትሽ ተሳፋሪ ሆኖ የሚተናኮልሽ የለም? ቅድስት- ማለት የኤርፖርት ታክሲ ስለሆነ የምሰራው ብዙም እንደዚህ ያለው ነገር አያጋጥምም ብዙ ጊዜ ከኤርፖርት ራሳቸውን ችለው; የኤርፖርት ትኬት ገዝተው የሚሄዱ ሰዎች ወደ ቤታቸው ወይም ወደ ሆቴል አንዳንዴም ወደ ሥራቸው ስለሆነ ብዙም እንደዚህ አይነት ሰዎች የሉም የሲቲ ታክሲ ስለማልሰራ ብዙም አልጨነቅም የሲቲ ታክሲ ግን ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያለው ነገር ሊከሰት ይችላል ዘ-ሐበሻ- በሚኒሶታ በሲቲ ታክሲ ውስጥ ሴት ሹፌር አለች እንዴ? ቅድስት- ! የለችም ዘ-ሐበሻ- እዚህ ሚኒያፖሊስ-ሴንትፖል ኤርፖርት ታክሲ ሥራ ላይ የተሰማሩ ስንት ኢትዮጵያውያን አሉ? ቅድስት- እስከ 150 የምንሆን ይመስለኛል ዘ-ሐበሻ- እንግዲህ ከነዚህ ሁሉ መካከል አንዷ ብቸኛ ሴት አንቺ ነሽና ውሎሽ ከወንዶች ጋር ነው ማለት ይቻላል ቅድስት- በሚገባ! ዘ-ሐበሻ- ታዲያ ከወንዶች ጋር እንደመዋልሽ ወንዶችን ምን ታዘብሻቸው? ቅድስት- ረዥም ሳቅ እኔ ከሕጻንነቴ ጀምሮ ወንዶችን ናቸው ጓደኞቼ ከሴቶች በላይ ከወንዶች ጋር ነው የምውለው አንዳንድ ጊዜ ሴት መሆኔንም የሚረሱበት አጋጣሚ አለ እነርሱ ብዙ ነገር ነው የሚያወሩት ሳቅ በጣም ደስ ብሎኝ ነው ከወንዶች ጋር የምውለው ምንም ያየሁባቸው የታዘብኳቸው ነገር የለም ደግሞ እንደየአካባቢያችን እና እንደምንግባባቸው ሰዎች ነው የምንቆመው አብረውኝ የሚቆሙት ተራ እስኪደርስ ለመጠበቅ ማለቷ ነው ያሉት "ኩል" የሆኑ ናቸው ዘ-ሐበሻ- ብዙ ጊዜ ወንዶች ስለምንድን ነው የሚያወሩት? ቅድስት- ሳቅ እሱ ጠፍቶህ ነው እኔን የምታደርቀኝ? ሳቅ ብዙ ጊዜ ሴት ያወራሉ ስለማህበራዊ ጉዳይ ያወራሉ ግን አብዛኛውን ጊዜ ስለሀገር ጉዳይ በማውራት ነው የሚያሳልፉት ስለሀይማኖት ጉዳይም ያወራሉ ግን ብዙ ትኩረት የሚሰጡት በሀገር ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ነው ዘ-ሐበሻ- አላማሽ ምንድን ነው? ቅድስት- አላማዬ መማር ነው ከዚህ ቀደምም ተምሬ አቋርጬው ነው አሁን እሱን ከተማርኩ በሗላ ወደ ሀገሬ መግባትና ከሕጻናት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን መስራት እፈልጋለሁ ሕጻናትን በጣም ስለምወድ እነርሱን ማስተማር ደስ ይለኛል የወሰድኩትም ትምህርት ከዚሁ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በዚህ ዙሪያ መሥራት እፈልጋለሁ ዘ-ሐበሻ- ብዙ ኢትዮጵያውያን ሀገሬ መግባት እፈልጋለሁ ይላሉ ልክ እንዳንቺ; ግን ሲገቡ አይታዩም ለምን ይመስልሻል? ቅድስት- መቼም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እዚህ ይኑር እንጂ ልቡ ያለው ሀገር ቤት ነው ስለሀገሩ የማያስብና የማይናፍቅ የለም ያለመሙላት ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም ቢገባ ደስ ይለዋል እኔም ከወጣሁ ቆይቻለው ሰውን ወደ ሀገሩ እንዳይሄድ የሚያደርገው የገንዘብ ጉዳይ ነው እዛ ሄዶ ከዚህ ዝቅ ብሎ መኖር ስለማይፈልግና ኢትዮጵያ ሄጄ ከዚህ ያነሰ ልኖር? እያለ ስለሚፈራ; እሄዳለሁ እንዳለ ሳይሳካለት እዚሁ ይቀራል እኔም የምፎክረው ገንዘብ ቢኖረኝ ዛሬ እሄዳለሁ እያልኩ ነው ዘ-ሐበሻ- ወደ ሥራሽ እንመለስና; ከመኪና ጋር አብሮ መዋል ብዙ አደጋ አለው ችግርም ያጋጥማል ለመሆኑ መንገድ ላይ እየሄድሽ ጎማ ቢፈነዳብሽ ራስሽ ነሽ የምትቀይሪው? ቅድስት-ሳቅ ኸረ እኔ አልችልም ጎማ ቢፈነዳብኝም ቢበላሽብኝም መኪናዬን አስገፍቼም ቶው አስደርጌ ይዤ ወደ መካኒክ ነው የምሮጠው ዘ-ሐበሻ- የሚኒሶታ አየር ትንሽ ይከብዳል በተለይ በክረምቱ ጊዜ ያለው በረዶ ጠንከር ያለ ነው አንቺ እንዴት ነው ይህንን አስቸጋሪ የክረምት ወራት ካለ አደጋ በረዶ ላይ በመንዳትና; በረዶ ላይ ቆሞ ወረፋ በመጠበቅ የምትሰሪው? ቅድስት- ይገርምሀል እኔ የሚኒሶታ ክረምት አይከብደኝም እንደውም ተስማምቶኝ ነው የምሰራው ለምን መስለህ ስዊድን ሀገር ከዚህ የባሰ በረዶ ስኖው አለ እናም ተስማምቶኝ ነው የምሰራው በደንብ ከለበስክ ከሚኒሶታ በጋ ክረምቱን እመርጣለሁ መንዳቱም ቢሆን ተጠንቅቀህ ከነዳህ መንሸራተትም አደጋም የለም ለታክሲ ስራ ገበያ የሚኖረው የክረምቱ ጊዜ እንደሆነም አትርሳ ሳቅ ስለዚህ ክረምቱን እወደዋለሁ ዘ-ሐበሻ- ኢትዮጵያውያን ወንዶች በቤት ስራ ደካሞች ናችሁ እንባላለንና አንቺም ከእነርሱ ጋር እንደመዋልሽ ሙያውም ጠፍቶብሽ ይሆን? ቅድስት- ሳቅ አልክድም እንደ ሴት መንጎዳጎድ አይሆንልኝም እንደውም እዚህ ያሉት በጣም ይፈታተኑኛል ሳቅ ሙያሽን እንቅመሰው እስኪ አገልግል ፈትፍተሽ አምጪ ይሉኛል; ግን አይሆንልኝም እኔም ሴትነቱ ጠፍቶኛል መሰለኝ አላበላም ብዬ ቁጭ ብያለሁ አልሞከርኩትም እንጂ ሳይጠፋኝ አይቀርም ለራሴም ቀባ ቀባ አድርጌ ነው የምበላው እንደወንዶቹ ቀለል ያሉ የፈረንጅ ምግብ; ሩዝ ወይም ፓስታ እያበሰልኩ ነው የምመገበው ወጣ ወጡን ነገር ሳልረሳው አልቀርም ዘ-ሐበሻ- አግብተሻል? ቅድስት- አላገባሁም ዘ-ሐበሻ- ለምን አላገባሽም ብዬ አልጠይቅሽም ግን ብዙ ጊዜ ከወንዶች ጋር ስለምትውይ ተጽእኖ አሳድሮብሽ ይሆን? ቅድስት- ኖ! ላሳደረብኝም የራሴ የሆነ ፐርሰናል ጉዳይ ያለማግባት ጉዳይ ነው ዘ-ሐበሻ- እሺ እንተወው የሕይ ወት ፍልስፍናሽ ምንድን ነው? ቅድስት- እኔ በእግዚአብሄር የማምን ሰው ነኝ የቤተክርስቲያን ሰው ነኝ ያደግኩትም ከእግዚአብሄር ቃል ጋር ነው በሕይወቴ የሚያጋጥሙኝ ነገሮችና የሚፈጠሩት ሁኔታዎች ሁሉ በእግዚአብሄር ፈቃድ ብዬ ነው የማምነው ከዛ በተረፈ እኔ ማድረግ ያለብኝን ነገር ሁሉ አደርጋለሁ ቀጥሎ ያለው በእግዚአብሔር የሚሆን ነው ዘ-ሐበሻ- በመጨረሻም ምን ትያለሽ? ቅድስት- ማለት የምፈልገው? ብዙ ጊዜ ለሀበሾች ታክሲ ነው የምነዳው ስል አንዳንዱ ይደነግጣል; አንዳንዱ ይገረማል; አንዳንዱ አብረታቶኝ ያልፋል አብዛኛው ሴት ሆኜ የታክሲ ሥራ ላይ ሲያየኝ 'ጉድ' ይላል እኔ የምለው ግን በተለይ ሴቶች የታክሲ ሥራ አያስፈራም; ቀላል ነው; ኑና ሞክሩት ነው የምለው ብዙ ጊዜ የእኛ ሴቶች ፈሪዎች ነን መንገድ እንፈራለን አይናፋር ነን ግን ኑ የታክሲ ሥራ ቀላልና የሰነፍ ሥራ ነው የምለው ሴቶች መጥተው ቢሞክሩት ደስ ይለኛል ዘ-ሐበሻ- እናመሰግናለን ቅድስት ቅድስት- እኔም አመሰግናለሁ ® ካሳሁን ገርማሞ በ1939 ዓም አዲስ አበባ ተወለደ ወላጅ እናቱ ወሮ ዘነበች አንጩ፣ አባቱ ገርማሞ ወናዬ ይባላሉ፡፡ ካሳሁን አዲስ አበባ ይወለድ እንጂ ያደገው ግን ተፈሪ ኬላ በምትባል አገር ነው፡፡ እድሜው ለትምህርት እንደደረሰም ተፈሪ ኬላ አንደኛ ደረጃ ትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ እዚያው ትምህርቱን በመከታተል ላይ እንዳለ ቤተሰቦቹ ተመልሰው ወደአአ በመምጣታቸው እሱም ወደ ትውልድ አገሩ ተመለሰ፡፡ አአ መጥቶ ልዑል መኮንን ትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገባ በተማሪዎች መማከርት በነበረው ንቁ ተሳትፎ ‹‹የባለታሪካችንን›› ገፀ ባህሪይ ወክሎ ተማሪዎች ፊት መታየት ጀመረ፡፡ በግጥሞችም የሁለገብ ችሎታውን አሳየ፡፡ ካሳሁንም እንዲህ እያለ ትምህርቱን ጨረሰ፡፡ ትምህርቱን ጨርሶ ግን አልቆመም ቀጥታ ያመራው ወደ ፖሊስ ሙዚቃና የቴአትር ክፍል ነው፡፡ በወቅቱም እንደርሱ ያለ ሰው ያስፈልግ ስለነበር ታህሳስ 1961 ዓም የቅጥር ውል ፈጽሞ በቋሚነት ስራውን ጀመረ፡፡ እዛም በመስራት ላይ እያለ ለታዋቂ ድምጻዊያኖች ግጥምና ዜማ በመስጠት ይታወቃል ግጥምና ዜማ ከሰጣቸው ድምጻዊያኖች መካከል ሒሩት በቀለ፣ ታደለ በቀለ፣ በኃይሉ እሸቴና ተስፋዬ በላይ…በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ ‹‹ካሳሁን ከመድረክ አስተዋዋቂነት ጎን ለጎን ግጥም ይጽፋል፣ ዜማ ይደርሳል፣ አዳዲስ የውዝዋዜ ስልቶችን ያወጣል፣ ሙዚቃ አሬንጅ ያደርጋል የመድረክ አስተዋዋቂ ነው ቀልድና ቁምነገር በአንድ ላይ ማዋሀድ ይችልበታል፡፡ በ1960ዎቹ ዓም በፖሊስ ሰራዊት ሙዚቃና ቴአትር ክፍል ውስጥ ካሳሁን ገርማሞ መድረኩን ሲመራ ጥላዬ አራጌ ስትወዛወዝ ሁለቱም ወጣቶች ለፍቅር ተጫጩ፤ የመድረክ ተወዛዋዥ ጥላዬ የተመልካችን አይን ብቻ ሳይሆን ካሳሁንንም ቀልብ ገዛች፡፡ እሷም በልዩ የመድረክ አቀራረብ ለዛው ተሳበች ተፈላለጉ ተዋደዱ ጐጆ ለመቀለስ ወሰኑ፡፡ በሐምሌ ወር 1967 ዓም የጋብቻ ስነስርዓታቸውን ፈጸሙ በሐምሌ ወር 1968 ዓም ቴዎድሮስ ካሳሁን ተወለደ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ ስለአባቱ ከተናገረው፡- አባቴና እናቴ የተገናኙበትን ጊዜ በትክክል ባላውቀውም መስሪያቤታቸው አንድ ላይ መሆኑን አውቅ ነበር እሱ የመድረክ መሪ እሷ ደግሞ የመድረክ ተወዛዋዥ ነበረች፡፡ የተጋቡት በ1967 ዓም ነው እናቴ ጥላዬ አራጌ የ17 ዓመት ወጣት ነበረች፡፡ እርሱ ደግሞ ወደ 20ዎቹ መጨረሻ ነበር ሲሉ አውቃለሁ በተጋቡ በአንድ አመታቸው እኔ ተወለድኩኝ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ብዙ አመት አብረው አልኖሩም የተለያዩበትን ቀን በትክክል ባላውቀውም ለ6ኛ የልደት ቀኔ እለት ግን እናቴ አልነበረችም፡፡ አባቴ ከዚያ በኋላ ለራሱ አልኖረም እናትም አባትም ሆኖ አሳደገኝ የኖረው ለኔ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት ቤት አስተምሮኛል፡፡ በዘመናዊ አስተዳደግና በጥሩ ስነምግባር አሳድጐኛል። አባቴ ሙዚቀኛ እንድሆን ፈጽሞ አይፈልግም አስቦትም አያውቅም ምክንያቱም በነሱ ዘመን በኪነጥበቡ አካባቢ የነበሩ ሰዎችን በኑሮ ውጤታማ አለመሆንን በማየት ይመስለኛል በተጨማሪም ልክ የምስራ ሳይሆን የማጠፋ ስለሚመስለው የኔን ሙዚቀኝነት አልወደደውም ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን የስራ ውጤቴን የኔንም ስነስርዓት ሲያየው ሞያዬን እየተቀበለው መጥቶ ነበር፡፡ ግን መጨረሻውን ሳያየው ቀረ የምወደው አባቴ በ1993 ዓም ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡ ‹‹ከአርቲስት ቤተሰብ መፈጠሩ ደስ ይለኛል›› ክቡር ዶር ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ አባቱ ካሳሁን ገርማሞ የፖሊስ ኦርኬስትራ አስተዋዋቂና የፖሊስ ፕሮግራም ጋዜጠኛ ነበር፡፡ እናቱ ወይዘሮ ጥላዬ እዚያው ክፍል ውስጥ በተወዛዋዥነት ሰርታለች፡፡ ቴዎድሮስ ከአርቲስት ቤተሰብ በመፈጠሩ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ከዚያ ቤተሰብ ወጥቶ ለዚህ መብቃቱ እጅግ ያኮራል፡፡ ልጁን እንደተመለከትኩት የእድሜ ማነስ ሳይሆን ቁም ነገር ያለው ተግባር ለመፈጸም እንደሚችል አውቃለሁ፡፡ በድምጹም ሆነ በስራው አደንቀዋለሁ፡፡ ሊሰራ የፈለጋቸውን ነገሮች ሁሉ አስቦ በራሱ ዜማ፣ በራሱ ግጥም፣ በራሱ ድምጽ አገናኝቶ መሰራት የሚችል ብቁ አርቲስት ነው ማለት እችላለሁ፡፡ ‹‹ዘውድ ብጭንና ቢዘፍንልኝ አልጠላም›› አቶ ውብሸት ወርቅአለማሁ የማስታወቂያ ስራ ባለሙያ ስለሱ ለመግለጽ በቂ ሀይል ያለው ቃል የሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ልጁ’ኮ ከስንት አንዴ ብቅ የሚል ውብ ጀምበር ነው፡፡ ባቀረባቸው አራቱ ምርጥ የመታሰቢያ ስራዎች፣ ለኃይሌ፣ ለግርማዊነታቸው፣ ለቀነኒሳና ለቦብማርሌ በዘፈናቸው ስራዎች እንዳከብረው አድርጐኛል፡፡ አጥንት ሰብረው ይገባሉ አእምሮው ከዘፈነላቸው ሯጮች በላይ እንደሚፈጥን ይሰማኛል፡፡ አእምሮህን እወደዋለሁ፡፡ ሸራተን ሆቴል መድረክ ላይ ሲጠየቅ በቅርብ አይቼዋለሁ፡፡ የመልሱ ፍጥነት ችሎታውን ገላጭ ነው፡፡ ምኞቴ፤ በዓለም ላይ የማይጠገቡ አራት ነገሮች አሉ፡፡ ሀብት፣ እድሜ፣ ስልጣንና ፍቅር እንዲያገኝ ነው፡፡ ልጁ ደግሞ ገንዘብ፣ ውበት፣ ዝና ወጣትነትና ብስለት አለው፡፡ ፍጹም ለትዳር የተመቸ ነው፡፡ ግብዝ አይደለም፡፡ ቢሆንማ ኖሮ እስካሁን ይበላሽ ነበር፡፡ በመጨረሻም ዘር ቆጥሬ ‹‹ዘውድ›› ብጭንና ቢዘፍንልኝ አልጠላም። ‘በከበሮ ጀመረ ዛሬ ለዚህ በቃ’ - አጐቱ አቶ ሃይሉ ገርማሞ የልጅነት ምኞቱ ምን ነበር? ፦ የማትለየው ትንሽ ከበሮ ነበረች፡፡ እሷን ሁሌ ይደልቃል፡፡ ዘፍነህ የት ልትደርስ ነው; እለው ነበር፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ያውቃል፤ አንድ ቀን ታየኛለህ›› ይለኛል፡፡ያሳደገችው እህቴ ለፀጉር መቀጠያ ያመጣችውን አርቴፊሻል ፀጉር አፄ ቴዎድሮስን ሆኖ ለመስራት ከቤት ይዞ ጠፋባትና ስለምትወደው ተወችለት፡፡ በከበሮ ጀመረ ዛሬ ለዚህ በቃ፡፡ ‹‹የሳይንስ ትምህርት ፍላጎት ነበረው›› መምህሩ ሐጎስ አርአያ ቤቴልሔም ትምህርት ቤት ውስጥ 6ኛ ክፍል ሳይንስ አስተምሬዋለሁ የሳይንስ ትምህርት ፍላጐት ነበረው፡፡ በክፈለ ጊዜው ለእረፍት ያህል መሐል ላይ መዝናኛዎች አይጠፉም የልብና የአንጀት ስዕሎች ሳቀርብ ቴዲ በግጥም ይገልጻቸዋል፡፡ ንቁ ተማሪ ነው፡፡ እያዝናና ጭንቅላታቸው ውስጥ እንዲቀረጽ ያደርጋል፡፡ ወደሌላ ክፍል እወስደውና ያነብላቸዋል በዚህ ምክንያት ሁሌም ተሰጥኦ እንዳለውና እንዲገፋበት እነግረው ነበር፡፡በትምህርት ቤት ክበባት ውስጥ በስነጽሁፍ ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ይወዳደራል ግጥሞቹንም በዘፈን መልክ ያቀርባቸዋል፡፡ አድጐ ‹‹ባይገርምሽ ገና እወድሻለሁ›› እያለ በቴሌቪዥን ሲጫወት ማየቴ ትንግርት ሆነብኝ ‹‹ይህ ልጅ ትልቅ ሰው ሆነ›› አልኩኝ፡፡ ከዘፈኖቹ ‹‹ታሪክ ተሰራ›› እና ‹‹ባይገርምሸን›› እወዳቸዋለሁ ‹‹አቡጊዳንም›› የራሱን ስልት ካሳየባቸው ስራዎች አንዱ ነው፡፡ ወደፊት የሱዳንና የጃፓን ስልቶችን በሙዚቃው ውስጥ ቢያካትት እመርጣለሁ፡፡ ‹‹ቴዲ ችሎታ ያለው ድምጻዊ ነው›› አቶ አዲሱ ገሠሠ የቴዎድሮስ ካሳሁን ማኔጀር ከጂጂ ጋር ብቻ ነበር የሰራነው፡፡ ተሰጥኦ ስላላት በዓለም ላይ ላስተዋውቃት ሞክሬያለሁ፡፡ ቴዲን በመጀመሪያ ወደ አሜሪካን ወሰድኩት፡፡ ዋሽንግተን ባቀረበው ስራ ተስፋ እንዳለው አወቅሁ፡፡ ከብዙ ሰዎች ጋርም አስተዋወቅሁት ተሰጥኦውን እንዲያውቁለት፣ ችሎታውን እንዲያደንቁለት አደረኩ፡፡ ከዚያም ወደአረብ ሀገራት በመሔድ የተለያዩ ዝግጅቶችን አቅርቧል፡፡ በዘፈኑ በኩል አንዳንዴ ትንሽ ልጁን ያለመረዳት ችግር እንዳለ አይቻለሁ፡፡ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰርቷል፡፡ ያው እንደተለመደው ብዙዎቹ የኪነጥበብ ሰዎች የሚያቀርቧቸው የፈጠራ ስራዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚተረጎምባቸው አውቃለሁ፡፡ ቦብ ማርሌም ይህ ደርሶበታል፡፡ ቴዲ ችሎታ ያለው ድምጻዊ ነው፡፡ በቀረበበት መድረክ ሁሉ ተቀባይነቱ እጅግ የደመቀ ነበር፡፡ እሱን ይዤ በመስራቴ እደሰታለሁ፡፡ በተለይ ስራዎቹን ከቤተሰቦቼ ጋር ሆነን ስናየው የተለየ ስሜት አሳድሮብናል፡፡ እንደእኔ አስተያየት አልበም ማውጣት ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የሰዎችን ፍላጐት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከተለያዩ አርቲስቶች ጋር እንደመኖሬ ቴዲ ለየት ይላል፡፡ ሙዚቃ ህይወቴ ወ ካሣ መንፈስ በቱባው ቋንቋ ተው ልጄ ኪነት- ከሀሁ ታረቅ በአንቺ ሆዬ ቃና- ዮራይስመሌ በጉራጊኛ በትዝታ ቃና- ፈርዲዳ ማሣርቦ በአንቺ ሆዬ ቃና- ደርፊ ምስ ጓላይ በትግሪኛ ቶሌ ቶሌ ያሚ ጋሪ ናቃሪ ፈያ በኦሮምኛ ወላይታ ካአ በወላይትኛ ሙዚቃ ህይወቴ ግዕዝና ዕዝል አራራይ የተሰጠች ከላይ ያሬዳዊ ስልቱ የሰማይ ፀጋ አቆራኘኋት ነፍሴን ከአንቺ ጋ፡፡ በአገሬ ቅኝት የብሔር ቋንቋ እደሰታለሁ እኔ አላዝነም በቃ፡፡ በአፋር ሲዳማ በጋምቤላ ቶም ልርገጥ ዳንኪራ እኔ አላዝንም ከቶም፡፡ መሀያበያባ መሃያበያባ በአፋርኛ ሃያባያ መሃያበያባ ሀያብዬ እኔስ ለአብዬ፡፡ ሙዚቃ ህይወቴ ግዕዝና ዕዝል አራራይ የተሰጠች ከላይ ተው ቢል አልሰማ በልጅነቴ ገርፎ ሲቀጣኝ ሲመክረኝ አባቴ ስንት ያየሁብሽ ሙዚቃ ህይወቴ ቆመህ ካላየህ አታምንምና ላባብልህ ዛሬ በክራሬ ቃና ለሟች ማዘን የለም ባለው መጽናናት ነው ብለህ እንዳስተማርከኝ ባንተው ምክር ሄጄ በአንተው አስጨከንከኝ እሱ እንዳለው ያ ሎሬቱ ሞትም ይሙት የታባቱ በሞትህ ላይ ፎክሬበት በዳንኪራ ትነሳለህ ከእኔ ጋራ መሀያበያባ መሃያበያባ ሀያብዬ አልሞትክም አብዬ መሃያበያባ መሃያበያባ ሃያብዬ እኔ አለሁ አብዬ፡፡ ሙዚቃ ህይወቴ ግዕዝና ዕዝል አራራይ የተሰጠች ከላይ በዚህ ኑሮ ብሎ ከላይ ካዘዘ ልጁ ምን ያድርግ ክራሩን ያዘ፡፡ አትዘንበት አደራ አብዲ አባቴ ማርኮት ቅኝቱ ምን ያድርግ ኧዲ፡፡ እኔ መሃያበያባ መሃያበያባ ሃያባያ መሃያበያባ መሃያበያባ መሃያበያባ ሃያብዬ ጀነቱን ለአብዬ፡፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን በቴዲ አፍሮ ‹‹ስራዎቹ የላቀ ኢትዮጵያዊ ስሜት አላቸው›› ተዋናይ፣ ፀሐፌተውኔት፣ አዘጋጅና ገጣሚ ጌትነት እንየው የግጥሞቹ ይዘት፦ የቴዲ የዘፈን ግጥሞች፣ ይዘታቸው፣ ስፋት አላቸው፡፡ ከሌሎች ከምንሰማቸው በጾታ ፍቅር ርዕስ ላይ ከሚያጠነጥኑት የላቀ ነው፡፡ ወደኋላ ታሪካዊ የሆኑ ድርጊቶችን ያነሳሉ፡፡ ጀግኖች ያወድሳሉ፡፡ ስለ አፄ ኃይለስላሴ፣ ስለኃይሌ ገብረስላሴ፣ ‹‹እንደየሩሳሌም›› የሚለውና ስለሩጫው የሰማነው ሁሉ ብሔራዊ ስሜትን የሚቀሰቅሱ ናቸው፡፡ ጭብጦች፦ የሚያነሳቸው ጭብጦች በፍቅር ብቻ የተወሰኑ አይደሉም፡፡ ብሔራዊ ማንነትን ይገልጻሉ፡፡ ይሔ ,,, የሚለው የእኛ አቡጊዳ ነው ከልጅነት የህይወት ያህል ይሰፋል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ስሰማው ያኔ ቁምጣ ለብሼ ቄስ ትምህርት ቤት ውስጥ በጅራፍ ተገርፌ አንገቴ ያበጠውን አስታውሳለሁ፡፡ ስራዎቹ የላቀ ኢትዮጵያዊ ስሜት አላቸው፡፡ በአንድ ምሽት እንደዚያ በጣም ስሜት የሚቀሰቅስ ጽሁፍ ድንገት የሚመጣ አይደለም፡፡ አቀራረብ፦ ከህጻናት እስከ ሀገር መሪዎች ድረስ ያደነቁት ሰፊና ታሪካዊ የሆኑ ጭብጦችን በቀላል ቋንቋ የመግለጽ ብቃት ስላለው ነው፡፡ ምናባዊ፣ ውስጣዊ የሚል ትርጓሜ ኖሮት ቃላቱ ሲፈቱ አይከረሙም፡፡ ይሰማል ይገባል፡፡ በቀላል ቋንቋ ለመግጠም የራስ የሆነ ብቃት ይጠይቃል፡፡ ለምሳሌ መንግስቱ ለማቀላል በሆኑ ቃላት፣ ቀለል ባሉ አገላለጽ የሚያፈላስፉ ጉዳዮችን ያነሳሉ፡፡ ቀላልና ተራ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ቀለል ያለው ቋንቋ አጠቃቀም ሙዚቃ ወዲያው እንዲገባ ይረዳል፡፡ እንደ መንግስቱ ለማ ጥልቅ ሀሳብን በቀላል ቋንቋ የሚያቀርቡ ጥቂት ናቸው፡፡ በዘፈኑ በኩል ቴዲን አግኝተናል፡፡ ‹‹እስካሁን እንድሮጥ አድርጐኛል አርጅቼም በከዘራ ሳልሮጥ አልቀርም! ›› አትሌት ኃይሌ ገስላሴ ክቡር ዶር • ዘፈንና ስሜት፦ - ‹‹አልሆንልህ አለኝ›› የሚለው ዘፈኑ ከምስል ጋር ተቀናብሮ መታየቱን ነገሩኝ፡፡ ያኔ አቴንስ ነበርኩ፡፡ ዜማውን በመጠኑ በስልክ አሰሙኝ፡፡ ብዙም ጥራት አልነበረውም፡፡ ስመጣ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመለከትኩት ያስለቅሳል፡፡ ውስጤ የሆነ ነገር ተላወሰ፡፡ ያንን መግለጽ ይከብደኛል፡፡ ስሜትን ይረብሻል እውነተኛ ህይወት ውስጥ ይከታል፡፡ የሚደነቅ አይነት ነበር፡፡ ያንን እያየሁ መተኛትም ሆነ መቀመጥ አልነበረብኝም ኦፕራሲዮን ሆኜ ሮጫለሁ፡፡ • የዜማ ኃይል፦ - ‹‹መርቆ ሸኝቶ ሀገር›› የሚለው ይስበኛል፡፡ ሽማግሌው ሲመጡ ሳይ፣ ቀነኒሳ ወደኋላ እየዞረ ሲመለከት ‹‹አንተን ጥሎ መሔድ…›› ሲል እነሱ ቦታዎች በጣም ይረብሹኛል፡፡ በመጀመሪያ ስለ እኔ በዘፈነው እስካሁን እንድሮጥ አድርጐኛል ለዚህ ደግሞ እኔ እንጃ አርጅቼም በከዘራ ሳልሮጥ አልቀርም፡፡ ‹‹እውነትን በዜማ ይነግረናል›› ደራሲና የፊልም ዳይሬክተር ተስፋዬ ማሞ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ምን ያህል ተዋህደው እንደሚኖሩ አንድ ምሳሌ ላንሳ፣ ወሎ ውስጥ አንድ ቤተክርስቲያን አለ፡፡ ስሙን ካልተሳሳትኩ ሩጋ ሚካኤል ይባላል፡፡ እዚያ የሚኖሩት አብዛኞቹ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ቀሳውስቱ በቁጥር ያንሳሉ፡፡ ካህናቱ ቤተክርስቲያኑን ለማስተዳደር አንስተው ደሴ ለማድረግ ያስባሉ ይሔኔ የአካባቢው ሙስሊሞች ይቃወማሉ፡፡ ተባብርን የጐለደውን አሟልተን ትኖራላችሁ እንጂ አትሔዱም ብለው ይከለክሏቸዋል፡፡ ኮሚቴ ተቋቁሞ፣ ገንዘብ ተዋጥቶ ቤተክርስቲያኑ እስካሁን እዚያው ይኖራል፡፡ ቴዲ ይህንን ነው በጥሩ ቋንቋ የገለጸው፡፡ ይህ ለኛ ብቻ አይደለም ለዓለም ሊሸጥ ይችላል፡፡ ዛሬ በአክሪራነት በግራና ቀኝ አለም በምትተራመስበት ሰዓት ኢትዮጵያ እንደትልቅ ተምሳሌት እንድትቆጠር ያደርጋታል፡፡ በመሆኑም በቴዲ እንኮራበታለን በልጅነቱ ያገር ሽማግሌ ስራ እንደመስራቱ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ‹‹ልቤ መጮህ ይፈልጋል›› ትርፌ ማንያህልሃል ዲጄ ኪን ቴዲ በግጥሞቹ፣ በዜማዎቹ እና በቅላጼው ትልቅ ስራ አበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ብዙ ነገሮች ማካተትን ችሏል፡፡ ቴዲን እንደጥላሁን ገሠሠ ነው የማየው በስሜት ነው የሚዘፍነው፡፡ የሰውን የልብ ትርታ የሚያውቅ ይመስለኛል ለዚህም ሳይሆን አይቀርም አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ዘፈኖቹን ያዳምጣቸዋል፡፡ እኔ አስከማውቀው ድረስ ለቦብ ማርሌ አድናቆት አለው፡፡ ከልቡ ይወደዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የሬጌን የሙዚቃ ስልት ሲሞከር አይቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ የጀማይካ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስልት ይጐላበታል፡፡ እናም የኛን ፈጥሯል ማለት እችላላሁ፡፡ ቴዲ ስለዘፈኑ ሲነግረኝ ልቤ መጮህ ይፈልጋል ይለኛል፡፡ እግዚአብሔር በሰጠኝ ተሰጥኦ ለህዝቡ ማገልገል አለብኝ ይላል፡፡ ቀዩን ቲሸርት በጥቁር መነጽር አድጎ ከ16 ወራት እስራት በሗላ የተፈታው ድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን በታሰረ ወቅት አብሮ ለታሰረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን አክብሮት ገለጸ ድምጻዊው ከእስር ከተፈታ በሗላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለምልልስ 'በእስር ቤቱ ከበርካታ መልካም ኢትዮጵያውያን ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፉን' ገልጧል በታሰረበት ወቅት ከአድናቂዎቹ የመጡለትንና ሲገለገልበት የነበረ ውን መጽሀፍት ለማረሚያ ቤቱ ቤተ-መጽሀሐፍት የሰጠው ቴዲ ያሉትን ልብሶቹን እና ቁሳቁሶቹንም ጠያቂ ለሌላቸው እስረኞች ጋር አከፋፍሏል በሐምሌ ወር እናት እና አባቱ ተጋብተው፣ በሐምሌ ወር የተ ወለደው፣ በሐምሌ ወር ለተወለዱት ለቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴ ዘፍኖ ሁለት ሐምሌዎችን በእስር ያሳለፈው ቴዎድሮስ ካሣሁን ገርማሞ ጥቅምት 23 ቀን 1 999 ዓም ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ከአስር ደቂቃ ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17 ክልል በቤተ መንግሥት አካባቢ ንብረትነቱ የግሉ በሆነው ኮድ 2-59868 አ ዲስ አበባ አው ቶሞቢል መኪናቸው ደጉ ይበልጣል የተባለ እግረኛ ገጭቶ ገድሎ አምልጧል በሚል በቀረበበት ክስ በወቅቱ ቴዲ አፍሮ በመኪና ገጭቶ ገድሎ ታል በሚል የተጠረጠረበትን የሟ ች ደጉ ይበልጣል የሕይወት ታሪክ በወቅቱ “ፎር ቹን” የተባለ የእንግሊዘኛ ጋዜጣ የሟች አባት አ ቶ ታምሩ ተፈሪን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሟች ከጎ ጃም መጥቶ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ከአጎቱ ጋር ይኖር የነበረ የ18 ዓመት ወጣት ነው። ደጉ መጠጥ ከሚ ጠጡ ልጆች ጋር በመግጠሙ ቤቱን ጥሎ ለጎዳ ና ሕይወት ይዳረጋል። ነገር ግን በሣምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ወደ ቤተሰቦቹ በመምጣት ይጠይ ቃቸው እንደነበር ነው ቴዲ በወቅቱ ለአዲስ አድማስ ና ሪፖርተር ጋዜጣ የሰጠው መልስ “ሰውን የሚያህል ክቡር ነገር ገጭቼ ላመልጥ አልችልም፣ እኔ ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ አልነ በርኩም፣ 'ሰው ገጭቶ አምልጧል' የተባለው ወሬ ሐሰትና ጉዳዩም ክብሬን የሚነካ ነው” ነበር ያለው። "እኔ ሀገር ውስጥ የገባሁት በጥቅምት 23 ቀን ነው፣ የምኒልክ ሆስፒታል ማስረጃ እንደሚያስረዳው ደግሞ ሟች የሞተው በጥቅምት 22 ቀን ነው። ” ብሎ በፍርድ ቤት ሲከራከር የቆየው ቴዲ አፍሮ 6 አመት በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተፈረደበት ወቅት "ዳኛው በቅንነት ክሴን አልተመለከቱትም" ሲል መክሰሱ ይታወሳል በዚህም የተነሳ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበው ቴዲ እስሩ ወደ 2 አመት ተቀንሶለት በአመክሮ ተፈቷልበቴዲ አፍሮ ዙሪያ የተጠናቀሩ ዘገባዎችን በውስጥ ገጽ ይፈልጉ። የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ ድምጻዊው ቴዲ አፍሮ በእስር ቆይታው ሰለሜ በሚለው የሙዚቃ አልበሙ አንድ ሰአሊ ሥራዬን ተጠ ቅሟል በሚል የ100 ሺህ ብር ክስ ቢመሰርትበትም ቴዲ በዚህም ክስ ከዚህ ቀደም ነጻ መውጣቱ ይታወሳል ስለ ፍቅርና ስለአንድነት የዘፈነው ቴዲ አፍሮ በተደጋጋሚ ፖለቲከኛ አለመሆኑን ቢገልጽም እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ስለ አንድነት መስበክም ሆነ ማውራት ምን ያህል ጥርስ ውስጥ እንደሚያስገባ የቴዲ ጉዳይ ያሳየናል የሚሉ ተንታኞች በርካታ ናቸው ® 1 የቴዲ አፍሮ ጉዳይ ፖለቲካዊ መምሰሉና ጠበቃው አቶ ሚሊዮን አሰፋ የኢህአዴግ ደጋፊና የምርጫ ቦርድ ጠበቃ ሆኖ፣ የቅንጅት አመራሮች እስር ቤት በነበሩበት ወቅት እስሩን ደግፎ ሞት ሊፈረድባቸው ይገባል እያለ በመንግሥት ራዲዮና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በየቀኑ መግለጫ ሲሰጥ የነበረ ጠበቃ መሆኑ፤ 2 ሁለተኛ ወንጀል ችሎት የነበሩትና ለሁለት ዓመታት የዘለቀውንና የቅንጅት አመራሮች የተከሰሱበትን ችሎት በቀኝ ዳኝነት ሲያስችሉ የነበሩት አቶ ልዑል ወማርያም በድንገት 8ኛ ወንጀል ችሎት መገኘት፤ አቶ ልኡል ለበርካታ ጋዜጠኞች መሰደድ መታሰር እና መታረዝ ዋና ምክንያት ነው ሰሞኑን አዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ የቴዲን ስም የጠሩና ፎቶ ግራፉ ያለበትን ቲሸርቱን የለበሱ መታሰራቸው፤ በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል የሚመራው መኢአድ በአዲስ አበባ አደባባዮች የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርግ በቴዲ አፍሮ ሙዚቃዎች እንዳይቀሰቅሱ መከልከላቸው፤ 3 ምኒልክ ሆስፒታል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦርጅናል የአስከሬን የምርመራ ውጤትን 'ተሳስቷል' በሚል መቀየሩ፤ 4 ችሎት በሚኖርበት ጊዜ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደህንነቶች ችሎቱን ማጨናነቃቸውና ችሎት ተከታታዩን ሰው ማስጨነቃቸው፤ 5 በቴዲ የፍርድ ቤት ንግግር ያለቀሱ አድናቂዎቹ መታሰርና መንገላታት 6 የቅንጅት አመራሮችን ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች ሳይታክቱ በችሎት በመገኘት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረጋቸው፤ 7 ቃሊቲ ከገባ በኋላ ለብቻው መታሰሩ፤ 8 ከተወሰኑ ሰዎች በስተቀር ማንም እንዳይጠይቀው መከልከሉ፤ በመኪና ሰው ገጭተሃል በሚል ተጠርጥሮ ለታሰረ ሰው ያልተለመዱ ድርጊቶች ናቸው። ''ኢትዮጵያዊ ኤልቪስ ፕሪስሊ '' ይሉታል የዛ ዘመን ሰዎች በሙዚቃ ሥራው በዛም ዘመን በእኛም ዘመን አዲስ ና ልዩ እንዲሁም የራሱ ፈጠራ ያለው ሰው ሆኖ እዚህ ደርሷል ''አዲስ አበባ ቤቴ አዲስ አበባ ቤቴ ሸጋ ልጅ ቆንጆ ልጅ አለች ጎረቤቴ '' ታዋቂው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ ''አለማየሁ እሽቴን እንዴት አድርገህ ትገልጸዋለህ ?'' በሚል መነን በሚባል መጽሄት ለቀረበለት ጥያቄ ትንሽ ቆም ብሎ በማሰብ ''ሦስት ነግሮች አሉት '' ሲል ይጀምራል ''አለማየሁ የራሱ የሆነ ፈጠራ አለው ከሁሉም ዘፈኞች ወጣ ያለ ባህሪ እንዲኖረው ይፈልጋል ከዚህም በላይ ለአዲስ ነገር ቅርብ ነው '' ሲል ይገልጸዋል ይህ የጥላሁን ገለጻ በእርግጥም ትክክል ነው በሾላ አካባቢ በገዛው መሬት የሚኖረው አለማየሁ እሸቴ አብዛኞቹ የሙያ አጋሮቹ ትዳር እና ሴት ሲቀያይሩ እስኩ ግን እሳካሁን በአንድ ሴት እንደጸና አለ በሁለተኛ ደረጃ ለአዲስ ነገር ቅርብ ነው ለሚለው የመጨረሻ ካሴቱን መመልከት ይቻላል ከ 2 አመት በፊት በአምባሰል ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ያወጣው ካሴቶ እጅግ ተወዳጅ የነበረ ሲሆን በክሊፑም ዘንድ የተዋጣለት መሆኑን አሳይቷል በ 3ኛ ደረጃ አሌክስን ልዩ የሚያደርገው ራሱን ከዘመኑ ጋር መለወጡ እና በቆመበት አለመቅረቱ ሲሆን ዘፈኖቹ ከምንም በላይ በምክር እና በትምህርት ላይ እንዲያተኩሩ ማድረጉ ላይ ነው ''ወደ ሙዚቃው ሙያ ለመግባት መሰት የሆነኝ ለኤልቪስ ያለኝ ፍቅር እና ክብር ነው '' የሚለው አለማየሁ ወደ ሙዚቃው ሕይወቱ ሲገባ በቤተሰቦቹ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ጫና ነበረበት በተለይ አባቱ ከሽመል በበለጠ እስከ ጠምንጃ መምዘዝ የደረሱበት ጊዜ ነበር ያኔ የዛ ዘመን ሰው ሙዚቀኛን እና ወርቅ አንጣሪን እንዴት ይመለከት እንደነበር ማስታወሱ በቂ ነው አለማየሁ ይቀጥላል '' በተለይ አባቴ በሙዚቃ ሕይወት ውስጥ ጠልቄ መግባቴን አልወደደልኝም ስዘፍን ውዬ ስመጣ ማምሻውን እቤቴ ዱላ ይጠብቀኛል የዛን ጊዜ የምንሰራው ለገንዘብ ሳይሆን ለሙያ ፍቅር ነበር እናም አንድ ዘፈን አወጣሁ ያ ዘፈን - የሴት ልጅ ከመባል ዘወትር የሚል ነበር ይህ ዘፈን መልእክቱ አባት መሞት እንደሌለበት አባት ከሞተ ልጅ የሴት ልጅ ቀማኛ ዱርዬ ተብሎ እንደሚሰደብ መልእክት ያለውና የአባትን ጥቅም አጉልቶ የሚያሳይ ነበር እናም አባቴ ይህን ዘፈን በራዲዮና በሽክላ ሲሰማ ለሙያዬ ልዩ ፍቅር አደረበት መኪና ገዝቶ ሰጠኝ ከዛም ያበረታታኝ ጀመር '' የአለማየሁ የሙዚቃ ሕይወት ጅማሮ ይህን ሲመስል በሙዚቃው ሕይወቱ እውቅናው በመላው ኢትዮጵያ እየተሰራጨ በመጣበት ወቅት በምጽዋ በኩል ጠፍቶ ወደ ሆሊውድ በባህር ጠፍቶ ሊሄድ ሲል ተይዞ መመለሱን ያስታውሳል ''ያኔ ወጣት እያለሁ ወደ ሆሊውድ መሄድ ፈልጌ ነበር ይህ ህልሜ ቢያሳካ ኖሮ በአለም ላይ ታዋቂ ሰው እሆን ነበር '' ይላል - አሌክስ ከአለማየሁ እሽቴ ጋር በጋራ ለመዝፈን እድሉ ካጋጠማቸው አርቲስቶች መካከል አንዷ ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ ነበረች አርቲስቷ ለአለማየሁ ያላትን ክብር የምትገልጸው በቃል ብቻ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም ''አለማየሁ '' ትላለች ''ዳንሱና የዘፈን ግጥሞቹና መልእክቶቹ ደስ ይሉኛል '' ትላለች አድናቂው እንደሆነች የምትናገረው ኩኩ አብራው በመዝፈኗ እድለኛ እንደሆነች ጭምር ታብራራለች በአራዳ ፒያሳ አካባቢ የቆርቆሮ የሙዚቃ ባንድ ሰርተው የሙዚቃ ጥማቸውን እጃቸው ላይ ልክ ማይክ እንዲመስል እንጨት ወይንም ማንኪያ ይዘው እየዘፈኑ ሙዚቃን የጀመሩት አሌክስና ጓደኞቹ እሱ በሙዚቃው ሥራውን አንቱታን ሲያተርፍ ሌሎቹ ግን በሌላ ሥራ ላይ እንደተሰማሩ ይናገራል በግልጽነቱና በትዳሩ ታማኝነቱ በምሳሌነት ከአርቲስቶቻችን የሚጠቀሰው አሌክስ - በ 1955 ፖሊስ ኦኬስትራ ውዝዋዜ ለመቀጠር ለመሰልጠን ሄዳ ፍቅር የሸመተችው እጅጋየሁ እስከዛሬ የአለማየሁ እሸቴ ሚስት ነች አለማየሁ እንደ አርቲስት ቀበጥ አይደለም ማለቴ ሲያገባ ሲፈታ የኖረ አይደለም ትዳሩን አክባሪ ነው በአንድ ወቅት ለትዳሩ እና ለልጆቹ ያለውን አመለካከት ሲነግረኝ ''ለሚስቴም ሆነ ለልጆቼ ያለኝን ፍቅር የሚተካውም ሆነ የሚለውጠው ምንም የለም ያለኝን ትርፍ ሰአት ከእነሱ ጋር ባሳልፍ ደስተኛነኝ ""ነው ያለኝ ''አሁንም ቅድምም ታሽካካለች ዶሮ እኔ አንቺን ማግኘቴ ሕልም ነው ዘንድሮ አዲስ አበባ ቤቴ አዲስ አበባ ቤቴ ሸጋ ልጅ ቆንጆ ልጅ አለች ጎረቤቴ አረ እንዳው ይመኙሻል አረ እንዳው ይመኙሻል በምኞት ቢጓዙ ወዴት ያገኙሻል '' እኚህ በፎቶ ግራፍ ላይ የምትመለከ ቷቸው ግለሰብ አምሀ እሸቴ ይሰኛሉ አምሀ እሸቴ የአባታቸው ስም ከአሌክስ አባት ጋር ሲመሳሰልባችሁ ወንድሙ እንዳይመስሏቸው ይልቅዬ በዛ ዘመን ታዋቂ የሙዚቃ አሳታሚ ነበሩ በ 1944 የመጀመሪያ የሸክላ ካሴቱን ለሕዝብ ሲያደርስ ሸክላውን ያሳተሙለት እኚሁ ግለሰብ ነበሩ አምሀ እሸቴ የሙዚቃ አሳታሚ የሚል ድርጅት የነበራቸው እኚሁ አባት ዛሬ በህይወት አይኑሩ እንጂ ከጥላሁን ገሰሰ ጀምሮ በዛ ዘመን የነበሩ ዘፈኞችን ዘፈኖቻቸውን በሽክላ አሳትመውላቸዋል በሙዚቃ ሕይወቱ ከአንድ መቶ በላይ ዘፈኖችን ለሕዝብ ያደረሰው አለማየሁ እሸቴ እስካሁን በካሴትና በሲዲ የሰራቸው ዘፈኖቹ 8 ብቻ ናቸው ''ኢትዮጵያዊ ኤልቪስ ፕሪስሊ '' አለማየሁ እሸቴ ከአማርኛ ሙዚቃዎች ሌላ የእንግሊዘኛ ሙዚቃዎች የሚዘፍን ሲሆን በተለይም አረብኛ ሙዚቃዎችን በሱዳንኛ ዜማ ይዘፍናል ከዚህም በተጨማሪ ሱማሊኛ ይዘፍናል አሁን ባለው ሥርአት በእጅጉ የማይወደደው አለማየሁ ለዚህ ምክንያቱ እንደ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች በተለያዩ የተቃዋ ሚ ፓርቲዎች መድረክ በተለይም በአብዮት አደባባይ ከሕዝብ ጋር ለተቃውሞ መውጣቱ በገዢው መደብ ሰዎች ጥርስ እንዲነክስበትና አንዳንድ ጫናዎችም እንዲደረጉበት ሆኗል ''ማን ይሁን ትልቅ ሰው ማን ይሁን ትልቅ ሰው ማን ይሁን ትልቅ ሰው ማ ን ይሁን ትልቅ ሰው ያንዱን ቁጅ አንደኛው ሲያኮስሰው ማን ይሁን ትልቅሰው ያንዱ ቤት ሲጎድል አንዱ እየተረፈው ክፉና ደጉን ዘመን ካሳለፈው እኔ ግን መራመድ ከቶ አልቻልኩም ገና ትኋን ! ትኋን ደሜን መጦ ደሜን መጦታልና ጊዜው ጎዳኝ እንጂ እኔ ሰው አላማም ዋ ያህያ ልጅ በቅሎ ወርቅ ተሽልማ ብናገር ወረኛ ባለጌ ይሉኛል ብቻ ግን በሆዴ ቢቀር ይሻለኛል !! የአሌክስን ይህን ተወዳጅ ሙዚቃ በድምጹ ሲያንቆረቁረው ለመስማት ላይ 13ኛውን ሙዚቃ ያዳምጡ አለማየሁ እሸቴ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላውን ጥበብ አብረን እንቆነጥራለንð ከሔኖክ ዓለማየሁ በሥራ ላይ እድገት አግኝተሽ ወደ ቤት ለመሄድ ቸኩለሻል ከመኪናሽ እንዴት እንደወረድሽ ራሱ ትዝ አይልሽም ለባለቤትሽ ይህን ታላቅ የምስራች ለመናገርና ደስታሽን አብራችሁ በመፈንደቅ ለማሳለፍ አቅደሻል "ፐ አሁን ባለቤቴ ሲሰማ እንዴት ይደሰት ይሆን? መቼም እቅፍ አድርጎ አንገቱ ስር ጠምጥሞ አስገብቶኝ ይስመኛል የእኔ ባለቤት እኮ አንበሳ ነሽ ይለኛል" እያልሽ በአይነ ሕሊናሽ እያሰብሽ ነበር መኪናሽን በፍጥነት እየነዳሽ ቤት የገባሽው የባለቤትሽን ስም እየተጣራሽ በየክፍሉ ስትፈልጊው ባለቤትሽ የለም "ውዴ የእኔ ፍቅር የት ነህ? " እየደጋገምሽ እየተጣራሽ ነው ግን ባለቤትሽ በቤት ውስጥ የለም በሁኔታው በጣም ተደናግጠሽ ወደ ቤትሽ ጀርባ ስትሄጂ ባለቤትሽ ብቻውን ባልተመለደ መልኩ ተቀምጧል እሱን ከቁብ ሳትቆጥሪ ደስታሽን መናገር ቀጠልሽ ""የሥራ እድገት አገኘሁ እኮ"" ብለሽ ስትነግሪው ባለቤትሽ እንዳሰብሽው ከእቅፍሽ አስገብቶ ሳይስምሽ ወይም ደስታሽ ደስታዬ ነው ሳይልሽ ጥሎሽ ቢሄድ ምን ትያለሽ? በትዳርሽ ውስጥ አንድ ትልቅ ችግር አለ ማለት ነው ይህን እንዳወቅሽ ከባለቤትሽ ጋር ንትርክ ትጀምሪያለሽ ወይስ ምን ታደርጊያለሽ? የዛሬው የመጀመሪያው የ"ዘ-ሀበሻ" ጋዜጣ የመጀመሪያው እትም የሳይኮሎጂ አምድ ጽፉፌ በስኬታማ ትዳር ላይ ያተኩራል አብረን እንቆይ በሺዎች የሚቆጠሩ ትዳሮች ውስጥ ባልና ሚስት በቤ ት ውስጥ የጎሪጥ የመተያየታቸው ነገር ይታያል የአብዛኞቹ ትዳር ውስጥ ፍቅር በፍቅረኛነት ዘመን ያለቀ ይመስል አንድ ቤት ውስጥ አንድ ሶፋ ላይ ተቀምጠው ጀርባና ፊት መሰጣጠት የተለመደ ሆኗል ሁለታችሁም ከሥራ ገብታችሁ አንቺ ወደ ጓደኞችሽ ደውለሽ ስልክ የምታወሪ ከሆነ እሱም ጋዜጣ ይዞ ተቀምጦ የሚያነብ ከሆነ ፍቅራችሁ ውስጥ መሰለቻቸት የገባ አይመስላችሁም? አብሮ ተቻችሎ መኖር እጅግ ከባድ ነገር ቢሆንም ይህንን የሚወጡ ባለትዳሮች ከጀግናም በላይ ጀግና አድርገው ሳይኮሎጂስቶች የሚጠሯቸው ለምን ይመስላችኍል?? የሀገሬ ሰው ''ባል እና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ"" ብሎ የተረተውም ከላይ ያልኩትን ሀሳብ ያወፍርልኛል ባልና ሚስት ከአንድ ባልዲ ይቀዳሉ ሲባል ሁለቱን አንድ አይነት ሀሳብ ያስባሉ ማለት ብቻ ሳይሆን በአይን ተነጋግረው ይግባባሉ በአይን ብቻ ፍቅር ይሰራሉ የሚፋቀሩ ከሆነ ቢጣሉ እንኳን የትም ዞረው ይገናኛሉ የሚሉትንም ያጠቃልላል የትዳር አጋሩን ሀሳብና ፍላጎት የማይረዳ ካለ እርሱ ከትዳር አጋሩ ጋር በአንድ ባልዲ ውስጥ እንዳለ ውሀ አይደለም ማለት ነው በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ወይም ሰላማዊ ትዳር ላለመምራት እክል ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች የታወቁ ቢሆኑም ብዙ ጊዜ ልብ ብለን እነዛን ነገሮች ለማስተካከል ስለማንሄድ ችግሩ አፍጦ መጥቶ ጋብቻን እንደ ከርቸሌ እስር ቤት የምንቆጥር ብዙ ነን ከጭንቀት እና ፍርሀት ረዥም ሰአት ከመስራት ከድካም የሰው ወሬ ከመስማት ያለሆነ ነገር በአእምሮ ፈጥሮ ከማሰብ የተነሳ የትዳር አጋርን ጣል ጣል የማድረግ ነገር ይመጣል ""ረዥም ሰአት የሚሠራ ፍርሀት እና ጭንቀት ያለበት እንዲሁም የሚደክመው ሰው ችግሩን ቀስ ብሎ ከማስረዳት ይልቅ ቁጣ ቁጣ ይለዋል"" የሚሉት የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ""ንግግሩ ሁሉ የፍቅርና ትህትህናን የተሞላ ሳይሆን የንቀትና በጣም የጮኸ ስለሚሆን የትዳር አጋርን ሊበጠብጥና ወደ አልተፈለገ ንትርክ ሊመራ ይችላል"" ይላሉ እነዚህ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ለዚህ እንደመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርቡት ባልና ሚስት ረዥም ሰአት የሚፈጅ ሥራ መስራት እንደሌለባቸው ነው ሁለት ሙሉ ሰአት ሥራ የሚሠራ አንድ ወገን ለ16 ሰአታት ከሚስቱ ተለይቶ በሥራ ላይ ተወጥሮ ውሎ በ17ኛው ሰአት እቤቱ ሲገባ አልጋው ነው የሚናፍቀው ወይስ ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ የፍቅር ጨዋታ መጫወት? አብዛኞቻችን በትዳር ውስጥ ችግሮች እንዴት እንደሚፈጠሩ በልምድም ልናውቀው ስለምንችል ወደ መፍትሄዎቹ ብናመራ የተሻለ ይሆናል ታደምጣታለህ ወይ? የትዳር አጋርህ ላንተ ልክ እንደ ሴት አያትህ ናት ይላሉ የስነልቦና ባለሙያዎች አያቶች ለልጅ ልጆቻቸው እድሜያቸው በገፋ ቁጥር ብዙ ማውራትን እና ብዙ መምከርን ያበዛሉ ስላሳለፉት ነገርም በብዛት ያወራሉ አያቶች ዝም ብሎ ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጣቸውን እንደሚወዱት ሁሉ የትዳር አጋርህም እንደዚያው ናት ምንም ዝምተኛ ሚስት አገባው ብትልም ሚስት ከባሉዋ የምትደብቀው የላትምና ያሳለፈችውን ውሎ ስትነገርህ ማዳመጥ አለብህ ወሬው የሚያስጠላ ቢሆን እንኳ በአጽንኦት እየተከታተልክ መሆንን ለማረጋገጥ ''እህ"" ""አሀ"" ""ከዛስ? '' እያልክ በማዳመጥ ልታበረታታት ይገባል ከትንሽ ጀምሮ ሚስትህን የምታደምጣት ከሆነ ጸብ ቢፈጠር እንኳ የመደማመጡ ባህልን ስላዳበርክ በአጭሩ እሳትን ማብረድ ትችላለህ እርሷ ስትናደድ ምን ታደርጋለህ? እርሷ ተናዳ በነገር ልትቆሰቁስህ ትችላለች ጮክ ብላ እየተናገረች ታቆስልሀለች በዚህ ወቅት አንተም እንደ እርሷ እሳት ትሆናለህ? መልስህ አዎ ከሆነ ተሳስተሀል አንዲት ሴት ልጅ ጮክ ብላ በንዴት ከተናገረች ""የጎደለኝ አለና ስማኝ"" እያለችህ መሆኑን ማስተዋል አለብህ የጎደለባትን ነገር ለማስተካከል መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ አብረሀት ብትጮህ እና ብትለፋልፍ ቃላት ብትወራወር ትርፉ ራስን ማዋረድ ነው ቃላት በተወራወርክ ቁጥር የሚያደማ ቃል ትነጋገሩና ቁርሾ ማሳደር ይሆናል ነገርን ከመፍታት ይልቅም የባስ ትልቅ ጦርነት በቤትህ አወጅክ ማለት ነው ለዚህ ነው በተለመዶ ""ትዳሩን መምራት ያልቻለ ሰው ለሀላፊነት አይበቃም"" የሚባለው ስለዚህ ለማዳመጥ የፈጠንክ ለመልስ የዘገየህ ሁንላት ይባስ ብለህ እንደውም እርሷ በምትበሳጭበትና ጮክ ብላ በምትናገርበት ወቅት ንዴት ውስጥ ብትሆንም ዓይን ዓይኑዋን እና ከንፈር ከንፈሯን ብቻ ተመልከት ይላሉ የስነ-ልቦና ሊቆች እርሷ በንዴት ውስጥ ሆና አንተ ዓይን ዓይኑዋን የምትመለከታት ከሆነ ንዴቷ እየበረደ ከመሄዱም በላይ ያሳለፋችሁትን መልካም ጊዜ በዛች ቅጽበት ውስጥ አስታውሳ እርሷም ታጋሽ ባል አለኝ ብላ እንድትኮራብህ ታደርጋታለህ ትንሽ በረድ ካለች በሗላ ደግሞ ከንፈሯ አተኩእርህ በመመልከት ከአንገት በላይ ከእርሷ ጋር አንድ ለመሆን ፍላጎትህን አሳያት ለስለስ ያለ የከንፈር ለከንፈር መሳሳም ቁጣን አብርዶ እቤትህ ውስጥ ሰላምን እንደሚፈጥርልህ ሁልጊዜም አስተውል ስልክ ባታነሳስ? አንተ ሥራ ቦታ ነህ እንበል እርሷ እቤት ውስጥ ነች ወይም ከቤት ውጭ ወጥታለች ባለቤትህ ናፍቃህ ወደ እርሷ ቴሌፎን ስትደውል የስልክ ጥሪ ባትመልስ ምን ታደርጋለህ? እንደ የስነልቦና ሊቆች አጠቋቆም ከ100 አስር የሚያህሉት እንኳ ሚስታቸው ቴሌፎን አለማንሳቷን በጥሩ ጎኑ አይመለከቱትም አብዛኛው ወንድ የሚያስብው ""ስልኩን ከሌላ ወንድ ጋር እያወራችበት ነው ወይኔ በእኔ ላይ ደርባ ይዛብኛለች"" ብሎ ነው ወዲያው የሚያስበው ምናልባት በኔት ወርክ ምክንያት እየጠራ እርሷ ጋር ላይሰማ ይችላል የቴሌፎን ባትሪ አልቆባት ይሆናል ምን አልባት ስልክ ማውራት የማትችልበት ቦታ ይሆናል ወይም ሥራ ቦታ ውጥረት ውስጥ ትሆናለች ብሎ የሚያስብ ከስንት አንድ ነው አንተም ለአጋርህ ስትደውል ስልክ የማትመልስ ከሆነ ወዲያውኑ በመጥፎ ጎኑ የምትመለከተው ከሆነ አመለካከትህ መልካም ስላለሆነ ለመቀየር ሞክር እድሜ ለቴክኖሎጂ ""የድምጽ መልእክት ማስተላለፊያ"" ተፈጥሮልናልና ይህን ተጠቀምበት ስልኩ ጠርቶ የማይነሳ ከሆነ ""የእኔ ፍቅር እንደዚህ ያሉትን ቃላት በጸብም ሆነ በፍቅር ጊዜ አትርሳ የእኔ ፍቅር ናፍቀሺኝ ደውዬልሽ ነበር ሆኖም ስልክ ማናገር በማትችይበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እገምታለው ስለዚህ በሗላ እንደዋወላለን እወድሻለው"" የሚል አይነት ትህትናንና ፍቅርን የተላበስ መልእክት አስቀምጥላት እንደዚህ ያሉት መልእክቶች ሚስትህ አንተ እንደምትጠረጥረው ከሌላ ወንድ ጋር እንኳ ሄዳ ቢሆን ትህትህናን እና አስተዋይነትህን አይታ ራሷን ትሰበስባለች ""ባለቤቴ ራሱን ስለሚያምን እኮ ነው እኔን የሚያምነኝ"" ብላ እንድታስብ ታደርጋታለህ አለበለዚያ ግን ለምን ስልክ አታነሺም እያልክ የምትጮህ ከሆነ የስልክ ጥሪ አለመመለሱዋንም በመጥፎ መንገድ የምታየው ከሆነ ""ራሱን የማያምን ሰው ሰውን አያምንም"" የሚለውን ብሒል እውን እንዲሆን ታደርጋለህ የፍቅረኛነት ዘመንን የሚያስታውስ ትዝታን ትፈጥራለህ ወይ? በፍቅረኛንት ዘመንህ ታሳያት የነበረህን የሰጪነት የለጋስነት ባህርይ ትዳር ውስጥ የሚከለከል እንዳይመስልህ ትዳር እስር ቤት አይደለም እንደውም በፍቅረኛንት ዘመን ከነበርክበት ጊዜ በበለጠ አሁን ከአጋርህ ጋር በነጻነት የምትገናኙበት ጊዜ ነውና ይበልጥ ለጋስነትህን ማሳደግ ይኖርብሀል ምንም እንኳ በፍልስፍና ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ""ሴቶች ፍላጎታቸውን አይደለም ወንድ ራሳቸውም አያውቁትም"" ቢሉም እንደፍላጎቷ ሁንላት በመንገድ ላይ ስትሄዱ የልብስ መሸጫ ሱቅ አጠገብ ስታልፉ ""ይህ ልብስ ያምራል"" ብትልህ እንድትገዛላት ፍላጎቷን እያሳየችህ ነው ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አብረሀት ልብሱን አድንቅ እንጂ ""አንቺ ደግሞ ሁሉም ያምርሻል"" ብለህ ፍላጎቷን ኩም አታድርገው ዛሬ ባትገዛላት ሌላ ጊዜ እንደምትገዛላት በፍቅር ቃላት ንገራት ይሄኔ ልብሱን የለበሰችው ያህል ከአፍህ የወጣው የትህትና ቃል ሰውነቷን ይሞላዋል ልክ እንደዚሁ ሁሉ በትዳር ውስጥ አብረህ በምትኖርበት ወቅት በተቻለህ መጠን የተዋወቃችሁበትን ቀን ሁልጊዜ አንተ አስተዋሽ ሆነህ አነሰም በዛም ስጦታ ስጣት ሴቶች እንደዚህ የሚያደርግን ወንድ እንደ ንጉሥ የመመልከት ባህርይ ስላላቸው በተቻለህ መጠን እርሷን ድንገት የሚያስደስቱ ነገሮችን ለማድረግ ሞክር በተለይ አመታዊ የትውውቅ በዓላችሁን ስታከብሩ ድሮ በፍቅረኛነት ዘመን ትዝናኑበት የነበረው ሆቴል ይዘሀት ሄደህ ራት ጋብዛት እዛም እደሩ ይህን ካደረግክ ቤቷ እንዲናፍቃት ከማደረግህ በላይ የፍቅረኛነት ጣፋጭ ጊዜያችሁን በትዝታ መነጽር ዞር ብላ እንድታስታውስ ታደርጋታለህ ይህ ሲባል ግን ራት ይዘሀት የምትወጣው የግድ በዓላትን መጠበቅ የለብህም አብሮ ለሚኖር ሰው ሁልጊዜ በዓል ነውð ሱዳን ላይ ውሃ ሲጠማህ የምትጠጣው ከዚህ እንስራ ቀድተህ ነው ምናልባት ትል እ ና ትናንሽ እንቁራሪቶች ሊገኙበት ቢችሉም ውሃ ስለሚጠማህ ብቻ ዝም ብለህ መጠጣት ነው ሰው በተለያየ አጋጣሚ ይሰደዳል እኔ ስደትን በሁለት አይነት እከፍለዋለሁ አንደኛው የቅንጦት ስደት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአስገዳጅ ሁኔታዎች የሚከሰት ስደት ነው የቅንጦት ስደት በኢትዮጵያ ሀገሩ መኖር እየቻለ የምእራብያውያን ናፋቂ የሆነው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ብዙሀኖቻችንን የሚወክል ይመስለኛል ጥቅምት 221997 አ ም ነበር ከኢትዮጵያ የወጣሁት በዚህ ቀን ከሀገሬ ከመውጣቴ በፊት አንድ ነገር በጣም አስገርሞኛል እሱም የኢትዮጵያን ደህንነት አሰራር የታዘብኩበት ነው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጣም ይፈለግ ስለነበር በኤርፖርትም በድንበርም ከሀገር እንዳይወጣ ስሙ ተላልፎ ነበር ለጊዜው ስሙን ወደማላውቀው ሀገር አንድ አውሮፕላን ይነሳል በዚህ አውሮፕላን ላይ እስከዳር ነጋ የምትባል ሴት ተሳፍራለች አውሮፕላኑ እንደተነሳ አየር ላይ 20 ደቂቃ እንደፈጀ ተመልሶ እንዲያርፍ ተደረገ የኢትዮጵያ ደህንነቶች ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አመለጠን ብለው ተራወጡ መጨረሻ ላይ አውሮፕላኑን አስመልሰው ሲፈትሹ የተገኘችው ወሮ እስከዳር ነጋ ናት እንግዲህ ይታያችሁ ወንድና ሴት መለየት የማይችሉ ስዎችን አውሮፕላኑን ደግመው ከማሳረፍ ከአየር መንገዱ የበረራ ሪፖርት መመዝገቢያ ላይ የሴትየዋን ማንነት ማረጋገጥ ይሻላል ወይስ? በዚህ የተነሳ የመተማን ድንበር አቋርጬ ወደ ሱዳን ለመግባት ምንም ፍራቻ አላደረብኝም እንደነ ነዋይ ደበበ ''በገዳሪፍ ካርቱም'' የሚለውን ዘፈን እየዘፈንኩ ገዳሪፍን አልፌ ካርቱም ገባሁ ተወርቶ የማያልቅላት ዴም ካርቱምና የሀበሻ ስም ከተነሳ 'ዴም ' አትቀርም ዴም ዛሬ አውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ ሊቢያን ለረገጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሕይወታቸው አንድ ክፍል ናት ብል አላጋነንኩም ለምሳሌ እስኪ ዴም አዝመራን ; እማማ ነብሳቸውን ይማር ከሞቱ አመት ሊሞላቸው ነው የማያውቅ ማነው? በተለይ እማማ ቤት ግድግዳ ላይ ከተጻፉ የግድግዳ ላይ ጽሁፎች በተለይ የጨርቆስ አካባቢ ልጆች የሳቸው ድንበኛ ነበሩ እማማ ሥራቸው አንድ ትልቅ ቤት ተከራይተው ''ኬሻ በጠረባ '' ሊባል በሚችል አተኛኘት በቀን 2 የሱዳን ሊራ እየተቀበሉ የሚያሳድሩ ሴት ናቸው ካርቱም ላይ በሙቀት የተነሳ ከቤት ውጭ ስለሚተኛ ለሳቸው ገበያ በጣም ተስማሚ ነው ምክንያቱም ያቺን የሲባጎ አልጋ ማታ ማታ እየዘረጉ ያሳድራሉ በጣም የሚገርመው እማማ ቤት በአንድ ለሊት እስከ 60 ሊደርስ የሚችል ሰው ማደሩ ነው ''ትንሽ ጨቅጫቃ ናት ; ግን የዋህ ናት '' የሚል ስም ያላት አዝመራ ቤት ውስጥ ከተለጠፉ ጥቅሶች መካከል ይህን ጽፌ ነበር- ይህ ጥቅስ የሚያሳየው የካርቱም የሀበሻ ኑሮ ምነኛ አስቀያሚ እንደሆነ ያሳያል ከምግብ ውስጥ ርካሹ ፉል ነው ሱዳን ውስጥ ይህ የሚጠፋበት ጊዜ ብዙ ነው ለብዙዎቻችን ፉል እንኳ መግዢያ የሱዳን 50 ሳንቲም ጅኔ ይጠፋል እናም ይህን ለማሳየት ነው ጥቅሱ የተጻፈው ካርቱም ላይ እጅግ ታዋቂ ከሆኑ ሰዎች ሁለቱን ከጠቀስኩ ከዴም ጀምሮ ; ከሰሀፋ ዘለጥ እስከ ጅሬፍ; ከአባሁማማ እስከ አንዱርማን እና ሌሎችም ሰፈሮች የቃረምኳቸውን ታሪኮች ተራ በተራ ላስነበብ ሣራ ሣራ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መጠሪያ ስም ነው ካርቱም ላይ አንዷን ሴት አግኝተህ ማነው ስምሽ ብትላት ሣራ ትልሀለች ለምንድን ነው ዋና ስምሽን የምትቀይሪው ስትላት 'ለአጠራር እንዲመች' የሚል ተልካሻ ምክንያት ያቀርቡልሀል ዋናው ምክንያታቸው ራሳቸውን ለመደበቅ እንደሆነ የታወቀ ነው ራሳቸውን ከማን ይደብቃሉ ? እንዳትሉኝ ዛሬ ሳራ የሆነቸው ሴት ነገ 'ሀያት ' ከነገ ወዲያ 'ኢማን ' ይሆኑላችኍል ለምን ስማቸውን ይቀይራሉ? በቀጣይ ዘገባዎቼ መልስ ታገኛላችሁ በዚህ የተነሳ የሱዳን ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሴት ሁሉ ሣራ ይመስላቸዋል አንዲትን ኢትዮጵያዊትን ሴት መንገድ ላይ ሲጣሩ እንኳ ሣራ ነው የሚሉት በብዛት ተክለሀይማኖት አካባቢ እንደተወልደች የምትናገረው ሣራ የሱዳንን ምድር ከረገጠች 2 አመት ሊሞላት የቀናት እድሜ ብቻ ነበር የቀሯት ለምን ወደ ሱዳን መጣሽ? ነበር ያልኳት - የምትሰራበት የላስቲክ ሻይ መሸጫ ቤት ውስጥ ገብቼ ቁጭ ካልኩና ብዙ ከእርሷ ጋር ከተግባባው በኍላ 'ከዚህ ቀደም በሌላ አረብ ሀገር ነበር የምኖረው የአረብ ገረድ መሆን መረረኝ እስኪ የአውሮፓን ሕይወት ልይ ብዬ ወደ ሱዳን መጣሁ' ስትል ትረካዋን የጀመረችው ሳራ 'ወሬውን የሰማሁት አዲስ አበባ እያለሁ ነው ብዙ ስዎች ሱዳንን አቋርጠው በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን ይገባል ሲሉ ሰምቼ መጣሁ ከእኔ ጋር የመጣች ልጅ አሁን ሊቢያ ትገኛለች እኔ እድሌ ሆኖ ሱዳን ቀረሁ ' አለችን በቁጭት ለሳራ ሊቢያ መግባት ትልቅ ስኬት ነው ሊቢያ ምን ስቃይ ይኑር ; ይሙቅ ይድላ የምታውቀው የላትም ብቻ እሷ ሰዎች ያንን መንገድ ተጠቅመው ጣሊያን ስለሚገቡ ብቻ ሊቢያ የስኬቷ ምንጭ ነው ጥያቄዬ አላቋረጠም 'ለምን አልሄድሽም ታዲያ ?' አልኳት እምባዋ በአይኖቿ ጎን ብቅ ማለት ጀመሩ ታሪኬ ብዙ ነው ተወኝ አለችና እንደመመናቀርም ብላ ወደ ጓዳ ገባች በጣም ጓጓሁ ልጅቷ አንድ የተደበቀ ምስጢር አላት አልኩ ታዲያ ይህን ለማግኘት የግድ እርሷን መቅረብ ይገባኛልና ቀረብኳት ከብዙ ውትወታ በኍላ ልጅቷን 'አማራት' 41 የሚባለው ሰፈር የሚገኘው ጋልፍ መዝናኛ ቀጠርኳት ሱዳን ላይ በተለይ ሴት ልጅ ጋር ቀጠሮ የምትይዘው እሑድ አሀድ ወይም ጁምአ አርብ ነው እነዚህ ሁለት ቀኖች ብዙ ኢትዮጵያዊያን ኢጃዛ እረፍት የሚወጡበት ቀን ነው ለምን ቀጠሮውን አረፈድሽ አልኳት ብዙ እንዳስጠበቀችኝ ለማስገንዘብ 'ሴትየዋ ጨቅጫቃ ናት ቶሎ አትለቀኝም አሁንም አኩርፋ ነው የመጣሁት እኔ ከቤት ስወጣ አትወድም' የትኛዋ ሴትዮ ብዬ ሳልጠይቃት የምትሰራበት በላስቲክና በሸምበቆ የተወጠረው ሻይ ቤት የሌላ ሀበሻ ሴት ንብረት እንደሆነና እሷ በቀን 10 የሱዳን ዲናር እየተከፈላት እንደምትሰራ ነገረችኝ 'አየህ ሱዳኖች ወንዶቹ የኛን ሴቶች ይፈልጋሉ የኛን ሴቶች ለማየት ሲፈልጉ ወደሻይ ቤታችን ይመጣሉ ሻይ ፍለጋ ሳይሆን እኛን ' የምትለው ሳራ ወደ ሻይ ሥራ ለምን እንደገባች ስታስረዳ ታሪኩ ብዙ ነው ትላለች በወር 150 ዶላር ደመወዝ ይከፍልሻል ብለው ወደሱዳን ያመጡዋት አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ደላሎች ናቸው ለሱዳን 5 ሺህ ብር ክፍላ መምጣቷ ሳያንስ በሱዳን አሰሪዎቿ የደረሰባት ነገር እጅግ ያሳዝናል- 'አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ እንደወትሮዬ ከሁሉም ቀድሜ ተነስቼ ቤቱን የማጸዳው እኔ ስለነበርኩ አይኔን ሳልገልጥ ስወጣ ቤቱ ደጃፍ ላይ ድመት ታርዶ አንገቱና ሰውነቱ ተለያይቶ ተጥሎ አገኘሁ ' ''የታረደውን ድመት እንዳየሁ አዞሮኝ ወደቅኩ ከዛ በኍላ ራሴን ያወቅኩት ከአንድ ቀን በኍላ ነው የሴትዮዬ ማዳሟን ነው ባል ከአጠገቤ ተቀምጦ ነበር ከዛም የሆነውን ሁሉ ጠየቅኩት ድመት አርደው በር ላይ እንዲጥሉ ያደረጋቸው እምነታቸው እንደሆነ ነገረኝ '' የምትለው ሳራ ከዛ በኍላ ራሷም የእምነቱ ተከታይ በመድሐኒት እንዳደረጓት እምባዋ እየወረደ ነገረችኝ ሱዳን በሳይንስ የተረጋገጠ መረጃ ባላገኝም እንደሚወራው ከሕንድ ቀጥሎ ሁለተኛዋ የባድ ስፕሪት ጠንቋይ ሀገር ናት ሙአሰላት አውቶቡስ ውስጥ እየሄድክ ከአጠገብህ ጀለቢያ ያደረገ ቁመተ ረዥም ሱዳኒ ማግኘት የአፈር ያህል ነው ይህን ሱዳን ትንሽ እንዳወራህው ስለ ግል ህይወቱ ብትጠይቀው ጥንቆላ እንዳለበት ካለምንም ማፈር ይነግርሀል አንድ ቀን የሀበሻ ምግብ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ በምሰማት ጥቂት አረብኛ ቋንቋ አንዱ ጠብደል ሱዳን ለኛ ሴት ክንዱ ላይ በቁልፍ የታሰረ ቀበቶ ያሳያታል እሱም ይህን እያሳያት የሚነግራት ነገር ያሰረው በቁልፍ የታሰረው ቀበቶ ማንኛዋም ያናገራት ሴት እንድታፈቅረው እንደሚያደርግ እና ጥይት ቢተኮስበት እንኳን ይህ እንደ ሚከላከልለት ሲነግራት ስምቻለሁ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ሱዳን ውስጥ ስለ ጥንቆላ ማውራት በጣም አይቸግርም ይህን ስል ሱዳን ያሉ የእኛም ሰዎች ጤነኛ ናቸው ማለት አይደለም አብዛኞቹ ቀን ቀን ካርቱም መድሐኒአለም ማታ ማታ ሱቀል ዴም ያለው ጠንቋይ ቤት አይጠፉም ብዙሀኑን የሀበሻ የላስቲክ ቤት ሻይ ቤቶች ስትጎበኙም መሬቱን ስታዩ ጥቁር አዝሙድ ተንስንሶ ታያላችሁ ጥቁር አዝሙድ እና ጥንቆላ ምን አገናኘው ብዬ ጠይቄ ግን ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም **** **** ***** እምባሽን አቁሚ ብዬ እያባበልኩ ጨዋታዋን እንድተቀጥልልኝ አደረግኩ ሱዳንና ሱዳናውያንን እየቃኘን ነው የኛ ሰው በሱዳን ምን እንደሚመስል እያየን ነው አብዛኞቹ በባእድ አምልኮ ወደውም ይሁን ሳይወዱ እንዴት እንደሚገቡ ለማሳየት እየሞከርኩ ነው ሳራ በታረደ ድመት ዞሮባት የባእድ እምነቱን መከተል ጀምራለች ''ከወደቅኩበት እንደተነሳው የተነገረኝ ነገር ቢኖር ያዳነኝ አምላክ ድመቱ የታረደለት እንደሆነ ነበር '' ያለችኝ ሳራ የአሰሪዋ እናት በካርቱም ታዋቂ ጠንቋይ እንደሆኑ አስረግጣ ነገረችኝ ከዛስ? 'ከዛማ ወደ አባይ ወንዝ ካርቱምን የሚያቋርጠው መሄድ ጀመርኩ አንድ ምሽት ሴትዮዬ ልጃቸው እና እኔ ሆነን ወደ ባህር ሄድን ከሌሊቱ 6 ሰአት አካባቢ ነው ባህሩ ከምሰራበት አንዱርማን የ 30 ደቂቃ መንገድ ቢኖረው ነው እዛ ሄደን ከመኪናው እንደወረድን ሴትዮዬ ቀድማ ወደ ባህሩ ተጠጋች ከዛም መኪናው ውስጥ ከያዝነው የተቀጣጠለ ክሰል ጋር እጣን ነስንሳ ወደ ባህሩ ጋር ተጠጋች የሚሆነው ነገር ሁሉ በጣም እያስገረመኝ መጣ ሴትዬዋ ተንበርክካ እያለቀሰች አንዳንዴም እያጓራች እጣኑን ወደባህሩ ይዛው ትንሽ ገባ አለች የዛን ጊዜ ከወንዙ ውስጥ ያሉት አሶች ወደላይ እየዘለሉ እየወጡ ሲገቡ ተመለከትኩ በጣም ደነገጥኩ አጠገቤ ያለው ልጃቸውና ሚስቱ ተንበርከክው ማጉዋራት ጀመሩ ራሴን ስቼ ወደቅኩ'' በሚል ታሪኳን ተረከች ተመስጬ እያዳመጥኳት ነው ''ከሁለት ቀን በኍላ ነው የነቃሁት ሴትዮዬ ስነቃ ወደ እኔ መጥታ ከአሁን በኍላ እኔ ቤት ሥራ አትሠሪም የባህሩና የድመቱ አምላክ ላንቺ የሚሆንሽን ሰው መርጦልሻል'' ብላ ከአንድ ሀብታም የዚህ ባእድ አምልኮ ተከታይ ሱዳን እንዳጋባቻትና ከዚህ ሰው ጋር አብራ ለጥቂት ጊዜ እንደኖረች ነገረችኝ ከዛም ይህ ሱዳን እሷን የሚፈልገውን ያህል ከተጫወተባት በኍላ ለሥራ ቤቱ ከተቀጠረች ሌላ ኢትዮጵያዊት ጋር ግንኙነት ጀምሮ በእኩለ ሌሊት ከእቤት እንዳስወጣት ጨምራ እያለቀሰች ነገረችኝ የምትነግረኝ ነገር ስሜቴን እየጎዳው ነው በዛ ላይ የምታነባው እምባ በጣም ልብን ይነካል ሰው መሆንንና መፈጠርን ሁሉ ያስመርራል መጨረሻዋ ሻይ ቤት መሥራት ይሁን እንጂ እዚህ ላይ እንዴት እንደደረሰች ጠየቅኳት ''አንዱርማን የሚኖሩ ሀበሾች አብዛኞቹ የተጣባቸው ባእድ አምልኮ ስላለ እነሱ ምንም ይረዱኛል ብዬ ሳላስብ ወደ ካርቱም መጥቼ ዴም ያሉ ሀበሾች ይረዱኝ ዘንድ መጣሁ እዛ እንደመጣሁ ወደ ሊቢያ የሚሄዱ የአዲስ አበባ ልጆች አገኘሁ ስምሽ ማነው ሲሉኝ ቤቲ አልኳቸው ስሜን ለሦስተኛ ጊዜ መቀየሬ ነው የደረሰብኝን ሳልነግራቸው አዲስ መጤ እንደሆንኩና ሱዳንን ምንም እንደማላውቅ ብሎም ገንዘብ እንደሌለኝ እያለቀስኩ ነገርኳቸው አዘኑና እኛም ቤት የለንም ቢሆንም በቀን ሁለት ብር እየከፈልን የምንኖረው አዝመ ራ ቤት ነው ሥራ እስከምትጀምሪ ድረስ እኛ የምንበላ ውን ፉል እየበላሽ ትኖሪያለሽ; የአልጋም እንከፍላለን አሉ ''ከእነሱ ጋር ለ3 ቀናት ያህል እንደተቀመጥኩ 'ማዳም ቤት' የሰው ቤት ሥራ ማለት ነው ሥራ አገኘሁ ቢቸግረኝም አልሰራም አልኩ ልጆቹ ለምን አሉ? ሥራ አትወጂም ማለት ነው ብለው የሚያስከፋ ቃላትን ሰነዘሩብኝ እኔ ማዳም ቤት ሥራ አልሰራም ያልኩት የደረሰብኝ አሰቃቂ አደጋ እንዲደገም ስለማልፈልግ እንጂ ለሌላ አልነበረም ቢሆንም ልጆቹ ጥሩ ነገር ቢያደርጉልኝም ስሜቴ ቶሎ ስለሚጎዳ ትቼ ወጥቼ መንገድ ላይ ስሄድ አንድ ሀበሻ አግኝቶኝ እኚህ ሴትዮ ቤት ሥራ አስገባኝ '' አለች የቀድሞዋ ሣራ የአሁኗ ቤቲ በጣም የሚያሳዝነው የቤቲ ሕይወት ከድጡ ወደማጡ ነው ከሱዳን ቤት የወገኔ ቤት ይሻለኛል ብትልም እኚህም ሴት ያው ናቸው ለምሳሌ አንድ ቀን እሳቸው ቤት ሻይ ልጠጣ ከካርቱም ጓደኞቼ ጋር ገብቼ ሳላውቅ አንድ ጥግ ስር የጎዘጎዙትን ሳር የበተኑትን ጥቁር አዝሙድና ፈንዲሻ ረግጭባቸው ሁለተኛ እዚህ ቤት እንዳትደርስ ብለው አባረውኛል ግን ዝንጉ ስለሆኑ በሌላ ቀን ስሄድ አስገብተውኛል ''በቀን 5 ጊዜ ለአሮጊቷ ቡና ማፍላት አለብኝ ጠዋት የላስቲክ ቤቱን ሻይቤት ከመክፈቴ በፊት እግሯን የተቆረጠች እርግብ አለቻቸው ለእርሷ ስንዴ መበተን አለብኝ ያንን ባላደረግኩ ቀን ገበያ የለም ቤቱ ጭር ብሎ ይውላል ታዲያ ማታ ሂሳብ ስንሰራ ሂሳቡ ሲያንስባቸው አሮጊቷ አያስቀምጡኝም ለምን ለእርግቧ ስንዴ አልበተንሽም ; ለምን ጥቁር አዝሙድ መሬቱ ላይ አልነሰነስሽም በሚል ብዙ ውርጂብኝ ያወርዱብኛል '' ብላኛለች ያው የእኔ ሥራ ከማዳመጥ በቀር መጠየቅ ነውና ለምን ታዲያ ቤቱን ለቀሽላቸው አትወጪም ስላት ''ምን እንዳዞሩብኝ አላውቅም አንዲትም ቀን ቤቱን ስለመልቀቅ አላስብም የምፈልገውን ቢዝነስ አገኛለሁ'' አለችኝ ቢዝነስ በካርቱም ሌላ ትርጉም አላት አብዛኞቹ ሻይ ቤት የሚሰሩ ሴቶቻችን ቢዝነስ አላቸው ምን? ሐበሻ በሱዳን በቀጣዩ እትም ይቀጥላል። ወደ ታሪኩ ከመግባታችን በፊት ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፤ ዛሬ አብሮሽ በትዳር ያለ ጓደኛሽ ወይም በወሲብ የምታውቂው እጮኛሽ የኤች አይቪ ቫይረስ በደሙ እንዳለ እያወቀ ካንቺ ጋር አልጋ ላይ ቢወድቅና አንቺም ትዳር ላይ ከገባችሁ በኋላ ይሕንን ብታውቂ ምን ታደርጊያለሽ? ያንቺን ውሳኔ እወቂና ምህረት አስቻለው ያጠናቀረውን እውነተኛ ታሪክ ተከታተይ። ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ነው፡፡ ምሽት አሥራ ሁለት ሠዓት ገደማ ወደ አንድ ደሳሳ ቤት ጠጋ ብለን በር አንኳኳን ምንም ምላሽ አላገኘንም፡፡ ደግመን ስናንኳኳ ግቡ የሚል የወንድ ድምፅ ከወደ ውስጥ ሠማን፡፡ የቆርቆሮውን በር ገፋ አድርገን ስንገባ ፊት ለፊት በግምት እድሜው ሦስት ዓመት የሚሆን ህፃን ፊት ለፊት ወንበር ላይ፣ አይናቸው ላይ መሀረብ ጣል አድርገው ጠባብ አልጋ ላይ ተንጋለው የተገኙ አዛውንት ተመለከትን፡፡ አዛውንቱ ህፃኑን እናቱን እንዲጠራ አዘዙት፡፡ ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገችው ወሮ ተወልዳ ያደገችው አዲስ ዘመን የሚባል አካባቢ እንደሆነ፤ ትዳር የመሠረተችውም አዛውንቱን ያገባችው በቤተሰብ በኩል እንደሆነ ገልፃልናለች፡፡ ጋብቻ የመሠረቱት 1986 ዓም ላይ ነበር፤ በዚያ ወቅት ባለቤቷ በጦር ሠራዊት ውስጥ ያገለግሉ እንደነበርም አስታውሳለች፡፡ ሦስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ የመጀመሪያው የአሥራ አራት፣ ሁለተኛዋ የዘጠኝ ዓመት፣ በር ከፍተን ስንገባ የተመለከትነው ህፃን ደግሞ የመጨረሻ ልጃቸው ሲሆን ሦስት ዓመቱ ነው፡፡ ከጡረታ በሚገኝ ገንዘብና አትክልት እየቸረቸረች ወይዘሮዋ ቤተሰባቸውን ታስተዳድራለች ልጆቿንም ታስተምራለች፡፡ “ባለቤቴ በተደጋጋሚ ይታመም ነበር፡፡ ሁለተኛዋ ልጄም ዘወትር ትታመም ስለነበር ጥርጣሬ አደረብኝ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደግሞ ባለቤቴ ከጦር ሠራዊት ተሰናበተ፡፡ የባለቤቴም የዘጠኝ ዓመት ልጄም ህመም ቀን ከቀን እየበረታ መጣ፡፡ ባለቤቴ ይጠጣል በዚህም ዘወትር እንጋጫለን፡፡ ትዳራችን በብዙ መልኩ ችግር ውስጥ ገባ” ብላለች፡፡ ህፃን ልጇ በጣም መታመም ስለጀመረች ወደ ሆስፒታል መሄድ የግድ ሆነ፡፡ ለህፃኗ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ የህፃኗ እናት መሆኗን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንድታመጣና እሷም የኤች አይ ቪ ምርመራ እንድታደርግ እንደተነገራት አስታውሳለች፡፡ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በህፃኗም በእሷም ደም ውስጥ መኖሩ ተነገራት፡፡ ይህን ካወቀች በኋላ ትዳራቸው መፍረስ እንዳለበት በማመን ባለቤቷን እንዲፋቱ ጠይቃቸዋለች፡፡ ባለቤቷ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ፍርድ ቤት በማመልከት ፍቺ ጠይቃለች፡፡ ጉዳያቸው በመታየት ላይ እያለ ባለቤቷና ሌሎቹ ልጆቿ የኤች አይ ቪ ምርመራ አድርገው እነሱም ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩ ሊታወቅ ችሏል፡፡ ይህ ደግሞ የወይዘሮዋን ቁጣ አባባሰው፡፡ “የልጃገረድ ባለቤቴ ነው፡፡ ከተጋባንም ወዲያ እኔ የማውቀው ነገር አልነበረኝም፡፡ እሱ ግን ስለህመሙ እያወቀ እንድንጋባ፤ ከዚያም እነዚህን ልጆች እንድንወልድ ማድረጉ በጣም አስቆጣኝ፡፡ በትዳር በቆየንባቸው ጊዜያት ሁሉ አንድም ቀን ምንም ብሎ አያውቅም” ትላለች፡፡ ወይዘሮዋ እንደምትለው፣ ቀደም ሲል በተለይም ገጠር እያለች ስለ ኤች አይ ቪ ብዙም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ባለቤቷና ህፃን ልጅዋ በተደጋጋሚ ይታመሙ ስለነበር ይህም ጥርጣሬ ይፈጥርባት የነበረ ቢሆንም የኤች አይ ቪ ቫይረስ በእሷና በባለቤቷ እንዲሁም በሦስት ልጆቿ ደም ውስጥ መገኘቱን መቀበል በጣም ፈታኝ ሆኖባት ነበር፡፡ ባለቤቷ፣ እሷና ሁለተኛ ልጇ ቫይረሱ በደማቸው መኖሩ እንደታወቀ ወዲያው ፀረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒት ጀምረዋል፡፡ “እያወቀ እኔን እንዳገባኝና እነዚህ ልጆችም እንዲፈጠሩ አደረገ ብዬ ባለቤቴን ሠላም አሳጣሁት፡፡ ቤት ውስጥ ሠላም ጠፋ፡፡ ባለቤቴም ከቤት ወጥቶ ሔዶ ነበር፡፡ እኔም በአንድ በኩል ህመምና ድህነት፤ በሌላ በኩል ብስጭት አእምሮዬን እንድስት አደረገኝ፡፡ ጉዳያችንን ፍርድ ቤት እየተመለከተው እያለ እኔም እየተረጋጋሁ መጣሁ፡፡ ከባለቤቴ ጋር ተለያይቼ የማገኘው የተሻለ ነገር የለም፡፡ ምን አልባትም ህይወት ሊከብደኝ ይችላል ብዬ አሰብኩኝ” በማለት ትዳሯን የማፍረስ ሃሳቧን ቀይራ በይቅርታ ከባለቤቷ ጋር ለመኖር መወሰኗን ነገረችን፡፡ ህመም በርትቶባት በተለያዩ ጊዜአት ተኝታ ነበር፡፡ ባለቤቷም በተደጋጋሚ ይታመማሉ፡፡ ከሁሉም በይበልጥ የምትታመመው ግን ህፃን ልጇ ነች፡፡ ጐረቤቶች በተለያየ አጋጣሚ ሽንት ቤት እንዳትጠቀም በማድረግና በለሎች ነገሮች አግልለዋት ነበር፡፡ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ግን ጐረቤቶቿ ከማግለል ይልቅ ሊያቀርቧት እንደሚፈልጉ፤ እሷ ግን ያለፈውን ትታ በይቅርታ እንደቀድሞ ከጐረቤቶቿ ጋር መቀራረብ አለመቻሏን በሀዘኔታ ገልፃልናለች፡፡ “ተመርምረን ራሳችንን ካወቅን ሁለት ዓመት ሆነን፡፡ በጣም አስቸጋሪ የሆነብኝ የሴቷ ልጄ ሁኔታ ነው፡፡ ዘጠኝ ዓመቷ ነው ግን ዘወትር ስለምትታመም ሠውነቷ ድቅቅ ያለ ነው” በማለት የሦስት ዓመቱን የመጨረሻ ልጇን ጭንቅላት በመዳሰስ “እሱን ነው የምታክለው” አለችን፡፡ “በቂ ምግብ ስለማታገኝም እንደሆነ አላውቅም መድሀኒቱን አልቻለችውም፡፡ ሁለት ጊዜ አስቀይሬላታለሁ፡፡ መድኃኒት የምትወስድበትን ሠዓት ለይታ ስለምታውቅ በዚያ ሠዓት ወደ መንደር ሔዳ ትጠፋብኛለች፡፡ የዋጠች መስላ ትተፋዋለች፡፡ እሷን ለመቆጣጠር ብዬ እኔም እሷም መድኃኒት የምንወስድበት ሠዓት አንድ ዓይነት አደረግኩት” የመጀመሪያ ልጇ አሥራ አራት ዓመቱ ቢሆንም ስለ እናትና አባቱም ሆነ ስለታናሽ እህቱ ህመም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ስለራሱ ውጤትም አልተነገረውም፡፡ ፀረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒት የምትወስደው ህፃን ግን ሁሌም መድኃኒት ውሰጂ ስትባል ለምን እያለች ትጠይቃለች፣ ላለመውሰድም ትታገላለች፡፡ð በአፍሪካ ሕብረት መዲና አዲስ አበባ እና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች ''ኦባማ ቅዱስ ገብርኤል ይከተልህ'' ''ይቻላል"" እና የተለያዩ መፈክሮች ያሉበት የኦባማን ምስል የያዙ ቲሸርቶች ከምርጫው በፊት ገበያውን ሲመሩት ነበር እያንዳንዱ ሕዝብ የአሜሪካንን ምርጫ በአጽንኦት ሲከታተል የነበረ ሲሆን በአዲስ አበባ ሰፊ ተመልካች ያላቸው አልጀዚራ እና ሲኤንኤን የቲቪ ቻናሎች ሕዝባችንን በመረጃ ቀልበውታል ''ኦባማ የአፍሪካውያን ተስፋ"" የሚሉት አፍሪካውያን ከምርጫው ማሸነፍ ማግስት በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ይገኛሉ አሁን ምርጫው ከተጠናቀቀ በሗላ ደግሞ ኦባማን ተስፋ በማድረግ ላይ ይገኛሉ እንደሚታወቀው አፍሪካችን የመልካም አስተዳደር እጦት; ረሀብ; ጦርነት [ዲሞክራቲክ ኮንጎ በዚህ ወቅት በጦርነት ላይ ናት]; የኢኮኖሚ ቀውስ; ስደት; አለመደማመጥ; በሽታ; እና ሌሎችም ነገሮች እያሰቃዩዋት ይገኛሉ በተለይ የሀገሬ ሰው እንደሚተርተው 'በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ'' እንዲሉ በአሜሪካ ባንኮች ላይ የደረሰውን ኪሳራ ተከትሎ በዓለም ላይ የደረሰው የኢኮኖሚ መናጋት ለአፍሪካ ትልቅ ራስ ምታት ነው በዚህ ወቅት አፍሮ- አሜሪካዊው የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ መጥቷል አፍሪካ እጆቿን ወደ ባራክ ኦባማ ትዘረጋለች ቀጣዩን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ ይከታተሉ ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ ምናልባት መጠኑን በትክክል ለመናገር ያዳግት እንደሆን እንጂ በአፍሪቃ ልማት ላይም ተጽዕኖ እንደሚኖረው የሚታመን ነው። ታዲያ ይህ ስጋት አፍሪቃ ችግሩን ለመወጣት የራሷን አቅም እንድታዳብር ግፊት መፍጠሩ አልቀረም። በአሜሪካ የቤት ባለቤቶች ዕዳና የባንኮች ክስረት ሳቢያ ዓለምን ያዳረሰው የፊናንስ ቀውስ ለአፍሪቃ ልማትም ቢቀር በአማካይና በረጅም ጊዜ ብዙ ችግር እንዳይፈጥር አሳሳቢ ነው የሆነው። ሁኔታው በተለይም የክፍለ-ዓለሚቱን የኤኮኖሚ ባለሥልጣናት ብርቱ ስጋት ላይ ሲጥል ያለፉት ዓመታት የዕድገት ሂደት እንዳይሰናከል ገቺ ዕርምጃዎችን የመውሰዱም አስፈላጊነት ጎልቶ መታየቱ አልቀረም። በዚሁ የተነሣም የአፍሪቃ የፊናንስ ሚኒስትሮችና የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪዎች ቱኒስ ላይ ተሰብስበው መፍትሄ ለማፈላለግ ያቅዳሉ። የአፍሪቃ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ኮሜሣር ዶርማክስዌል እምኩዌዛላምባ ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይ በዓለምአቀፉ የፊናንስ ላይ ስላለው አመለካከት፣ በዓለምአቀፉ የምንዛሪ ተቁዋም ሚና፣ በልማት ዕርዳታና በክፍለ-ዓለሚቱ የራስ መፍትሄ ፍለጋ ሃሣብ አዲስ አበባ ላይ ሰፋ ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የሕብረቱን ጥረት ዓላማም ለማብራራት ሞክረዋል። “ስብሰባው የታቀደው በአንደኛ ደረጃ ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ በአፍሪቃ ኤኮኖሚ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ መመርመር ሲሆን በአፍሪቃ የልማት ባንክ ተግባራት ላይ የሚያስከትለውን ግፊትም ያጤናል። ዓለምአቀፉ የዕርዳታ አቅርቦት ሁኔታም ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው” የአፍሪቃ ሃገራት ኤኮኖሚ ብዙም ከዓለምአቀፉ የፊናንስ ገበዮች ጋር የተሳሰረ ባለመሆኑ በዚሁ የሚገጥመው ተጽዕኖ ከባድ አይሆንም የሚሉ አይታጡም። ይሁንና በበለጸጉት ሃገራት በፊናንሱ ችግር የተቀሰቀሰው የኤኮኖሚ ቀውስ አደጋ ቢቀር በንግድና በመዋዕለ-ነዋይ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው የአፍሪቃው ኮሚሢዮን ባለሥልጣን ዕምነት ነው። “ሁላችንም እንደምናውቀው በርካቶቹ የአፍሪቃ ሃገራት ከበለጸጉት መንግሥታት ጋር ብዙ የሚነግዱ ናቸው። እና በዚያ እያሰጋ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ የተነሣ የንግዳችን ሂደት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል። የንግዱና የመዋዕለ-ነዋዩ ፍሰት ጉድለት በምርት ዕድገትና በሥራ መስኮች ላይ የሚከሰት ነገር ነው። እና ለብዙ የአፍሪቃ ሃገራት ሁኔታው እክል ሳይፈጥር የሚቀር አይመስለኝም” አፍሪቃ በበለጸገው ዓለም የልማት ዕርዳታ ላይ በሰፊው ጥገኛ መሆኗ ይታወቃል። በፊናንሱ ቀውስ ሳቢያ የልማት ዕርዳታው መቀነስ ደግሞ አፍሪቃ ከ 2015 የሚሌኒየም ግቦች ለመድረስ የያዘችውን ጥረት ከንቱ ሊያደርግ የሚችል ነው። በአውሮፓና በአሜሪካ የተፈጠረው የፊናንስ ችግር በመጪዎቹ ዓመታት የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰትንና የልማት ዕርዳታን ጋብ እንደሚያደርግ ብዙም አያጠራጥርም። የበለጸጉት መንግሥታት የልማት ዕርዳታቸውን ከፍ ለማድረግ የገቡት ቃልም ገቢር ይሆናል ብሎ መጠበቁ የሚያድግት ነው። በመሆኑም የአፍሪቃ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ኮሜሣር ዶርማክስዌል እምኩዌዛላምባ የራስን ዘዴ መመርመር ግድ ነው ባይ ናቸው። “ችግሩን ጠለቅ አድርጎ መረዳቱ አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን። በመሆኑም በወቅቱ ከአፍሪቃ የኤኮኖሚ ኮሚሢዮንና ከአፍሪቃ የልማት ባንክ ጋር በጉዳዩ ጥናት እያካሄድን ነው። የዚህ ጥናት ውጤት ለቱኒስ ሰብሰባ ቀርቦ ንግግር ይደረግበታል። ከዚሁ ተያይዞ የዓለምአቀፉ ምንዛሪ ተቁዋም የ ሚናም የሚጤን ጉዳይ ነው” የዓለምአቀፉ ምንዛሪ ተቁዋም የፊናንስ ዕርዳታ በምሥራቅ አውሮፓ በሰፊው ማተኮር በአፍሪቃውያኑ ዘንድ ችላ የመባልን ስሜት ማሳደሩ አልቀረም። “የምንዛሪው ተቁዋም የኤኮኖሚ ዕድገትን ለማራመድ ተብሎ የሚቀርብለትን ገንዘብ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሃገራትን ለመደገፍ እንዴት በሥራ ላይ እንደሚያውል መጤን አለበት። በቅርቡ ለኡክራኒያ 16 ቢሊዮን፤ ለሁንጋሪያም 15 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ወስኗል። , በግልጽ ለመናገር ለሌሎች አገሮች በተለይም ለአፍሪቃ ብዙ ገንዘብ አይተርፍም ማለት ነው” ምርጫው በአንድ በኩል በዓለምአቀፍ ደረጃ ተደማጭነውን ማግኘት መቻል ሲሆን ይበልጡን ግን አቅምን አሰባስቦ ችግሩን በራስ ለመወጣት ተገቢውን ሁኔታ ማመቻቸት ነው። ከዚሁ እንዱም የአፍሪቃን ማዕከላዊና የመዋዕለ-ነዋይ ባንኮች፤ እንዲሁም የምንዛሪ ተቁዋም በክፍለ-ዓለም ደረጃ ለመፍጠር የተያዘው ጥረት ሲሆን ይህም በመካሄድ ላይ ይገኛል። ለአፍሪቃ ልማት የሚያስፈልገውን የራስ ብቃት ለማረጋገጥ ተግባሩ መፋጠን የሚኖርበት ነው። እንደ ሕብረቱ የኤኮኖሚ ኮሜሣር ከሆነ ይህ ዕርምጃ በአፍሪቃ አገሮች መካከል ያለውን ንግድም የሚያጠናክር ሲሆን ከወቅቱ መሰል ቀውስ ምታትም ሊሰውር የሚችል ነው። የአፍሪቃ ሕብረት ለክፍለ-ዓለሚቱ ልማት ማራመድ ከሚኖርበት ነገሮች አንዱ ውስጣዊውን ንግድ ማጠናከሩ ይሆናል። በዚሁ ረገድ የአፍሪቃ የአካባቢ የኤኮኖሚ ማሕበረሰቦች በጋራ ነጻ የገበያ ክልል ለመፍጠር በቅርቡ ካምፓላ ላይ ተስማምተዋል። የታሰበው ከሆነ በ 624 ሚሊያርድ ዶላር የሚገመት አጠቃላይ ምርት ያለውን ገበያ ትስስር የሚያሰፍን ነው የሚሆነው። የኡጋንዳው ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ እንዳሉት ታላቁ የአፍሪቃ ጠላትና ዋነኛው የድክመቷ መንስዔ፤ አንድነት ማጣት፤ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ትስስር በጥቂቱ እንኳ ማስፈን አለመቻል ናቸው። ታላቅ ገበዮች ሕዝቡን ከድሀነት ለማሳቀቅ ስልታዊ መሣሪያዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል።። ነጻውን የጋራ የንግድ ክልል የሚፈጥሩት ወገኖች የምሥራቅና ደቡብ አፍሪቃ ማሕበረሰብ ኮሜሣ፣ የምሥራቃዊው አፍሪቃ ማሕበረሰብ እንዲሁም የደቡባዊው አፍሪቃ የልማት ማሕበር ናቸው። ትስስሩ ደረጃ በደረጃ እንዲሰፍን የታሰበ ሲሆን ትክክለኛው የጊዜ ገደብ በአንድ ዓመት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። 26 ሃገራትን የሚያቅፈው ነጻ የንግድ ክልል ዕውን ቢሆን ለዕድገት ታላቅ ሚና እንደሚኖረው አንድና ሁለት የለውም። በአጠቃላይ ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ በተነሳባት በአሜሪካ በባራክ ኦባማ ፕሬዚደንት ሆኖ መመረጥ አዲስ የተሥፋ ዘመን ተከፍቷል። ተሥፋው የአሜሪካውያን ብቻ ሣይሆን የመላው ዓለም ነው። የአፍሪቃም ጭምር! ð በትንሾቹ የአሳ ማስገሪያ ጀልባዎች የኤደንን ባሕረ ሰላጤ ተሻግረው ወደ የመን ለመግባት ሲሞከሩ ሰጥመው ህይወታቸውን ያጡ ስድሳ የጀልባ ስደተኞች አስከሬኖች በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በየመን ጠረፍ አቅራቢያ መገኘቱን ድንበር የማይገድበው የሀኪሞች ድርጅት አስታወቀ። ከሱማሊያ ወደ የመን ለመግባት ሲሞክሩ በባህር ሰጥመው ሲሞቱ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አለመሆናቸውን የጠቆመው በዚህ ዓመት ብቻ ከ400 በላይ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ስደተኞች በዚህ ባህር ውስጥ ሰጥመው ቀርተዋል አሁን ከሞቱት ወደ ስድሳ የሚጠጉት ስደተኞች መካከል ምን ያህሉ የሶማሌያ ምን ያህሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች መሆናቸው አልታወቀም በየመን የሚገኙት የድርጅቱ ባለስልጣን አንድሪያስ ኩፒፓስ ለጀርመን የዜና ወኪል እንዳስረዱት፡ ስደተኞቹ የሞቱት ህገ ወጦቹ የጀልባዎቹ ሰራተኞች በተለያየ ምክንያት ባሕር ውስጥ እንዲዘሉ ባስስገደዱበት ጊዜ ነበር። በሕገወጥ መንግድ ባህርን አቋርጦ የአንድን ሀገር ድንበር ሰብሮ ለመግባት በሚደረግ ትግል ምናልባት ድንበር ጠባቂ ፖሊስ እጅ ላለመግባት ሲሉ የጀልባዎቹ ሰራተኞች ደላሎች ስደተኞችን ወደ ባህር እንዲሰምጡ እንደሚያስገድዷቸው ያወሱት እኚሁ ባለስልጣን በተለይ በዚህ አመት በኤደን ባህር የሞቱት ቁጥር ከፍ ማለቱ አሳስቧቸዋል በሀገር ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመቋቋም የተሳናቸው ኢትዮጵያው ያን ኤርትራዊያን ሶማሊያውያን ስደተኞች በሊቢያ ወደ ጣሊያን በሞሮኮ ወደ ስፔን በቱርክ ወደ ግሪክ ለመግባት በሚያደርጉት የባህር ጉዞ በርካቶች ለሞት ይዳረጋሉ እነዚህ ሁሉ መከራዎች አልፈው ለስኬት የበቁ ጥቂት ሰዎች እንደሚናገሩት ""የአንድን ሀገር ድንበር ስታቋርጥ መሞት መታሰር ወይም የምትፈልገው ሀገር መድረስ ይኖራል እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ገንዝብ ያስፈልጋል የምታቋርጠበት ሀገር ፖሊስ ገንዝብ ከፍለህ እዛ እንደደረስክ ስለሚያውቅ ሊረዳህ አይችልም እንደውም ገንዝብ ካልከፈልክ እስር ቤት ትማቅቃለህ"" ይላሉ በየመን የኤደን ባህረ ሰላጤን አቋርጠው ምናልባት ከሞት እና በፖሊስ ካለመያዝ ቢተርፉ እንኳ የመን ውስጥ ገብቶ ሥራ ሰርቶ ለመኖር እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ በርከት ያሉ በስፍራው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይናገራሉ በዩናይትድ ኔሽን ተመዝግቦ እንኳ ወደ 3ኛ ሀገር ለመሄድ በየመን እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ የሚናገሩት ስደተኞች ''የየመን ፖሊሶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰጠውን የስደተኛነት ወረቀት እስከመቅደድ ይደርሳሉ ለዚህም የሚናገራቸው የለም"" ይላሉ አንድ በሱማሊያ አድርጎ የመን የገባ ስድተኛ ሲናገር ''ሞትን አምልጬ የመን ገባሁ አሁንም ላለመሞት እየታገልኩ ነው"" ይላል ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ሕትመት እየገባን ባለንበት ወቅት የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ባሰራጨው ዘገባ በዚሁ በየመን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ላለመያዝ ፣ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ሰዎችን በአደን ባህረ-ሰላጤ በኩል ወደ የመን የሚያሸጋግሩ ሰዎች 240 ስደተኞች ከመርከብ ወደ ባህር አየዘለሉ እንዲዋኙ በማስገደዳ ቸው 18 ሲሰጥሙ ከ 70 በላይ የሚሆኑት ደብዛቸው መጥፋቱ ተነገረ። የተረፉት ደቡብ የመን ከተማ ፣ አህዋር መግባታቸው ተገልጿል። ስደተኞቹ፣ በአመዛኙ ከሶማልያ ጥቂቶቹም ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ተመልክቷል። ð በኢትዮጵያ የተከሰተዉ የዉጪ ምንዛሪ እጥረት በመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች ላይ አሉታዊ ተፅኖ እያሳደረ ነዉ ዛሬ የሀገሪቱ ሕዝቦች ችጋር እና የኑሮ ውድነት ስንግ ይዟቸው መንግስት በፍጠረው ችግር ምክንያት ከዓለም የደሀዎች ደሀ የምትመደበው ሀገራችን ይህ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መከሰቱ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል የመንግስት ባለስልጣናት ''በእኛ አመራር የመጣ ልማት ነው; ኢኮኖሚያችን ከሚገባው በላይ አድጓል"" እያሉ በሰፊው እየተናገሩ ቢሆንም ችግሮች አግጥጠው እየታዩ ይገኛሉ ረሀብ እና የኑሮ ውድነት እያሰቃየው ያለው ሕዝብ ችግሬ ከዛሬ ነገ ይቃለላል እያለ በተስፋ እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት የውጭ ምንዛሬ በሀገሪቱ ባለመኖሩ ፋብሪካዎች በአደጋ ላይ ሲሆኑ ሰራተኞችም በመበተን አደጋ ውስጥ ወድቀዋል ሙሉ ለሙሉ በብሔራዊ ባንክና በንግድ ባንክ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ የሌለ በመሆኑ ነጋዴዎች ጥሬ እቃ ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከመቸገራቸውም በላይ በሀገር ውስጥ የተሰማሩበት ሥራ በመቆሙ ሀገሪቱ ወትሮ ከነበረችበት ችግር የባስ አዘቅት ውስጥ እየገባች መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ ነዳጅ በዓለም አቀፍ ላይ ከ50 ዶላር በታች እያሽቆለቆለ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ግን በሚገርም ሁኔታ ላይ ነው ያለው በአሜሪካ ከሁለት ወር በፊት ከነበረው የነዳጅ ዋጋ አሁን በግማሽ ያህል እየተሸጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን በሳንቲም ደረጃ ቅናሽ ያደረገው ይህ የሆነበት ምክንያት የረከሰውን ነዳጅ ለመግዛት የውጭ ምንዛሬ ስለሌላቸው በነዳጅ እጥረት ሕዝቡ እየታመሰ ይገኛል አሁን የተከሰተው የውጭ ምንዛሬ እጥረት መንግሥት የልማት እቅዶቹን በቁነና እንዲያፅ ፈፅም ወይም በጣም-አስፈላጊና አስፈላጊ የሚል ቅደም ተከተል እንዲያወጣ እያስገደደዉ ነዉ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖችና የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች እንደሚሉት በእጥረቱ ምክንያት መንግሥት በጣም አስፈላጊ ለሚላቸዉ የልማት ፕሮጄክቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ አስገድዶታል ይህ ደግሞ የሀገሪቱን ደሀ ሕዝብ በእጅጉ ይጎዳል መንግስት የምንዛሬው እጥረት የመጣበትን ምክንያት በውል እንደማያውቅ ቢገልጽም ተቃዋሚዎች ግን ''በብድር እና በእርዳታ የሚመጣውን የውጭ ሀገር ገንዝብ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም እየቦጠቦጡ በውጭ ሀገር ባንኮች ውስጥ እያከማቹ ሀገሪቱን ባዶ በማስቀረታቸው የንግዱ ማሕበረሰብ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳያድግ ሲገደብ; አሁን ደግሞ ብዙ ፋብሪካዎች ለመዘጋት እንደተገደዱ'' ይናገራሉð ከሮቤል ሔኖክ ድሬደዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በአስተዳደር የምትመራ ሁለተኛዋ ከተማ ናት ድሬደዋ ከኦሮሚኛ ወደ አማርና ሲተረጎም "የመድሀኒት ሜዳ" ማለት ሲሆን ከሶማሊኛ ወደ እንግሊዘኛ ሲረጎም ደግሞ " " የሚል ትርጓሜ እንዳለው በሱማሊኛ የተጻፉ ጽሁፎች ይጠቁማሉ የድሬደዋ አስተዳደር በሁለት ወረዳዎች የተከ ፈለ ሲሆን አንደኛው ኢሳ ሁለተኛው ጉርጉራ ይሰኛሉ በኢትዮጵያ ፓርላማ 2 መቀመጫ ቦታም አላቸው በድሬደዋ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲገኝ በከተማዋ ደግሞ 'አባ ጤና ደጃዝማች ይልማ ኢንተርናሽ ናል ኤርፖርት""; አንድ ስታዲየም; የምድር ባቡር እና የተለያዩ የገበያ ቦታዎች ይገኛሉ የአዲስ አባባ ጅቡቲ ምድር ባቡር መስመርን ተከትሎ በ1902 አም የተቆረቆረችው ድሬደዋ ከአስር አመታት ወዲህ ለሁለት ጊዜያት በጎርፍ አደጋ መመታቷ የሚዘነጋ አይደለም በነዚህ የጎርፍ አደጋዎች በርከት ያለ ሰው ሕይወት እና የንብረት ላይ አደጋ ከመድረሱ በተጨማሪ ለብዙዎች መሰደድ ምክንያት ሆኗል በወቅቱ የዓለማችንን ሚዲያ ትኩረት ሥቦ የነበረው የድሬደዋ በጎርፍ አደጋ መጥለቅለቅን ተከትሎ ዛሬ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ባራክ ኦባማ በሥፍራው ተገኝተው መመልከታቸውን የምናስታውስ አለን? በፎቶ ግራፉ ላይ የምንመለከተው ኦባማ ኦገስት 30 2006 በድሬ ደዋ ከተማ በጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውን አካባቢዎች ሲጎበኙና አደጋ የደረሰባቸውን ወግኖቻችንንም ሲያጽናኑ ነው በፎቶ ግራፉ ላይ አብረዋቸው የምናያቸው ኢትዮጵያውይው አቶ አበራ ቶላ ሲሆኑ እኚህ ሰው የኦክስፋም አሜሪካ የቀጠና ዳይሬክተር ናቸው አቶ አበራ ቶላ ለኦባማ ስለደረሰው አደጋ ገለጻ አድርገው ኦባማን አስጎብኝተዋል ኦባማም ኦክስፋም አሜሪካ በድሬደዋ በወቅቱ በደረሰው አደጋ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አድርሰዋል ዛሬስ? 150 ሰው ያለቀበት ከ12ሺህ ሰዎች በላይ ጉዳት ባደረሰው አደጋ ወቅት ኦባማ እንደደረሱት በኢትዮጵያ መልካም አስተዳድር ሰፍኖ አንጨላጭሎ የነበረው የዴሞክራሲ በር እንዳይዘጋ ምን ያግዙን ይሆን? በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ ብዙዎች የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከምርጫው በፊት ኢሕአዴግ ለዴሞክራሲ የከፈተው በር አሁን ጥርቅም ተደርጎ ተዘግቷል ኦባማ ልክ በድሬደዋው አደጋ እንደደረሱት ሁሉ ዛሬም በኢትዮጵያ ለሰብአዊ መብቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቅ?? በነገራችን ላይ ድሬደዋ ከአዲስ አበባ 310 ማይልስ ርቀት ላይ የምትገኝ ከታላላቅ የኢትዮጵያ የንግድ ከተሞች መካከል አንዷ ናት በድሬደዋ አስተዳደር ካውንስል ውስጥ ካሉት ሕዝቦች መካከል 40% ኦሮሞዎች 277% አማሮች 139% ሶማሊዎች 45% ጉራጌዎች 23% ሰባት ቤት 08% ሶዶ 14% ስልጤ እና 59% የሌሎች ብሄሮች ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ የድሬደዋ ዋና ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን 632% የእስልምና; 345% የኦርቶዶክስ ክርስቲያን; 15% የፕሮቴስታንት; 07% የካቶሊክ እና 01% የሌሎች እምነት ተከታዮች ይኖራሉð "አብረን ከሮጥን እርሱን አስቀድመዋለው"" ሲል ጀግናው የኢትዮጵያ አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ ያወደሰው በዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ከፍተኛ የክብር ቦታ የሚሰጠው ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ""እውነትን በዜማ የሚናገር የሕዝብ ልጅ"" ሲሉ ብዙሀኖች ያወድሱታል ድምጻዊ የዜናማና የግጥም ደራሲ በመሆን ተፈጥሮ ሁሉን አሟልታ የሰጠችው የሚባልለት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ “ሰው ገድለሀል ተብሎ በተጠረጠበት “ወንጀል” ቴዲ አፍሮ ጥፋተኛ ተባለ። ፍርዱ ዲሰምበር 5 የሚሰጥ ሲሆን እና የዲሴምበር አንዱን ችሎት በገጽ 3 ላይ ይከታተሉ። ""የመለስ አስተዳደር ድራማ ሲሰራ አሰራሩን አያውቅበትም"" ነበር ያለችው ችሎቱን የተከታተለች አንዲት ወጣት ""ድራማቸው ሁሉ የሕጻናት ስለሆነ ሁልጊዜ ይጋለጣሉ"" የምትለው ይህችው ወጣት ከዲሴምበር አንዱ የቴዲ ችሎት በፊት በሕዝቡ ላይ እየተደረገ የነበረው ነገር ሁሉ በቴዲ ላይ ቀድሞ የተጻፈ ነገር እንደሚፈረድበት ያስታወቀ ነበር ትላለችከጥቂት ቀናት በፊት መሰብሰብ የተከላከለው ሕዝባችን በመስቀል አደባባይ ለታላቁ ሩጫ በተሰበሰበት ወቅት ''ቴዲ ኦባማ; መለስ አሳማ"" እያለ እየዘፈነ ብሶቱን ሲያሰማ የቴዲን ቲሸርት የለበሰ; ስለቴዲ ጮክ ብሎ የተናገረ አይን እና ጆሮ በሌላቸው የፌደራል ፖሊሶች ተወግረው እስር ቤት አድረው; ፈርመው መለቀቃቸው በአንድ ''ሰውን ገጭተሀል ለተባለ እስረኛ'' የማይገባ ነገር ነበር ድራማው ይህ ነው የምትለው ወጣት ከጥቂት ቀናት በፊት በኢንጂነር ሀይሉ ሻውል የሚመራው የመኢአድ ፓርቲ በአደባባይ በአይሱዙ መኪና የቴዲ አፍሮን 'ጃ ያስተሰርያል" ሙዚቃ ከፍቶ ስለ ሰላማዊ ትግል በመቀስቀሱ ዘፈኑን ከፍተው መቀስቀስ እንደማይችሉ ፖሊሶች ገልጸው ቅሰቀሳውን ያፈኑ ሲሆን ከቀናት በሗላ ያቺው ለቅስቀሳ የወጣችው አይሱዙ መኪና የቴዲ ዘፈኖች ስለተከፈተና ስለተቀሰቀሰባት ብቻ መኪናው ታስሯል እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች እንዲሁም ቴዲ ችሎት በቀረበ ቁጥር ችሎቱን የሚከታተል ሰው ካለፈቃዱ ቪዲዮ መቀረጹ አሁንም በትራፊክ ሕግ መጣስ ለተከሰሰ የማይገባ ነው ትላለች ይህችው ወጣት እነዚህ እና ሌሎችምክንያቶች ተደማምረው በቴዲ ላይ የቀረበው ክስ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው ትናገራለችዲሴምበር 1 በዋለው ችሎት ላይ የሕወሐት አባሉ ዳኛ አቶ ልኡል ገብረማርያም ካለምንም ማገናዘብ ግልጽ የሆኑ ማስረጃዎችን በቅንነት ባለመተርጎም በአርቲስቱ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወስነዋል እኚህ ዳኛ በቴዲ ላይ ለመፍረድ ከተቀየሩበት ችሎት መምጣታቸው ሌላው ድራማ ሲሆን ዳኛው ከዚህ ቀደም በመንግስት ላይ ጥቂት ተቃውሞ ባላቸው ሰዎች ላይ በአንካሳው ሕግ በመፍረድ ይታወቃሉ በውስጥ ገጾች ላይ ይመልከቱ አርብ ዲሴምበር 5 ፍርድ የሚጠብቀው ቴዲ በፍርድ ቤቱ የጥፋት ማቅለያ አቅርብ ቢባልም ""በሐቅ ለማይፈርድ ፍርድ ቤት ምንም አይነት የቅጣት ማቀለያ ከዚህ በላይ የለኝም እውነት ምንጊዜም ታፍና አትቀርም እኔ ንጹህሰው ነኝ'፤ ማንንም ሰው አልገደልኩም'; ብሏል በፖሊስ ታጅቦ እየሄደ ባለበት ወቅትም ለተሰበሰበው ሕዝብ ‘ከ እንግዲህ ያላችሁኝ እናንተ እና ፈጣሪ ብቻ ናችሁ” ሲል መናገሩን ሪፖርተራችን ከአ አ ዘግቧል። ቴዲ አፍሮ ላይ ለመፍረድ በአንካሳው ሕግ የተቀመጡት አቶ ልኡል ጥፋት ማቀለያ ቀረበም አልቀረበም አርብ እለት የተጻፈላቸውን ፍርድ ለቴዲ ማንበባቸው አይቀሬ ነው ብዙዎች ቴዲ ""17 መርፌ ብሎ ዘፍኖ 17 ዐመት ሊፈርዱበት ነው"" እያሉ እንደቀልድ ቢጤ ጣል ቢያደርጉም ልጁ በተጠቀሰበት አንቀጽ ከ5 እስከ 15 ዐመት ይፈርዱበታል ተብሎ ይጠበቃል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ያነጋገራቸው የፖለቲካ ምሁራን እንደሚሉት በቴዲ ላይ እየደረሰው ያለው ነገር ነገ ማንም ዘፋኝ ተነስቶ ሰለፖለቲካ እንዳይዘፍን እና መንግስትን በዘፈን እንዳይቃወም ታቅዶ የተደረገ ነው ሆኖም ግን ይላሉ እነዚሁ ምሁራን ''ሆኖም ግን በልጁ ላይ የተፈረደው ፍርድ ሕዝቡን የበለጠ በስርአቱ ላይ እንዲነሳና የትግሉን መንፈስ ያጠናክራል"" ይላሉ በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ ወንጀሉን ሰርቷል ብለው የሚያምኑ ወገኖች ''የፈሰሰው የደሀ ነፍስ እስከሆነ ድረስ ቴዲም እንደማንኛውም ሰው ፍርዱን መቀበል አለበት'' ይላሉምስክሮች ሟች ደጉ ይበልጣል አስከሬኑ ለምርመራ ምኒልክ ሆስፒታል በጥቅምት 22 ቀን 1999 ዓም ገብቶ፣ በጥቅምት 23 ቀን 1999 ዓም ምርመራ እንደተደረገለት የሚገልጸውን ማስረጃ ቢሰጡም; አርቲስቱ ከውጭ ሀገር የገባው ጥቅምት 23 ነው ፖሊስ ሰነዱን በሀይል ደጉ ይበልጣል የሞተው ጥቅምት 23 እንደሆነና የሬሳ ምርመራ የተደረገለትም በ24 እንደሆነ አስደርጎ ሰነዱን ማስቀየሩ በግልጽ በፍርድ ቤት ቢመሰከርም; ዳኛው ልኡል ነውና ጥፋተኛ ነህ ብሎታል ቴዲ አፍሮ አርብ የሚፈርድበትን ፍርድ ለማወቅ ወደ ዘ-ሀበሻ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ከአርብ ከሰአት ጀምሮ ብትደውሉ መረጃ እንሰጣችሗለንበሌላ በዘገባው አቃቤ ሕጉ ማነው? ዳኛው ልዑል ገማርያምስ ማነው? ከዳኛው የሚጠበቅ ፍርድ ተሰጠ ወይ? የሚሉ ምርጥ እና ወቅታዊ ሁሉን አቀፍ ሚዛናዊ ዘገባ ይዘናል ይከታተሉንየቴዲ አፍሮ ክስ አቃቤ ሕግ ማነው? በሻሸመኔ ከተማ ተወልዶ የመጀመሪያ ትምህርቱን እዛው አጠናቆ ከ7ኛ እና 8ኛ ክፍል በሗላወደ አሩሲ ያመራው ይህ ሰው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአሰላ ከተማ ተከታትሏል ከዛም በ1992 ከአዲስ አበባዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የተመረቀው የቴዲ አፍሮን ክስ በአቃቢ ሕግነት የሚመራው ፈቃዱ ጸጋ ነው አቃቤ ህጉ የቴዲ አፍሮንክስ ማን ነው የሠራው?? በሚል በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ልዩ ዘጋቢ ለቀረበለት ጥያቄ ''ክሱን እኔ አላዘጋጀሁትምክስ በፖሊስ ተዘጋጅቶ ለአቃቤ ሕግ ይቀርባል አቃቤ ህግ ያስከስሳል አያስከስስም የሚለውን መርምሮ ለፍርድ ቤትያቀርባል'' ብሏልቴዲ አፍሮ በተከሰሰበት ወንጀል ዓይነትከዚህ በፊት ታዋቂው አትሌት ተስፋዬቶላ በዋስ ተለቆ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ ሲከታተል ነበር; አሁን ለምን ቴዲ አፍሮ ለምን ታስሮ እንዲከታተልሆነ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ አቃቤ ህጉ ''በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ተስፋዬ ቶላ መንጃ ፈቃድ ነበረው'' በሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል ተባባሪ ዘጋቢያችን ለአቃቤ ህጉ ከዚህ በፊት በዚሁ ክስ ቴዲ አፍሮ በ15 ሺህ ብር ዋስ መለቀቁን አስታውሶ ለምን ያን ጊዜ ተለቆ አሁን ይታሰራል? የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር አቃቤ ህግ ፈቃደ ጸጋ ''አዎ ከዚህ በፊት በዋስትና ተለቆ ነበር ከአሁኑ ጋር ልዩነት አለው ያኔ ገና የፖሊስ ምርመራ ላይ ነበር ምርመራው ካላለቀና ጉዳዩ ተጠርጣሪውን ያስከስሰዋል ወይስ አያስከስሰውም የሚለው ጥያቄ ገና ካልተወሰነ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጥሮ ይሰጣል በዚያ ጊዜ ተጠርጣሪው በዋስትና ይለቀቃል ወይም አይለቀቅም የቴዲ ቁርጥቀን ከገጽ 1 የዞረተብሎም በፍርድ ቤት ይወሰናል ጉዳዩ በፖሊስ ነው የሚከናወነው በዋስትና ተለቀቀ ማለት ጉዳዩ የሚያስከስስ ሆኖ ከተገኘ ወደ ተከሰሰበት ቦታ እንዲቀርብ ዋስ ጠራ ማለት ነው ከዚያ በሗላ ምርመራው አልቆ ወደ አቃቤ ሕግ ይመጣል ፖሊሶች በምን እንደሚከሰስ ስለማያውቁት ነው ዋስትና አስጠርተው የሚለቁት አቃቤ ህግ ነው ሁሉን መርምሮ ከህግ ጋር አያይዞ የሚከሰው በተጠቀሰው አንቀጽም አቃቤ ሕግ ዋስትና እንዲከለከል ይጠይቃል'' ብለዋልአዲስ የወጣው የኢትዮጵያ የትራፊክ ሕግ ከሁለት ሰው በላይ ገጭቶ በመግደል የተጠረጠረ ወይም በመጠጥ ሀይል ሲያሽከረክር ሰው የገደለ ሰው የዋስትና መብቱ ይከለከላል ይላል ቴዲ የተጠረጠረው በአንድ ሰው መግደል ነውና ለምን በዋስ እንዲከታተል አልተደረገም ለሚለው ጥያቄ ''ዋስትና የሚያስከለክለውም የሚፈቅደውም ሕጉ ነው እኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ የጠቀስነው የወንጀል ሕግ 543 ንኡስ ቁጥር 3 ነው አራት ነገሮች ተጠቅሰዋል ከአንድ በላይ ከገደለ ወይም ግልጽ የሆነ ደንብ ተላለፎ ወንጀሉን ከፈጸመ ወይም የሚያሰክር ነገር ወሶድ ወንጀሉን ከፈጸመ ወይም የሚያፈዙ እጾችን ወስዶ ወንጀሉን ከፈጸመ የሚሉ ናቸው - 4ቱነጥቦች ከእነዚህ መካከል አንዱን የሚያሟላ ከሆነ ዋስትና ያስከለክላል በቴዎድሮስ ላይ የጠቀስነው ወንጀል ግልጽ የሆነ ደንብ ተላልፏል ብለን ነው መኪና ለማሽከርከር ከሚመለከተው ባለስልጣን መቤት መንጃ ፈቃድ ሊሰጠው ይገባል ግን መንጃፈቃድ አልተሰጠውም ተብለናል ስለዚህ ያለመንጃ ፈቃድ ነው የትራፊክን ደንብ በማፍረስ የተከሰሰው ይህ ወንጀል ከ5 እስከ 10 ዓመት ያስፈርዳል የሰው ሕይወት ያለፈበት ደግሞ እስከ 15 ዓመት ያስቀጣል ስለዚህ ዋስትና ያከለከለው ዳኛው; አቃቤ ህጉ አይደሉም ህጉ ነው'' ሲሉ አብራርተዋልከፍርዱ ቀን አስቀድሞ የቴዲ አፍሮ ፍርድ ደርሷል ለመጨረሻ ቀጠሮ ተቀጥሯል ከፍርዱ ምን ይጠብቃሉ የሚል ጥያቄ ለአቃቤ ህጉ ቀርቦላቸዋል ''አድናቂዎቹም ሆኖ ሌሎች ሰዎች ማየት ያለባቸው ነገር አለ ቴዎድሮስ ታዋቂ ነው; ግን ታዋቂ ሰው ወንጀል አይሰራም የሚል ነገር የለም ይሄንን ወንጀል ሆነ ብሎ ፈጽሞታል የተባለ አይደለም; በቸልተኝነት ፈጽሞታል ነው የተባለው ቸልተኝነት ደግሞ ከሰው ባህሪይ የሚመጣ ነገር ነው ነገር ግን ቸልተኛ ላለመሆን መሞከር ነበረበት ነው; የክሱ ሀሳብ በእርግጥ በሁሉም ነገር ቸልተኛ ስለሆነ አይቀጣም ግን በቸልተኝነት ያደረሰው ጉዳት ይታያል ዋናው ነገር ቴዎድሮስ ታዋቂ ስለሆነወንጀል ሊሰራ አይችልም; ከሰራም ሊጠየቅ አይገባም ማለት ተገቢ አይደለም እንደማንኛችንም የሰው ፍጡር ነው ብሎ ማሰብ ነው የሚገባን በእኛ በኩል ወንጀሉን ሰርቶ ከሆነ በደጋፊዎቹ እምነት ወንጀሉን አልሰራም ከሆነ ሁሉን ነገር ማስረጃ ነው የሚወስነው'' ሲሉ ''የዳኛው መቀየር በፍርዱ ላይ ምን ተጽእኖ ያመጣል; በተለይ ዳኛው አቶ ልኡል የፖለቲካ ሰው ነው ተብሎ ይነገራልና'' በሚለው ላይ አስተያየት ለመስጠት እንደማይፈልጉና ተገቢው ፍርድ ይሰጣል፤ ፍርዱንም ማንም መቀበል አለበት ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋልዳኛው አቶ ልዑል ገማርያምበመጨረሻው ሰአት ፍርዱን እንዲሰጡ ከሌላ ቸሎት ተቀይረው የመጡት አቶ ልዑል ከዚህ ቀደም በኦነግ ጉዳይ; በኡጋዴን ነጻ አውጪ ተከሳሾች ላይ; በቅንጅት መሪዎች ላይ; በበርካታ ጋዜጠኞች ላይ እድሜ ልክ እና የረዥም ዓመት ክስ የፈረዱ አንባገነን ዳኛ ናቸው ይሏቸዋል እርሳቸውን የሚያውቁዋቸው አቶ ልዑልን የሚያውቋቸው ሰዎች እንደሚናገሩት ገዢው ፓርቲ የሚፈልገውን ሕግን አጣሞ የመፍረድ ሥራ እንዲሰሩ በቦታው ላይ የተቀመጡ ናቸው አሁንም በመጨረሻው ሰዓት የቴዲ አፍሮ ክስ እኚሁ ዳኛ እጅ ላይ መውደቁ ትክክለኛ ፍርድ ይሰጣል ተብሎ እንደማይጠበቅ ብዙሀን ይመሰክራሉ ከዚህ ቀደም በአቶ ልዑል ዳኝነት 5 ዓመት እስር ቤት ቆይቶ የወጣ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኛ 'በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተር ተመቶ መወድቁን መዘገቡን" ተከትሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው "የሄሊኮፕተሩን ስባሪ አምጣ'' እንዳሉት ገልጾ; በዚህ የተነሳ 5 ዓመት እስር ቤት ቆይቶ ወጥቷል በጣም የሚገርመው ይህ ሂሊኮፕተር መወደቁ እውነት መሆኑንና በጦርነቱ ወቅት አብራሪው በዛብህ ጴጥሮስ የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ወንድም እስካሁን በኤርትራ መንግስት እጅ የት እንደተሰወሩ እንደማይታወቅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ሁሉ ሲነገር ነበር በበርካታ ሀገር ወዳድ ወገኖች ላይ አሰቃቂ ፍርድ የሰጡት አቶ ልኡል በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ አለማየሁ ላይም በትራቸውን አሳልፈዋል እኚህ ዳኛ ጋዜጠኛውን በኢትዮጵያ እያለ በሚያሳትመው መዲና ጋዜጣ የተነሳ በጋዜጣው ላይ 'የደህነንት ሚንስትሩን አቶ ክንፈ ገብረመድህንን እነማን ገደሉት? ' በሚል ባወጣው ምስጢራዊ ዘገባ በዚህ ግድያ ላይም የኢትዮጵያ ገዥ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት በመጻፉና በማጋለጡ ለ3 ቀናት በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ በጨለማ ክፍል ከታሰረ በሗላ በ5ሺህ ብር ዋስትና መለቀቁ; በፍርድ ቤት ቆይታውም የክሱ አዝማሚያ ፖለቲካው ይዘትን እየያዘ በመምጣቱ ከሀገር በዚህ እና በሌሎች 12 ክሶችየተነሳ መውጣቱን ጋዜጠኛው ይናገራል በሌላ በኩልም ሔኖክ ከሕወሓት ከተገነጠሉትና እስር ቤት ተወርውረው ከነበሩት ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር በማእከላዊ ምርመራ ማስተባበሪያ በታሰረበት ወቅት እኚህን የቀድሞ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ከ እስር ቤት ቃለ-ምልልስ አድርጎ በጋዜጣው ላይ በማተሙ በተከሰሰበት ክስ አቶ ልኡል ሄኖክን በ5 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ ከእስር እንዲወጣ አድርገዋል። አንድን ሰው ኢንተርቪው አድርገሃል በሚል መክሰስና ይህን በሚያህል ብር በዋስ መልቀቅ አሳፋሪም አስገራሚም ነገር ነው። ጨርሶም መክሰስ አይገባም። አቶ ልዑል የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች በሙሉ ክስ እርሱ በሚቀመጥበት ችሎት እንዲታይ ተደርጎ በየጋዜጠኛው ላይ የቂም በቀል ፍርድ ሲሰጥ የከረመ ሲሆን በዚህም በጋዜጠኞች ዘንድ አንድ ክስ እርሱ ችሎት ከደረሰ ''አለቀልህ'' ተብሎ ፍርዱን ቀድሞ ማወቅ እንደሚቻል ይነገራል በጋዜጣ ላይ የጋዜጣ ቀን አልጻፍክም ብሎ ካለምንም ማስጠንቀቂያ 2000 ብር የሚፈርደው አቶ ልኡል እጅ የገባ ክስ የፈለገ ማስረጃ ቢቀርብ ነጻ አይወጣም; ይልቁንም ስንት አመት ይፈረድብኝ ይሆን? ብሎ ማሰብ ይቀላል የሚሉ ብዙ ናቸውቴዲ አፍሮ የምስክርነቱን ቃል ሲሰጥ- ”በጥቅምት 23 ቀን 1999 ዓም አዲስ አበባ ገባሁ። ምትኩ ግርማ የተባለው ጓደኛዬ ከማናጀሬ ቀጥሎ ጉዳዬን የሚፈጽምልኝ ሲሆን፣ በዕለቱ ከኤርፖርት ከተቀበለኝ በኋላ ሚኪስ ፋሽን የተባለ ልብስ ቤት ሄደን ልብስ ገዛሁ። ምሳ ከበላን በኋላ ወደ ያሲን ቤት ሄድኩ። ከዚያም እዚያ ውለን ወደ አራት ሰዓት አካባቢ ማምሻውን ከያሲን ቤት ወጥተን መስቀል ፍላወር አካባቢ ያለ ቤት አመሸን፣ በኋላ ሳምሶን የተባለ ጓደኛዬ መጥቶ ነበር። ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ከዛ ወጣን፣ እኔና ሳምሶን ኦሎምፒያ ድረስ አብረን ሄድን፣ እኔ የማሲንቆ ጨዋታ እወድ ስለነበር ወደ ካሳንችስ ይወዳል ቤት እየነዳሁሄድኩ። እዚያ ከደረስኩ በኋላ ሃሳቤን ቀየርኩና ወደ ቤቴ ሲኤም ሲ መንገድ ጀመርኩ፣ ምንግዜም ከውጭ ስመጣ የሄድኩባቸው ሀገራትና የዚህ ሀገር የእንቅልፍ ሰዓት ለማስተካከል ስለሚከብደኝ ነበር ቀኑን ውጭ ያሳለፍኩት። እንደሚታወቀውና ሐኪምም እንደሚለው እንዲህ ዓይነት የእንቅልፍ መዛባት ሲገጥም መኪና መንዳት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል። በዚህ ላይ ውጭ በነበርኩበት ግዜ ተጀምሮ በምኖርበት ሲኤም ሲ አካባቢ የመንገድ ኮንስትራክሽን ሥራ ተጀምሮ ስለነበር አባጣና ጎርባጣውን መንገድ አላየሁትም ነበርና ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባበቢ ከግዑዝ ነገር ጋር ተጋጨሁ። በሰዓቱ ብዙ ነገሮችን ወደሚረዳኝ ምትኩ ጋር ደወልኩ፣ስልኩን ሊያነሳልኝ አልቻለም። መኪናዬ ውስጥ ያሉትን ካሴቶቼንና ወረቀቶቼን ሰብስቤ በላስቲክ ካደረኩ በኋላ ሠፈራችን ያለ የፔፕሲ ሠራተኛ አግኝቶኝ በመኪናው ወደ ቤቱ ወሰደኝ። ጠዋት ምትኩ የደወልኩለትን ስልክ አይቶ ደወለለኝ። የደረሰብኝን ነገርኩትና መኪናዋ መንገድ ዘግታ ስለቆመች እንዲያስጎትትልኝ ነገርኩት። በኋላ ላይ መኪናው በትራፊክ ጽሕፈት ቤት ሲያልፍ ታርጋ የለውም ተብሎ መታሠሩን ሰማሁ። ሌላ አንድ ላስገነዝብ የምፈልገው ነገር እኔ ሀገር ውስጥ የገባሁት በጥቅምት 23 ቀን ነው፣ የምኒልክ ሆስፒታል ማስረጃ እንደሚያስረዳው ደግሞ ሟች የሞተው በጥቅምት 22 ቀን ነው። ” ብሏል አቶ ልዑል የፈለገ ማስረጃ ቢቀርብ ማስረጃውን እንደ እራሱ አመለካከት የሚመለከት እንጂ የሚያገናዝብ እንዳልሆነ በቴዲ አፍሮ ፍርድ ላይ አሳይቶአል የሚሉ ወገኖች አሉ። ዳኛው በተለምዶ እንደታየው ነገሮችን በሙሉ በቅንነት የመተርጎም ባህሪይ የለውም። ዳኛ ለተከሳሽም ለከሳሽም እኩል እንደሆነ የማይገነዘበው ከአቶ ልዑል እጅ መልካም ፍርድ መጠበቅ፤ መለስ ዜናዊ የሚተርትባቸው እነዛ ትላልቅ ግመሎች በመርፌ ቀዳዳ እንዲሾልኩ እንደመጠበቅ ይቆጠራል የሚሉ በርካታ ናቸው። ከአሁን በሁዋላ ምን ይጠበቃል? በሚለው ጉዳይ ላይ አንድ የሕግ ባለሙያ ፕሮፌሰር ይስሀቅ ኤፍሬም እና አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ አርቲስቱን ከዚህ ቀደም እስር ቤት ድረስ ሄደው ልክ ከዚህ ቀደም በቅንጅት መሪዎች ላይ እንዳደረጉት ማነጋገራቸውን እንደ አንድ ምክንያት; እንዲሁም ዳኛው አቶ ልዑል ገብረማርያም የሕወሓትኢሕአዴግ አባል መሆናቸውን በማውሳት ቴዲ ከፍርዱ በሗላ ልክ እንደቅንጅት መሪዎች በይቅርታ ሰበብ ሊፈታ ይችል ይሆናል የሚል ግምታቸውን ሲሰጡ; በርካቶች ቴዲ አፍሮ የአንካሳው ሕግ ሰለባ ሆኖ ፍርዱን ጨርሶ ነጻ ይወጣል የሚል እምነት አላቸው። ይሄው ዳኛ ከ7 ዓመት በፊት በሞት እንዲቀጡ የወሰነባቸው 44የኦነግ አባላት ሰሞኑን በፕሮፌሰር ይስሃቅ እና ፓስተር ዳንኤል “አማላጅነት” በይቅርታ ሰበብ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። እነዚህ የኦነግ አባላት ሁለተኛ ወደፖለቲካ አንገባም ሕዝብንም እንዳይሳሳት እንቀስቅሳለን ብለው በመለስ ዜናዊ ሚዲያ ðላይ እየተናገሩ ይገኛሉ። እውን ይህች ቤተክርስቲያን የሁላችን አይደለችም እንዴ? ስለ ሃገራችን ሰላም፣ ስለ ቤተክርስቲያን ሰላም እናልቅስ። የሰላም አባት መድኅኒዓለም ክርስቶስ መልካሙን ያሰማን ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካን መዲና በሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ላይ "የአገልጋዮች ጉባኤ" በሚል ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ጉባኤ ጉባኤ በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር ፕሮቴስታንት እምነቱ ይህ ነው ሥርዓቱም ይህ ነው ለማለት አይቻለም ይልቁንም በአብዛኛው የራሳቸው የሆነ ወጥ ሥርዓት የሌላቸው በመሆናቸው ማንነታቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ እኝህ ነበሩ ላለፉት ፳ ዓመታ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ፕሬዘደንት ከዛም ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ ላለፉት ሁለት ወራት በሕዝብ መገናኛዎች አለመ ሰሞኑን በአንድ የፌስ ቡክ ግድግዳ ላይ ተለጥፎ ያየነው ነገር ዓይናችንን ስቦት ትንሽ ነበብ ስናደርገው እንዲህ ይላል “ ኢየሱስ ሳያቆስል የማረካቸው ” ይላል ዝርዝሩን ለመመል ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንል ወላዲተ አምላክ ዘይትነብብ በዕለተ ሠሉስ ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣች የብርሃ ምንጻፍ ይነጸፋል አቶ በጋሻው ዛሬም የውዝግብ ማዕከል ሆኗል ወደ ሉንድ፣ስዊድን የገባበት ሰነድ በራሱ አወዛጋቢ ሆኗል፣ ሉንድ፣ስዊድን የሚገኘው ቴዎሎጂ ዩንቨርስቲ የግለሰቡን ወደ ስዊድን መምጣት እንደሚ አንድ የዘወትር አንባቢያችን ከላስቬጋስ አካባቢ በተለይ በሐመረ ኖሕ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በመሆን እያገለገሉ ስላሉት መነኮስ እና ሥራቸው መጠነኛ የሆነ መረጃዎችን ልኮልናል። ምዕመን የማወቅ መብት አለ “ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በህወሃት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አሰሙ” የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ህወሃት በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ። አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …? ” በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ነዋሪዎች ውይይት በተካሄደበት ጊዜ ነው። በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3132007 ዓም በአቶ ተስፋአለም ተወልደብርሃን የመቀሌ ከንቲባ፣ አቶ አሰፋ ተገኝ ምክትል ከንቲባ የተመራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን “የህወሓት ጉባኤ ምን ይመስላል? ” የሚል አጀንዳ ተሰጥቶት ነበር። የትግራዩ አንጃ በጉባኤው ወቅት በፌስቡክና በተባራሪ ወሬ የአቶ አባይ ወልዱ ስም ክፉኛ ጠፍቷል በሚል እሳቤ የስም እዳሴ እያካሄዱ ነው። 2 ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በትግራይ የሰጠው ቃለ መጠይቆች ውሸት ናቸው። 4 የጉባኤው ተሳታፊዎች ሚስጢር እንዲጠብቁ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም በቀጥታ ስርጭት ሊባል በሚችል ደረጃ የስብሰባው መረጃ በፌስቡክ ተዘግቧል። 5 በአሁኑ ሰዓት ሁለት ዓይነት ጠላቶች አሉን። ፊት ለፊት ወጥተው የሚታገሉን እንደ ዓረና የመሰሉ እና በውስጣችን ሆነው የሚታገሉን ኪራይ ሰብሳቢ ሃይሎች ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በፌስቡክ ደረጃ ህወሓት መስለው ጀርባችን የሚወጉን ሃይሎች ናቸው። 6 አባይ ወልዱ ሙስናን የሚጠየፍ፣ ታግሎ የሚያታግለን ጀግናና ብቁ መሪ ነው። 7 በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን። 8 ጉባኤው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና በድል የተጠናቀቀ ነበር ወዘተ ተሰብሳቢዎቹ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በጥንቃቄ የተመረጡ ቢሆኑም ያቀረቡት ሃሳብና ተቃውሞ ግን ስብሰባው ላዘጋጀው አካል አስደንጋጭ ነበር። ሀ አባይ ወልዱ በጉባኤተኛ በ20ኛ የፌስቡክ ማህበረሰብ ከክፍል 20ኛ፤ ከዩኒት 1ኛ ብሎ የቀለደበት ነው ደረጃ ተመርጦ እያለ በሊቀመንበርነት እንዴት ሊመረጥ ቻለ? እዚህ ላይ የጉባኤው ዲሞክራሲያዊነት የቱ ላይ ነው? ለ እነ አርከበ በድምፅ እንዲሳተፉ የተደረገበት፣ ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይወዳደሩ የተከለከሉበት አሰራር በየትኛው ደንብ ይገኛል? ሐ ዘመኑ ያመጣው የፌስቡክ ቴክኖሎጂ ህዝቡ እንዳይጠቀም እርምጃ እንወስዳለን ማለታችሁ ጊዜው የ21ኛ ክፍለ ዘመን መሆኑ ስላልገባችሁ ነው? የሃይል እርምጃው ቴክኖሎጂውን ምን ያህል ይቆጣጠረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ? መ አቶ ዳዊትና ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚነሱት ጉዳይ በመሬት ያለና በየዕለቱ የሚያጋጥመን ሃቅ ሆኖ ሳለ አትመኑት፤ ውሸት ነው፤ ማለታችሁ ችግሮቹን ለመፍታት አቅም እንዳጠራችሁ አያመላክትም ወይ? የሚሉትና ሌሎች ፈታኝ ጥያቄዎችና ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆኑ የመቀሌ ከንቲባና ምክትሉ የሚመልሱት አጥተው አንገታቸው አቀርቅረው በሃፍረት ከስብሰባው ወጥተዋል። የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች የመሩት የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባዎች እየተካሄዱ ያሉ ሲሆኑ ዘመቻው አቶ አባይ ወልዱ የደረሰባቸው የይውረድልንና የስም ማጥፋት ዘመቻና የጠፋው ስም እንደገና የማደስ ስራ ተጠምደው ይገኛሉ። የዚህ ዘመቻ ትኩረት ተደርጎ ያለው ፌስቡክና የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው። ሰብሳቢዎች በተለያዩ መድረኮች ፌስቡክ ወጣቱ ትውልድ በአሉታዊ ጎን እያበላሸው፣ የተቃውሞ መንፈስ እየበረዘውና እየበከለው በመሆኑ መንግስት እርምጃ ይወስዳል በማለት አዋጅ እያስነገሩ ይገኛሉ። እቺ ነገር መንግስቱ ሃይለማርያም “ትጥቅ አቀረብን፣ ስንቅ አቀረብን፣ አሁን የቀረን ልብ ማደል ነው። እንደ ወያነ ጠንክራችሁ አትዋጉም ወይ…! ” ብሎ ያደረገው የተስፋ መቁረጥና የስርዓቱ ማብቅያ አመላካች ንግግር በእጅጉ ይመሳሰላል። የህወሓት አንጃዎች ክፍፍል ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በነዶር ሰለሞን ዑንቋይ ለቀናት የፈጀ ሽምግልና ከመበተን እንደዳኑ ፀሓይ የሞቀ ሃቅ ለመካድ ቢሞክሩም ከህዝቡ የተሸፈነ ግን አልነበረም። አሁን በመላ የትግራይ ወረዳዎች የአባይ ወልዱን ስም ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት በመካሄድ ላይ ይገኛል። የአዲስ አበባው አንጃ ፊታውራሪ የሆኑት ደብረፅዮን በ12ኛ ጉባኤ ላይ በፌስቡክ የሚነሱ ሃሳቦች እንደ ትልቅ የሃሳብ ምንጭ ተቆጥረው በጉባኤው ቀርበው እንደተወያዩበትና ለጉባኤው እንደ ግብአት እንደተጠቀሙበት ለቪኦኤ መግለፃቸው ይታወሳል። የአባይ ወልዱን ስም ለማጥፋት አገልግሎት ላይ ውለዋል የተባለው ፌስቡክና ተቃዋሚ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። የእርምጃው ዓይነት ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን በውል አልታወቀም። ሆኖም የኢንቴርኔት ማእከላት ሊዘጉ ይችላሉ። ማነው ትግራይ ሰሜን ኮርያ ያላት? ያው ውድድራችን ከሰሜን ኮርያ መሆኑ ነው። ትግራይ ለምትገኙ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያውያን አብዮታዊ እርምጃ እንዳይወሰድባችሁ የመንፈስ ዝግጅት ብታደርጉ እንመክራለን። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“ የኔ ሃሳብ ” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት ኤዲቶሪያል መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“ የኔ ሃሳብ ” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ከሚሆኑት አየር መንገዶች ውስጥ አንዱ አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተቀዳሚነት እንዲታይ እና መንገዶኞቻችን በይበልጥ የሀገራችንን አየር መንገድ እንዲጠቀሙ በማሰብ ቅድሚያ የተሰጠው ሲሆን፣ ሌሎችም እንደ ብሪትሽ አየር መንገድ ሉፍታንዛ እና ቨርጂን እና ኬኤልኤም የመሳሰሉት አየር መንገዶችንም ያቀፈ ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ትኬትዎን ከኢንተርኔት ላይ ይቁረጡ ባሁኑ ወቅት የቦ የጉዞ ወኪል ወብ ሳይት ለደንበኞቹ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀን ክፍት ሲሆን፣ ማናኛውም ተሳፋሪ የክሬዲት ካርድ እና ኢንተርኔት መስመር ማግኘት እስከቻለ ድረስ ካለምንም እንከን ጉዞውን ከሞቀ ቤቱ ቁጭ ብሎ በፈለገው መልክና የተስማማውን ዋጋ እራሱ መርጦ ትኬቱን መግዛት ሲችል፣ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሌክትሮኒክ ትኬትን _ መጠቀም ሲጀምር አንድ ተሳፋሪ ከአንድ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ትኬቱን መቁረጥ እና የቀረውን ጊዜ ለሌላ ነገር ማዋል ይችላል ይችል፡፡ እንዲሁም በብዛት ተሳፋሪዎች ዋጋ ለማዋቅ ከተሌዪ የጉዞዎኪሎች በመደወል የሚያተፉትን ጊዜ ይቆጥባል፡፡ እንዲሁም በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ሀገሮች ያሉ ተሳፋሪዎች የሃገር ውስጥ በረራ ትኬት መቁረጥ ከፈለጉ ከወብሳይታችን ላይ ከታዋቂ የኢንተርኔት የጉµ ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት ስመሰረትን በድህረ ገፃችን ላይ በመሄድ መቁረጥ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ አውሮፕላን፣ መኪናና ሆቴል አሜሪንና አውሮፓ ለመከራየት ከ ኦርቢትስ ፣ ከኤክስፒድያ እና ቺፕትኬትስ ከተባሉ ድርጅቶት ጋር ግንኙነት ስላለን የሀገር ውስጥ በረራዎችን ከድህረ ገፃችን ላይ ጎራ በማለት መቁረጥ ትችላላችሁ፡፡ ለወደፊቱም የቦ የጉµ ወኪል የደንበኞቻችን ጊዚ ለመቆጠብ ተጓዡ በተመቸው ቀንና ሰዓት የመኪና፣ የሆቴልና የባቡር መከራዬትን የሚያስችል ድህረ ገፅ ለማቅረብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከቢሯችን ጎራ ቢሉ ወይም ከወብሳይታችን ቢሄዱ የፓስፖረት ማመልከቻ ፎርም እንዲሁም ሰለ ጉዝዎ ከሀገር ውስጥ ሰለተሰጡ የጉዞ ማሳሰቢያወችንማስጠንቀቂያወ ማንበብ ሲችሉ፣ ከቢሯችን በመምጣት ደግሞ የፓስፖረት ፎቶ፣ የትርጉም ስራ፣ የኖቶሪ ኅትመት የማድረግ አገልግሎት ሲኖረን፣ የፋክስ ማድረግ የኢሜል እና የኢሚግሬሽን ማመልከቻዎችንም የመስጠት አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ በበለጠ ለመረዳት እባክዎ ዛሬ ነገ ሳይሉ ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡ እንዲሁም የእርስዎ አስተያየትም ሆነ ጥቆማ አገልግሎታችንን ለማሻሻል ስለሚጠቅሙን እባክዎ በ @ ይፃፉልን፡፡ ነግር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል ሴት መጋቢዎች ሰባኪዎች? መጽሐፍ ቅዱስ በአገልግሎት ውስጥ ስለ ሴቶች ምን ይላል? መልስ፤ ምናልባት ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች እንደ መጋቢዎችሰባኪዎች የማገልገላቸውን ጉዳይ የበለጠ ሞቅ ያለ አከራካሪ ጉዳይ ሌላ የለም፡፡ ስለሆነም ይህን ጉዳይ ልክ ወንዶችን ከሴቶች ጋር እንደ ማወዳደሩ አለማየቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ሴቶች እንደ መጋቢዎች ማገልገል እንደሌለባቸው እና መጽሐፍ ቅዱስ በሴቶች አገልግሎት ላይ ገደቦችን እንዳስቀመጠ ያን የሚያምኑ ሴቶች አሉ፤ እና ሴቶች እንደ ሰባኪዎች ማገልገል እንደሚችሉ የሚያምኑ እና በአገልግሎት ውስጥ በሴቶች ላይ ገደቦች እንደሌሉ ያን የሚያምኑ ወንዶች አሉ፡፡ ይሄ የመድልዎ ወይም የማግለል ጉዳይ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ጉዳይ ነው፡፡ “ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። ” እያለ የእግዚአብሔር ቃል ያውጃል 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-12፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔር የተለያዩ ኃላፊነቶችን ለወንዶችና ለሴቶች ሰጥቷል፡፡ ይህ የሰው ዘር የተፈጠረበት መንገድ እና ኃጥአት ወደ ዓለም የገባበት መንገድ ውጤት ነው 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡13-14፡፡ እግዚአብሔር በሐዋሪያው ጳውሎስ በኩል ሴቶችን በማስተማሩ ኃላፊነት ከማገልገል እናወይም በእነርሱ ላይ መንፈሳዊ ሥልጣን እንዳይኖራቸው ይገድባል፡፡ ይህ ሴቶችን እንደ መጋቢነት ፤ በትክክል መስበክን፣ ማስተማርን እና በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ሥልጣን ማግኘትን የሚያጠቃልለውን እንዳያገለግሉ ይከለክላል፡፡ በዚህ አገልግሎት ውስጥ ሴቶችን በተመለከተ ብዙ ተቃውሞዎች አሉ፡፡ የተለመደው ጳውሎስ ሴቶችን ከማስተማር ይገድባል፤ ምክንያቱም በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ሴቶች ያልተማሩ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-14 የትምህርት ደረጃን በየትም ስፍራ አልጠቀሰም፡፡ ትምህርት ለአገልግሎት መስፈርት ቢሆን ኖሮ ብዙኃኖቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ብቁ ባልሆኑ ነበር፡፡ ሁለተኛው የጋራ ተቃውሞ ጳውሎስ ከማስተማር ያገደው የኤፌሶንን ሴቶች ብቻ ነው 1ኛ ጢሞቴዎስ የተጻፈው በኤፌሶን ለነበረች ቤተክርስቲያን መጋቢ ለነበረው ለጢሞቴዎስ ነበር፡፡ የኤፌሶን ከተማ የግሪክሮማ የሀሰት አማልክቶች በአርጤምስ ቤተ-መቅደስ ይታወቅ ነበር፡፡ ሴቶች አርጤምስን በማምለኩ ሥልጣን ነበራቸው፡፡ ሆኖም ግን የ1ኛ ጢሞቴዎስ መጽሐፍም ሆነ ጳውሎስ በየትም ሥፍራ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-12 ውስጥ የአርጤምስን አምልኮ ለገደቡ እንደ ምክንያ አልተጠቀሰም፡፡ የተለመደው ሦስተኛው ተቃውሞ ጳውሎስ በአጠቃላይ ለወንዶች እና ለሴቶች ሳይሆን ባሎችንና ሚስቶችን ብቻ እያመለከተ ነው፡፡ በምንባቡ ውስጥ ያሉት የግሪኩ ቃላቶች ባሎችንና ሚስቶችን ሊያመለክት ይችላል፤ ሆኖም ግን የቃላቶቹ መሠረታዊ ትርጉም ወንዶችና ሴቶችን ያመለክታል፡፡ በተጨማሪ ተመሳሳይ የግሪክ ቃላቶች በቁጥር 8-10 ውስጥ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ያለ ቍጣና ያለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆቻቸውን እያነሱ የሚጸልዩት ወንዶች ብቻ ናቸው? ቁጥር 8፤ እንደሚገባ የሚለብሱት፣ መልካምን ሥራን በማድረግ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት ሚስቶች ብቻ ናቸው? ቁጥር 9-10፤ በእርግጥ አይደለም፡፡ ቁጥር 8-10 በግልጽ ባሎችና ሚስቶችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ወንዶችና ሴቶችን ያመለክታል፡፡ በቁጥር 11-14 በአገባቡ ውስጥ ወደ ባሎችና ሚስቶች መሸጋገርን የሚያመለክት ምንም ነገር የለም፡፡ አሁንም ለዚህ ሴቶችን በአገልግሎት ውስጥ በተመለከተ ለሚሰጠው ትርጓሜ ሌላው ተደጋጋሚ ተቃመውሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመሪነትን ቦታ ይዘው ከነበሩ ሴቶች ጋር በሚገናኝ መልኩ ነው፤ በተለይ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማሪያም፣ ዲቦራ እና ሕልዳና ናቸው፡፡ ይህ ተቃውሞ ጥቂት ዋና ጉዳዮችን ሳያካትት ቀርቷል፡፡ በመጀመሪያ ዲቦራ ከ13 ወንድ ፈራጆች መካከል ብቸኛዋ ሴት ፈራጅ ነበረች፡፡ ሕልዳና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው ከነበሩ ብዙ ወንድ ነብያቶች መካከል ብቸኛዋ ነብይት ነበረች፡፡ የማሪያም ከመሪነት ጋር የተገናኘው ብቸኛው መንገድ የሙሴ እና አሮን እህት መሆኗ ነበር፡፡ በነገሥታት ዘመን ሁለት በጣም ስመ-ጥር ሴቶች፤ጎቶልያ እና ኤልዛቤል፤ ከእግዚአብሔር የሆኑ የሴት መሪዎች ምሳሌዎች አልነበሩም፡፡ ምንም እንኳን በብሉይ ኪዳን የነበረው የሴቶች ስልጣን በጣም በዋናነት ከጉዳዩ ጋር ባይገናኝም፡፡ የ1ኛ ጢሞቴዎስ መጽሐፍ እና ሌሎች የመጋቢው መልእክቶች የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለቤተክርስቲያን አዲስ ምሳሌዎችን ያቀርባል እና ያ ምሳሌ ለእስራኤል ህዝብ ወይም ሌላ የብሉይ ኪዳን አካል ሳይሆን ለቤተክርስቲያን የስልጣን መዋቅርን ያካትታል፡፡ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጵርስቅላን እና ፎኤብን በመጠቀም ተመሳሳይ ክርክር ተደርጓል፡፡ በሐዋሪያት ሥራ 18 ውስጥ ጵርስቅላ እና አቂላ እንደ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋዮች እንደሆኑ ቀርቧል፡፡ ምናልባት ከባሏ ይልቅ በአገልግሎት የበለጠ “ስመ-ጥር” እንደነበረች በሚያመለክት የጵርስቅላ ስም በመጀመሪያ ተጠቅሷል፡፡ ሆኖም ግን ከ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፤11-14 ጋር በተቃራኒ ጵርስቅላ በየትም ስፍራ በአገልግሎት ሥራ ውስጥ ስትሳተፍ አይገልጽም፡፡ ጵርስቅላ እና አቂላ አጵሎስን ወደ ቤታቸው አምጥተው የእግዚአብሔርን ቃል በበለጠ በትክክል እያብራሩ ሁለቱም ደቀ-መዝሙር አደረጉት፡፡የሐዋሪያት ሥራ 18፤26 ወደ ሮሜ ሰዎች 16፡1 ውስጥ ፌበን ከ”አገልጋይነት” ፈንታ እንደ “ዲያቆን” ብትታሰብም እንኳ ያ ፌበን በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪ እንደነበረች አያመለክትም፡፡ “ማስተማር መቻል” ለመሪዎች እንደብቃት መለኪያ ተሰጠ እንጂ ለዲያቆናት አይደለም 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፤1-13፣ ወደ ቲቶ 1፤6-9፡፡ መሪዎች ወይም ጳጳሳት ወይም ዲያቆናት “የአንዲት ሚስት ባል”፣ “ልጆቻቸው ያመኑ” እና “የተከበሩ ሰዎች” እንደሆኑ ተገልፆአል፡፡ ሀሳቡ በግልጽ እነዚህ ብቃቶች ወንዶችን ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም በ1ኛ ጢሞቴዎስ 3፤1-13 እና ወደ ቲቶ 1፤6-9 ውስጥ መሪዎችንጳጳሳትንዲያቆናትን ለማመልከት ሙሉ ለሙሉ የተባዕታይ ጾታ ተውላጠ-ስም ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ የ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11-14 አገላለጽ “ምክንያቱን” በደንብ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ቁጥር 13 በ “ለ” ይጀምርና ለጳውሎ ዐረፍተ ነገር በ11-12 ቁጥሮች ውስጥ “መንስኤ” ይሰጣል፡፡ ሴቶች ወንዶችን ማስተማር ወይም በእነርሱ ላይ ስልጣን ማግኘት የሌለባቸው ለምንድነው? ምክንያቱም “አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ ከዚያም ሔዋን። የተታለለውም አዳም አልነበረም፥ የተታለለችው ሴቲቱ ነበረች፡፡” እግዚአብሔር መጀመሪያ አዳምን ፈጠረ ከዚያም ለአዳም “ረዳት” እንድትሆነው ሔዋንን ደግሞ ፈጠረ፡፡ ይኸ የፍጥረት ተዋረድ በቤተሰብ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፤22-23 እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በየትም የሚሆን ነው፡፡ በተጨማሪም ሔዋን የመታለሏ እውነታ ሴቶች እንደ መጋቢ እንዳያገለግሉ ወይም በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ስልጣን እንዳይኖራቸው እንደምክንያት ተሰጥቷል፡፡ ይህ ጥቂቶችን ሴቶች በበለጠ በቀላሉ በመታለላቸው ምክንያ እነርሱ ማስተማር የለባቸውም የሚለውን ወደ ማመን ይመራቸዋል፡፡ ያ ሀሳብ አከራካሪ ነው ነገር ግን ሴቶች በበለጠ በቀላሉ የሚታሉ ቢሆኑ ልጆችን በቀላሉ የሚታለሉትን እና ሌሎች ሴቶችን በጣም በቀላሉ ይታለላሉ የተባሉትን እንዲያስተምሩ ለምን ይፈቀድላቸዋል? ምንባቡ የሚለው ነገር አይደለም፡፡ ሔዋን በመታለሏ ምክንያት ሴቶች ወንዶችን ማስተማር ወይም በወንዶች ላይ መንፈሳዊ ስልጣን ሊኖራቸው አይገባም፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጀመሪያውን የማስተማር ሥልጣን ለወንዶች ሰጥቷል፡፡ ብዙ ሴቶች እንግዶችን በመቀበል ፤ በምህረት፤ በማስተማር እና በመርዳት ስጦታዎች ይልቃሉ፡፡ ብዙኃኑ የአጥቢያ ቤተክርስቲያናት አገልግሎት በሴቶች ላይ የተደገፈ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሴቶች በወንዶች ላይ ከመንፈሳዊ የማስተማር ሥልጣን ብቻ ተገድበዋል እንጂ በጉባኤ ከመፀለይ ወይም ትንቢትን ከመናገር አልተከለከሉም 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡5፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች ከመለማመድ የከለከለበት የትም ሥፍራ የለም1ኛ ቆሮንቶስ 12፡፡ ሴቶች ልክ የወንዶችን ያህል ሌሎችን ለማገልገል፣ የመንፈስ ፍሬዎችን ለማሳየት ወደ ገላቲያ ሰዎች 5፤22-23 እና ወንጌልን ለጠፉት ለማወጅ የማቴዎስ ወንጌል 28፤18-20፣ የሐዋርያት ሥራ 1፤8፣ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15 ተጠርተዋል፡፡ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈሳዊ የማስተማር ኃላፊነቶች ቦታ ወንዶች ብቻ እንዲያገለግሉ አዟል፡፡ ይኸ ወንዶች የግድ የተሻሉ አስተማሪዎች ስለሆኑ ወይም ሴቶች የበታች ወይም ያነሰ ችሎታ ያላቸው በመሆናቸው ምክንያት አይደለም፡፡ በቀላሉ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን እንዴት እንድትሠራ ያበጀበት መንገድ ነው፡፡ ወንዶች በህይወቶቻቸው እና በቃሎቻቸው በመንፈሳዊ መሪነት ምሳሌን ማሳየት ይገባቸዋል፡፡ ሴቶች ዝቅተኛውን የሥልጣን ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባቸዋል፡፡ ሴቶች ሌሎች ሴቶችን እንዲያስተምሩ ይበረታታሉ ወደ ቲቶ 2፤3-5፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች ልጆችን ከማስተማር አይከለክልም፡፡ ሴቶች የተከለከሉት ብቸኛው ተግባር ወንዶችን ከማስተማር ወይም በወንዶች ላይ ከሚኖራቸው መንፈሳዊ ሥልጣን ነው፡፡ ይኸ በተገቢው አስተሳሰብ ሴቶችን እንደ መጋቢ ወይም ሰባኪ እንዳያገለግሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይኸ በማንኛውም መንገድ ሴቶችን የማይጠቅሙ አያደርግም ነገር ግን ይልቁን ከእግዚአብሔር ዕቅድ ጋር የበለጠ የሚስማማውን እና ለእነርሱ በሰጣቸው ስጦታዎች ላይ ትኩረት ያደረገውን አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፉ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም ዓርብ ለቅዳሜ ምሽት፣ ጳጉሜን 52002 ዓ ም ማታ በኢትየጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ እያየሁ ነበር፡፡ ከአሜሪካ የገባሁት በዚያው ቀን ነበርና ዕንቅልፌ ሊስተካከልልኝ ስላልቻለ በደንብ ነበር የተከታተልኩት፡፡ እኩለ ሌሊት ሊደርስ ሲል ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ፡፡ የማከብራቸው አርቲስቶች ወደ መድረኩ ተሰባስበው ወጡና በዚያች ታሪካዊት ቀን ታሪካዊ ቀን ታሪካዊውን ስሕተት ሠሩት፡፡ እኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ሊሆን ሽርፍራፊ ሰኮንዶች ሲቀሩ «አዲሱ ዓመት ሊገባ ስለሆነ እንቁጠር» አሉና ወደ ኋላ አሥር፣ዘጠኝ፣ ስምንት፣ እያሉ እስከ ዜሮ ቆጠሩ፡፡ ከዚያም ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ አዲሱ ዓመት ገባ ብለው ዐወጁ፡፡ «ሊቃውንቱ ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል» ይላሉ፡፡ በጥንት ጊዜ አውስትራልያ የገባ አውሮፓዊ አይቷት የማያውቅ አዲስ ፍጡር ያይና የሀገሬውን ነዋሪ «ይህቺ እንስሳ ማን ትባላለች? » ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ያም የሀገሩ ነዋሪ «ካንጋሮ» ብሎ መለሰለት፡፡ ያም ሰው «ካንጋሮ» የምትባል እንስሳ አገኘሁ ብሎ ለዓለም ተናገረ፡፡ በሀገሬው ቋንቋ ግን «ካንጋሮ» ማለት «አላውቅም» ማለት ነበር፡፡ አንድ ሞኝ የተከለውን አምሳ ሊቃውንት አይነቅሉትም እንዲሉ ይሄው ስሟ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህ የአዲስ ዓመት መግቢያ ሰዓትም በየሚዲያው እና በየአዳራሹ ብቅ ጥልቅ እያለ ሰነበተና ስሕተት «ሕግ» ሆኖ በአደባባይ ታወጀ፡፡ ለመሆኑ ግን የስሕተቱ መነሻው ምንድን ነው? የመጀመርያው ቁርጥ ያለ ሕግ ካለመኖሩ የተነሣ ይመስለኛል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 5120 ላይ አንድ ወጥ ካላንደርን ማወጅ የፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሳላውቀው ታውጆ ካልሆነ በቀር እስካሁን የተወካዮች ምክር ቤት ካላንደርን በተመለከተ ያወጣው ሕግ የለም፡፡ ስለዚህም እንደ ዘመነ መሳፍንት «ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ጀመር»፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሚመለከታቸውን ባለሞያዎች በሚመለከታቸው ቦታ ያለማሳተፍ ልማዳችን የፈጠረው ሊሆንም ይችላል፡፡ አንድ ሰው እድሉን እና መድረኩን ካገኘ፤ ታውቃለህ ከተባለ፤ አጋጣሚውም ከተፈጠረለት ሁሉንም ይሆናል፡፡ ደራሲም፣ አዘጋጅም፣ ዳይሬክተርም፣ ተዋናይም፣ ይሆናል፡፡ ዘፋኝም፣ ኮምፖዘርም፣ ደራሲም፣ የድምፅ ባለሞያም ይሆናል፡፡ ይኼ ልማዳችን የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተም በሞያው የደከሙ፣ ከልክ በላይ የሠለጠኑ፤ ነገሩን ከነምክንያቱ ሊያስረዱ የሚችሉ ሊቃውንት እያሉ ሞያውን የማያውቁት እና ለሞያውም ትኩረት የማይሰጡ አካላት ገቡበትና ሁሉም የየራሱን መንገድ ፈጠረ፡፡ እንደገናም ደግሞ ፈረንጅ ያደረገው ሁሉ ትክክል ነው የሚለው ክፉ ልማዳችንም ለዚህ ሳያጋልጠን አልቀረም፡፡ ፈረንጆቹ አዲሱን ዘመናቸውን የሚቀይሩት በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ያም እንኳ ቢሆን ትክክል ሆኖ አይደለም፡፡ የዘመን መለወጫ በሽርፍራፊ ሴኮንዶቹ የተነሣ በየጊዜው ይለዋወጣልና፡፡ ነገር ግን በልማድ ሕግ መሠረት በእኩለ ሌሊት ሰዓታቸውን በመጀመራቸው ከሰዓታቸው ጋር እንዲገጥም አድርገው ተጠቀሙበትና በዚያው ጸና፡፡ ታድያ እኛም ለመሠልጠን እንደ እነርሱ በእኩለ ሌሊት አዲሱን ዓመት መቀበል አለብን ተብሎ ሳይታሰብ አልቀረም፡፡ ፈረንጆቹ በእኩለ ሌሊት አዲስ ዓመታቸውን ቢቀበሉ እውነታቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም የእነርሱ የቀን አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት አንድ ሰዓት አልፎ ይጀምርና በእኩለ ሌሊት ያልቃል፡፡ አዲሱ ዓመታቸውም 00 ብሎ የሚጀምረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ኮፒ በሚጠቅም መንገድ ከተደረገ አንዳንድ ጊዜ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኮፒ ሲደረግ ለገልባጩ እንዲያመቸው አድርጎ ካልሆነ ከመኮረጅ የባሰ ስሕተት ይሠራል፡፡ ትምህርት ቤት እያለን የሚቀለድ አንድ ቀልድ ነበረ፡፡ አንድ ሰነፍ ተማሪ ነበረ ይባላል፡፡ ይኼ ተማሪ አራተኛ ክፍል ይደርስና እንዴት እንደሚያደርግ ግራ ይገባዋል፡፡ በመጨረሻም በፈተና ሰዓት አነጣጥሮ ተኳሽ መሆን እንደሚያዋጣው ራሱን አሳምኖ ፈተና ክፍል ይገባል፡፡ ከዚያም እያነጣጠረ ከጎበዙ ተማሪ መኮረጅ ይጀምራል፡፡ አንዲትም ጥያቄ ሳታመልጠው ይኮርጃል፡፡ በመጨረሻም ፈተና በሚመለስበት ቀን ግቢው ሁሉ በሳቅ አወካ፡፡ ለካስ ያ ሰነፍ ተማሪ ከጎበዙ ተማሪ ሲኮርጅ ከነ ስሙ እና ከነ ቁጥሩ ኑሯል የኮረጀው፡፡ የኛም አኮራረጅ የዚህን ሰነፍ ተማሪ ዓይነት ሆነ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ የአዲስ ዓመት በዓል አከባበራቸውን ወስደን የኛ አዲስ ዓመት በሚከበርበት ሰዓት ብናደርገው ከሰነፉ ተማሪ አኮራረጅ የተሻለ በኮረጅን ነበር፡፡ ምናልባትም ደግሞ ነገሮችን በአራቱም አቅጣጫ ካለማየት የመጣም ይሆናል፡፡ ዕውቀት ማለት ነገሮችን ከአራት አቅጣጫ ማየት መቻል ነው፡፡ ማንበብ፣ መጠየቅ፣ መመራመር፣ ማነፃፀር፣ ማወዳደር፣ መተንተን የሚባሉት ነገሮች የሚመጡት ነገሮችን ከአራቱም አቅጣጫዎች ለማየት ሲሞከር ነው፡፡ በእኩለ ሌሊት ተነሥተው አዲስ ዓመት ገብቷል ብለው የሚያውጁ አካላት ሌላው ቀርቶ የእጅ ሰዓታቸውን እንኳን ቢያዩት በታረሙ ነበር፡፡ «ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት» ነበር የሚለው፡፡ በዚያ ሰዓት ስድስት ሰዓት ካለ ደግሞ ሌሎች አምስት ሰዓታት ከፊቱ ሄደዋል፤ ወይንም ደግሞ ሌሎች ስድስት ሰዓታት ከኋላው ይቀሩታል ማለት ነው፡፡ በዚያ ሰዓት ስድስት ሰዓት ከተባለ ደግሞ ያ ሰዓት ያለፈው ቀን ቅጣይ እንጂ የአዲስ ቀን መጀመርያ አለመሆኑን መረዳት ይገባ ነበር፡፡ አንዳንዶች ይህንን የአዲስ ዓመት ጉዳይ ከገና እና ፋሲካ በዓላት ጋርም ያያይዙታል፡፡ በገና እና ፋሲካ በዓላት ጊዜ በዓሉ የሚበሰረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ከዚህ አያይዘውም አዲስ ዓመትም በእኩለ ሌሊት ይበሠራል ይላሉ፡፡ ገና እና ፋሲካ በእኩለ ሌሊት የሚበሠሩት በበዓላቱ ታሪካዊ ምክንያት የተነሣ እንጂ የበዓሉ ቀን በእኩለ ሌሊት ስለ ገባ አይደለም፡፡ ክርስቶስ የተወለደውም ሆነ ከሙታን የተነሣው በእኩለ ሌሊት ነው ተብሎ በቤተ ክርስቲያን ስለሚታመንበዓሉ በእኩለ ሌሊት ተከበረ እንጂ ዕለታቱ በስድስት ሰዓት ስለሚገቡአይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት አቆጣጠሮች አሉ፡፡ የፀሐይ አቆጣጠር እና የጨረቃ አቆጣጠር፡፡ የፀሐይ አቆጣጠር ከጠዋቱ አሥራ ሁለት በኋላ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ይደርሳል፡፡ አብዛኛውን የሕዝቡ በዓላት እና አቆጣጠር የተመሠረተው በዚህ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የጨረቃ አቆጣጠር ነው፡፡ ይህም በምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ያልቃል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የቤተ ክርስቲያኒቱ በዓላት፣ በተለይም ዐበይት በዓላት የሚወጡት ይህንን አቆጣጠር ከፀሐይ አቆጣጠር ጋር በማጣመር ስለሆነ ተብይጠራል፡፡ በሥርዓተ ጸሎት ምሽት ሲገባ የቀጣዩን ቀን ጸሎት የምናደርሰው የጸሎት አቆጣጠራችን የጨረቃን አቆጣጠር ጭምር ስለሚከተል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሁለቱንም አቆጣጠሮችእንደየአስፈላጊነታቸው ትጠቀምባቸዋለች፡፡ አንዳንድ መፍቀርያነ በዓል ደግሞ በዓሉ የሚያምረው እና የሚደምቀው በእኩለ ሌሊት ሲሆን ነውና በእኩለ ሌሊት ብናከብረው ምናለ ይላሉ፡፡ በዓሉን በእኩለ ሌሊት ማክበርና አዲሱ ዓመት በእኩለ ሌሊት ገባ ብሎ ማወጅ ይለያያሉ፡፡ የበዓሉን ዋዜማ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ ማክበር ይቻላል፡፡ የሺ ዘመናትን ሥርዓት እና አቆጣጠር በአንድ ሌሊት በማወቅ እና ባለማወቅ መናድ ግን በታሪክ እና በትውልድ የሚያስጠይቅ ነው፡፡ ሰለጠንን የምንል ሰዎች ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን በጎርጎርዮሳዊው ቀመር ሰዓታችንን እንሞላዋለን፡፡ በኛ የሰዓት አቆጣጠርም ዕለቱ የሚጀምረው በኛ ከሌሊቱ ስድስት በእናንተ ደግሞ ከሌሊቱ 00 ሰዓት ነው፡፡ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እያከበሩ በአውሮፓ ሰዓት መጠቀም ግን በዶሮ ወጥ ላይ ማርማላታ እንደ መጨመር ነው፡፡ ሁለቱንም አያይዞ ማጥፋት፡፡ ታድያ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚብተው ስንት ሰዓት ነው? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንችል ዘንድ አራት ነገሮችን እናንሣ፡፡ የመጀመርያው በኛ አቆጣጠር ዕለት የሚባለው ምንድን ነው? የሚለው ነው፡፡ ዕለት ሁለት ነገሮችን ይይዛል፡፡ ቀን እና ሌሊት፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ዕለት የሚባለው ከመንፈቀ ሌሊት እስከ ማለዳ ያለውን ግማሽ ሌሊት፣ ከዚያም ከማለዳ እስከ ማታ ያለውን ቀን እና ከማታ እስከ እከየለ ሌሊት ያለውን ግማሽ ሌሊት የያዘው ክፍል ነው፡፡ በኛ ግን አንድ ቀን እና አንድ ሌሊትን ብቻ የያዘ አቆጣጠር ነው፡፡ ስንክሳሩ መስከረም አንድን ሲጀምር «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው፤ እሱውም የግብጽ እና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመርያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው» ይላል፡፡ ይህ የሚያመለክተን በመስከረም አንድ ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል የሆነ አንድ ቀን እንጂ በግማሽ ሌሊት እና በሙሉ ቀን የሚቆጠር አይደለም ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን በየወራቱ የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት ልዩነት ቢኖረውም ሰዓቱ ግን እኩል አሥራ ሁለት ሰዓት ቀን እና ሌሊት ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካውያን በዓመት ሁለት ጊዜ የሰዓት ማስተካከያ ወደፊት እና ወደ ኋላ ያደርጋሉ፡፡ አውሮፓውያን፣ በተለይም ሰሜኖቹ ደግሞ ከአንድ ሰዓት ሌሊት እስከ ሁለት ሰዓት ቀን የሚደርሱበት ጊዜ አለ፡፡ በኛ ግን የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ይሆናሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን ቀኑም ሆነ ሌሊቱ ከአሥራ አምስት እንደማይረዝም፤ ከዘጠኝ እንደማያንስ ነው፡፡ እንግዲህ አዲስ ዓመት በመስከረም ወር እንዲብት የተደረገበት አንዱ ምክንያት ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል የሚሆንበት ጊዜ ስለሆነም ነው፡፡ ሁለተኛው ነገር ደግሞ የዓመቱን ወራት የምናወጣው በምን አቆጣጠር ነው የሚለው ነው፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነው የዓመቱን ወራት የምንቆጥረው በፀሐይ አቆጣጠር ነው፡፡ በፀሐይ አቆጣጠር ደግሞ መዓልቱ ሌሊቱ ይስበዋል፡፡ ምክንያቱም ፀሐይ የሚሠለጥነው በቀን ነውና ዘፍ 1፤14፣16፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ በአቆጣጠራችን ቀኑ ቀድሞ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የኛ አንድ ሰዓት ማለዳ ላይ እንጂ እኩለ ሌሊት ላይ ሊጀምር አይችልም፡፡ ሦስተኛው ደግሞ የሰዓት አቆጣጠራችን ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር አንድ ብሎ የሚጀምረው መቼ ነው? አዲሱን ዓመት በእኩለ ሌሊት የሚያውጁት ሚዲያዎች እንኳን መልሰው ጠዋት ይነሡና «መስከረም አንድ ቀን ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ነው» ይሉናል፡፡ የፈረንጆቹ ሰዓት ግን በዚያ ሰዓት 7 ሰዓት ነው የሚለው፡፡ ምክንያቱም እኩለ ሌሊት ላይ አንድ ብሎ ጀምሯልና፡፡ አንድ ሰዓት ደግሞ ስድሳ ደቂቃዎች እና 3600 ሰኮንዶች ነው፡፡ ስለዚህም አንድ ሰዓት ለማለት እነዚህ ተቆጥረው ማለቅ አለባቸው፡፡ እነዚህ መቆጠር የሚጀምሩት ደግሞ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አሥራ ሁለት ሰዓት የሌሊቱ ማጠናቀቂያ ነውና፡፡ አውሮፓውያንም ቢሆኑ ይህ በየዓመቱ ያለውን የወንጌላውያን መለያየት ያውቁታል፡፡ ነገር ግን የአዲስ ዓመት መግቢያቸውን በእኩለ ሌሊት ያደረጉት አንድ ወጥ ለማድረግ ነው፡፡እኛም በዚያው በእኩለ ሌሊቱ ብንቀጥለው ምናለ? የሚሉ ሃሳብ አቅራቢዎች አሉ፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነው የእነርሱ የዘመን መለወጫቸው ከሰዓት አቆጣጠራቸው ጋር አብሮ ይሄዳል፡፡ የኛ ግን ዘመን ለወጥን ብለን መልሰን ሰባት፣ ስምንት እያልን መቁጠሩ መምታታት ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህን ነጥቦች ስናያቸው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በእኩለ ሌሊት ሊጅምር የሚችለው የወንጌላውያንን መግቦት ከተከተልን በዘመነ ማርቆስ ብቻ ነው፡፡ ያም ቢሆን ከሰዓት አቆጣጠራችን ጋር ይጋጫል፡፡ ከሰዓት አቆጣጠራችንም ሆነ ከባህላችን ጋር፣ ብሎም ከመስከረም የቀን እና ሌሊት እኩል መሆን ጋር የሚገጥመው አዲሱን ዓመት በማለዳ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ መቀበሉ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች ጳጉሜ አምስት እና ስድስት ሌሊት ተነሥተው መከራ ከሚያሳዩን ሰነድ ማገላበጥ እና ምሁራኑን መጠየቅ አለባቸው፡፡ ሊቃውንቱም ቢሆኑ ደፍረው ወጥተው ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የውይይት መድረክ የሚያዘጋጁ አካላትም አንዱ የመወያያ ጉዳይ አድርገው ፈር እንድንይዝ ቢያደርጉ ይመሰገኑበታል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ያለ ምርምር በዘፈቀደ እየተፈጸመ ያለው ስሕተት ሕግ ሆኖ እንዳይቀጥል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 5120 መሠረት ፓርላማው አንዳች ነገር ማድረግ አለበት፡፡ በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የመወሰን ሥልጣን የተሰጠው የፌዴራሉ መንግሥት ሊቃውንቱን፣ ባለሞያዎችን እና ሕዝቡን አማክሮ፤ ሰነድ አገላብጦ እና ታሪክ መርምሮ ይህንን ዝብርቅርቁ የወጣውን የአዲስ ዓመት የመባቻ ሰዓት ጉዳይ አንዳች እልባት የሚሰጥ ዐዋጅ ማወጅ ይጠበቅበታል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ! ?=891 በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው፡፡” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው፡፡ “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው፡፡ በዓሉ ጌታችን የተሰቀለበትን ዕለት መጋቢት 27ን እና ሞትን ድል አድርጎ “ለይኩን ትንሣኤ ለሙታን! ” ብሎ የተነሳበትን መጋቢት 29ን ቀን ጠብቆ እንዳይከበር ያደረገው ትልቅ ምክንያት አለ፡፡ እርሱም፣ በየዓመቱ መጋቢት 29 ቀን እሑድ-እሑድ አለዋሉ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ከዘመናት በኋላ መጋቢት 29ን እየጠበቁ፣ አንዴ ሰኞ፣ ሌላም ጊዜ ማክሰኞ ወይም ረቡዕና ኀሙስ፣ ወዘተርፈ ይከበር የነበረውን የጌታ ትንሣኤ በዕለተ-እሑድ ለማክበር የሚያስችለውን ድንጋጌ፣ በ13ኛው ክፍለ ዘመን ላይ-አቡሻህር ኢብን ቡትሩስ ራሒብ ወይም ዮሐንስ የተባለው የእስከንደሪያ ካህን ገለጠው፡፡ በዚህም ድንጋጌ መሠረት የትንሣኤ በዓል ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ባሉት እሑዶች ውስጥ እየተዘዋወረ ይከበር ጀመር፡፡ በመሆኑም፣ የጾመ ነነዌና የዐብይ ጾም የሚጀርባቸው ዕለታት ሰኞ-ሰኞ እንዲሆኑ ተደነገገ፡፡ የሆሳዕና እና የትንሣኤም ዕለቶች ከእሑድ ውጪ እንዳይሆኑ ደንብ ተሠራ፡፡ የጸሎተ ኀሙስም-በዕለተ ኀሙስ፤ የስቅለት ዕለትም በያመቱ አርብ-አርብ እንዲሆን ተደረገ፡፡ የቅዳሜ ሥዑርም-ከቅዳሜ ውጪ እንዳይሆን ተደረገ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችንም የሞትን ቅኝ-ግዛት ድል የተቀዳጀበት ዕለት እሑድ ስለነበረ፣ የትንሣኤ በዓል ከእሑድ ውጪ እንዳይሆን ተደረገ፡፡ በዕለተ ኀሙስ ግን ሁለት የማይታለፉ ተግባራትን አከናወነ፡፡ የመጀመሪያው ወደ ተራራው ጫፍ ወጥቶ ያደረገው ጸሎት ነው፡፡ ደም እንደላብ እየወረደው በተመስጦ ሲጸልይና ሲተጋ ሳለ፣ ሦስቱ ነብያት ነብዩ ሄኖክ፣ ነብዩ ሙሴ፣ እና ነብዩ ኤልያስ የሰማየ-ሰማያትን አድማስ ጥሰው ከተፍ አሉ፡፡ እንዲጸናም አዘዙት፡፡ የእግዚአብሔርም ድምጽ እያስገመገመ መጣ፡፡ ፈጣሪያችን መጽናናትንም ለዓለም ላከ፡፡ ከተራራው ከወረዱ በኋላ የመጨረሻውን ራት ለመብላት ሄዱ፡፡ በዚህም ምሽት ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፡፡ “ነገ በመልዕልተ መስቀል ላይ የሚፈተተው ሥጋዬ እና የሚፈሰውም ደሜ ይህ ነው! ” ስለዚህም፣ በምሴተ-ኀሙስ ሥጋውን-በስንዴ፣ ደሙንም-በወይን አምሳል አድርጎ ለደቀ መዛሙርቱ የሠጠበት ምሽት ነው፡፡ ከዚህም ሌላ የደቀ መዛሙርቱን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትም ሰዓት ነው፡፡ እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንደዚህ አድርጉላቸው! ብሎም ያዘዘው በዚሁ ጊዜ ነበር፡፡ የጌታንም አርዓያነት በመከተል የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምእመናን ዕለተ-ኀሙስን ጸሎት በማድረግና የጌታንም ራት ለማሰብ ተብሎ የሚዘጋጀውን ጉልባን በመመገብ ታከብረዋለች፡፡ ከዚህም የመጨረሳ ራጽ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እስከሚነሳበት ለእሑድ አጥቢያ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ድረስ ምእመናን ምንም ነገር ከመመገብ ይታቀባሉ፤ ይጾማሉ፡፡ የአዱዋውን ድል የተጎናፀፍንበት ዕለት፣ በአለማችን ላይ ከተከሰቱት 15ቱ ታላላቅ ቀናት መካከል የምናስቀምጠው ነው፡፡ በአዲስጉዳይ መጽሔት ላይ 20120615 በሁለት ተከታታይ መጣጥፎች እንደገለጽኩት፣ የሰውን ልጆች ሰብዓዊ ክብርና የመንፈስ ሙላት ላቅ በማድረግ ከሚወሱትከሚጠቀሱት ቀናት መካከል አንዱ፣ “የአዱዋው ድል” ነው፡፡ የድሉ አብነትተምሳሌት፣ ብሎም የዘር-መድሎን በመፈወስ ሃይሉና የእኩልነትን አዋጅ በማወጅ አቅሙ አዱዋን የሚስተካከል የለም፡፡ ድሉ፣ የስልጡኗ አውሮፓንና የኋላ-ቀሯን አፍሪካ ጦርነት ነው የአሸናፊዎች አሸናፊ መለያም ነው፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ደግሞ አልፈው-ተርፈው “ የጥቁሮችና የነጮች ፍልሚያ” አድርገው ተመልክተውታል፡፡ የሃይማኖትን ታሪክ አጥኚ የሆኑት ምሁራን በበኩላቸው፣ የካቶሊካዊቷ ሮማና የኦርቶዶክሳዊቷ ኢትዮጵያ ፍልሚያ አድርገው አስበውታል፡፡ እርግጥ ነው፣ የጊዮርጊስ ጽላትታቦትና አቡኑና እጨጌውም በጦርነቱ ሥፍራ ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል፣ በአድዋው ጦርነት ወቅትና ከአርባ ዓመታት በኋላ በተደረገው የአምስት ዓመቱ የወረራም ዘመን ጅማሮ ላይ የሮማ ሊቃነ-ጳጳሳት በአደባባይ ተገኝተው የፋሺስትን ጦር በካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ስም ባርከው ልከዋል፡፡ በመሆኑም፣ ጦርነቱ የጊዮርጊስ ጽላትታቦት ተሸክመው የዘመቱት “ኦርቶዶክሳዊያን” እና በሊቀ-ጳጳሳቶቻቸው ቡራኬ አገር እንዲያቀኑ ተባርከው የተሸኙት “ኮተሊኮች ጦርነት” ሆነ፡፡ ውጤቱም ለኦርቶዶክሳውያኑ ያደላ ሆነ፡፡ የአዱዋ ጦርነት መንስኤ የታወቀው የውጫሌ ውል ነው፡፡ ውጫሌ በአንባሰልና በየጁ መካከል የሚገኝ፣ ለሐይቅ እስጢፋኖስ ቀረብ ያለ ቦታ ስም ነው፡፡ ይህ ስምምነት ሃያ አንቀፆች ያሉት ሲሆን፣ በሚያዝያ 25 ቀን 1881ዓም ተፈረመ፡፡ ለውዝግቡም ጉልሁን ድርሻ የሚወስደው “አንቀጽ 17” የተባለው አንቀጽ ነበር፡፡ ውሉን ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ የተረጎሙት ወይም የአማርኛውን ዘር ያረቀቁት ሰው፣ ግራዝማች ዮሴፍ ንጉሤ ይባላሉ፡፡ የጣሊያንኛውንም ቅጂ ያሰናዳው አንቶንሌ ነበር፡፡ አንቶንሌ ከአስር ዓመታት በላይ አንኮበርና በእንጦጦ አብያተ-መንግሥታት አካባቢ ስለኖረ አማርኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ ስለሆነም የሕጋዊ ዘይቤና አገባብ ያላቸውን ቃላትና ፍቺዎቻቸውንም አብጠርጥሮ እስከማወቅም ደርሶ ነበር፡፡ በዚህም እውቀቱ ተጠቅሞ በአማርኛና በጣሊያንኛ የተለያዩ ትርጓሜዎች ያሉትን አንቀጽ 17ን አሰናዳ፡፡ የአማርኛው እንዲህ ይላል፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር መገናኘት ከፈለገ የኢጣሊያንን መንግሥት አገልግሎት ሊጠቀም ይችላል፤ ” ሲል-የጣሊያንኛው ቅጂ ደግሞ “የኢትዮጵያ መንግሥት ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር መገናኘት ከፈለገ የኢጣሊያንን መንግሥት በኩል ይገለገላል፤ ” ይላል፡፡ በአዱዋው ጦርነት ዋዜማ ላይ ከሰኔ 1885 እስከ ጥቅምት 1888ዓም ድረስ ኢትዮጵያና ጣሊያን በየፊናቸው ዝግጅቶቻቸውን ሲያድርጉ ከረሙ፡፡ በጣሊያን በኩል የተለመደውን ተንኮልና ማጭበርበር ቀጠለ፡፡ ዋነኛው ተንኮል የከብት በሽታን ወደኢትዮጵያ ማስገባት ነበር፡፡ በዚህም ሰበብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶች አለቁ፡፡ ገበሬው ለእርሻ የሚጠቀምባቸው በሮችም አለቁ፡፡ በመሆኑም፣ ዋነኛው የእርሻ ግብዓት በበሽታው በመጠቃቱ፣ የገበሬው ምርታማነት እጅግ አሽቆለቆለ፡፡ ረሃብና ጠኔ በመላ ሀገሪቱ ተንሰራፋ፡፡ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ በኢትዮጵያ ምድር ተከሰተ፡፡ አዝማሪው እንዲህ ሲል አዜመ፤ “የበሬዎቹ ስም ጠፍብኝ ነበረ፤ አሁንስ ባስታውስ ከብት ዓለም ነበረ፡፡” አለ፡፡ እጅግ የታወቀው “ሞጣ ቀራኒዮ ምነው አይታረስ፤ በሬሳ ላይ መጣሁ፣ ከዚህ እስከዚያ ድረስ፡፡”ም የተባለው በዚያ ወቅት ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ያለቁትን ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ፀሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “ይኼ ዘመን የእግዚአብሔር መዓት ከሰማይ የወረደበት” ዘመን ነው ብለውታል፡፡ ይህንን ዘመን ሕዝቡ፣ “የክፉ ቀን” እያለ ሲጠራው፣ ሰብዓዊ ቀውሱ የትየሌሌ ነበር፡፡ ገጣሚው እንዲህ ሲል ገልፆታል፤ በዚህ ወቅት ነበር የሞጃ ቤተሰብ ግንባር ቀደም መሪ የነበሩት ደጃች ገርማሜ ለክፉ ቀን ብለው ያከማቹትን እህልና የዘር ሰብል ለሕዝቡ በነፃ የደሉት፡፡ በትውልድ አጥቢያቸው የነበሩትም አለቃ ገብረሃናም ፍትሐ ነገሥቱ በሚያዘው መሠረት፣ ቤተ-ክርስቲያኗ ያከማቸችውን እህልና ገንዘብ አውጥተው ለምዕመናኑ ያደሉት በዚህ ወቅት ነበር፡፡ የደሰው ቀውስና በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጠቅላላ አቋም ላይ የፈጠረው ጫና እጅግ መራራ ነበር፡፡ ነገር ግን በንጉሠ ነገሥቱ ቆራጥ አመራርና በነበሯቸው ቆፍጣና ባለሟሎች ብርቱ ትጋት 1886 እና 87ዓም እንዳያልፉት የለምና አለፈ፡፡ ጣሊያንም በነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደፍልፈል እየተሳበ ከመረብ ምላሽ ወደሰሜንና ደቡብ ትግራይ አቅጣጫ መስፋፋት ጀመረ፡፡ ይህንን ዘመን በአኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ ጥንካሬያችን እጅግ የተፈተንበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዚህ ዘመን ጋር የሚስተካከሉ ታሪካዊ ወቅቶች ካሉም የአህመድ ግራኝ ዘመንና የ1928-1933ዓም የነበረው የወረራ ዘመናት ናቸው፡፡ ያም ሆኖ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እልህ አስጨራሽ ትግልና የአደጋ መከላከል ሥራ ሲከናወን ቆየ፡፡ በመሆኑም፣ ያለማንም ወዳጅ አገር ርዳታና ምጽዋት የሞተው ሞቶ፣ ያለቀውም ከብትና እንሰሳት ሁሉ በየፈፋው ቀርተው በ1887ዓም የበረከት ተስፋ ፈነጠቀ፡፡ በሚያዝያ 1887ዓም ንጉሠ ነገሥቱ ራሳቸው ዶማና አካፋ ይዘው ለበልግ እርሻ ወጡ፡፡ ባለሟሎቻቸውና መሳፍንቱም የእረሳቸውን አርዓያነት ተከተሉ፡፡ በ1887ዓም ገበሬው አረሰ፤ ነጋዴው ነገደ፤ ሸማኔውም ሸመነ፤ ቀጥቃጩም ብረቱን አዘበጠ፤ ወታደሩም ወኔው ተንተገተገ፡፡ የኢትዮጵያውያን የአትንኩኝ ባይነት መንፈስ እንደገና ታደሰ፡፡ “ክፉ ቀን” ኢትዮጵየውያንን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ አንድ አደረጋቸው፡፡ የጣሊያን መንግሥት ሊጠቀመው የሞከረውን ያረጀና ያፈጀ የሮማውያን ከፋፍለህ-ግዛ ስልት መልበስ ተጀመረ፡፡ ለዚህ ደግሞ የግንባር ቀደምነቱን ሚና የተጫወቱት የአፄ ዮሐንስ ልጅ ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው፡፡ ቀጥ ብለው አዲስ አበባ አፄ ምኒልክ ዘንድ መጥተው በብሔራዊ ጥቅምና በሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ ወዛና ፈዛዛ እንደማያሳዩ አረጋገጡ፡፡ ቪቫ ራስ መንገሻ! ቪቫ-ቪቫ! ሌላም መታወስ ያለበት ነጥብ አለ፡፡ የአድዋን ድል ተከትሎ ስለመጣው የኢትዮጵያ ወሰን ጉዳይ ነው፡፡ በግንቦት 1889ዓም ጣሊያኖቹ ከአፄ ምኒልክ ጋር ስለወሰን ጉዳይ እንዲነጋገር ኔራዚኒ የተባለውን መልዕከተኛ ላኩት፡፡ አፄ ምኒልክ ራሳቸው፣ በአንድ ካርታ ላይ የኢትዮጵያን ወሰን አስመልክተው መስመር አሰመሩና ማስመሩም ላይ ማኅተማቸውን አድርገውበት ሲያበቁ፣ “የኢትዮጵያ ወሰን ከዚህ እስከዚህ ድረስ ነው፤” ብለው ለኔራዚኒ ሰጡት፡፡ ከሁለት ወራት በኋላም የጣሊያን መንግሥት የአፄ ምኒልክን የወሰን ካርታ እንደተቀበለው አስታወቀ፡፡ ሆኖም፣ አፄ ምኒልክ አንድ ትልቅ ስኅተት ሠሩ፡፡ ለኔራዚኒ ካርታውን ሲሠጡት ለራሳቸው ቅጂ አላስቀሩም ነበር መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ ፤ ገጽ 148፡፡ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ወሰን በሰሜን-ከኤርትራ፣ በምስራቅ ከሶማሊያ እና በምዕራብም ከሱዳን ጋር እንደላስቲክ እንዳንዴ ሲሳብ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲሰበሰብ አንድ መቶ አስራ አምስት አመታት ተቆጠሩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በ1999 ዓም ባሳተመውና፣ ፊሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም “የሕይወቴ ታሪክኦቶባዮግራፊ ” ብለው በጻፉት መጽሐፋቸው በገጽ-73 ላይ እንደገለጹት፣ “ራስ መኮንንና አፄ ምኒልክ በዘመናቸው የሠሩት ሥራ የሚደነቅ ነው፡፡ ነገር ግን፤ ስህተታቸውን አውሮፓ ለትምህርት ከሔድኩ በኋላ እየገመትኩት መገረሜ አልቀረም፡፡ ይሁን እንጂ፣ የዚያን ጊዜ ዕውቀትና ኃይል በማነሱ ይቅርታ ሊደረግላቸው የተገባ ነው፡፡ እነሱ በደከሙበት ሥራ ብዙ ተጠቅመናል፡፡ በስህተታቸውም አደጋ ተቀብለንበታል፡፡ …የጣሊያን መንግሥት በዐዱዋ ጊዜ ዕውቀቱም ኃይሉም ትንሽ ነበር፡፡ …በእኛ ስህተት አገር-በጁ እንደሆነ ስለቀረ ኤርትራን ማለታቸው ነው፤ ሃምሳ ዓመታት ያህል ቆይቶ ተሰናዳና አጠቃን፤… ” ሲሉ እርር ድብን ይላሉ፡፡ ከፍ ብለውም፣ “ዐዱዋ ላይ ያን ያህል ሰዎች ተላለቁና፣ ጣሊያን የወሰደብንን አገር ሳናስለቅቅ ሄድን፡፡…የድሉን ዋጋ ዐዱዋ ከራስ መኮንን ጋር በዘመትኩ ጊዜ ለመገመቻ የሚሆን ዕውቀት አልነበረኝም፡፡ ኋላ፣ በአውሮፓ መማር ከጀመርኩ በኋላ ግን እያስታወስኩት እንደ እሳት ያቃጥለኝ ጀመር፡፡” እያሉ ስለዐዱዋ ድልና ጥሎት ስላለፈው ጠባሳ ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ ቀደም የፃፍኩት ቢሆንም፣ በውስጥም ሆነ በውጪ የምኒልክን ያህል መስፈሬ-ግርማ የተጎናጸፈ መሪ የለም፡፡ የፈረንጅን ጦር በአዱዋ ጦር ሜዳ ላይ ድል መትቶ፣ ከፈረንጅ መንግሥት ጋር በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የዕርቅና የሰላም ውል የተዋዋለ አፍሪካዊ መሪ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ብቻ ናቸው፡፡ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ ጥበብም ያስመዘገቡት ድል ከአዱዋው ድል ያልተናነሰ ነው፡፡ አራቱ የአውሮፓ ኃያላን ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና እንግሊዝ ኢትዮጵያን ሊቀራመቷት አሰፍስፈው በነበረበት በዚያ ቀውጢ ወቅት፣ ከቅኝ-ግዛት ቅርምት የታደጋት የአዱዋው ድል ብቻ አይደለም፤ የንጉሡ የዲፕሎማሲና የፖለቲካም ጥበብ ነው፡፡ አንዱን በማባበል፤ ሌላውን በማስፈራራት፤ የአንዱን የጥቅም ዝንባሌ አጢኖ ከሌላው ግብዝ ጋር በማጋጨት እርስ-በርስ እንዲፋጠጡ በማድረግ የአራቱንም ኮሎኒያሊስቶች ፖሊሲ እንዳይስማማ አድርገውታል፡፡ ዘንድሮም ደግመን፣ ቪቫ ኢትዮጵያ! ቪቫ ምኒልክ! ልንል እንወደለን፡፡…መልካም የአዱዋ የድል በዓል ይሁንልን፡፡ በ አዲስጉዳይ መጽሔት፣ በቅጽ 8 ቁጥር 205፣ ቅዳሜ የካቲት 22፣ 2006 ዓም ዕት ም ላይ የወጣ ነው፡፡ የኢትዮጵያና የአፍሪካ አኅጉር መናገሻ ከተማ በሆነችው በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ሃውልቶች መካከል፣ አምስቱ በኢትዮጵያና በኢጣሊያን መካከል በ1886ዓም እና በ1928-1933ዓም ለተደረጉት ጦርነቶች የድልና የግፍ መታሰቢያ የታነጹ ናቸው፡፡ አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘው “የአዱዋን ድል” የምንዘክርበትና አራት ኪሎ አደባባይ ላይ የቆመው “የሚያዝያ 27ን የነፃነትና የድል በዓል” ለመዘከር የቆሙ ሁለት ሃውልቶች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ለገሀር የሚገኘው “የይሁዳ አንበሳ” ሃውልት ደግሞ በፋሺስት ኢጣሊያን በ1928ዓም ዘርፎ ተወስዶ የነበረና፣ በጥቅምት 231955ዓም እንደገና ተመልሶ የቆመ ነው፡፡ አሁን በባቡር መስመር ግንባታ ሰበብ የተነሳውና በአምስት ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ የቆመው የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልትም አራተኛው ማሳያ ነው፡፡ አምስተኛውና በቁመት ከሁሉም ጠሚበልጠው ደግሞ፣ በ1951ዓም በዩጎዝሎቫያው ፕሬዝዳንት ማርሻል ዴኒስ ቲቶ ልዩ ድጋፍ እንደገና የቆመው የስድስት ኪሎው “የየካቲት 12ቱ ሰማዕታት” መታሰቢያ ሃውልት ነው፡፡ ሁለት የድል ማብሰሪያ ሃውልቶች፣ እና ሦስት የመከራና የእልቂት መዘከሪያ ሃውልቶች ቆመዋል፡፡ በዛሬው መጣጥፋችንም ስለዚህ ስለአምስተኛው ሃውልትና ሊዘክራቸው ስለቆመው በመቶ ሺዎች ሲለሚቆጠሩት ሰማዕታት ይሆናል፤ መልካም ንባብ እንደሚሆንላችሁ እንመኛለን፡፡ የካቲት 12 ቀን 1929ዓም የዋለው በዕለተ ዓርብ ነበር፡፡ ሩዶልፎ ግራዚያኒ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ረፋድ 4፡00 ሰዓት ላይ፣ ከቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ መልስ በገነተ-ልዑል ቤተ መንግሥት ፊት-ለፊት የዛሬው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ካምፓስ ፏፏቴው ጋር ነው፤ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፡፡ ለነዲያንና ለችግረኞችም ለእያንዳንዳቸው ሁለት-ሁለት ሊሬ እንደሚሰጥ ጭምር አስለፈፈ፡፡ ነገር ግን፣ “ልክ በ4፡00 ሰዓት ይጀምራል” የተባለው ፕሮግራም እስከ 4፡55 ድረስ ሳይጀመር ቀረ፡፡ ሰበቡም የግብፃዊው አቡን፣ አቡነ ቄርሎስ፣ “ታምሜያለሁ! ” ብሎ በመቅረቱበመዘግየቱ የተነሳ ነበር፡፡ እስኪመጣም ድረስ የዕለቱ መርሃ-ግበር ለአንድ ሰዓት ያህል ዘገየ፡፡ ወታደሮች ተላኩና አበኑ ልክ 4፡55 ሲሆን ቤተ መንግሥት ደረሰ፡፡ ወንበር መጣለትና ከግራዚያኒ በስተቀኝ በኩል፣ ከከፍተኛዎቹ የፋሺስት ባለስልጣናትም ጎን ተቀመጠ፡፡ ከግራዚያኒም በስተግራ በኩል ጄኔራል ጋሪባልዲ፣ ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ የአፄ ዮሐንስ የልጅ-ልጅ፣ ራስ ኃይሉየጎጃሙ ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ልጅ እና ከሌሎች ባንዶችም ጋር ተጎልቶ ነበር፡፡ ልክ 5፡00 ሲል ግራዚያኒ ሻኛው እንዳበጠ ኮርማ ቁና-ቁና እየተነፈሰ ኢትዮጵያውያንን ያበሻቅጥ ጀመር፡፡ “ይኼው አለሁ! ሞቷል እያላችሁ የምታወሩትና የምታስወሩት ኹሉ ከንቱ ሟርት ነው፡፡” እያለ የኢትዮጵያን ሕዝብ በገዛ አገሩና በገዛ መሬቱ ላይ ያዋርደው ጀመር፡፡ ግራዚያኒና ተባባሪዎቹ የነበሩበት ቦታ ወደ ራስ መኮንን አዳራሽ መግቢያ በር ላይ ያለው-የቤተ መንግሥቱ በረንዳ ላይ እንደነበር ልብ ይሏል፡፡ ልክ 5፡15 ሰዓት ገደማ ሲሆን አብራሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉት ሁለት የኤርትራ ክፍለ-ሀገር ተወላጆች ከበረንዳው በላይ ባለው ፎቅ ላይግራዚያኒ ከቆመበት ሥፍራ ላይ ጥቁር ሸሚዝ ፋሺስቶች ለባንዶች ያለብሱት የነበረውን ወታደራዊየአስካሪስ ልብስ ለብሰው፣ ኩታቸውን ተከናንበው ታዩ፡፡ ዓይኖቻቸው በንቃት ይንተገተጋሉ፡፡ ልክ 5፡30 ሲሆንም ለነዲያን ምጽዋት መሠጠት ተጀመረ፡፡ በሥፍራው ከሦስት ሺህ ሁለት መቶ 3,200 በላይ ነዲያን ተሰብስበው ነበር፡፡ እንዲሁም ግብር-ሊበሉ የመጡ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ግራዚያኒና ግብረ-አበሮቹ ከቆሙበት ስፍራ በአሥር ወይም አሥራ ሁለት ሜትር ርቀት ላይ ከበው ቆመዋል፡፡ ከሰዎቹም ፈንጠር ብለው ከዘጠና የማያንሱ መትረየሳቸውን የደገኑ ሶላቶዎችና አስካሪዎች በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ነዲያኑን ከበረንዳው አካባቢ ራቅ እንዲሉ ይገፏቸው ጀመር፡፡ ጫጫታና ውካታው ከፍ ብሎም ለአስር ደቂቃዎች ያህል ተሰማ፡፡ ነገር ግን፣ ኢያን ካምፔል ; “ ” ብሎ በ2003ዓም ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ እንደዘገበልን ከሆነ፣ በግምት ከ5፡40 እስከ 5፡45 ድረስ ባሉት አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ተከታትለው ቦንቦች እነአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ካሉበት ደርብ ላይ ቁልቀል ተወረወሩ፡፡ የመጀመሪያው ቦንብ እንደተመረወረ፣ ብዙዎቹ ታዳሚዎች ለስብሰባው ማድመቂያ መድፍ የተተኮሰ ነበር-የመሰላቸው፡፡ ሁለተኛው ሲወረወር ግን፣ አቡነ ቄርሎስና ግራዚያኒ መሬት ያዙ፡፡ በስተ-ግራ በኩልም ያሉት ሁለት ጥበቃዎች ወዲያውኑ ሞቱ፡፡ ሦስተኛውም ሲወረመር፣ ግራዚያኒ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሊገባ ፊቱን አዙሮ መሸምጠጥ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም፣ የሦስተኛው ቦንብ ፍንጣሪዎች አቆሠሉት፡፡ ዳኒሎ ብቢሪንዴሊ የተባው የካሜራ ባለሙያም እየደማና እያቃሰተ የነበረውን ግራዚያኒን ከወደቀበት አንስቶ፣ ከ5፡50 እስከ 6፡00 ባሉት አስር ደቂቃዎች ውስጥ ወደ መኪናው ከተተው፡፡ በፍጥነት ወደ “ኦስፒዳሌ ኢታሊያኖ” “የጣሊያ ሆስፒታል” ለማለት ነው፤ የዛሬው “ራስ ደስታ ሆስፒታል” መሆኑን ልብ ይሏል፤ ወሰዱት፡፡ ከየካቲት 12 ቀን 1929ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓትም ጀምሮ እስከ የካቲት 14 ቀን 1929 ዓም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ድረስ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በግፍ ተፈጁ፡፡ የሚነገረው ቁጥር በአዲስ አበባ ብቻ የተፈፀመውን ግድያ የሚያሳይ ብቻ ነው፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገድምና በዝቋላ አቦ የተረሸኑትም መነኮሳትና ምዕመናን እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በ1934ዓም የመጀመሪያው የየካቲት 12ቱ ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በተከበረበት ዕለት የወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ክስተቱን እንዲህ ሲል ነበር የዘገበው፤ “ያቺን ቀን እናስባት፤ አንርሳት፡፡ የኢትዮጵያ ሰማዕታት የክብር አክሊል የተቀበሉባትን፣ ደማቸው እንደጎርፍ በግፍ የፈሰሰባትን፣ ሥጋቸው እንደክትፎ የተከተፈባትን፣ አጥንታቸው እንደገል የተከሰከሰባትን፣ ዕለተ-ዓርብን፣ ያቺን ቀን አንርሳት! መቼም የዕለተ-ዓርብ መከራና ሃዘን ማለቂያ የለውም! አስቀድሞ፣ ንጹሑ ክርስቶስስ በዕለተ-ዓርብ በ33ዓም አልነበር የተሰቀለው!? የካቲት 121929ዓም ደግሞ ሁለተኛው የንጹኃን ደም በከንቱ የፈሰሰበት ዕለት ኾነ፤” እያለ ይቀጥላል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለም፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት፣ በፋሺስት ኢጣሊያ ስላለቁት ወገኖቻችንና ስለደም ካሳቸው በተመለከተ ጥያቄ ማቅረብ የጀመረው ከ1936ዓም ወዲህ ነው፡፡ ጥያቄውን የበለጠ ፖለቲካዊና ዓለማቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ወደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተቀየረበት የመጀመሪያው ዓመት ላይ፣ በ1938ዓም የኢትዮጵያ መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ሦስት ጥያቄዎችን አቅርቦ ነበር፡፡ “አንደኛ፣ ለኢጣሊያ ፋሺስታዊ መንግሥት ወረራ መነሻ የሆኑት ጥንታዊ ክፍለ-ሀገሮች ኤርትራና ሱማሊያ፣ ለኢትዮጵያ እንዲመለሱላት፤ ” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛ፣ “ለተቃጠሉት አብያተ-ክርስቲያናት፣ ለተበረበሩትና ለተዘረፉት ንዋየ-ቅዱሳት፣ ለተደመሰሰው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብትና ንብረት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በግፍ ለተሰውት ከ750ሺህ በላይ ንጹኃን ኢትዮጵያውያን ሕይወት፣ የኢጣሊያን መንግሥት ካሳ እንዲከፍል ፤” የሚጠይቅ ነበር፡፡ ሦስተኛው ጥያቄ ደግሞ፣ “በኢትዮጵያ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ኹሉ ዓብይ አርእስት ሆኖ የሚገመተው በግራዚያኒ መሪነት የተፈፀመው የየካቲት 121929ኙ ዓም ዕልቂት፣ ከማናቸውም የፋሺስት የግፍ ሥራዎች ኹሉ ከፍተኝነትና ኢ-ሰብዓዊነት ስላለውም፣ ጭፍጨፋው እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት የጦር አዛዦችና ግብረ-አበሮቻቸው በሙሉ፣ ፍርዳቸውን ግፉን በሰሩበት ቦታ እንዲቀበሉና ግፉ ስለተፈፀመባቸውም ወገኖቻችን የደም ካሳ እንዲከፈል ፤” የሚጠይቅ ነበር፡፡ በኹሉምበሦስቱም ጥያቄዎች ውስጥ ገኖ የሚታየው ጥያቄ፣ “የጥቁሮቹ ሰማዕታት” ጩኸት ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ በሚያዝያ 191940ዓም ኢትዮጵያ ያ ን ጊዜ፣ በምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በነበሩት-ክቡር አቶ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አማካይነት ያቀረበችው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፡፡ ይህንም ውሳኔ እንደኔዘርላንድና ኢራን የመሳሰሉት አገሮች በፓርላማዎቻቸው አቅርበው አጸድቀውታልም፡፡ ነገር ግን፣ የኢጣሊያና የሮማንያ መንግሥታት ባቀረቡት ይግባኝ መሠረት፣ ለመንግሥታቱ ዋና ፀሐፊ ባስገቡት ማመልከቻ መሠረት፣ ጉዳዩ እንደገና እንዲመረምር ተደረገ፡፡ ከዚያንም ጊዜ ጀምሮ፣ እስካለንበት ዘመን ድረስ እንደተዳፈነ ነው፡፡ ይባስም ብሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ጭፍጨፋው እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት የጦር አዛዦችና ግብረ-አበሮቻቸው በሞላ የጦር ወንጀሉን በፈጸመበት ቦታሀገር ፍርዳቸውን መቀበል ይገባቸዋል፤” ብሎ ያመለከተውን እግዚኦታ ከቁብም ሳይቆጥሩ፣ ለዚያ የተኩላ ልጅ የሚላኑ መስፍን ብለው ሃውልት አቆሙለት፡፡ ይህ አባዜ፣ የነጩ ዓለም ለጥቁሮች ያለውን ከፍተኛ ንቀትና መዘባበት የሚያሳብቅ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ግዙፍ እውነት ከፊታችን ተገትሯል፡፡ እርሱም የያንኪዎቹና የያፌታውያኑ ናላ፣ ለእኛ ለካማውያን ወንድሞቹ ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ በተከታዮቹ አንቀፆች አማካይነት ላብራራው እወዳለኹ፡፡ ነገር ግን፣ የቦሲኒያውና የሄርዞ-ጎቪኒያው ጉዳይ ሲመጣ ሌላ ሽፋን ይሰጡታል፡፡ የሃይማኖት መለያየት የፈጠረው ጣጣ እንደሆነ ሊሰብኩን ይጣጣራሉ፡፡ አለያም ደግሞ የርዕዮተ-ዓለም ግጭቶች ጣጣ ውጤት እንደተፈጠረ አድርገው ሊያሳምኑን ይፍጨረጨራሉ፡፡ ይህ ዘረኛና ከያፌታዊ ትምክህት የመነጨው አስተሳሰብ ነው፤ በተለያየ ዘመን በከንቱ የተሰውትን ጥቋቁር ሰማዕታት ደመ-ከልብ ያደረጋቸው፡፡ በየትም ቦታ ጥቁሮች ለያፌታውያንና ለአንዳንድ ቡርዣ ሴማውያን አሽከርና አገልጋይ ሆነው የምጽዓት ጊዜ እንዲደርስ ይፈለጋል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችልበት መጠነኛ እድልም አለው፡፡ የካም ቤት ተከፋፍሎና ተበታትኖ ነው ያለው፡፡ ታላቁ ንጉሠ ነገሥታችን አፄ ኃይለ ሥላሴና እነአቶ ከተማ ይፍሩ የተለሙትን አፍሪካንና መላውን የጥቁር ህዝብ አስተባብረን እንዲረዳዳ ማድረግ ካልቻልን ያፌታውያኑ እንደልባቸው ይፈነጩብናል፡፡ አንዳንድ ሴማዊ ቡርዣዎችም፣ እንደባሪያ ፈንጋይ እየሆኑ፣ ሴቶቻችንን ለጭን-ገረድነት፣ ወንዶቻችንንም ለዘበኝነት ይዳርጓቸዋል፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ፣ በአሜሪካንም-ይህ ወር የጥቁሮች ወር ነው፡፡ በአፍሪካ ደግሞ ትልቁ የጥቁር ህዝብ ድል የተበሰረበት የአዱዋም ድል የሚከበረው በዚሁ ወር ነው፡፡ በተጨማሪም ትልቁ የጥቁር ሕዝቦች ኢ-ሰብዓዊ ጭፍጨፋም የተካሄደበት ወር ነው፡፡ በመሆኑም፣ በመላው ዓለም ያሉትን ጥቁሮች፣ በከንቱ ስለቀሩት “ጥቋቁር ሰማዕታት” ጋራ ልንጮኽላቸው ይገባናል፡፡ በሀገራችን የኖረ አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው፣ “በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል፤ ወይም እኩል ነው፤” ይባላል፡፡ የባርነትን ዋጋ ባንቀምሰው ኖሮ፣ የነፃነትን ዋጋና ጣዕምም አናውቀውም ነበር፡፡ በነፃነት ደጃፍ መኖርን የለመደ ሰው፣ ከባርነት ይልቅ ሞትን ይመርጣል፡፡ ለኢትዮጵያውያንንና ለመላው የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች የባርነትን ብርቱ ስቃይ ከሚያሳዩት ቀኖችም አንዱ “የየካቲት 12ቱ የጥቋቁር ሰማዕታት” በዓል ነው፡፡ ከሰባ ስምንት ዓመታት በፊት በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመው ግፍ ያዩት ሰዎች እጅግ ነው የሚያንገፈግፋቸው፡፡ የብሔራዊ ነፃነታችን ምልክት የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን በኢትዮጵያና በአፍሪካ አኅጉር መናገሻ ከተማ በማይውለበለብብት በዚያ የባርነት ወቅት፣ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ እንኳን ከሰላሳ ሺህ በላ ይ ዜጎች አልቀዋል፡፡ ሰንደቅ ዓላማችን በግፍ ወርዶ የፋሺስት ባንዲራ ከተካው አስር ወር እንኳን ሳይሞላው፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ኃዘን ሰፍኖ ነበር፡፡ ህዝቡ አቀርቅሮ መሄድ ጀምሯል፡፡ ኩራት የለም! እራትም አልነበረም፡፡ አለኝታ የለም፤ ገበያና አደባባይም ወጥቶ በሰላም ለመመለስ ዋስትና አልነበረም፡፡ የጥቁር ህዝብ የድል-ብስራት ማወጃ የሆነችው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በባርነት ሥር ሆነው እጅግ ተሳቀዋል፡፡ በባርነት ስር ያለ ህዝብ ማናቸውም ነገር ሊደርስበት ይችላል፡፡ ቢታሰር፣ ቢረገጥ፣ በሰደብ፣ ቢደበደብም ሆነ ቢገደል ለምን ብሎ መጠየቅ አይችልም፡፡ ምክንያቱም፣ በባርነት ቀንበር ሥር ያለ ህዝብ ማናቸውም መዓት ይደርስበታላ! በባርነት ሥር ያለ ህልውና በእርግጥ ምንም ትርጉም የለውም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በነፃነት መኖር ሕይወታችን ነው፡፡ ኑሯችን ነው፡፡ በነፃነት መሥራት፣ በነፃነት ማሰብ፣ በነፃነት መማርና በነፃነት መብትን የማስከበር ልዩ ትዕምርት አለን፡፡ ልዩ ባሕልም አለን፡፡ እነዚህ ከሌሉ ሕይወታችን የለችም፡፡ “ያለነፃነት የምንኖር ከሆንን፣ እንደሮቦት የምንንቀሳቀስ ሕቁራን ፍጡሮች ነን፤” ማለት ነው፡፡ ከዚህ ሕቁርነት ሰውሮን፣ የጥቁሮቹን ሰማዕታት ደም ሕያው ለማድረግ ያብቃን! የኢትዮጵያ ወጣቶች በሦስት መስቀለኛ መንገዶች ላይ ቆመዋል፡፡ የመጀመሪያው መንገድ ከባህልና ከልማድ የተወረሰ ነው፡፡ ዘፈን፣ ቀረርቶና ሽለላም አለው፡፡ አፋሩ፣ “ዳሀር ቦር ናሬ! ” ይላል፡፡ “ግመሎቼና ከብቶቼ፣ እውጪ ማደር ልማዳችሁ ነው፤ እኔም እንደናንተ ጠላቴን ሳመነዥገው ደጅ-አድራለሁ! ” እያለ ይዘፍናል፡፡ ኦሮሞውም፣ “አቢቹ ነጊያ ነጊያ! ” የሚል ዜማ አለው፡፡ የወንድሞችህን ገዳዮች አሰቃይተህ እስከምትገላቸው ድረስ፣ እንቅፋትም አይንካህ! ድል-በድል ያድርግህም! ” የሚል መልዕክት አለው፡፡ የአማርኛ ተናጋሪውም ቢሆን፣ “ጥራኝ ደኑ! ጥራኝ ዱሩ! ላንተም ይሻልሃል ብቻ ከማደሩ! ” እያለ ይሸልላል፡፡ ይህ የሚሆነው እንግዲህ ወጣቱ ያኮረፈ ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱ ሊለያይ ይችላል፤ ነገር ግን፣ ወጣቱ ኩርፊያውን ለመግለጽ የሚጠቀምበት ባህላዊ መንገድ “ሽፍትነትን” ነበር፡፡ አብዛኞቹም ሽፍቶች በአካንዱራ በባህላዊ የጦር ስልት የተካኑና የተፈጥሮ አደጋዎችን መቋቋም የሚችል ተክለ-ሰውነት ነበራቸው ፡፡ የቤተ-ክህነትም ሆነ የዘመናዊ ትምህርት የላቸውም፡፡ ዛሬ ላይ፣ ይሄን ባህልና ልማድ ጠብቆ ለመሄድ የሚያመች ነባራዊ ኹኔታ የለም፡፡ ደኖች ተጨፍጭፈዋል፤ ተቃጥለዋልም፡፡ በሌላም በኩል፣ የዘመናዊ ትምህርትና የዘመናዊ አኗኗር ዘይቤዎች ወጣቱ ባህልና ልማዱን ተከትሎ እንዳይሄድ ደንቃራ ሆነውበታል፡፡ ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች በሚ ሰ ባሰቡባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ኮሌጆች፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጪም ሀገራት ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞአቸውን የማሰማት አማራጭን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ ነገሩ፣ በ19456 ዓም ከኮሪያ ዘመቻ በተመለሱ የክብር ዘበኛ ወጣት መኮንኖችና በቀ ኃሥ ዩኒቨርሲቲ-ኮሌጅ ተማሪዎች አማካይነት እንደተጀመረም ይታወቃል፡፡ ዛሬ ላይ ግን፣ ከኢትዮጵያ ዳር ድንበሮችም አልፎ በወጪ አገራት በሚገኙ የአትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትም ዘንድ ተንሰራፍቷል፡፡ “ጥራኝ ደኑ! ጥራኝ ዱሩ! ” በሚለው ሽለላ ምትክ፣ “ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ! ” ወደሚል ተሸጋግሯል፡፡ ለምን? ከላይ እንደጠቀስነው፣ የደኑ መጨፍጨፍና መቃጠል፣ የወጣቱ በዘመናዊ ትምህርት እያደገ መሄድ፣ የዓለም አቀፉ ተጽዕኖ እያደገ መሄድ፣ የግለኝነት ንቃተ-ህሊና መጎልበትና የተከታታይ ሥርዓቶች ያሰረፁት ፍርሃት ቦቅቧቃነት- ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገጣሚው ኃይሉ ገብረ ዮሐንስን ከ1958-66ዓም ድረስ፣ “ኧረ! የወንድ ያለህ! ” እያለ ያስጮኸው ይኼው የወንድየወኔ ዕጦት ጣጣ ወጣቱ አካባቢ “ስላጣ” ነበር፡፡ ያም ሆኖ፣ ዛሬ-ዛሬ፣ “ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ! ” የሚለው የወጣቶች እንቢተኝነት፣ ከአረቦቹ የፀደይ አብዮት በኋላ የሚጠበቅ ነው ፡፡ በሦስተኝነት የሚመጣው አማራጭ የወጣቶች ብሔራዊ እንቢተኝነት የሚገለጽበት መንገድ ደግሞ ሽብርተኝነት ነው፡፡ ይህንን መንገድ ለመከተል የሚያመች ነባራዊ ሁኔታ የለም የሚሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አጋጥመውኛል፡፡ በግንባር ቀደምትነት የሚመጡት ፕር መስፍን ወማርያም ናቸው፡፡ የእርሳቸውን ንግግሮችም የሚጋሩ በርካታ የግል መገናኛ ብዙኃን ፀሐፍትና አዘጋጆችም አሉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ባላጋራ መሪዎችምተቀናቃኝ የፖለቲካ ማኅበሮችም ከፕር መስፍን አባባል ጋር ይስማማሉ፡፡ “የገዢው ፓርቲ መሪዎችና ካድሬዎች፣ ይኼንን ከኢትዮጵያውያን ባህልና ልማድ ጋር የማይሄድ ቋንቋ የሚጠቀሙት የተቃዋሚ አባላትንና የግል ጋዜጠኞችን ለማሰርና ለማሸማቀቅ እንዲያመቻቸው ብለው ነው፤” ሲሉም ይከራከራሉ፡፡ በእርግጠኝነትም፣ የእነአንዱዓለም አራጌንና የርዮት ዓለሙን እስር ከዚህ ጋር ያገናኙታል፡፡ በ198990 ላይ ተደርገው የነበሩትንም የነዶር ታዬ ወሰማያትና የሌችንም የፖለቲካና የሙያ ማህበራት መሪዎች የእስር ሂደት ያወሳሉ፡፡ በብያኔውና በትርጓሜው ላይ ብንስማማም-ባንስማማም “ሽብርተኝነት” የኢትዮጵያ ወጣቶች ሊሳቡበት ከሚችሉበት የእንቢተኝነት መንገዳቸው አ ን ዱ ነው፡፡ በእርግጥ! አለ ወይስ የለም? የሚለውን ክርክር ለየቅላን ብንተወው ይሻላል፡፡ እስካሁን የተነጋገርንባቸውን ሦስት ሃሳቦች በሌላ ቋንቋ መነጋገር አስፈላጊ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች የተቃውሞና “የአልገዛም ባይነት” እንቅስቃሴዎችን በተጠናከረ ኹኔታ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ እንቅስቃሴዎቻቸውም ሦስት ዓይነት መልኮችን በመያዝ ላይ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የጎዳና ላይ ትዕይንተ-ተቃውሞ ነው፡፡ መነሻውም-መድረሻውም ሰላማዊ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በዋናነት በከፍተኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ይታይ ነበር፡፡ ከዓመት ከመንፈቅ ወዲህ ደግሞ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥ የማይናቅ አቅም አጎልብቷል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፣ የሽምቅ ውጊያ ይዘት አለው፡፡ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ገደማ የኦሮምኛ፣ የሶማሊኛና የአፋርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በእጅጉ ሲለፉበትና ሲደክሙበት ቆይተዋል፡፡ የትግራይና የኤርትራ ወጣቶችም በዚሁ ዓይነት መንገድ “ናጽነት” አገኘን ብለዋል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ፣ ይሄው የሽምቅ ውጊያ የርስ-በርስ ጦርነት አዝማሚያ ወደ ጋንቤላ፣ ወደ ደቡባዊት ኢትዮጵያና ወደ አማርኛ ተናጋሪ-ወጣቶችም ዘንድ ተዛምቶ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ባብዛኛው የኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍሎች ውስጥ መታየት ጀምሯል፡፡ የአኙዋክ ወጣቶች ንቅናቄ አወን፣ የደቡብ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ደወጋን፣ እና የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ አወጋን የሚባሉት ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተመሠረቱ “ወጣት-ተኮር” ድርጅቶች ናቸው፡፡ በሦስተኛው ዓይነት የኢትዮጵያ ወጣቶች ተቃውሞአቸውንና “ያልገዛም ባይነታቸውን” የሚገልጹበት መንገድ በኅቡዕ የመደራጀት አማራጭ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አደረጃጀት መነሻውም-ሆነ-መድረሻው ምስጢራዊ ነው፡፡ ሄዶ-ሄዶም፣ የራሱን የመገናኛ ኮድና የራሱን ጠንካራ የሰው ኃይል አደራጅቶ ወደ ሽብርተኝነት ያድጋል፡፡ በርግጥ! ብዙዎች “የኢትዮጵያ ህዝብ የባህል፣ የሃይማኖትና የማኅበራዊ ኹኔታ ለዚህ አደረጃጀት ለሽብርተኝነት ኔትዎርክ የሚመች አይደለም” ይላሉ፡፡ ከዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች መካከልም ፕር መስፍን ወማርያም ይገኙበታል “አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” የሚለውን መጽሐፋቸውን መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ ኢትዮጵያን የሽብርተኝነት አደጋ እየተጋረጠባት ነው በማለት፣ ገዢው ፓርቲ ወያኔ-ኢህአዴግም ሁለት አዋጆችን አውጥቷል፡፡ አንደኛው “የፀረ-ሽብር ሕግ” አዋጅ ቀጥር 6522001 እየተባለ የሚታወቀው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ “ሽብርተኝነትን በገንዘብና ቁሳቁስ መደገፍን የሚከለክል ሕግ” አዋጅ ቁጥር 7802005 ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊጤን የሚገባው ትልቅ ቁምነገር አለ፡፡ እርሱም፣ ሽብርተኝነት ከባህልና ከሃይማኖት፣ ብሎም ከፖለቲካ-ኤኮኖሚ ጋር አያይዞ አለመመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ ከ1957 ዓም ወዲህ እንዳየነው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች አይሮፕላን የመጥለፍም ሆነ የአቬሽን እንቅስቃሴዎችን የማስተጓጎል ባህልና ዝንባሌ አልነበራቸውም፡፡ ግና፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ኮሞሮስ ደሴቶች አካባቢ በግዳጅ እስካረፈው አይሮፕላናችን ድረስ ኢትዮጵያውያኑ ጉዳት የማድረስ አቅምም ክህሎትም እንዳላቸው ታይቷል፡፡ ነገሩ የዓለም ዓቀፉ ትኩሳትም ማሳያ ነጸብራቅ አካል ነው፡፡ በቀላል አማርኛም የየዘመኑን ፋሽን የመከተልም ዝንባሌ ስበት ተደርጎም ሊወሰድ ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን፣ ወደ ሽብርተኝነትና ወደ ኅቡዕ መዋቅሮች ውስጥ ሊገቡ የሚችሉት ወጣቶች ከአንድ ከተወሰነ ሃይማኖት፣ የኤኮኖሚ መደብ፣ ከሆነ ዘርብሔር፣ አለያም ደግሞ ከአንድ የማኅበራዊ መድሎ ከደረሰበት ክፍል ብቻ አድርጎ ማሰላሰሉ አያዋጣም፡፡ ወደ ሽብርተኝነቱ ጎራ ለመቀላቀል የሚፈልጉ ወጣቶች ካሉ የሚከተሉት ሦስት አማራጮች ምቹ መደላድሎች ይሆኗቸዋል፡፡ 1ኛ የፖለቲካ-ኤኮኖሚው የሚፈጥርባቸው ኩርፊያ ነው፡፡ በዚህ በኩል ደግሞ፣ ገዢዎቻችን እንደሚነግሩን ሳይሆን ስር-የሰደደ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ዱካክ ወጣቱን አስኮርፎታል፡፡ መሥራት ከሚችሉት መካከል 45% በመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ወጣቶች ሥራ-አጥ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ችሎታውና አቅሙ እያላቸው በክልል መንግሥታትና ሹመኞች ፖለቲካዊ በሆነ አድሎና መድሎ ለሥራ-የደረሱ እጆቻቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ጉዳይ ፖለቲካዊ በመሆኑና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውም ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ ከፍተኛ ኩርፊያን አስከትሏል፡፡ ኩርፊያውም እያደገ ወደ ከባድ የተስፋ መቁረጥን ደረጃ በመድረስ ላይ ይገኛል፡፡ 2ኛው ችግር ደግሞ ከወጣቱ ንቃተ-ኅሊና ጋር የማይሄድ የገዢዎቹ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ገዠዎቹ “ወጣቱ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢ ነው፤” እያሉ ሲሸነግሉት ኖረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ወጣቱ “የአሁኒቷም ኢትዮጵያ ባለድርሻ ነኝና የሚገባኝን ድርሻዬን አምጡ፤” በማለት ላይ ይገኛል፡፡ የገዢዎቹ “ወደፊት ጠብቁና” የወጣቶቹ “አሁኑኑ አምጡ” ንትርክ ማቆሚያም ያለው አይመስልም፡፡ ስለሆነም አስገድዶ ድርሻን ለመንጠቅ የሽብር አማራጭ ሊከተል ይችላል፡፡ ዛሬ፣ ተደራጅተው የልጃገረዶችን ተንቀሳቃሽ ስልኮችና ጌጣጌጦች ከመንጠቅ አልፈው፣ ትልልቅ የኮንተራባንድና የዕጽ-ማዘዋወር ተግባራት ላይ ኔትወርክድ ሆነው ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ ሦስተኛ3ኛው ነጥብ ደግሞ፣ የወጣቶቹ በዘመን አመጣሽ አስተሳሰቦች መማረክና በባዕዳን ኃሎች የመጠለፍ እድላቸው እያደገ የመሄዱ ጉዳይ ነው፡፡ በ1960ዎቹ የነበሩት የኢትዮጵያ ወጣቶች በኮሚኒዝም አስተምህሮዎችና መሪዎች እንደተሳቡት ሁሉ፣ ያሁኖቹ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅና በሩቅ ምስራቅ አካባቢ ባሉ የኅቡዕ ድርጅቶችና መሪዎች ሊማረኩ የማይችሉበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ይህ የስሜት የ ጉዳይ ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ፣ በአሁኑ ሰዓት ድንበር-ዘለል የኅቡዕ ድርጅቶ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጉርሻና ጠቀም ያለ ክፍያን ለወጣቱም ሆነ ለቤተሰቡ ይከፍላሉ፡፡ ይህ ማበረታቻም ከስሜት ድጋፍ ሰጭነታቸው ባሻገር፣ ሳቢና ማራኪ ነው፡፡ ይህንን የሽብር አማራጭ ሳይጠቀሙ የተሻለና እጅግ አመርቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለው መንገድ የትኛው ነው በሚለው ላይ የበለጠ መነጋገር፤ መወያየትም የተገባ ነው፡፡ ከ“ጥራኝ ደኑም ሆነ ከሽብሩ መንገድ” ይልቅ “የጥራኝ ጎዳናው! የጥራኝ መንገዱ! ” አማራጭ እጅግ አዋጪ ነው፡፡ የህንን የምለው የግብጽን፣ የቱኒዚያንና የሌሎችን አረብ አገር “የፀደይ ወራት! ” ብሔራዊ እንቢተኝነት እንድገም ለማለት አይደለም፡፡ በዚህ አመለካከቴም፣ ከልጅ ተመስጌን ደሳለኝና ከተወሰኑት ባልደረቦቹ የተለየ አቋም ነው ያለኝ፡፡ እነርሱ፤ “መስቀል አደባባይን የጣህሪር አደባባይ እናደርጋታለን” የሚል ሃሳብ ያንፀባርቃሉ አዲስ ታይምስ መጽሔት፣ 2005ዓም፣ ቁጥር-3ን ይመልከቱ፡፡ የምለው፤ በ1966እና በ1983ዓም እንዳደረግነው፣ ሕዝባዊ እንቢተኝነታችንን ለታጣቂ ኃይሎች ላለማስከብ፣ በቅድሚያ ጠንክረን መሥራት ይገባናል ነው፡፡ የመጀመሪያው ሥራ፣ ወጣቱንና ሕዝቡን በተሳካ ኹኔታ በማደራጀት ነው፡፡ ከገጠር እስከ ከተማ ድረስ ጠንካራና ሰላማዊ የሆነ ድርጅት መሥራት የግድ ይላል፡፡ ከገዢው ፓርቲ ጋር የሚደረገውም ትንቅንቅ ቀላል አይሆንም፡፡ ያንን ተቋቁሞ የተሳካ አደረጃጀትና ታዓማኒነት ያለው የፖለቲካ አመራር ማዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡ “ሥልጣን” የምትባለውን ጉደኛና አደገኛ “ሰይጣንም” ለመያዝ፣ በወታደሩና በፀጥታ ኃይሎች አካባቢ የሰላማዊ ታጋዮቹ አላማና ርዕይ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያለመታከት መሥራትን ይጠይቃል፡፡ የወጣቶቹ ሰላማዊ አደረጃጀትና ተዓማኒነት ያለው አመራር ዕውን ከሆነ፣ በወታደራዊውም ሆነ በፀጥታና በደኅንነቱ አካላት ዘንድ ያሉትን በመቶ ሺ የገመቱ ወጣቶችን ልብ ለማሸፈት አቅም ይኖረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚዳጁት ወጣቶች ያሏቸውን የተለያዩ የመገናኛና የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች ይበልጥ ጠንካራና የማይታወኩ አድርገው መሥራት አለባቸው፡፡ ለዚህም ተግባር የሚያግዙ በርካታ በጎ ፈቃደኞችንና የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞችን የሚያገኙ የቴሌ፣ የፖስታ፣ የመንገድ ትራንስፖርት፣ የአቬሽንና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ከወዲሁ ማዘጋትም የግድ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉትንና በተለያዩ ኤጀንሲዎች ተጽፎ የሚሰጣቸውን መግለጫና ዜና ለእጀራቸው ብለው የሚያቡትን የሚያነበንቡትን ጋዜጠኞች መጥላቱም ሆነ ማጥላላቱ ጊዜ ማጥፋት ነው፡፡ ከእነርሱ ይልቅ፣ ከኋላ ሆነው የሚያቅዱትና ስልቶችን የሚነድፉት “ጎበዞችና ጎበዛዝት” ላይ ማተኮሩ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ሃሳብ ወደ አንድ አቅጣጫ ይመራናል፡፡ ወጣቱ ያለውን ውሱን ጥሪትና የሰው ሃይል በሚገባው ቦታና ሰዓት አውሎ፣ ትግሉን አስተማማኝና እጅግ ሰላማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ከፈለገ፣ የሚያተኩርባቸውን “ጎበዞችና ጎበዛዝት” ማንነት፣ አድራሻ ቦታ፣ የዘወትር እንቅስቃሴያቸውንና የእነማን ወዳጅና ጠላት እንደሆኑ ኹሉ አብጠርጥሮ ማወቅ አለበት፡፡ እነማን የንግድ ሸሪኮቻቸው እንደሆኑ፣ እነማንስ ቂመኞቻቸው እነደሆኑ ከወዲሁ ለይቶ ማወቅ ይገባዋል፡፡ ይህንን ማድረጉ ለሁለት ነገሮች ይጠቅመዋል፡፡ አንደኛ፣ እባብ ተይዞ በትር ስለማይፈለግ ነው፡፡ በእርግጥም፣ ለፍርድ መቅረብ ያለባቸውን ከሌለባቸው ለመለየት ስለሚበጅ ነው፡፡ ሁለተኛ፣ “መረጃ አይናቅም፣ አይደነቅም! ” ከሚለው መርሆም በመነሳት ነው፡፡ ለብሔራዊ እንቢተኝነት የሚዘጋጁትን ወጣቶችና ደጋፊዎቻቸውን እነማን እያሳደዷቸው እንደሆኑና እነማንስ ያላግባብ በህዝብና በሀገር ክብር ላይ እየቆመሩ እንዳሉ ማወቁ በራሱ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ ክፍል-2ን ሳምንት ይጠብቁ፡፡ ባለፈው ሳምንት በወጣው የአዲስ ጉዳይ ቅጽ 7፣ ቁጥር 150 የካቲት 2 ቀን 2005 ዓም ዕትማችን ላይ ወይም ደግሞ 201306- ስለሐረርነት እና ስለጎንደርነት ተናግረን ነበር፡፡ በዚህ ዕትማችን በቁጥር 150ኛው ላይ ደግሞ ስለ“ጎንደርነት እና ሐረርነት” እንጽፋለን፡፡ ባለፈው ዕትማችን ላይ እንደገለጽነው ስለጎንደርነትና ስለሐረርነት ማውራት ማለት ስለጎንደሬዎች እና ስለሐረሮች ማውራት ማለት አይደለም፡፡ ልናወሳ የምንፈልገው፣ ስለጎንደር እና ስለሐረር ስለቦታዎቹ ነው፡፡ በመሆኑም፣ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ በምናነሳቸው አንኳር- አንኳር ነጥቦች፣ የዛሬዎቹን ሐረሮች እና ጎንደሮች እያሰብን አልጻፍነውም፡፡ እንዲያውም ፍላጎታችን፣ ከደርግ መራሹ ወያኔ-ኢህአዲግ መምጣት በፊት ስለነበሩት ጎንደር እና ሐረር ለመዘከር ነው፡፡ በመሆኑም፣ አንዳንድ ነጥቦችን ስታገኙ በቀጥታ ከዚህ ዘመንና ከዚህ ወቅት ጋር ባታናጽሩት ይመከራል፡፡ ካነጻጸራችሁትም፣ የእናንተ የአንባቢያኑ ነፃነት እንጂ የጸሐፊው ፍላጎት አለመሆኑን ልብ ይሏል፡፡ የ“ጎንደርነት” ኩራት በዋናነት የነገሥታቱ አብያተ-መንግስታት እና ከጢስ ዐባይ አጠገብዝቅ ብሎ ያለው፣ “የአፄ ፋሲል ድልድይ” ወይም “የዕንቁላል ድልድይ” ነው፡፡ ያሬድ ግርማ ኃይሌ የተባሉ ፀሐፊ በ1999 ዓም ባሳተሙት “ የጎንደር ታሪክ፣ ከኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር” በሚለው መጽሐፋቸው እንደገለጹት፣ “አፄ ፋሲል፣ የተለያዩ የእደ ጥበብ ሙያ ያላቸውን፤ የሽመና፣ የግንብ ሥራ፣ የብረታ ብረት ሥራ፣ የአንጥረኝነት፣ የኖራ አቡኪ፣ ሸክላ ሠሪዎችን፣ ኮርቻ ሠሪዎችን፣ እና ወዘተ… ከተለያዩ ቦታዎች አሰባስበው በቤተ መንግሥቱ ዙሪያ አስፍረው ማሠራት ጀመሩ፤” እያለ ይቀጥላል፡፡ ደራሲው ያሬድ ግርማ ዋናውን ምስጢር አልተናገረም፡፡ ዋናው ቁምነገር፣ እነዚህ የስነ ሕንጻና የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች “ከየትኞቹ የተለያዩ ቦታዎች ነው አሰባስበው ያመጧቸው? ” የሚለው ነው፡፡ “ከተለያዩ ቦታዎች” የሚለው ሃረግ አሻሚ ነው፡፡ “ከሀገር ውስጥ ነው ወይስ ከውጭ አገር? ” የሚለውን አያሳይም፡፡ “ፋሲል ይንገስ! ሃይማኖት ይመለስ! ” ተብሎ ፋሲል ሲነግስና አባቱ አፄ ሱስንዮስም በአዋጅ ቀይሮት የነበረው ካቶሊክነት ተወግዶ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሲመለስ፣ “አፄ ፋሲል ሙሉ ለሙሉ ፖርቹጋሎቹን ከኢትዮጵያ አስወጥቷቸዋልን? ” ወይስ “የተወሰኑ የስነ-ሕንጻ ባለሙያዎችን መርጦ አስቀርቶ ነበር? ” “የፋሲልየእንቁላል-ድልድይ” የሚባለውንስ ከጢስ ዐባይ ዝቅ ብሎ የሚገኘውን ድልድይስ ማነው የገነባው? ” በዕርግጥ፣ ኢትዮጵያውያን ናቸውን ወይስ ከክርቶፎር ዳጋማ ጋር የመጡት 400ዎቹ ፖርቹጋሎች መካከል የስነ-ሕንጻና የድልድይ ሥራ መሃንዲሶችም መጥተው ነበር? ” እነዚህንና እነዚህን መሠል ጥያቄዎች ደህና አድርገን እንዳናገኝ ያገደን፣ የአፄ ፋሲል ዜና መዋዕል ያለመገኘቱ ጉዳይ ነው ሥርግው ኃብለ ሥላሴ 1957፤ አፄ ምንሊክ የአዲሷ ኢትዮጵያ ስልጣኔ መስራች ፤ ገጽ 47-8፡፡ በተመሳሳይ መልኩም፣ የ“ሐረርነት” ኩራት የሆነው የጀጎል ግንብና በውስጡም ያሉት መኖሪያ ቤቶች ናቸው፡፡ አረብ ፋቂህ የተባለው ፀሐፊ በፃፈውና ሬኔ ባሴት በተረጎሙት “ፍቱሕ አል ሀበሽ” በተባለው መጽሐፍ ላይ በገጽ 168 እንዳሰፈረው ከሆነ፣ “በ1540-42 ባሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ አሚር ኑር ኢብን ሙጃሂድ፣ 481,812 ሜትር ካሬ ያለውን የጀጎል ግንብ፣ ከክርስቲያኖችና ከኦሮሞዎችም እየተከላከለ ሐረርጌ ተቀምጦ በሚያስተዳድርበት ጊዜ፣ ከተማዋ ሐረር የወረራ አደጋ እንዳይደርስባት ዙረያዋን በግንብ አሳጠራት” ይላል፡፡ ባሳየውም መልካም አስተዳደርና ባሠራውም በዚህ ግንብ የተነሣ በዘመኑ በነበሩ የእስልምና ተከታዮች ዘንድ እንደጻድቅ የሚቆጠር መልካም አሚር መስፍን እንደነበረ፤ በዘመኑ ከነበሩት ታሪክ ፀሐፊዎች መኻከል እነአቡበከር ኢብን መሐመድ አልዊ ሰንባልም ያረጋግጣሉ፡፡ ነገር ግን፣ በግራኝ ዘመን የመጡትና ከልብነ ድንግል እንዲሁም ከገላውዲዮስ ጋር ለአህመድ ግራኝ ወግነው ይዋጉ የነበሩት የቱርክ ወታደሮች፣ በአሚር ኑር ዘመን ሙሉ ለሙሉ ከሐረር ይውጡ ወይስ አይውጡ፣ አረብ ፋቂህም ሆነ እነአቡበከር መሐመድ አይገልጹም፡፡ ምናልባትም፣ መድፍና ዐረር ይዘው ከቱርክ የመጡት ሙጃሂዲኖች መካከል የተወሰኑት የስነ-ሕንፃና የግንባታ ባለሙያዎች የነበሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ይኼንን የሚያሰኘውም፣ ከአሚር ኑር በኋላ፣ ሌላ ተመሳሳይ ጀጎል ወይም ግንብ በቅርብ እርቀት ላይ ወይም የወላስሞች መናገሻ በሆነችው ሰመራ ወይም ሚሌ አካባቢ እንኳን አለመሰራቱን ስለምናውቅ ነው፡፡ የጎንደርንም ሆነ የሐረርን ግንባታዎች ማንም ሠራቸው ማንም፣ ትልቁ ቁምነገር ያለው “ማን አሰባቸው? ” የሚለው ጥያቄ ላይ ነው፡፡ የጎንደርን እና የሐረርን ግንቦች ከሠሯቸው ግንበኞች ይልቅ፣ “ሐረር እና ጎንደር በግንብ መታጠር አለባቸው! ” ብለው ያሰቡትና ያቀዱት አሚር ኑርና አፄ ፋሲል ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ለመገንባት ሲነሱም ከጎናቸው ሌሎች ሕዝቦችና ወገኖች ነበሩ፡፡ ጎንደርነት የተገነባው የሸዋን፣ የወሎን፣ የጎጃምንና የጎንደርን እንዲሁም የትግራይንና የባሕረ-ነጋሽን ሕዝብ ግብር በመቀበል ነው፡፡ “ፃዲቁ ዮሐንስ” እየተባሉ ከሚጠሩት፣ ከአፄ ዮሐንስ 1ኛ 1659-1674 እና ከመናኒው ንጉሥ አድያም ሰገድ እያሱ በስተቀር፣ ሌሎች ነገስታት ከፍተኛ ግብር ይሰበስቡ ነበር፡፡ ያንንም ግብር ለአብያተ-ክርስቲያናትና ለአበያተ-መንግሥታት መሥሪያ አዋሉት፡፡ በተለየ መልኩም፣ አሚር ኑርና ቀዳሚው ኢማም አህመድ ግራኝ፣ ከሸዋ፣ ከወሎ፣ ከጎጃም፣ ከጎንደር፣ ከትግራይና ከደቡብ ኢትዮጵያ አብያተ-ክርስቲያናትና የነገሥታት አምባዎች በበዘበዙት ሀብትና ቅርስ የራሳቸውን ግንብ፣ ለራሳቸውና ለሕዝባቸው ሠሩበት፡፡ ዞሮ ዞሮ፣ “የጎደርነት ኩራት” የሆነውም የፋሲል ግንብ ሆነ፣ “የሐረርነት ኩራት” የሆነው የጀጎል ግንብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብትና ንብረት እንጂ የጎንደሬዎች ወይም የሐረሬዎች ብቻ አይደሉም፡፡ ሊሆኑም አይችሉም፡፡ የሚያሳዝነው የኢትዮጵያውያን ሀብትና ንብረት በግብርም ሆነ በዘረፋ ሲበዘበዝ ኖሮ፣ ላለፉት አራት መቶ ሃምሳ ዓመታትና ከዚያም በላይ ለሚሆኑ ዘመናት፣ ሌላ የመሳፍንትና የሕዝብ መኖሪያ የሆነ “የጀጎል ግንብ” እና ሌላ የነገሥታት መናገሻ የሆነ የ“ፋሲል ግንብ” አለመሥራታችን ነው፡፡ በጥር 1879 ዓም የእስልምና መናኸሪያዋ ሐረር፣ በክርስቲያኖች መዳፍ ውስጥ ገባች፡፡ በአፍጋኒስታን ታሊባንን መራሹ የአሜሪካን ጦር ሐሚድ ካርዛይን ፕሬዝዳንት ብሎ እንዳነገሰው ሁሉ፣ በሐረርም ግፈኛውን አሚር መሐመድ ኢብን ዐሊን በሕዝቡ ትብብር ያስወገደው የግብፁ ቄሳራዊ ጦር ሐረርን ለቆ በ1878 ሲወጣ አሚር አብዱላሂን አንግሦ ወጣ፡፡ ከሸዋ በዘመተው ጦር የተሸነፈው የአሚር አብዱላሂ “ፈሪ የናቱ ልጅ ነው! ” ብሎ ወደሶማሊያ ፈረጠጠ፡፡ አፄ ምንሊክም፣ ሁሉም የያዘውን ሃይማኖት ሳይቀይር “ሃይማኖት የግል፣ አገር የጋራ ነው! ” ብለው አዋጅ ስላስነገሩ፣ እስልምና የሐረርነት የተከበረ ሃይማኖት ሆኖ ቀጠለ፡፡ አንዲትም መስኪድ ያለዲፕሎማሲያዊ ድርድርና ታክቲክ አልፈረሰም፡፡ በጀጎል ውስጥ ያለውን ዋና መንገድ “አንደኛ መንገድ” ይባላል ለማውጣት ሲስማሙ የአሚር አብዱላሂ አጎት አቡበከርና ሌሎች የሐረር ሽማግሌዎች ከምንሊክ ጋር ፊት-ለፊት “በሰጥቶ መቀበል መርህ” ተደራድረዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን፣ በጥር 1880 ዓም ወደ ጎንደር የገሠገሠው ጂሃዳዊው የደርቡሽ ጦር፣ የጎጃሙን ንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን አሸንፎ፣ ጎንደርን በዘበዛት፤ አቃጠላት፡፡ ከአርባ-አራቱ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አራቱ ብቻ በተዐምራት ተረፉ፡፡ አርባዎቹ ሙሉ ለሙሉ ወደሙ፡፡ በርካታ ክርስቲያኖች ተማርከው በመተማ በኩል ወደሱዳን ተወሰዱ፡፡ “ አይታሰስም ምጣድ በግምጃ፤ ዘንድሮ ደርቡሽ መጽረፉን እንጃ! ” ብሎ ፎክሮ ሄዶ የነበረው የጎጃም ጦር ክፉኛ ተመታ፡፡ ወታደሩም ተፈታ፡፡ የሞተው ሞቶ፤ የሸሸውም ፈርጥጦ፣ የተያዘውም ተማረከ፡፡ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖትና ጥቂት አዛዦቹም ምንትዋብ የምትባለውን የተክለ ሃይማኖትን ሁለተኛ ሚስት እንኳን ሳይዙ ሸሽተው አመለጡ፡፡ ለዚህም ነው፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት በጎንደሬዎች ዘንድ “አትከልክልሞይ ተክለ ሃይማኖት፣ ይዘህ አለንጋህን፤ አሞራ ደርቡሽ ሲበላው የገዛ ገላህን ምንትዋብህን! ” ተብሎ የተወቀሰው፡፡ ሐረርነት ውስጥ “ሃይማኖና ሀገር” የተለያዩ መሆናቸው ተስተውሎ ሐረር ከጥፋትና ከቃጠሎ ስትድን፤ ጎንደርነት ውስጥ ግን “ሃይማኖትና ሀገር አንድ ናችሁ! ” ተብለው፣ በአንድነት ተገደሉ፤ ተቃጠሉ ተክል ጻድቅ መኩሪያ 1982 አፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት ፣ ገጽ 292 እና 450-451 ላይ ይመልከቱ፡፡ ሌላው ጎንደርነትን እና ሐረርነትን የሚያመሳስላቸው የጣሊያን ወረራ ነው፡፡ ጣሊያን ከወረራው ሦስት ዓመታት ቀደም ብሎ በሐረርና በጎንደር ላይ ቆንስላ ከፍቶ ነበር፡፡ ሕዝቡንም በስኳርና በሳሙና፣ በፓስታና በሹታ እርዳታ ስም መደለል ጀምሮ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎችንም ልብ አሸፍቶ ነበር፡፡ በተለይም የወጣቶችን ልብ አማልሎ ነበር፡፡ መንግሥቱ ለማ፣ “ኧረ ሄደ-ሄደ፣ ሄደ ኮበለለ፤ በስኳር ብስኩት እየተደለለ! ” ያሉት ነገር ለዚህም ጊዜ ይሠራል፡፡ ጥሊያን ሲኒማ ቤቶችን ያሠራው ከ1927 በፊት ነበር፡፡ ለወጣቶቹም የፋሺስትን መርዘኛ ፊልሞች ማሳየት ጀምሮ ነበር፡፡ “ባሊላ” የተባሉትም የፋሺስት ትምህርት ቤቶች በሐረርና በጎንደር ተከፍተው ነበር፡፡ የሐረሩ ልዑል ራስ መኮንን ትምህርት ቤትን ለወንዶቹ ልጆች፤ የወይዘሮ የሺ እመቤትን ትምህርት ቤትንም ለሴቶች ያሠራው በወረራው ወቅት ነበር፡፡ ዛሬ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች በሌላ መጠሪያ ስም ነው የሚታወቁት፡፡ በጎንደርም፣ የፋሲለደስ ትምህርት ቤትን ሕንጻ ገንብቶ በርካታ ወጣቶችን ለፋሺስታዊ እኩይ ተግባሩ እያዘጋጃቸው ነበር፡፡ ጣሊያን ከሐረር 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን ጠመዝማዛ የደንገጎ መንገድ ለወታደርና ስንቅ ማመላለሻ በ182728 ሲሠራው፤ ከደባርቅ ወረድ ብሎ ያለውንም የሊማ-ሊሞን ጠመዝማዛ መንገድ ለተመሣሣይ ዓላማ ከ1927-1929 ዓም ባሉት ጥቂት ዓማታት ውስጥ አጠናቋቸዋል፡፡ ጎንደርነት፣ በደርግ ዘመን ክፉኛ በቀይ ሽብር ቸነፈርና አለንጋ ተመቶ ነበር፡፡ ግፈኛው መላኩ ተፈራ የጎንደርን ወጣቶች ለሶሻሊዝም ባዕድ ርዕዮት-ዓለምአምልኮው ሲል አስፋልት ላይ ረፈረፋቸው፡፡ የጎንደሩ ሰው መላኩ ተፈራ በገዛ ወገኖቹ ላይ ከኔሮና ከግራዚያኒም የማይተናነስ ጭካኔ አሳየ፡፡ ጎንደርነት ከፍተኛ አደጋ ተጋረጠበት፡፡ የጎንደር ወጣቶች በበረሃ እያሳበሩ ወደሱዳን ተመሙ፡፡ አንዲት ጎስቋላ እናት “መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም፤ የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም! ” ያለችው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ በአንፃሩ፣ ሐረርነት በብዛት በቀይ ሽብር አልተጎደም፡፡ በመጠኑም ቢሆን ግን በተለይ የአማርኛና የኦሮሚኛ ተናጋሪ ወጣቶችን ገሏል፡፡ በኮሎኔል ዘለቀ በየነ ይመራ የነበረው የቀይ ሽብር ገዳይ ግብረ-ሃይል በርካታ ወጣቶችን ያለ ፍርድ ገድሏል፡፡ ብቻውን አልነበረም፡፡ የሐረር ተወላጆቹን እነአዲል አሊን ይዞ ነበር፡፡ አዲል አሊ፣ ኢህአዲግ በግንቦት 26 ቀን 1983 ዓም ሐረርን ሲቆጣጠር ፈርጥጦ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ተቀመጠ፡፡ የሐረር ወጣት የሚሰደደውም በጅቡቲ በኩል ነበር፡፡ ብዙ ወጣቶች እግሬ አውጭኝ ብለዋል፡፡ ብልጦቹም፣ “ቪቫህ ደርጎ-ቪቫህ ደርጎ! ይገባሃል ወተቲና ኢርጎ! ” ብለው ዘፍነው ዘመኑን አጎንብሰው በጥበብ ተርፈዋል፡፡ ሐረርነት እና ጎንደርነት ብዙ ልጆች በውጭ ሀገራት ስላሏቸው፣ ከውጭ የሚላክ ዶላር ና ወርቅ አላጡም፡፡ ዛሬ አቦከርና አዘዞ የሚገነቡት ምርጥ ምርጥ ቪላዎች ከውጭ አገር በሚላኩ ገንዘቦች መሆኑን ማስታወስ ይገባል፡፡ ከሼክ አባድር ዘመነ ጀምሮ እስልምና በጎንደር እና በሐረር ፀንቶ የቆየ ነበረ፡፡ የሼክ አባድርን በረከት ለማግኘት ለመዘየር አንድ ሺህ ኪሎ ሜትሮች በላይ ተጉዘው የጎንደር እስላሞች ሐረር ይመጡ ነበር መርደቻይ አብር፤ ኢትዮጵያ፤ በዘመነ መሳፍንት ባለው መጽሐፉ እንደገለፀው ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ በነዚህ ጎንደሬዎች ድካም ያዘኑት ሼክ አባድር፣ የብረት ዘንጋቸውን አርቀው ሲወረውሩት ተሰወረ፡፡ ከጎንደር ለመጡት በረከት ፈላጊዎችም እንዲህ አሏቸው፤ “ሂዱ፣ ይሄንን ዘንጌን ከአንገረብ ወንዝ ማዶ ታገኙታላችሁ፡፡ እዚያ ሆናችሁ ጸልዩ፡፡ እዚህ ሐረር ያለውን በረከት ሁሉም እዚያው ጎንደር ታገኙታላችሁ! ” አሏቸው፡፡ መንገደኞቹም ዝየራቸውን ፈጽመው ተመልሰው ጎንደር ሲገቡ ዘንጉን ፈለጉት፡፡ ከአንገረብ ወንዝ ማዶም ተሰክቶ አገኙት፡፡ ዘንጉም ሲነቀል ቅዱስ ውሃ ፈለቀ፡፡ በአው አባድርም ትዕዛዝ ሐረርነትና ጎንደርነት አንድን በረከት እየተካፈለ፣ በ1,101 ኪሜትር ርቀት ላይ በየፊናው ሥልጣኔውንና ባሕሉን ሲከተል ለዘመናት ኖረ፡፡ ያንን ቦታ ከ1966 ዓም በፊት ልዕልት ተናኘ ወርቅ፣ የአባድር እርሻ ልማት ብላ ለበጎአድራጎት ስራ ታሳርሰው ነበር፡፡ ደርግ መጣና በ1967 ዓም ለሕብረተሰቡ ጥቅም ወረሰው፡፡ በጎንደርነት እና በሐረርነት መካከል ያለውን ዋነኛ የመንፈስ ልዩነት ማውሳት ያሻል፡፡ ልዩነታቸውም የተገነባው አው አባዲር አትመላለሱ ስላሏቸው ሳይሆን፣ ከግንቦቻቸው እና ከቅጥሮቻቸው አሠራር ጋር በተገናኘ ነው፡፡ የሐረርነት እና የጎንደርነትም ፖለቲካዊ ፍልስፍና የሚያጠነጥነው እዚህም ላይ ነው፡፡ ሐረርነት በአሚር ኑር አማካይነት የሐረርን ጀጎል ሲገነባ፣ ለአሚሮቹ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡም ደኅነነትና ሰላም መጨነቁንና መጠበቡን ያሳያል፡፡ “በአሚርነት ክብርና” በተራው “የሐረር ሕዝብ ክብር” መካከል የሠፋ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ልዩነት እንዳይኖር አድርጎ ወጠነው፡፡ በዚህም የተነሳ እስከ ዘመናችን ድረስ እንደምናየው፣ ሐረርነት ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሕዝቡ የስነ-ልቦና ትስስር በጣም የተራራቀ አይደለም፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ በቀላሉ በአይን ጥቅሻ ፍጥነት ከፍተኛ መግባባትና መተማመን ይታያል፡፡ መስኪዶች እና ሕንጻዎች በያመቱ በረመዳን ወር ይታደሳሉ፡፡ የፈረሰና የተደረመሰም ካለ በሕዝቡ ትብብር ይገነባል፡፡ ይህም ነገር ለመጤዎችና ለአንዳንድ ጉዳዩን በቅጡ ለማይረዱት ሰዎች “ዘረኝነት ወይም ጠባብነት” ይመስል ይሆናል፡፡ ግን አይደለም፡፡ ላለፉት 450 ዓመታት ያህል “ለሐረርነትና ለደኅንነት አስፈላጊ ነው” ተብሎ የተያዘ የኑሮ ዘዴ ነው፡፡ ሐረርነትን ከኦሮሞዎችና ከሌሎችም የጦርና የባህል ወረራዎችም የታደጋትም ይኼው ሕዝባዊነቷ ነው፡፡ በአንፃሩ፣ ጎንደርነት በአፄ ፋሲል አሳቢነት ስትገነባ የነገሥታቱን እና የሕዝቡን ልዩነት በጉልህ አስምሮበት ነው፡፡ ነገሥታቱ በረጃጅም ግንብ በታጠረውና በምቹ ሁኔታ በተሠራው ቅንጡ ቤተ-መንግሥታቸው ሲኖሩ፣ ሕዝቡ ግን ከግንቡ ውጭ በጎጆ ቤት እንዲኖር ተደርጓል፡፡ ነገሥታቱ ከሕዝባቸው ደኅንነት ይልቅ የራሳቸውን ክብር አስበልጠዋል፡፡ በዚህም የተነሳ፣ በ1880 የመጣውን የደርቡሽ ጦር ሕዝቡ በትጋት ሳይከላከለው ቀርቶ ከፍተኛ ጉዳት በአብያተ-መንግሥቱ ላይና በአብያተ-ክርስቲያናቱ ላይ ደረሰ፡፡ አሁንም ቢሆን፣ የጎንደርነት ኩራት የሆኑትን የፋሲልን ግንብና አብያተ-ክርስቲያናቱን ለማደስ ሲፈለግ ለጋሾች ተለምነው ነው፡፡ ሕዝቡ የእኔነት ስሜት እንዳይሰማው ስለተደረገ፣ የጎንደርነት ኩራቶች በአግባቡ አይጠበቁም፤ በወቅቱም አይታደሱም፡፡ ቸር እንስብት! እግዚአብሔር እኛን ለመሥራት በተለያዩ የሕይወት ጎዳናዎች ያሳልፈናል፡፡የልቅሶ ዘመን አለ፤የመከራ ዘመን አለ፤የጭንቅ ዘመን አለ፤የእጦት ዘመን አለ፤ደግሞም የዕረፍት እና የበረከት ዘመን ይኖራል፡፡የእግዚአብሔር ቃል የልቅሶ ዘመን በሕይወታችን እንደሚኖር ሲያበስረን እንዲህ ይላል፡- እግዚአብሔር ሊሠራንና ሊያበጃጀን መዝ 119፡73 ብሎም ከእኛ ላይ እልህን፣በገዛ ፈቃድ መሄድንን፣ትዕቢትን ሊያራግፍ እና ሊያለዝበን በብዙ ነገሮች ውስጥ ያሳልፈናል፡፡አዎ! እርግጥ ነው የፈተና፣የንቀት፣የስድብ እና የመከራ ዘመን አለ፡፡የጌታ ጊዜ ሲደርስ ደግሞ ግሩም የሆነ የዕረፍት ዘመን ይመጣል፡፡የፈተናው እና የመከራው ዘመን ያማል፣አንገትን ያስደፋል፣ያስለቅሳል፣ግራ ያጋባል ወዘተ፡፡በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ከእሱ ጋር ተጣብቀንና አጥብቀን የጌታን ፊት የምንፈልግ ከሆነ፣እግዚአብሔር እንደሚደግፍ፣እንደሚያጽናና፣እንደሚረዳ በተግባር ደረጃ የምናውቅበት ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡ ‹‹ከዚያም የወይን ቦታዋን የተስፋ በርም እንዲሆንላት የአኮርን ሸለቆ እሰጣታለሁ፤በዚያም ከግብጽ ምድር እንደ ወጣችበት ቀን እንደ ህጻንነትዋ ወራት ትዘምራለች፡፡በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ በኣሌ ብለሽ አትጠሪኝም ይላል እግዚአብሔር፤የበአሊምን ስም ከአፍሽ አስወግደዋለሁና በስማቸውም እንግዲህ አይታሰቡምና›› ሆሴዕ 2፡17-19 ከዚህ ምንባብ እንደምንረዳው፣ያ ምድረ በዳ እና የመከራ ቦታ፣ለእስራኤል ትልቅ መንፈሳዊ ለውጥንና በረከትን እንዳመጣ እንገነዘባለን፡፡ሕብረታቸው፣አምልኮአቸውና ከጌታ ጋር ያላቸው ግንኑነት እንደታደሰና እንደጠለቀ እናያለን፡፡የሚጓጓለት አስደናቂ ለውጥ! በመከራ ዘመን ከድሎት ዘመን ይልቅ ብዙ ጸሎትና የጌታን ፊት መፈለግ ይስተዋላል፡፡ና አይባልም እንጂ የመከራ ጊዜ የመማሪያና የመሞረጃ ጊዜ መሆኑን ብዙ ሰዎች ይስማማሉ፡፡ጊዜው መርዘሙ ቢያታክተንና ጉስቁልናው ተጭኖ ቢያስጨንቀንም፣ለመንፈሳዊ ዕድገት ትልቅ አጋጣሚ መሆኑ የሚያስማማን ይመስለኛል፤ለዚህ ነው ሐዋርያው ያዕቆብ እንዲህ ብሎ የሚመክረው፡- ‹‹ወንድሞቼ ሆይ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፡፡ትዕግሥትም ምንም የሚጎደላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም›› ያዕ 1፡1-4 አገር ቤቱ ዳያስፖራ፤ ዳያስፖራው ደግሞ አገር ቤት እየሆነ በመጣበት በዚህ ህልሙም፤ ቅዠቱም፤ ባህሉም፤ ኑሮውም ተወራራሺ በሆነበት ዘመን የሥነ ጥበብ ሰዎች አስጎምዥ የትረካ አውድማ እንደተቸሩ ሳውቅ ሰንብቻለሁ። የምሕረት ደበበ ልቦለድ ታሪክ ስድሰት ሺህ ማይል አራርቋቸው በሚኖሩ ያበሻ ሕበረተስቦች ሁለንተናዊ ባሕርይና ዕጣ-ፈንታ ላይ የተመሠረተ ነው። የደራሲው አንድ እግር አሜሪካ፤ ሌላኛው እግር ደግሞ ኢትዮጵያ መሆን የሁለቱንም ሕብረተሰቦች ውጫዊና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ ባሕርይ፤ እንዲሁም የየቤቱን ውሎና ከራሞ በቅርብ ለማስተዋል ዕድል እንደሰጠው ከትርካዎቹ ማስተዋል ይቻላል። ሁለቱም ሕብረተሰቦች ውስጥ እየተከሰተ ያለው ፈጣንና አንዳንዴም አስፈሪ የሆነ ማሕበራዊ ለውጥ የብዙ ደራሲያንን እንዲሁም በየሙያ ዘርፉ ያሉ ጠቢባንን የሰላ አእምሮና ብዕር የሚጋብዝ ነውና እንደ ምሕረት ደበበ ያሉ ብዕር ሲያነሱ ደስ ይላል። የመጽሐፉ ጭብጥ በዘመናችን ሕብረተሰብ አመለካከቶች፤ የኑሮ ምርጫዎችና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ ለውጦች ላይ ያተኮረ ነው - አገር ውስጥም ውጭም ባለነው ላይ። ገጸ-ባህርያቱ ተአማኒነትና መልካም ስብጥርም አላቸው። አሜሪካ ተሻግራ ሃብታም ለመሆን ባላት ምኞት የድሜ አቻዋ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር ያገባችው ስንክሳር አገር ቤት ግድግዳ አስደግፋ የተወችውን የወጣትነት ፍቅረኛዋን የመላኩን ልብ መልሳ ለማሸነፍ የምታደርገው ሴራ ውስብስብና እጅግ መሠሪነት የበዛበት ሰለሆነ ስንክሳርን በጣሙን ትጠሏታላችሁ፤ ትፈሯታላቸሁ፤ ልታንቋትም ይከጅላችሁ ይሆናል። መጨረሻ ላይ ደግሞ እርሷ ራሷ በደረተችው ተንኮል ተጠልፋ ዙሪያ ዓለሟ እየፈራረሰባት ስታዩ “ሰው ተፀፅቶ ከልብ የሚወደውን ቢሻ ይህን ያህል ፍርድ ሊቀበል ይገባዋል ወይ? ” የምትሉም አትጠፉ። መላኩ ባንዲት ሴትዮ ትሩፋት ምንጥ ካለ ድህነት የተረፈና በውጭ አገር ጭምር ትምህርቱን ተከታትሎ “ባገሬ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ” ብሎ በምግባረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ ሀቀኛ ጥረት የሚያደርግ ሰው ነው። በመልካም ባህርዩም፤ በጥልቅ አስተሳሰቡም፤ በፍቅረኛው በስንክሳር በመገፋቱም ለመላኩ ስስ ልብ ይኖራችሗል። አብሮ ያላደጋቸውን ዘመዶቹን ፈልጎ በማግኝት ከድህነት መቀመቅ ለማውጣት ያደረገውን ጥረትና ይህ ዘመቻው ፍሬ እንዲያገኝ መሣሪያ የሆነችውን ግን በትምህርት ያልገፋችውን ያክስቱን ልጅ በጣሙን ትወዷታላቸሁ። ደራሲ ምሕረት ደበበ የሥነ-አዕምሮ ጠበብት ስለሆነ በገጸ-ባሕርያቱ ውይይት ውስጥ በርካታና ጥልቀት ያላቸው የአዕምሮ አሠራር ሁነቶችን እየሰነገ ያስገባል። ለዋቢ ያህል ስለ “ኦቲዝም” እና ስላገር አመራር የተካሄዱትን ውይይቶች ማንሳት ይቻላል። አንዳንዶች “የትረካውን ፍሰት አደናቀፈብኝ” ሊሉ እንደሚቸሉ እረዳለሁ። ወይንም የሰበካ ያህል ሊቆጥሩት እነደሚችሉ እገምታለሁ። በበኩሌ ግን በደራሲው የዕውቀት ደረጃ ያሉና የነበሩ ሰዎች ፀጋቸውን በልቦለድ ትረካ አጊጠው ሲያካፍሉን አይቸ አላውቅምና ሥራውን እጅግ በጣም ነው የወድኩት። አድናቂውም ሆኛለሁ። ይህን አስተያዬት ስሰነዝር የማተሚያ ቤት ልምዴንና ከደራሲያን ጋር ለመዋል ያጋጠምኝን ሰፊ እድል ዋቢ ጠርቸ ነው። “የተቆለፈበት ቁልፍ” ባወቃቀርም በሴራም ደረጃ የተዋጣለት ሥራ ስለሆነ ነው ባንድ ዓመት እድሜ ለሶስተኛ እትም የበቃው። በቀድሞዎቹ ዘመናት ለሁለተኛና ሦስተኛ እትም የበቁ ደራሲያን በጣት መቆጠራቸውን ግንዛቤ ስናስገባና ባሁኑ ዘመን ደግሞ እንደነ ይስማእከ ዴርቶጋዳ ያሉ ደራሲያን ላሥረኛ እትም መብቃታቸውን ስናይ የመግዛት አቅም ያለውና የተማረው ሕበረተሰባችን መስፋቱን እንረዳለን። ይህ ታዲያ ደራሲያንን ሊያበረታታ ይገባል። ደራሲ ተጨንቆና ተጠቦ የሚጽፈው ሥራው ይነበብለት ዘንድ ባለው ምኞት ተገፋፍቶ ነው። ሌሎች እንደ ዓላማ የሚጠቀሱ አነሳሾች በኔም በብዙዎችም ዘንድ ሚዛን አይደፉም። በዚህ ረገድ ደራሲ ምሕረት ደበበ ባገኘው ተቀባይነት በጅጉ መደሰት አለበት። የሚቀጥለው ሥራው በዚህኛው ስኬት ተበረታትቶና ባገኘው ልምድ ይበልጡን በልጽጎ እነደሚቀርብ አልጠራጠርምና “በርታ! ” እለዋለሁ። “ድሮም ሆኖ አያውቅም፣ ትናንት ሆነ ዛሬም አንድ የንብ አውራ ነው- ከሺህ ሰራዊት ጋር ውጤትን የሚያሳይ- የሚጋግረው ማር፡፡” ዳግማዊ ዳዊት - ጥቅምት 2002 @ እንደ ግምገማ - ኩችዩ “መጽሐፍ! ” ሲሉት ሰፍ የሚል ከራማ ቢጤ አለብኝ መሰል ስዬ አብርሃ ደረሱ የተባለው መድብል እጄ እስኪገባ ቸኩዬ ነበር። ባገራችን የቅርብ ዘመን ታሪክ ላይ አሻራቸውን ካተሙት ጥቂት ስዎች መሀል ናቸውና እኒህ ሰው የሚሉትን ለማወቅ ብተጋ አይፈረድኝም። ጀመርሁ የሚሉት የሁለተኛው ምዕራፍ ጉዟቸው የምንፈልገው ዓይነት መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች ያዘለ ሊሆን ስለሚችልም መጽሐፉን ለማንበብ በቂ ምክንያት አለ። ላወቀበት በመስመሮቹ መሀል የተሰነጉትን ሁሉ መመርመር ነው። የትኛውም የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ከወቅት ጋር ባለው ተዛምዶ መነበብ አለበትና ደራሲው ለምንና አሁን መናገር ፈለጉ? የሚለውን ለመመለስ ሞክሬያአለሁ። አንድም የጎደፈ ስምን ለማጽዳት፤ አንድም የገዘፈ ችግር አገራዊ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድርግ፤ አንድም ላዲስ የፖለቲካ ግብ መደላድል ለመፍጠር፤ አንድም ደግሞ ለበቀል ሊሆን ይችላል አልኩ። የጠቀስኳቸው አነሳሾች ነውር ወይንም መሰሪነት አላቸው ለማለት አይደለም። ያ እያንዳንዱ አንባቢ በየበኩሉ የሚደርስበት ድምዳሜ ነው። ሌላው ታሳቢ ደግሞ ከደራሲው ጀርባ-አጥንት ጋር ተያይዞ ብቅ የሚለው የጥርጣሬ መንፈስ ይመስለኛል። በዚህ ረገድ ብዙዎቻችን እንደ ጎጃሙ ገበሬ እንደ ተክለዬስ የፖለቲካ ሰዎችን የምናየው በጎሪጥ ነው። እንኳንስ እኛ የሶስተኛ ዓለም ሰዎች ያንደኛ ዓለሙ ያሜሪካ ሕዝብ 70% ያህሉ በፖለቲከኞች ላይ ዕምነት አጥቶ የለም እንዴ? የነስዬ ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ ነገሩ በመጠኑ ወሰብሰብ ይላል። ከብሔር ፖለቲካ ካምፕ ወደ ሕብረብሔር ፖለቲካ ካምፕ የዘለለን ሰው ባንዴ ሊያቅፉት ያሰቸግራልና ለተወሰነ ጊዜ በጥርጣሬ ዳመና ተከበው መሥራታቸው የማይቀር ነው። የጨዋታው ሕግ ስለሆነ ይህን አይስቱትም በዬ እገምታለሁ። ይሁን እንጅ፤ የኔዋ የጥርጣሬ ዳመና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን እየመዘነች፤ ደረጃ በደረጃ እየጠራች ለመሄድ የተዘጋጀች ናት። እንደምንም ብዬ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረስኳት ይምስለኛል። ሚዛናዊነቷ ደግሞ ለየትኛውም ወገኔ ነው። ተስፋ በትናንት ላይ ሳይሆን በዛሬውና በወደፊቱ ውሎ ላይ የሚገንባ እሴት ነውና ዝንተ-ዓለም የጥርጣሬ ተገዥ ልንሆን አይገባም ከሚሉት ወገን ነኝ። ቁም ነገሩም፤ ብልህነቱም ያለው አዕምሮን አትግቶ ልብን ከፍቶ ማዳምጡ ላይ እንጂ ማለቂያ ለሌው የ “ጠርጥር! ” ባህል ተገዥ እመሆን ላይ አይደለም። ይህን ማድረግ ያልቻለ ህሊና ራሱን ቢታዘብ ይሻለዋል። “በደል ደርሶብኛል! ንጽህናዬ ሊታወቅልኝ ይገባል! ማስረጃዬም ይኸው! ” ብሎ ወደ ህሊና አደባባይ የሚመጣ ሰው በመሠረቱ ሊከበር ይገባል - በታሪካችን ውሰጥ ይህን ያደረጉ ብዙ አይደሉምና። ካላችሁስ ጥርጣሬን ማጠንከር ተከሶና ታምቶ ፀጥ በሚለው ላይ ነው። ደራሲው ስዬ ነገሮችን እንደማያደባልቁ በመጽሐፉ ምርቃት ላይ አሳውቀዋል። ህዝብ ከርሳችው የሚጠብቀው “የሕወሀትን ታሪክ፤ ወሰጠ-ነገሩን፤ ውጣ-ውረዱን፤ ሹም-ሺሩን… ወዘተ እንድተርክለት መሆኑን አውቃለሁ” ብለዋል። ዕድሜውን ከሰጣቸው ለታሪክና ለተመክሮ ቅርስ የሚሆኑ ፅሁፎች እንደሚያቀርቡም ቃል ገብተዋል። ሰለሆነም ለጊዜው ልንተቻቸው የምንችለው ለህትመት ባበቁት “ነፃነትና ዳኝነት በኢትዮጵያ” በሚለው አቅርቦት ላይ ብቻ ነው። እንደኛ ባለ አገር ዳኝንት በገዥው ፓርቲና በመንግሥት ተጽእኖ ውስጥ ለመሆኑ ክርክር የሚያስፈልገው አይመስለኝም - የሁዋላ-ቀርነታችንም ሆነ የንዝንዛችን መነሻ ይኽው ነው። ያቶ ስዬ መጽሃፍ የችሎቱንና የእሥር ቤቱን ድራማ የሲኒማ ያህል ነው ቀርጾ የሚያሳየን። የደራሲው ተማጽኖ “በኔ ላይ የደረሰው የፍትህ መዛባት በመላ አገሪቱ ወስጥ ባሉ ወገኖቼ ላይ እየደረሰ ያለ ለመሆኑ ቋሚ ምስክር ነኝ! ” የሚል ይመስላል። ከሌሎች ጋር ተዳምሮ፤ ይሄ ግንዛቤ በሰውዬው የፖለቲካ አስተሳሰብ ለውጥ ላይ ተጽዕኖ አላደረገም ማለት የሚቻል አይመስለኝም። በሁለተኛ ደረጃ ያጤንሁትና ደራሲው በጽኑ እንዲታወቅላቸው የፈለጉት ጭብጥ ደግሞ በርሳቸው ቡድንና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ቡድን መሀከል የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን አስመልክቶ የተፈጠረው ያቋም ልዩነት ሰለባ እንዳደረጋቸው ነው። “በህወሐት ውስጥ ለተከሰተው መሰነጣጠቅ ዋናው መንስኤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዙሪያ የተከሰተው ጦርነት ነበር” በማለት ፈርጠም አርገው ይከራከራሉ። የነስዬ ወገን “የወራሪውን ጦር አከርካሪ መስበር የተያዘውን መሬት እርግጠኛ በሆነ መልኩ እንዲመለስ ያደርጋል፤ በኤርትራ የሚኖረው መንግሥት ለዘለቄታው በኢትዮጵያም ሆነ ባካባቢያችን የስጋት ጠንቅ ያልሆነና ልኩን ያወቀ እንዲሆን ያደረጋል…በሁለቱ አገሮች መሀከል በእንጥልጥል ያሉ ችግሮች ተፈትተው የሁለቱም ግንኙነት በጠንካራ መደላድል ላይ የሚገነባበት ሁኔታ ይፈጠራል” የሚል አቋም እንደነበረው ደራሲው ያስረዳሉ። ባንጻሩ ደግሞ ያቶ መለስ ቡድን፤ በተለይም አቶ መለስ ይህን የመከላከያ ጦርነት ዓላማ እነዳልደገፉና፤ ዓላማው በኢሕአዴግ ምክር ቤት ከጸደቀ በሗላም ለተፈጻሚነቱ መሰናክል እንደሆኑ ነው ጠንክረው የሚያትቱት። የገጽ ማዕቀቤ ብዙ እንዳትት አይፈቅድልኝምና ዝርዝሩን ከመጽሐፉ ብታገኙ ይሻላል እላለሁ። መጽሐፉ እጅግ በርካታ በሆኑ ያገራችን ጉዳዮች ላይ ጮራ ይፈነጥቃል። በፖለቲካው፤ በማህበራዊው፤ በመንግሥት ቁንጮና በዙሪያው ስለተቀመጡት ሰዎች ምንነትና ማንነት፤ በረጅም ዘመን መከራ የተፈተነ ወዳጅነት ለህልውናና ለጥቅም እንዴት ተኖ እንደሚጠፋ፤ እነዚህን ሁሉ በመጽሀፉ ውሰጥ ከዳር እሰከዳር ተርከፍክፈው ታገኟቸዋላቸሁ። ከላይ እንደጠቆምሁት ደግሞ በመስመሮቹ መሀል የተሰነጉትን ፍንጮች በቅጡ መመርመር የሚችል ብዙ ያገኝበታል። በውጭ የሚኖረው ወጣት ባገሩ ፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ አለመሆኑ ያሳዝነኛል። አንዳንዴማ ከዚያም ያለፈ ነው የሚያደርገኝ። ሰሞኑን ታዲያ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ የተባለ ኦሮሞ ወገኔ ተስፋ ዘራብኝ። ዲሲ በተካሄደው ዓውደ ጥናት ላይ ነው የ24 ዓመቱ ጃዋር “ዱድ” ሥራውን ሲያቀርብ ያዳመጥሁት። የነጠሩ ሊቆች የሚወጡበት የስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ነውና የዋዛ 24 ዓመት እንዳይመስላችሁ። ባንፃሩ ደግሞ ከጃዋር ጋር መድረክ የተጋሩት ምሁራን ባገራችን ፓለቲካ ውስጥ ቆይታ ያደረጉ፤ የቤታችንን ግድግዳ ጌጦች ያህል የምናውቃቸው ባለውለታዎቻችን ነበሩ። እዚህ ላይ በጃዋርና በሌሎቹ መሀከል የነበረው የዕድሜ ልዩነት ከልክ በላይ እንዳስደመመኝና ጥያቄዎች እንደጫረብኝ ልደብቃችሁ አልችልም። ያነሳቸው ነጥቦች ጆሮዬ ላይ ሲዘምሩብኝ ነው የከረሙትና ላከፍላችሁ ብዕሬን አነሳሁ። ሦስት ቀን ስለፈጀው ዓውደ ጥናት ባንዲት አንቀጽ ውስጥ ጥቂት ልበልና ጃዋር በምሳሌነት እንዲያገለግለኝ ወደመረጥሁት ወደ ወጣቱ ጉዳይ እመለሳለሁ። ያለጥርጥር እጅግ የተሳካ ስብሰባ ነበር። አዘጋጆቹ ብዙ ጉልበት እንዳፈሰሱበት የሚመሰክሩ አሻራዎች ስላየሁ አብዝቼ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። አቅራቢዎቹም፤ ታዳሚውም ሀላፊነታቸውን ሲወጡ ያየሁት ፍጹም በሰከነ ቋንቋና በደርባባ ባህርይ ስለነበር ስልጡን ፖለቲካ ተገቢ ቦታውን እያገኘ ነው አልሁ። ታዲያ በባህላችን “ግን” ካልተጨመረበት ምስጋና ምስጋና አይሆንምና ለወደፊቱ ይታሰብበት ዘንድ ላዘጋጆቹ ትንሺ ቅር ያለኝን ነገር ላካፍላቸው እወዳለሁ። የኢትዮጵያ ችግር በርካታ ሆኖባችሁ ይመስለኛል ሁሉን ርዕስ ለመሸፈን ባደረጋችሁት ሙከራ ዓቢይ ጉዳዮች ላይ ሊያወያዩን የመጡ ምሁራን ሰዓት እያነሳቸው ነገራቸውን እንዲቆራርጡ መገደዳቸው አሳቆኛል። ያቅራቢዎቹን ቁጥር ሰብሰብ ማድረግ ቅያሜ የሚያስከትል ሆኖባችሁ ይሆን? የጃዋር አቀራረብ የወጣት ለዛና የወጣት ነፃ አስተሳሰብ የተንጸባረቀበት ነበር። በዝግጅት ደረጃም የተሻለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ - ፓወር-ፖይንት ተክኖሎጅን ተጠቅሟል፤ የኢትዮጵያ ፖሊቲካ ምን ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ ለማስረዳት በቃላት ጋጋታና በ “እጠቅሳልሁ” “አልጠቅስም” አባዜ አልታሰረም። በአዕምሮ ውስጥ ታትሞ በሚቀር ቪዡዋል ቻርት አማካይነት በሁለት የፖለቲካ ጠርዞች ላይ የሚገኙትን አስተሳሰቦች ደህና አድርጎ ተንትኖ መፍትሔው መሀል ላይ መገናኘት ብቻ መሆኑን በሚገባ አስረድቷል። በርሱ ስሌት በ “ብሔርተኛውም” ሆነ “ኢትዮጵያዊነት” በሚለው ካምፕ ውስጥ አክራሪ ዓይነት አቋም ያላቸው ከ 20% አይበልጡም። ቀሪው 80% ፍጹም ሠላማዊ ኑሮ ፈላጊና የብሔር ቅርሱን ለማዳበር የሚያስችል ሥርዓት እስካገኘ ድረስ በኢትዮጵያዊነት መለያው የሚኮራ ነው። “ሆኖም ግን በየመድረኩና በየቤቱ ከሚመነዘሩት የመልካም ምኞት መግለጫዎች ባሻገር ተጨባጭ ሥራ መሠራት አለበት” አለ። “ፈተናው እዚህ ላይ ነው ወገኖቼ! አዲሱ ትውልድ ለዙሪያ ጥምጥም ፍልስፍና፤ ለዲስኩርና ለቃላት ማንጠር ትዕግሥትም አንጀትም የለውም” ሲል አስጠነቀቀ ጃዋር ድምጹን ከረር አድርጎ። አውራ ጣቱንና የታጠፈች ሌባ ጣቱን ሕዝቡ እንዲያይለት ከፍ አድርጎ ደጋገሞ እያፋተገ “ይህ ትውልድ የ ሾው-ሚ-ዘ መኒ! ትውልድ መሆኑን መቀበል አለብን! ” አለ። ጭብጨባውና ቻቻታው መለኪያ ከሆነ በዚያች ወቅት የታዳሚውን ቀልብ ሙልጭ አድርጎ ኪሱ እንዳስገባ አልጠራጠርኩም። ለዚህም ነው “ዱድ! ብሩን አሳዬኝ! ” የምትለዋን የጽሑፌ ርዕስ ያደረግኋት። ጃዋር “ሾው-ሚ-ዘ መኒ! ” ሲል ወጣቱ ትውልድ እንደሸቀጥ በገንዘብ የሚገዛ ነው ለማለት አልነበረም። “ባዶ ቃላት አትመግበኝ! ከዚህ የጥርጣሬ ዘመን ወደመተማመን ዘመን እንዴት እንደምንሸጋገር ያለህን ተጨባጭ የመፍትሄ ሀሳብ እፊቴ ቁጭ አድርግልኝ” ማለቱ ነበር። የጃዋር ትውልድ ባጠቃላይ፤ የአማራትግሬ ዝርያ የሌለው ክፍል ደግሞ በተለይ፤ አዲሱ የኢትዮጵያዊነት ገጽታ በማያሻማና ቅሬታን በሚያጠፋ መልኩ ተነድፎ ሲተገበር መሳተፍ እንደሚፈልግ ጃዋር አሳውቋል። ይህን ዕውን ለማደረግ የሚወሰዱ ርምጃዎችም በዕለት-ተለት ግንኙነቶቻችን ሳይቀር የሚንጸባረቁ መሆን እንደሚገባቸው በአጽንኦት ነበር ያስረዳው። ነጥቡን ለማስረገጥ መሰለኝ፤ መድረኩ ላይ ከርሱ ጋር የተሰየሙትንና ዞር ብሎም ታዳሚውን ሕዝብ በዓይኑ ቃኘት አድርጎ “ይህ ፎቶግራፍ ኢትዮጵያዊነትን በቅጡ ስለማንጸባረቁ እርግጠኛ አይደለሁም” አለ። በዚህ ጊዜ ነበር የጉባዔው አዘጋጆች ወደ መድረኩ ብቅ ብለው በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያገባቸውን ሁሉ መጋበዛቸውን የገለጹት። በድረ ገፆች አማካይነት ከተደረገው ግልጽ ግብዣ በተጨማሪ ካንዳንዶቹ ጋር ቀጥታ ግንኙነቶች ተደርጎ አመርቂ ምላሺ እንዳልተገኘ አስረዱ። እዚህም ላይ “ሕምምም! ” ያሰኘ ቅጽበት ተፈጥሮ ነበር። ጃዋር ያዘጋጆቹን ጥረት አድንቆ እርሱ ራሱ ጉባኤው ላይ ቢገኝ ምን ዓይነት ምቾት እንደሚሰማው ጥርጣሬ አድሮበት እንደነበረ ተናዘዘ። ሆኖም ግን ላቀረባቸው ነጥቦች ሕዝቡ ይሰጠው የነበረውን ከበሬታ ካዬ በኋላ በውሳኔው እንደኮራ አልሸሸገም። በመቀጠልም “የቀሩት ወገኖቻችን ካልመጡ ከመንገዳችን ወጥተን የምናደርገው የማግባባትና የማረጋጋት ሥራ በቂ አልነበረም ማለት ነው” ብሎ በዚህ ረገድ ብዙ እንደሚቀረን አስተማረ። ይህ ሰው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ገና ብዙ ሚና እንደሚኖረው፤ በዕድሜም በብሔሩም በዕምነቱም እርሱን መሰል ዜጎችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጻኦ እንደሚያደርግ ፍንትው ብሎ ነው የታየኝ። በዚህ ስብሰባ ላይ ወጣቱን ትውልድ ወደፊት የማምጣቱ አስፈላጊነት አንገብጋቢ እንደሆነ በብዛት ተወስቷል። የ 24 ዓመቱ ወጣት 55+ ሶች ጋር መቅረቡ ነው ጥያቄውን ከምኔውም በበለጠ ትርጉም የሰጠው። አንዳንዶቹ አቅራቢዎች ይህን ጉዳይ ሲያወሱ ጥፋት እንዳጠፋ ሰው መሸማቀቅ አይቸባቸዋለሁ። በዚህ ፈጽሞ አልስማማም። የቀድሞዎቹ ብዙ መሥዋዕትነት ለመክፈላቸውና ብዙ ለማስተማራቸው አጠያያቂ አይደለም። በወቅቱ ተረካቢ አለማፍራታቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ወንበር የሙጥኝ ማለታቸው፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ወጣቱን የሚስብ ራዕይና የሚጥመው አሠራር አለመንደፋቸው ጥፋት ነው። አባጣ ጎባጣ ያልበዛበት የትውልድ ሺግግር ሳያደርጉ በየጓዳቸው ቢከተቱ ግን የጥፋትም ጥፋት ይሆንባቸዋል። ስለዚህ እስቲ ፈረንጆቹ “ሜንተርሺፕ” የሚሉትን ነገር ይሞክሩት። ያንዳንድ ወጣት እጅ ይያዙ። እንግዲህ ያልሆነ ትርጉም ለመስጠትና አጉል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አትጣደፉ! ጃዋር በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን፤ የነገው እንጅ ያለፈው ብዙም ፋይዳ እንደሌለው የተረዳ፤ ነገር ግን አዲሱ የኢትዮጵያዊነት ራዕይ አንዱን እላይ ሌላውን እታች በማያደርግ መልኩ በድፍረትና በስልት መቀረጽ እንዳለበት ነው ያሳወቀው። ዜጎችንና ብሔረሰቦችን የሚያቀራርብ፤ መተማመንን የሚያሰርጽ ድልድይ በያቅጣጫው ተዘርግቶ ባዲስ ጥርጊያ መንገድ ጉዟችንን እንድንጀምር ነው የሚመኘው። ችግራችንን በሠላማዊ ትግልና ተጨባጭ ርምጃዎች በመውሰድ እናስወግድ ነው የሚለው። ለኔም ለናንተም ጆሮ ከዚህ የተሻለ ጥዑም ሙዚቃ አለ? የጃዋርን ዋና ቁምነገር አትርሱ። ወደድንም ጠላንም አዲሱ ትውልድ መድረክ ላይ ብቅ እያለ ነው። የተፈጥሮ ግዴታ ጭምር ነውና። አዲሱ ትውልድ ደግሞ የ “ሾው-ሚ-ዘ መኒ! ” ትውልድ ነው። ከተስፋ ይልቅ ተጨባጭ ርምጃ፤ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር፤ ከቃላት ጋጋት ይልቅ ቅልጥፍ ባለ ቋንቋ እንድናወጋው ነው የሚፈልገው። ለሚንዛዛና ለቃላት አንጥረኛ ጊዜ የለውም። ለርሱ ጊዜ ወርቁ ነው። በሕዝብ አዕምሮ ውስጥ ጥርጣሬ የመፍጠርን ያህል የፕሮፓጋንዳ ድል የለም። ለዚህ ማስረጃ ከፈለጋችሁ የሂትለር ቀኝ-እጅና የፕሮፓጋንዳ ጠበብት የነበረውን ጎብልስን ጠይቁት። ዓለም ሲፈጠር የት ነበርክ ትሉኛላችሁ እንጅ ከያን ጊዜ ጀምሮ ይመስለኛል ጥርጣሬ መፍጠር የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆነው። ቀልጠፍ ብዬ ወደተነሳሁበት ርዕስ ልመለስና “በርግጥ ተቃዋሚው አገር የመምራት ብቃት አለው? ” የሚል ጥያቄ መናፈስ የጀመረው በ‘97 ምርጫ ማግስት እንደነበር ትዝ ይለኛል። ቅንጅት ውስጥ በተፈጠረው ውዝግብ ቆሺታቸው ያረረ ደጋፊዎች ሳይቀሩ ነው አባባሉን የብስጭታቸው መወጫ ያደረጉት - ትልቅ ስህተት! በጣም ትልቅ ስህተት! ኢሕአዴግ ደግሞ እንኳንስ ይችን ያህል ቀዳዳ አግኝቶ እንዲያውም እንዲያው ነው በሕዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን የጥርጣሬና የብሺቀት መንፈስ ደህና አድርጎ አራገበው። እዚህ ላይ ባንድ ነገር እንስማማ። የሰው ልጅ በፍጥረቱ ተጠራጣሪና የ7 ቀን 24 ሠዓት ኑሮው በስጋት የታጠረ መሆኑን አትክዱኝም። ለዚህ አይደል እንዴ ኢንሹራንስ የሚገዛው? አጥር የሚያጥረው? ብቻውን የሚያወራውና የሚቃዠው? ልብ ብላችሁ ከሆነ ፖለቲከኞች ይህን ሰብዓዊ ደካማ ጎን ደህና አድርገው ነው የሚበዘብዙት “ነውጠኞች የቀድሞውን ሥርዓት ሊያመጡብህ ነው! እኛ ከሌለን አገር ትበተናለች! ሠላማዊ ኑሮህ ይናጋል! የብሔረሰቦች ነጻነት ይገፈፋል! የርስ በርስ ጦርነት ይነሳል! የስልምና አክራሪዎች አገርህን ይወሩታል! ተቃዋሚው አገር የማስተዳደር አቅም የለውም! ” ታዲያ ሁለት ዓቢይ ችግሮች ይታዩኛል። አንደኛው ችግር ተቃዋሚው ወገን የዚህን ፕሮፓጋንዳ አደገኛነት ተገንዝቦ ቀጣይነት ያለው አምካኝ ፕሮፓጋንዳ በፈረንጁ ሰፈር ጭምር አለማካሄዱ ሲሆን ሁለተኛው ችግር ደግሞ የተቃዋሚው የፖለቲካ ገጽታ በመንግሥት እንዲነደፍ መፈቀዱ ነው። በሁለቱም ላይ ያለኝን የተሙን ሀሳብ አካፍላችኋለሁ። በደፋር አስተያየት ልጀምርና ይህ ዘመን ኢትዮጵያን ወደከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር ከምን ጊዜም የበለጠ ተነሳሺነት የገነነበት፤ የሰለጠነ የሰውና የማቴሪያል ኃይል የተከማቸበት ነው እላለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚው ክፍል፤ በተለይም “መድረክ” ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያለው ብቃት ከየትኛውም ፓርቲና ስብስብ የላቀ ነው እላለሁ። እንዳላሰለቻችሁ በሦስት ዋቢዎች ብቻ ልወሰን። የፖለቲካ ፕላትፎርም። የአንድነትመድረክ ፖለቲካ ፕሮግራም የዜጎችን ችግር አበጥሮ የተረዳ ብቻ ሳይሆን ያጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሄዎቻቸውንም የሚዘረዝር ነው። ያልተገደበ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እንደሚኖር፤ የግል መሬትና ንብረት የሕገ መንግሥት ጽኑ ድጋፍ አግኝተው የኤኮኖሚና የማሕበራዊ እድገት አንቀሳቃሺ ሞተር እንደሚሆኑ፤ የኢትዮጵያ አንድነትና ልኡዋላዊነት ለድርድር የሚቀርብ እንደማይሆን፤ ብሔረሰቦችን የሚከፋፈል ፖሊሲ ተወግዶ ያንድ አገርና ያንድ ታላቅ ራዕይ ልጆች በሚያደርግ ፖሊሲ እንደሚተካ፤ 85ሚሊዮን ሕዝብ ህልውናውንና ስትራቴጅያዊ ጥቅሙን አደጋ ላይ በማይጥል መልክ ወደ ባሕር የመውጣት መብቱ እንደሚከበር፤ ወዘተ ያስቀምጣል። ትናንት የቅንጅት ዛሬ ደግሞ ያንድነት የሆነው ራዕይ ገዥው ፓርቲ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ከሚለው ራዕይ በዓይነትም በጥራትም የተሻለ፤ እጅግ በጣም የተሻለ ለመሆኑ ሕዝብ በቅጡ ያውቃል። ለዚህ ነበር በ ‘97ቱ ምርጫ ቅንጅትን የሾመው። ለዚህም ነው ዛሬ በአንድነትና በመድረክ ዙሪያ በሚያስደንቅ ቁርጠኝነት እየተሰባስበ ያለው። ሌላውን ለጊዜው እንተወውና በትግራይ ክልል እየተገለጸ ያለው የፓራዳይም ለውጥ አላስደነቃችሁም? ጥልቅና የምሥራች ትርጉም እንዳለው አልተረዳችሁም? በቢሮክራሲ ልቀጥል። ማንኛውም ለሥልጣን የሚበቃ መንግሥት ሀገሪቱ አዳብራ ባቆየችው ያስተዳደር መዋቅር ቢሮክራሲ መገልገሉ ሀቅ ነው። ይህ የጦር ሠራዊቱን ይጨምራል። ምኒልክ ከዮሐንስ፤ ኃይለ ሥላሴ ከምኒልክ፤ ደርግ ከኃይለ ሥላሴ፤ ኢሕአዴግ ከደርግ በተረከቡት ቢሮክራሲ ነው አገር የመሩት። ሌላው ሀቅ ደግሞ እያንዳንዱ መንግሥት የተረከበውን ቢሮክራሲ አሻሽሎና አዳብሮ ለሚቀጥለው መንግሥት የማስረከቡ ዕውነታ ነው። በዚህ ስሌት እንደ ኢሕአዴግ ጠንካራ መሠረት ያለው፤ በተማረ የሰው ኃይልና በዘመናዊ የማኔጅመንት ዘይቤዎች የዳበረ ቢሮክራሲ የወረሰ መንግሥት አልነበረም። ኢሕአዴግ ራሱ ምን ዓይነት የመንግሥት-አስተዳደርና የማኔጅመንት ልምድ ይዞ በ1991 አዲስ አበባ እንደደረሰ የያኔ ሬዙሜውን ማዬት ይበቃል። በራሴ ላይ የጣልኩት የገጽ ማዕቀብ ከለከለኝ እንጅ ከአፄ ዮሐንስ እስከ ኢሕአዴግ ያሉት መንግሥታት ሥልጣን ሲይዙ የነበረባቸውን ፈተና አነጻጽርላችሁ ነበር። ላለፉት መንግሥታት ከልብ ታዝኑላቸዋላችሁ። እዚህ ላይ ያች ልማዴ እንዳትቀር አንዳፍታ ከመሥመር ወጣ ልል ነው። ስለ ቢሮክራሲ ካወጋን ዘንድ “ቢሮክራሲ” ከፍተኛ የሥም ማጥፋት ዘመቻ የተካሄደበት ያገር ኃብት ነውና ይህን የተዛባ አመለካከት ማቃናት አለብን እላለሁ። ካጭር ትርጉሙ ብንነሳ “ቢሮክራሲ” ያንድ ትልቅና ውስብስብ መዋቅር አስተዳደራዊ አቅም ነው። በሹመት እየመጡ አናት ላይ ጉብ ከሚሉት አላፊዎች በስተቀር ሌላው ሕዝበ-ሠራዊት በሙያ ሚዛን እየተለካ እንደሚቀጠርበት ግዙፍ አገራዊ ፋብሪካ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። መንግሥት ቢለወጥ፤ ሹም ከርቸሌ ቢወርድ፤ ጎርፍ ቢያጥለቀልቅ፤ ቢሮክራሲ ከቦታው ንቅንቅ አይልም። እንደ ዝቋላ ተራራና እንደ አዋሺ ወንዝ ካስቀመጡት ቦታ የሚገኝ ውሉን የማይስት ያገር ኃብት ነው ማለት ነው። ቢሮክራሲን ያልሆነ ጥላሸት የቀባው ባላባቱን፤ ከበርቴውን፤ ካፒታሊስቱንና ኢምፔሪያሊስቱን የሕዝብ ጠላት በማድረግ አንጀቱ ያልራሰለት የኮሚኒስት ሥርዓት ነበር። እንዲያው በሞቴ ኮሚኒስቶች የሚሉትን ከቁብ የሚጥፍ ሰው ተርፎ ይሆን? በፓራዳይም ለውጥ ላጠቃል። ሦስተኛው ቁምነገር ደግሞ ለመድረክ መፈጠር ምክንያት የሆነ የፖለቲካ ክስተት መኖሩ ነው። የብሔር ፖለቲካ ከመሣሪያነት አልፎ ማቴሪያላዊም ሆነ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንደማያስገኝለት ሕዝቡ መረዳት ከጀመረ ሰንበት ብሏል። መቼም ፖለቲከኞች ብልጥ አይደሉም? - የፓራዳይም ለውጥ ሕዝብ ውስጥ ሥር መስደዱን ከማረጋገጣቸው በፊት የአቋምና ያሰላለፍ ለውጥ አያደርጉም። ለዚህ ነው እንገነጠላለን ከሚሉት ጀምሮ ለዘብተኛ እስከሚባሉት ድረስ በብሔር ፖለቲካ ላይ ያላቸውን አቋም ሲከልሱ እያየን ያለነው። ዓለም ወደ አንድ ትንሺ መንደርነት እየተለወጠች በምትገኝበት በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የብሔር ፖለቲካ የሚያራምዱ ሰዎች ከሌላ ፕላኔት እንደመጡ ፍጡሮች ይቆጠራሉና መለወጣቸው እሰዬ የሚያሰኝ ነው። የብሔር ፓለቲካ ያራምዱ የነበሩ ፓርቲዎች በመድረክ ውስጥ መሰባሰባቸው፤ በብሔር ፖለቲካ ዓለም ውስጥ ስማቸው የተጠራ እንደነ ስዬ አብርሃ፤ ነጋሶ ጊዳዳ፤ ገብሩ አሥራት፤ አረጋሺ አዳነና ቡልቻ ደመቅሳን የመሳሰሉ በመድረክ ውስጥ መሰባሰባቸው አንዳንዶች ሊያምኑ ከሚፈልጉት በላይ ጥልቅ መልዕክት ያዘለ ነው። ባጋጣሚና በድንገት የተከሰተ ፓራዳይም ሳይሆን ከ 45 ዓመት ተመክሮ የተወለደ ነው። እዚህ ላይ “ተቃዋሚው ኢትዮጵያን ለመምራት ብቃት አለው? ” ከሚል ጥያቄ ጋር ምን አገናኘው ብትሉ አልፈረድባችሁም። አያችሁ! ኢሕአዴግ ባለሙያና ደጋፊ የሚጨልፈው የብሔር ፖለቲካን በውድም በግድም ከሚያራምዱ ቁጥራቸው እየቀነሰና ወርዳቸው እየጠበበ ከሚገኝ የህብረተሰብ ኩሬዎች ነው። ባንጻሩ ደግሞ መድረክ ደጋፊና ባለሙያ የሚቀዳው እጅግ ሰፊ ከሆነ የህብረተሰብ ሃይቅ ነው። ለዚህ ነው ተቃዋሚው ክፍል፤ በተለይም “መድረክ” ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያለው ብቃት ከየትኛውም ፓርቲና ስብስብ የላቀ ነው ያልኩት - እመነሻዬ ላይ። የለየልኝ ቅን-አሳቢ መሆኔን ደጋግሜ ተናዝዣለሁና ቀሪዎቹ በብሔር ፖለቲካ ጠርዝ ላይ የሚገኙ ያገሬ ልጆች ከፊታቸው የተጋረደውን መጋረጃ እየቀደዱ አንድነትን፤ ኢትዮጵያዊነትንና ትልቅነትን እንዲያቅፉ እመኛለሁ። ሹም መሆን ብዙ ፈተና አለው ወዳጄ! አንዲት አነስተኛ ወረዳ ውስጥ አስተዳዳሪ ሆኖ የተመረጠ ሰው የህዝቡን ተሳትፎ ለማግኘት ቁርጥ ሀሳብ ያደርጋል። የነጋዴው፤ ያስተማሪው፤ የተማሪው፤ የገበሬው በር አልቀረውም። የሁሉንም አንኳኳ። አንዱን ቀን እግሩ ካንድ ገበሬ ቤት ይጥለውና “የዛሬው አመጣጤ አንድ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት እንዲሳተፉልኝ ለመጠዬቅ ነው” ይላል አስተዳዳሪው። ይችን ጨዋታ ያካፈለኝ አንዱ እጁ ከመጽሐፍ አንዱ ደግሞ ከላፕቶፕ ገበታ ላይ የማይነሳ ሌላው ወዳጄ ነው። ይንግሊንግ ቢራችንን ይሄኔ እኮ ያሜሪካ ቀዳማዊ ቢራ መሆኑን የማታውቁ ትኖራላችሁ! ጨብጠን በሌላ ርዕስ ላይ ገራ-ገር ጨዋታ ስንሰልቅ ነው አንቀጹን ያነበበልኝ። አጉል ልማድ አይለቅምና ሀሳቤ እንደገና ወደኛው ጉዳይ አቀና ስንቶቻችን ነን የዶሮዋን ያህል አስተዋጽኦ እያደረግን ያለነው? ስንቶችስ ናቸው የበሬውን ያህል ራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት የቆረጡ? “ሠላማዊ ትግል” በሚለው አንቀጽ ውስጥ “ሠላም” የምትለዋ ቃል አዘናጊ ሆና ትታየኛለች - በዚህ ጎራ የሚታገሉ ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው ያለችግርና በሠላም ውለው የሚያድሩ ታስመስላለችና። ዕውነቱ ግን ይህ አይደለም። በሙሉም ይሁን በከፊል አዱኛቸውን እርግፍ አርገው የሚጥሩ ሁሉ ችግር ይኖራቸዋል። ፓርቲዎቹስ ቢሆኑ ከየት በመጣ ገንዘብ ነው ከክልል ክልል ተዘዋውረው በምርጫው የሚወዳደሩት? ሕዝቡስ ጋር የሚገናኙት? በርግጥ ከመንግሥት የሚሰጥ በጀት እንዳለ ሰምቻለሁ። ግን ዘጠኝ ሺህ የኢትዮጵያ ብር የት ታደርሳልች? አባባሌ አገር ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን መደገፍ የዜግነትና የህሊና ግዴታ አለበት ለማለት ነው። የዚህ ወይንም የዚያ ፓርቲ ደጋፊ መሆናችን አይደለም ቁምነገሩ። ለሀገራችን ዴሞክራሲንና ሠላምን የምንመኝ እስከሆነ ድረስ ለዚህ ለግንቦት 2002ቱ ምርጫ የሚረዳ አሥርና ሃያ ብር ለሚመስለን ፓርቲ ማዋጣቱ ላይ ነው ቁምነገሩ። እርስ በርስ የሚጋጭ ሃሳብ ያዘለ ስለሚመስል “የባላንጣዎች ቡድን” ብሎ ነገር ግር ሊል ይችላል። ስመ ጥሩዋ የታሪክ ተመራማሪ ዶሪስ ጉድዊን “ ” በሚል ርዕስ ስለ አብርሃም ሊንከን ያቀለመችው ድንቅ መጽሀፍ ነው ። ከዛሬ ነገ አነበዋለሁ በሚል አባዜ ውስጥ መጠመዴን የታዘበ ወዳጄ ነው ሰበብ ለማሳጣት ጭምር ይህን መጽሐፍ ጀባ ያለኝ። “ስለ አብርሀም ሊንከን አሥር ሺህ የሚደርሱ መጻህፍትና መጽሔቶች ታትመው ሳለ ዶሪስ ምን ይሁን ብላ ነው ሌላ መጽሐፍ የምትጨምረው? ” ያሉ ሁሉ አፋቸውን በጨው አጥበዋል። ዶሪስ ታሪክን የምታበጥረው ለርሷ ብቻ በተቸረ ዓይነት የተመራማሪነት ስልት ነውና መጽሐፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንብብያን አገኘ። “በሥልጣን ላይ ያሉትና ለሥልጣን የሚዘጋጁት መሪዎቻችን ይህን መጽሐፍ በጥሞና ቢያነቡ ምን ያህል ትምህርት ባገኙበት? ” አልሁ። “ባንባቢነት ለሚታሙት ለጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ቀበቶዬን አስሬም ቢሆን ገዝቼ ልላክላቸው? ” የሚል ነገርም ዳዳኝ። 1855-1865 አሜሪካ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በአጭር ትረካ ልጀምር። ዘመኑ ባሜሪካው ሰሜናዊና ደቡባዊ ስቴቶች መሀከል የጥቅም፤ የተደማጭነትና ያስተሳስብ ፉክክር የጎላበት ነበር። ሁለቱን ወገኖች ያንድ ታሪክ ሕዝብና ያንድ ትልቅ ራዕይ ማሕበርተኛ አድርገው የሚያስተሳስሩ ድርና ማጎች የመብዛታቸውን ያህል ክልል-ተኮር ስሜቶችና የኤሊቶችን ጥቅም ለማስከበር ሲባል የተፈለሰሙ የፖለቲካ እንዝርቶች የጦዙበትም ዘመን ነበር። የሰሜኑ ኤሊት በሁለት ዓቢይ ምክንያቶች ባርነት እንዲያከትም ፈለገ። አንደኛው ምክንያት የባሪያዎች ነጻ መውጣት በታሪካዊው ያሜሪካ ሕገ መንግሥት ውስጥ በጉልህ የተቀረጸውን የሰው ልጆች እኩልነት ዕውን የሚያደርግ ሲሆን ሁለተኛዋና ስውሯ ምክንያት ደግሞ የባርነት መወገድ ሰሜኑ ክፍል ለልማትና ለፋብሪካዎች መስፋፋት የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ስለሚያፈልስለት ነበር። ብሔራዊ አንድነትን የሚፈታተን፤ የሕይወትና የንብረት ጥፋትን የሚያስከትል ጥቁር ዳመና ባንዣበበበት በዚያ ቀውጢ ዘመን አብርሃም ሊንከን በፕሬዚደንትነት ተመርጦ ካቢኔ ለማቋቋም ይንደፋደፍ ነበር። ዕውቀቱም ልምዱም ሁሉም አላቸው የሚባሉት ምሁሮች እርስ በርስ ሲናቆሩ ነበርና ሊንከን ሹልክ ብሎ ፕሬዚዳንት የሆነው ባገሪቱ ውስጥ የጥርጣሬ አየር ሰፈነ። በዚያው ልክም የሊንከን ጣጣ በረከተ የሕዝቡንና አብረውት የሚሠሩትን ሰዎች አመኔታ ባጭር ጊዜ ውስጥ ማሸነፍ ነበረበት፤ የበርካታ ተጻራሪ ሃይሎችን የጥቅም ግጭት ማስታረቅ ነበረበት፤ የርስ በርስ ጦርነቱ የሚጠይቀውን የሰውና የማቴሪያል ኃይል ስለማግኘቱ እርግጠኛ መሆን ነበረበት፤ ባሪያዎች ነፃ መውጣት አለባቸው በሚለው ጥያቄ ላይ በራሱ ፓርቲ ውስጥ እንኳ ወጥ አመለካከት አልነበረምና እንዲጣጣም ማድረግ ነበረበት፤ በዲፕሎማሲው መስክ ደግሞ አውሮፓውያን “ሕዝባዊ መንግሥት” የሚሉት ነገር እያፈረጠመ መሄዱ ያባንናቸው ነበርና ኮንፌደርሬቱን ቢደግፉ የኃይል ሚዛን ወደደቡብ ያጋድላል የሚል ስጋትም ያስጨንቀው ነበር። አሜሪካ እንዲህ ያለ ፈተና ገጥሟት አያውቅም። ጥርጣሬ የነገሰበትና ልጆቿ ፊትና ጀርባ የሆኑበት ጊዜ አልነበረም። በብዙ መስዋዕትነት የተገነባው ብሔራዊ አንድነቷ እንዲህ የተፈተነበት ወቅት አልነበረም። የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም ብዙ ፈተናዎች አልፎ ነው የአብርሃም ሊንከን ቡድን ዛሬ የምናውቃትን የዴሞክራሲ ቀንዲል፤ የሁሉ መጠጊያና መጠለያ የሆነችውን አሜሪካን ያቆየን። “የባላንጣዎች ቡድን” ሊንከን አሜሪካ የገጠማትን ታላቅ ፈተና በድል መወጣት የምትችለው በዕውቀትም በልምድም የነጠሩ ሰዎችን ማሰባሰብ ከቻልሁ ብቻ ነው ብሎ በጹኑ ያምን ነበር። አስተዳደሩ ሁሉንም ስቴቶች እንደመስታወት የሚያሳይና ሁሉንም በሀቅ የሚወክል፤ ስጋቶችንና ምኞቶችን ያገናዘበ እንዲሆን ይፈልግ ነበር። ከዚህ ዕምነቱ ተነስቶ ነው በምርጫ ላይ ያሸነፋቸውን ባላንጣዎቹን ጭምር በካቢኔው ውስጥ እንዲያገለግሉ ቅድሚያ ጥሪ ያደረገላቸው። “ገና የሺንፈቱ ምሬት ሳይጠፋላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደሚንቁት እያወቀ ባላንጣዎቹን አብረውት እንዲሠሩ መጋበዙ የለየለት የዋህነት ነው! ” አሉ ያደባባይ ተችዎችና ጋዜጠኞች። ሊንከን በራሱም በዜጎቹም ላይ ያለው ዕምነት ጠንካራ ነበርና ተፎካካሪዎቹን እቤታቸው ድረስ እየሄደ ከማግባባት ወደኋላ አላለም። አሜሪካ የገጠማት ፈተና የያንዳንዳቸውን እውቀትና መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ አሳሰባቸው። ጥሪውን ከተቀበሉ ደግሞ በሙሉ ነጻነትና ከሙሉ ድጋፍ ጋር እንደሚሠሩ ቃል ገባላቸው። አገሪቱ ያለችበትን ችግር በፖለቲካው ውስጥ ከሰነበቱት ባላንጣዎች ይበልጥ የሚረዳ አልነበረምና፤ እንዲሁም ደግሞ በሊንከን ያልተፈተነ ያመራር ችሎታ ሀሳብ ገብቷቸው ነበርና ባላንጣዎቹ ጥሪውን ተቀብለው ካቢኔውን ተቀላቀሉ። ዊሊያም ሲዋርድን፤ ኤድዋርድ ስታንተንን፤ ሳልመን ቸስን፤ ኤድዋርድ ቤትስን፤ እነዚህን ከባድ ባላንጣዎች አጠገቡ ሳያደርግ መረጋጋትና ድል አጠራጣሪ ይሆኑበት ነበርና ሊንከን በጣሙን ነበር የዘየደው። በሳል፤ ታዋቂና ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ያላቸውን ፖለቲከኞች ባንድ ካቢኔ ውስጥ ማሰባሰቡ በጣሙን ጠቀመው። የካቢኔው ተቀዳሚ ተግባር ጦርነት እንዲቆምና እርቅ እንዲወርድ የሚያደርጉ ሀሳቦችን በጥልቀትና በድፍረት ማማንጨት ነበር። ከሀገር መገንጠል በመለስ ሊደርጉ የሚችሉ ሰጥቶ-መቀበሎችን መመዘን ነበር። የሠላም አማራጮች ፋይዳ ባይሰጡ ደግሞ ጦርነቱ በሰው ኃይል፤ በፋይናንስ በዲፕሎማሲና በሌላው ዘርፍ የሚጠይቀውን አቅም ማጥናትና እንዴትስ እንደሚሰባሰብ ስትራቴጅ ማውጣት ነበር። የሠላም አማራጭች ገዥ ቦታ ይኖራቸው ዘንድ የሊንከን ዓይነ-ልቦና ምንጊዜም ክፍት ነው። የተለያዩና አንዳንዴም የማይዋጡ የሚመስሉ የክልል ፍላጎቶችን ለማስተናገድ ወኔ አንሶት አያውቅም። ትናንት በፉክክርና በጥርጣሬ መጋረጃዎች ተለያይተው የነበሩ ባላንጣዎች በአንድ ሰው ጥረት፤ አስተዋይነትና የማስተባበር ችሎታ አንድ-አካል አንድ-አምሳል ሆነው አገርና ወገንን በመታደግ ክቡር ሥራ ላይ ተሰማሩ። ባላንጣነት በልብ ወዳጅነትና በወንድማማችነት ስሜት ተተካ። ቀጥሎ ደግሞ ሊንከንን ታላቅ መሪ፤ የባላንጣዎችን ቡድን ደግሞ የቻምፒዎን ቡድን እንዲሆኑ የረዱትን ባህርዮች በጭር ባጭሩ ላነጥብላችሁ እሞክራለሁ! • የራዕይ ጥራት ~ የሰሜን-ደቡብ ቅራኔ ለብዙዎች ባርነትን የማጥፋትና ያለማጥፋት ጥያቄ ይሁን እንጅ ለሊንከን ከዚያ የበለጠ ትርጉም ነበረው። “ያሜሪካ መፈራረስ የሕዝቦች-በሕዝቦች-ለሕዝቦች የተሰኘው አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ራሱን ችሎ መቆም የማይችል ቅዠት ነው ለሚሉ ወገኖች የፖለቲካ መሣሪያ ይሆናልና ያንድነት ኃይሎችን መሸነፍ እንደ አማራጭ አንቀበለውም” አለ። የዚያ ትውልድ ኃፊነት ዓለማቀፋዊ እንድምታ እንዳለውም አሳየ። ከዚህም ሌላ “ባሜሪካ መገነጣጠል የሚጠቀሙት ዜጎች ሳይሆኑ እዚህና እዚያ በሚፈጠሩ ትናንሺ ግዛቶች መንበር የሚፈልጉ የሥልጣን ጥመኞች” መሆናችውን አበክሮ ተከራከረ። • ስሜታዊነት ጠላት ነው ~ አገርን የማስተዳደር ያህል ውቅያኖስ ውስጥ የተነከረ ሀላፊ የሚያበሳጨውና አንዳንዴም የሚያሳብደው ነገር ያጣል ማለት ዘበት ነው። ሊንከን ለዚህ ጥሩ ዘዴ ነበረው። ደብዳቤ ይጽፍና በይደር ያቆየዋል። ታዲያ በማግስቱ ብስጭቱም ስሜታዊነቱም ሲረግብ የሚልከው ደብዳቤ የሚቆጭበት አይሆንም። በስሜታዊነት ድባብ ውስጥ እንዳለ ያመለጡ ዳብዳቤዎች ቢኖሩ እንኳ ሰውየውን የሚያረጋጋና ቂም ያልያዘበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ተከታይ ደብዳቤ ይልክለታል። ፀያፍ ቃል ካፉ ወጥቶ አያውቅም። • ርሕራሄና ታላቅነት ~ ሊንከን ፍጹም ሩህሩህ፤ ከቅጣት ይልቅ ምሕረት ሰዎችን ወደበጎ የመመለስ ኃይል አለው ብሎ የሚያምን ሰው ነበረ። በጦር ሜዳ ያሸነፋቸው ጀኔራሎች ላይ ውርደት እንዳይደርስ፤ የተፈታው ጦር ሠራዊት ደግሞ ከነፈረሱና ከነመሣሪያው ቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሎ ኑሮውን እንዲቀጥል መፍቀዱ የወዳጆቹንም የባላንጣዎቹንም ከበሬታ አስገኘለት። ሀገሪቱን ወደ እርቅና ስምምነት ጎዳና አፋጥኖ ወሰዳት። ለዚህ ነው ሊንከን “አባታችን” የሚለውን የፍቅርና የአቅርቦት ቅጽል ሥም ከወገኖቹ የተቸረው። እርቅና ስምምነት ~ ጦርነቱ አብቅቶ ሊንከን ለሁለተኛ ጊዜ ተመረጠ። ባስመዘገባቸው ድሎች ከመኩራራት ይልቅ ታሪካዊ ንግግሩን ብሔራዊ እርቅ አንዲሰፍንና የአንድነት ስሜት እንደገና እንዲነግስ መንገድ መክፈቻ አደረገው። ብሔራዊው የትኩረት አቅጣጫ ምን ሊሆን እንደሚገባ ማመላከቻ አጋጣሚ አደረገው። ያ አቅጣጫ በብሩህ ተስፋ የተቃኘ፤ በዕርቅና በሠላም መዓዛ የታጀበ ነበርና አገሪቱን ከዳር-እዳር አወዳት። • በምሳሌነት መምራት ~ ሊንከን ከሕዝብ መሀል የወጣ ስለሆነ ከሕዝብ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ማድረግን ይወድ ነበር። ስለሆነም ቤተመንግሥቱን ለጎብኝዎች ክፍት አደረገ። ዜጎችን ወደ ጦር ሜዳ ከማሰማራት የከበደ ውሳኔ የለምና ሊንከን ራሱን ከጦር ሜዳ ለይቶ አያውቅም። ከወታደሩ ጋር ይወያያል፤ ብሶታቸውን ያዳምጣል፤ ያበረታታቸዋል፤ ያስተምራቸዋልም። ይህን በማድረጉ ከታሸና ከተኳኳለ የሹሞች ሪፖርት ራሱን መከለል ቻለ። የሊንከን የጦር ሜዳ ጉብኝት የወታደሩን ሞራል ለማነቃቃት ጠቃሚ ቢሆንም አደጋ ይደርስበታል ብለው ለሚሰጉ ጀኔራሎቹ ግን ራስ ምታት ነበር። • ዘና ማለትማ ተፈጥሯዊ ነው ~ በሥራ ብዛት የተወጠረች ነፍስ ዕረፍት እንደሚያስፈልጋትና የተሟጠጠ ጉልበት በሳቅና በጨዋታ መታደስ እንዳለበት ሊንከን ከልቡ ያምን ነበር። እርሱ ራሱ የተዋጣለት ቀልድ አውሪ ብቻ ሳይሆን አስተዳደሩ በውጥረት ቅንፍ ውስጥ ተወጥሮ እንዳይሠራ የተቻለውን ሁሉ አድርጓል። የቱን ያህል ጫና ቢበዛበት ለቲያትር ቤት ጊዜ አያጣም ነበር። ሊንከን ማስመስልና መኮፈስ የማይወድ ውነተኛ ሰው ነበር። እዚህ ላይ ባጠቃልለው ደግ መስለኝ። ያሜሪካው የርስ በርስ ጦርነት 620 ሺህ ያህል ሕይወት የጠፋበት እጅግ አስከፊ ጦርነት ነበር። ከሚሊዮን በላይ ዜጎች አካለ ስንኩል ሆነውበታል፤ ሠላማዊ ኑሮ ተናግቶ ዕድገት የኋልዮሺ ተመልሳለች። ይህ ጦርነት ሊወገድ ይችል ነበር ወይ የሚለው ጥያቄ “ሙት” ጥያቄ ነውና ፋይዳው አስተማሪነቱ ላይ ብቻ ነው። ራሳችንን በማታለል አባዜ ውስጥ ተተብትበን ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ማሕበራዊ ቀውስ የመከሰቱ አደጋ የማይታሰብ ነው የሚባል አይደለም። ያንዱ አስተዋጽኦ ከሌላው ይለይ እንደሁ እንጅ ባገሪቷ ፖለቲካ ውስጥ ሚና ያላቸው ድርጅቶች ይህ ቀውስ እንዳይከሰት ኃላፊነት የተሞላው ርምጃ ሲወስዱ አለመታየታቸው ያሳስበናል። የፖለቲካ ቅራኔዎች እየተንገዋለሉ እንዲቆዩ ማድረግ ባልታወቀ ሠዓት የሚፈነዳ ቦምብ አቅፎ የመተኛት ያህል ነውና ስንባንን መኖር የለብንም። ልዩነቶቻችንን ማቀራረብ አለመቻላችን፤ የጠባብ ብሔር ስሜት እንዲስፋፋ ማድረጋችን፤ ሕዝቦች እየተራራቁ እየተፈራሩና መግባቢያ ቋንቋ እያጡ እንዲሄዱ ማድረጋችን የራሳችንን እግር ደግመንና ደጋግመን በጥይት የማቁሰል ያህል ቂልነት አለው። ወለጋ ስባተኛን ክፍል ጨርሳ ከቤተሰቦቿ ጋር አዲሳባ ስትዛወር ከሦስተኛ ክፍል ጀምሪ የተባለችዋ ወጣት የሥርዓታችንን ድህነት ታስረዳችኋለች። ያዲሳባውና የወለጋው ወጣት የሚግባቡበት ቋንቋ ተደልዟላ! አሜሪካ አንድ ታላቅ መሪ ባስፈለጋት ሰዓት ሊንከንን አግኝታለች። የሊንከንን የባላንጣዎች ቡድን አዋቅራ ከመዓት ድናለች። እኛ ደግሞ ሳይውልና ሳያድር የራሳችንን ሊንከን መፍጠራችን ወሳኝ ነው። ማለቂያ በሌለው ጉስቁልና የሚማቅቀውን ሕዝባችንን የሚታደግ የባላንጣዎች ቡድን ለማደራጀት ከዚህ የተሻለ የታሪክ አጋጣሚ የለም። አስፈላጊነቱም እንዲህ አንገብጋቢ ሆኖ አያውቅም። መቼም ዳጎስ ያለ ቁርስ ጎርሶና ትከሻውን ቼብ-ቼብ ተደርጎ የወጣ ወንድ የልብ ሳያደርስ አይመለስምና ወርደ-ሰፊ አካፋየን እያውለበለብሁና ውርድ ከርሱ እንደሚሆን እያስጠነቀቅሁ በረዶ ላይ ጦርነት ከፈትሁ። አጀማመሬን በጣሙን ወደድሁት። በዚህ አያያዝ በራሴ ቀዬ ላይ የሚደነፋው ብቻ ሳይሆን ጎረቤት መበለቷ ደጃፍ ላይ የተከመረውም እንደማይተርፈኝ አወቅሁት። የልብ ልብ ተሰማኝና አካፋውን ካፍ-እስከገደፉ እየሞላሁ አቶ በረዶን በትከሻየ ላይ እያሻገርሁ አሺቀነጥረው ጀመር። እንዲህ ያካፋውን ስነፈትና የትከሻየን ልግመት በመታዘብ ላይ እንዳለሁ ነው ከመበለቷ ቤት አቅጣጫ “ርርርርርርር! ” የሚል የሞተር ድምጽ ሰምቼ ዞር ያልሁት። እመቤቲቱ በረዶ መንፊያ መንኮራኩራቸው ላይ ቂጢጥ ብለው ቀያቸው ላይ በድፍረት የተጋረጠውን በረዶ ይመነጥሩታል። እጃቸውን አውለበለቡልኝ። እኔም አውለበለብሁላቸው። “እናም ሀይሉ ሻውል 2010 ምርጫ ውስጥ ለመግባት መወሰኑ ከምን መጣ? በእሥር የተንገላታበት የቅንጅት ባለ ስምንት ነጥብ ቅድመ ሁኔታስ ምን ጅብ በላው? ከትናንት በስቲያ የብርቱካን መፈታት ቅድመ ሁኔታ ነው አላለም ነበር ወይ? በርግጥ ሀብቱንና ንብረቱን ካደጋ ለመጠበቅ ሲል ያደረገው ሰጥቶ-መቀበል ነው? በ2005 ምርጫ ያሳዘናቸውን ደጋፊዎቹን እንደገና ማሰባሰብ እችላለሁ ቢል የለየለት እብደት አይደለም ወይ? ” እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ወዳጄ ላይ ያራገፍሁት እንደመትረዬስ ነበር። በንዲህ ያለ ስሜታዊነት ጨዋታ በጀመርኩ ቁጥር ምንጊዜም ዓይኑ ወደጣራው እጁ ወደ ቡናው ስኒ ነው የሚያመራው። በርጋታ ፉት ብሎ እስኪያጣጥም ድረስ የኔ ስሜት ሳይወድ-በግዱ እንደሚበርድ ያውቃል። ሰው የዚህን ያህል ውስጣችሁን ሲያነብ እህ! አትሉም? ቀጥልኩ ደግሞ ስለምርጫው - “የኢሕአዴግ ስሌት ምን ይመስልሀል? ምን ያህል ያገር ውስጥና የውጭ መንግሥታት ተጽዕኖ አለበት? ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም ያለው አቅምስ? የኦባማስ አዲስ ፖሊሲ? ኢዩስ? የብርቱካንስ ጉዳይ? መድረክ ምርጫው ውስጥ የሚሳተፍ ይመስልሀል?